🔔 ራስን ድል መንሳት
❖ የስጋ ምኞትንና ፍላጎትን አስመልክቶ ጾምና ድንግልናን ራስን ድል የመንሳት መንገዶች ናቸው፤ ነፍስን አስመልክቶ የሚጠቀስም ሌላ መንገድ አለ፤ ራሱን የሚገዛና እርሱነቱን ወደ ዓለማዊ ደስታ ከማዘንበል የሚያግድ ሰው ብጹዕ ነው።
❖ ማንነት ልታይ ልታይ ሲል ጉራውን ሊገልጥ ሊታበይ ይችላል፤ በዚህ ሁሉ ግን ልንቃወመው ይገባናል፤ ለእኛ ከእግዚአብሔር ጋር መደሰትና መልካም የሆነው ነገር ለመጪው ህይወት ብናቆይ የሚሻለን መሆኑን ራሳችንን ልናሳምነው ይገባናል፤ በዚህ ዓለም ድስታን ለማግኘት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ የመድኋኒ ዓለም ቃል ይመሰክርባቸዋል።
✍" . . . እውነት እላችኋለው፡- ዋጋቸውን ተቀብለዋል"
📖ማቴ 6፥5
❖ ስለዚህ በምድር ላይ ያሉ መብቶችህን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እግዚአብሔር እያንዳንዱ ዕንባህን ከዓይኖችህ ላይ የሚጠርግበት በወድያኛው ዓለም ቢሆንልህ ይሻልሃልና።
❖ ማንነትህ ወይም ስጋህ አሁን ላለህበት ዓለም ደስታ የሚያዘም ከሆነ በርትተህ ተከላከላቸው፤ በራስህ ወይም በስጋህ ላይ የምይወስደው ይህ እርምጃ ጭካኔ አደለም፤ለእነርሱ ዘላለማዊ ሕይወትን ማረጋገጫ እንጂ።
❖ ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የሚንከባከባት ያጠፋታል፤ ራሱን በጥብቅ ከመቆጣጠር ችላ የሚል ሰው በእርሱ ላይ ኋይል እንዲኖረው ያደርጋል፤ ስለሆነም ራሱን ለጽድቅ ከሚያለማምደውና የእግዚአብሔር መንገድ ከሚተገብረው ሰው በተለየ ሁኔታ በመንፈሳዊ ጠባዩ ላይ እንዲያምጽ ያደርገዋል።
❖ ራስን ድል መንሳት የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ከስጋ ደስታ ጋር እንደማይነጻጸር እርግጠኛ ሁን፤ ከሁሉ በጣም የሚያስደንቀው የራስ ጉራ ሙሉ ለሙሉ መጥፋት በሚገባው በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ከፍ ከፍ ማለቱ ነው።
📌ምንጭ
✍️ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@Kedusan2

ሕማማት መስቀል " ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦
1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ
5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ
6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል
በችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።
@Sihela_adhno
@Sihela_adhno
@Sihela_adhno shere

💚💛❤️
# ልብ_ብለህ_አስተውል
#አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡ ዘፍጥ 3÷1-8
# አትቅና፦ እንደ ቃየል ወ ንድምህን ትገላለህ፡፡ ዘፍጥ 4÷1-
#አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡
ዘፍጥ 19÷30-38
# ዓለምን አትመልከ ት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ
ሆነህ ትቀራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷22-23
#በአባትህ አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡ ዘፍጥ 9÷20
#እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡ ዘፀ 14÷28
# በሐሰት አትመስክ ር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ
ትገባለህ፡፡ መጽ.አስቴ 7÷1
#ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡ 2ነገ
19÷35
#ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ
ትወድቃለህ፡፡ መጽ.መሳ 16÷15
#አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን
እንድታመልክ ያደርግሃል፡፡ 1ነገ 11÷1-8
#ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ
ትነሣለህ፡፡ 2ነገ ሳሙ 15÷13-17
ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡ ማቴ
26÷14÷16
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ
ክቡር አሜን!!!
ሼር

#ተዋህዶ
#ሰማዕታት_በደም የፃፉሽ ውብ ፊደል ፤
#የሐዋርያት ትምህርት የቅዱሳን ገድል ፤
#የፃድቃን ትሩፋት በእምባቸው
የታተምሽ፤
#የገሀነም ደጆች ከቶም የማይችሉሽ ፤
#ራስሽ_ክርስቶስ በቃሉ ያፀናሽ ፤
#ከትውልድ ትውልድ የምታበሪ ደምቀሽ፤
#የማንነቴ ምንጭ ክብሬ በረከቴ፤
መድመቂያ መታያ ውበት ሰገነቴ፤
በፍቅር በጥበብ ሞልተሽ ያሳደግሽኝ፤
ልጅነቴን ባርከሽ በሞገስ ያቆምሽኝ፤
#በልቤ_የታተመ ፍቅርሽ በደም ስሬ፤
#በቅኔ_የሞላሽኝ አፌን በዝማሬ፤
#ከውጊያ_ማሞለጫ ምሽግ ከለላዬ፤
ለነፍሴም ማትረፊያ መንገድ ጠራጊዬ፤
የእድሜ ልክ ቃል ኪዳን ያሰርኩብሽ ውዴ፤
አክሊል ማህተሜ ነሽ አይጠፋም መውደዴ፤
በአለም ድካም ቢዝል ቢሳሳ ጉልበቴ ፤
#ምስጢር ገመናዬ መሸሸጊያ ቤቴ ፤
#ማልደራደርብሽ የዘለአለም ሀብቴ ፤
#ሰንደቅ_መለያዬ አርማ የኔነቴ ፤
አንቺ ነሽ መፅናኛ ; አንቺ ነሽ ደስታዬ; ፤
አንቺ ነሽ ህይወቴ!
ተዋህዶ እምነቴ 🙏
@Kedusan2
@Kedusan2
#ሰማዕታት_በደም የፃፉሽ ውብ ፊደል ፤
#የሐዋርያት ትምህርት የቅዱሳን ገድል ፤
#የፃድቃን ትሩፋት በእምባቸው
የታተምሽ፤
#የገሀነም ደጆች ከቶም የማይችሉሽ ፤
#ራስሽ_ክርስቶስ በቃሉ ያፀናሽ ፤
#ከትውልድ ትውልድ የምታበሪ ደምቀሽ፤
#የማንነቴ ምንጭ ክብሬ በረከቴ፤
መድመቂያ መታያ ውበት ሰገነቴ፤
በፍቅር በጥበብ ሞልተሽ ያሳደግሽኝ፤
ልጅነቴን ባርከሽ በሞገስ ያቆምሽኝ፤
#በልቤ_የታተመ ፍቅርሽ በደም ስሬ፤
#በቅኔ_የሞላሽኝ አፌን በዝማሬ፤
#ከውጊያ_ማሞለጫ ምሽግ ከለላዬ፤
ለነፍሴም ማትረፊያ መንገድ ጠራጊዬ፤
የእድሜ ልክ ቃል ኪዳን ያሰርኩብሽ ውዴ፤
አክሊል ማህተሜ ነሽ አይጠፋም መውደዴ፤
በአለም ድካም ቢዝል ቢሳሳ ጉልበቴ ፤
#ምስጢር ገመናዬ መሸሸጊያ ቤቴ ፤
#ማልደራደርብሽ የዘለአለም ሀብቴ ፤
#ሰንደቅ_መለያዬ አርማ የኔነቴ ፤
አንቺ ነሽ መፅናኛ ; አንቺ ነሽ ደስታዬ; ፤
አንቺ ነሽ ህይወቴ!
ተዋህዶ እምነቴ 🙏
@Kedusan2
@Kedusan2
ተክለሀይማኖት ባህታዊ
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል (2)
ቃል ኪዳን አለህ የገነነ ፤ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውሃ አጠጥተን ፤ ዋጋችን በዝቷል አባታችን
ተክለሃይማኖት ባህታዊ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
እኛም ሆነናል ልጆችህ ፤ ማርኮ አስቀርቶ ምግባርህ
በምልጃህ ፀሎት ትሩፋት፤ ቤታችን ሞላ በረከት
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
ምህረት ይዘንባል ከሰማይ፤ ባንድ እግርህ ቆመህ ስትፀልይ
ብዙ ተጋድሎን አትርፈሃል፤ ያገለገልከው አኩርቶሃል
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
ተሰባበሩ ጣዎታቱ፤ አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ካፉ ወጥቶ፤ የአምላክ አድርጎል ሁሉን ገዝቶ
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
እኛም ሆነናል ልጆችህ ፤ ማርኮ አስቀርቶ ምግባርህ
በምልጃህ ፀሎት ትሩፋት፤ ቤታችን ሞላ በረከት
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል (2)
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል (2)
ቃል ኪዳን አለህ የገነነ ፤ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውሃ አጠጥተን ፤ ዋጋችን በዝቷል አባታችን
ተክለሃይማኖት ባህታዊ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
እኛም ሆነናል ልጆችህ ፤ ማርኮ አስቀርቶ ምግባርህ
በምልጃህ ፀሎት ትሩፋት፤ ቤታችን ሞላ በረከት
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
ምህረት ይዘንባል ከሰማይ፤ ባንድ እግርህ ቆመህ ስትፀልይ
ብዙ ተጋድሎን አትርፈሃል፤ ያገለገልከው አኩርቶሃል
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
ተሰባበሩ ጣዎታቱ፤ አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ካፉ ወጥቶ፤ የአምላክ አድርጎል ሁሉን ገዝቶ
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል
እኛም ሆነናል ልጆችህ ፤ ማርኮ አስቀርቶ ምግባርህ
በምልጃህ ፀሎት ትሩፋት፤ ቤታችን ሞላ በረከት
ተክለሃይማኖት ባህታዊ ፤ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
ባደባባዩ ተተክለሃል ፤ ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል (2)
❤️ [በዓለ ሆሣዕና] ❤️
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ክንፋቸው ትእምርተ መስቀል የሚሠራው ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸከሙት ጌታ በትሕትና ኾኖ ጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ባለባት በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡
♥ ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡
♥ ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡
♥ በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡
❤ በልደቱ ማንም ያልገባባት የማይገባባት የሕዝቅኤል የታተመች መቅደስ የተባለች ዘላለማዊት ድንግል እመቤታችንን እንደመረጠ ዛሬም በሆሣዕና ማንም ሰው ያልተቀመጠባት አህያን ከውርንጫዋ ጋር እንዲያመጡ አዘዘ።
♦ ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና።
♥ ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡” ይላል።
♥ ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑን ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል።
♥ አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ። ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ በማለት መተርጉማን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም ልብስ በልጅነት ይመሰላልና የተገፈፍነውን የጸጋ ልብሳችን (ልጅነትን) ትመልስልናለህ ሲሉ ነው፨
♥ ቅዱስ ኤፍሬም ይኽነን ሲተረጉም "ልብሳቸውን አውልቀው ያነጠፉለት ሰዎች አሮጌውን ማንነታቸውን ትተው ዐዲሱን ልብስ ክርስቶስን መልበሳቸውን ያስረዳል። ሐዋርያ ጳውሎስ “አሮጌውን ሰውነት አስወግዳችሁ አዲሱን ሰው ልበሱት” እንዳለው (ኤፌ.4፣23) ይኸውም ጥምቀት ነው" ይላል።
♥ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡
♥ ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ። በተጨማሪም መተርጉማን እንዳመሰጠሩት በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡
♥ በተጨማሪም አህያ ሲፈጥራት በጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ያላት ናትና ትእምርተ መስቀል ያለባት እእርሷ እንድትፈታ ማዘዙ ከ5 ቀን በኋላ በመስቀል ተሰቅሎ በሲኦል የታሠሩትን የሰው ልጆችን ነጻ ሊያወጣ መጥቷልና አህያን መርጧታል፨
♥ ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት አመስጥሯል፡፡
♥ ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው (መዝ.49፡12)፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደ አህያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጿል፡፡
♥ ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነበር። እንስሳዋ እንኳን ጌታ ቢቀመጥባት እንዲህ ክብር ያገኘች ከሆነ ያደረባቸው ቅዱሳንማ የሚገባቸው ክብር ምን ያህል ይሆን? ይልቁኑ 9 ወር ከ5 ቀናት በማሕፀኗ የተሸከመችው ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የሆነውን አምላክ የወለደችው የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርማ እጅጉን ታላቅ ነው።
❤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡

Forwarded from Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ
በ፳፻፲ወ፬ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ ብፀዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት አስተላለፉ።የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ ፦
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፤
• ብፁዕ አቡነ ያሬድ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የምሥራቅ ጎጃምና የአርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኃላፊ፤
• ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የሲዳማ፣ የጌድኦ፣ የአማሮና ጉርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
• በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ ቅዱስ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦
በዓለም ውስጥ የሰላምና የአንድነት ማእከል ሆና ታገለግል ዘንድ ቤተክርስቲያንን በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ዐራት ዓ.ም የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ አደረሳችሁ !!
“ወሩፁ ኀበ ሰላም ምስለ ኵሉ ፤ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ” (ዕብ.፲፪፥፲፬)፤
ሁላችንም እንደ ምንገነዘበው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም መመሥረት ዋና ዓላማ ሕዝብንና አሕዛብን በክርስቶስ ትምህርተ ሰላም፣ አገናኝታ፣ አቀራርባና አንድ አድርጋ በሃይማኖት ለእግዚአብሔር መንግሥት ንጹህ ወገንን ማቅረብ ነው፡፡ ለዚህ ለተቀደሰ መለኮታዊ ዓላማ እውን መሆን ሲባል ከራሱ ከባለ ቤቱ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አንሥቶ ብዙ ቅዱሳን አበው የደም ዋጋ ከፍለዋል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ክቡር ደም አማካኝነት ድል በድል እየተሻገረችና እየተራመደች እስካሁን ደርሳለች ዛሬ በክብር የተቀመጥንበት ወንበርም የዚህ ደም ውጤት እንደ ሆነ አሳምረን እናውቃለን፡፡
በየጊዜው በኃላፊነት የተቀመጡ ቅዱሳን አበው መከራ መስቀሉን ፈርተውና ተሰቅቀው ቢያፈገፍጉ ኖሮ ይህ እኛ ዛሬ የተሰየምንበት ክብረ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚገኝ አልነበረም፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉዞ አንድ ተብሎ ሲጀመር በፍኖተ መስቀል ስለ ሆነ ፍኖተ መስቀሉ ተቋርጦ አያውቅም፤ ለወደፊትም ይቋረጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡
በዚህ ፍኖት የሚጓዙ ቅዱሳንም አይታጡም ብቻ ሳይሆን እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፤ ፍኖተ መስቀል በልዩ ልዩ ዕንቅፋቶችና መሰናክሎች የተሞላ፣ አባጣ ጐርባጣ፣ ወጣ ገባ ቢሆንም መጨረሻው ስኬትና ድል ነውና ለፍጹም ዘለዓለማዊ ሰላምና አንድነት ሲባል የሚጓዙበት መንገድ ነው፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
የዘመናችን ፍኖተ መስቀልም መሰናክሉንና ዕንቅፋቱን በሀገራችን፣ በቤተ ክርስቲያናችንና በምእመናን ልጆቻችን ጫናው እያበረታ እንደ ሆነ መጠራጠር ያለብን አይመስለንም፡፡
የምእመናን፣ የካህናትና የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳት አሁንም ገዝፎና ሰፍቶ እየቀጠለ ነው፡፡ ስጋትና ጭንቀት፣ አለመተማመንና ቀቢፀ ተስፋ ተንሰራፍቶአል፤ አብሮ ተከባብሮ፣ ከመኖር ይልቅ ሌላውን ጥሎ ኮርቻ ላይ ለመውጣት የሚደረገው እሽቅድምድም በሰፊው እየተሠራበት እንደሆነ እየታዘብን ነው፡፡
ይህንን አደገኛ አካሄድ ለማሳካት ሲባል የሚደረገው ያልነበረ ልማድም ቤተ ክርስቲያናችንን እየተጋፋ ነው፤ ምእመናንንም እያሳዘነ ነው፤
ቤተ ክርስቲያናችን በሃይማኖት ነጻነት መከበር ችግር ባይኖርባትም በአጉል ፉክክር የሚደረጉ፣ ካሁን በፊት ያልነበሩ የሥርዓተ ሃይማኖታችን አደባባዮችን ለመቀራመት የሚደረገው አካሄድ ተገቢ ነው አንልም፡፡
ይህ ሁኔታ ለሁሉም በሚበጅና ሁሉም በየራሱ የሚስተናገድበት የየራሱ የሆነ ክቡር ስፍራ አግኝቶ ሊስተናገድ የሚችልበት ሁኔታ ካልተፈጠረ ጥሩ ሊሆን አይችልም፤ ችግሩም በግልፅ እየታየ ስለ ሆነ የሚመለከተው አካል ፈጣን መፍትሔ ሊያበጅበት ይገባል፡፡
ከታሪክ፣ ከነባር ባህል ጥበቃ፣ ከሃይማኖት ክብርና መብት ባሻገር በአንድ ስፍራ ሁለት የተለያዩ ሃይማኖታውያን እንዲገለገሉ የሚደረግ ከሆነ ሁለት የተለያየ እምነት ያላቸው ሃይማኖታውያን በዓላቸው በአንድ ቀን ቢውል ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡
ሃይማኖታውያንም ለራሳቸው ሲሉ ይህንን ችግር ራሳቸው የመፍትሔ አካል መሆን የኖርባቸዋል፤ የሰላም ጠበቆች መሆናቸውንም በዚህ ሊያሳዩ ይገባል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት !!
የሰላም አስፈላጊነት በየቀኑ ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዷ ሰከንድ ለሃይማኖታችን መጠበቅና ለሕዝባችን ደኅንነት መረጋገጥ ትልቅ ዋጋ አላት፡፡
ሰላም በደፈረሰ ቍጥር የምናጣው ብዙ ነው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሰው ሁሉ ከማንም ተግባር በፊት ሰላምን መጠበቅ ላይ ቢሠራና ሰላምን ገንዘብ አድርጎ ቢመላለስ በሁሉም ነገር ስኬታማ መሆን ይችላል፡፡
በተለይም ሕዝብን በኃላፊነት በመምራት የምንገኘው ዓለማውያንም ሆን ሃይማኖታውያን ከማናቸውም ተግባር በፊት ሰላምን ማረጋገጥ ላይ መሥራት ይጠበቅብናል፤ ምክንያቱም ሃይማኖታዊም ሆነ ሀገራዊ ጥቅም ያለ ሰላም በምንም ተአምር ሊመጣ አይችልምና ነው፡፡
ሰላም ከሞላ ጐደል ፍጥረት ሁሉ የሚፈልጋት ውድ ነገር ብትሆንም መገኛዋን በተመለከተ ግን ብዙ አናውቀውም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሰላም በጕልበት አትገኝም፤ በሀብትም አትገኝም፤ በሥልጣንም ሆነ በነጠላ ዕውቀትም አትገኝም፡፡
እውነተኛዋና ዘላቂነት ያላት ሰላም የምትገኘው “ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ” በሚለው ትምህርተ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሰው ሌላውን ቸል ብሎ ራሱን ሲያስቀድም የሰላም ፀር ይሆናል፤ ራሱን ሳይሆን ሌላውን ሲያስቀድም ግን የሰላም ጠበቃ ይሆናል፡፡
በሀገራችን ተከሥቶ ሕዝባችንን እያንገላታ የሚታየው ክሥተት ይህ ራስን ማብለጥ ሌላውን ማንጓጠጥ ነው፤ ይህንን በአግባቡ አርመን አንተ ትበልጣለህ አንተ ትሻላለህ ወደ ሚል ፍና ትሕትና ካልተመለስንና ነገሮችን በፍቅር ለመለወጥ ካልጣርን የሕዝባችንን መከራ ማሳጠር አንችልም፡፡
“ዕርቅ ደም ያደርቅ” እንዲሉ የዕርቅን ጥቅም በመቀበል ወደ ተሻለ ነገር መራመድ ጊዜው የሚጠይቀን ተግባር ነው፡፡
ይህንን በማስተማርና በመምከር ሕዝቡን ወደ ዕርቅና ወደ ይቅርታ ማምጣት ደግሞ የኛው የሃይማኖት አባቶች ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ ምክንያቱም “ወደ ሰላም ሩጡ” ተብለናልና!
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!
በአሁኑ ጊዜ ከምንም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያናችን በፈተና ላይ የምትገኝበት ወቅት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፤ ደማቸው በየአቅጣጫው እንደ ጐርፍ እየፈሰሰ ያለው የልጆቻችን ብሎም የወገኖቻችን ደም ነው፡፡
በጦርነትና በድርቅ፣ እንደዚሁም በተለያዩ ግጭቶች በረኃብ እየረገፉ ያሉት እኛ አጥምቀን የሥላሴ ልጅነትን አሰጥተን በልጅነት ያከበርናቸው፣ እግዚአብሔር ጥብቅ በሆነ አደራ ያስረከበን የመንፈስ ልጆቻችን ናቸው፡፡
የእነሱ ልሳን ሆነን ዛሬ ከጎናቸው ካልቆምን ነገ የኛ አባትነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነገር ሊመጣ ይችላል፡፡
ስለ ሆነም ይህ ቅዱስ ጉባኤ፣ ራሱን ከማናቸውም አደረጃጀት ነጻ አድርጎ የሰላም ጥሪን በማሰማት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም መረጋገጥ ለሰላም በሰላም መሥራት መጣርና ውጤት ማምጣት ይጠበቅበታል፡፡

በዚህ ዙርያ ይህ ዓቢይ ጉባኤ በስፋት ተወያይቶ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ይጠበቃል፤
በመጨረሻም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው መልእክት ሰላምንና አንድነትን ለማረጋገጥ ጕልበትን እንደ አማራጭ መውሰድ አቁመን፣ የተከሠቱብንን ችግሮች በውይይትና በድርድር ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት የላቀ ድጋፍ በመስጠት በጦርነትና በረኃብ፣ በድርቅና በበሽታ እያለቁ ያሉ ልጆቻችንንና ወገኖቻችንን እንድንታደግ በእግዚአብሔር ስም በመማፀን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፤
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ ፤
ኢትዮጵያንንና ሕዝቦችዋንም ይቀድስ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን ፤
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፬ ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ -
ኢትዮጵያ ።
🔎ዩቲዩብ ቻናል➠ https://m.youtube.com/channel/UCNjEKBSeBmsSGrHdlN3aSpQ
🔎ፌስቡክ ገጽ➠https://m.facebook.com/EMislene
🔎ቴሌግራም ቻናል➠ https://t.me/EMislene
🔎ኢንስተግራም➠https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
🔎ቲክቶክ ➠ https://vm.tiktok.com/ZMdm9g2TR
🔎ድረ ገጽ➠ https://www.debregelila.org
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
Subscribe_Share_Like_Comment

💚💛❤️ "ሰላም ለፍልሰተ ሥጋከ፡፡ እምውሳጤ ገዳም ዔላመ። ወእምነ ዔላምኒ ደብረ ሊባኖስ ዳግመ። ተክለ ሃይማኖት ባህለ ከመ ወንጌላዊ ቀደመ። እመ ረከቡ ደቂቅከ በዓለም ሕማመ። በኀቤከ፡አባ ይርከቡ ሰላመ"። ትርጉም፦ ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ከገዳመ ዔላም (ደብረ አስቦ) ወደገዳመ ደብረ ሊባኖስ ለፈለሰው ሥጋህ ሰላም እላለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፤ ስብከተ ወንጌላዊ ስብከት ነው እኮን። አባት ሆይ ልጆችህ በዚህ ዓለም ብዙ መከራ ቢያገኛቸውም በአንተ ዘንድ ፍጹም ሰላምና ዕረፍትን እንደሚያገኙ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ። መልክአ ተክለሃይማኖት።
የመነኰሳት ሁሉ አለቃ ሐዋርያ ሰማዕት የታላቁ መምህር የክቡር አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሥጋው ፍልሰት፦ የፍልሰቱም ምክንያት በሃምሳ ስድስት(57) ዓመት ከዋሻ (ደብረ አስቦ) ውስጥ ወደ አነፁልህ መቃብር ያፈልሱታል ብሎ እግዚአብሔር የነገው ዘመን በደረሰ ጊዜ ያንጊዜም ተአምር ተደርጎ ዕውራን አዩ አንካሶች ተስተካከሉ።
ይህም በወራሴ መንበሩ በአባ ሕዝቅያስ ዘመን ሆነ ዕለቱም ግንቦት ዐሥራ ሁለት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ተጋዳይ በሆነ ሰው በጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጌታን ደስ በአሰኙት በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 12 ስንክሳር።
https://t.me/semaet

The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 29 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.