Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👍8🥰4😍2❤1🙏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤6👍3😍3🙏1
KB CREATIVES™
ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት #Orthodox #Quote #Profile #Post #Story ✨@KB_Creatives✨
ነሐሴ ፲፪
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስከ አሸነፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።
ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እናደርግ ዘንድ አዘዙን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
✨@KB_Creatives✨
❤4🥰2😍2👍1🙏1
📖🧐📖 ከአነበበነው የቀረበ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
┏━━━━° •❈• ° ━━━━┓
#ደብረ_ታቦር #(ቡሄ)
┗━━━━° •❈• ° ━━━━┛
👉#ደብረ_ታቦር የሚለው ቃል የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን ደብር ማለት ተራራ ማለት ሲሆን ታቦር ደግሞ በእስራኤል ከገሊላ ባህር በምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ 572 ሜትር ከፍታ የሚደርስ ቅዱስ ተራራ ነው
👉 ለምን ይከበራል?
ደብረ ታቦር የሚከበርበት ምክንያት የእግዚአብሔር ምስጢረ መንግስት በምስጢረ ሥላሴ የተገለጠበት አንድም ምስጢረ ሐዋርያትን አስከትሎ መለኮታዊ ክብሩን የገለጠበት የፍስሐ በዓል ስለሆነ ።
👉 ክርስቶስ ስለምን መለኮታዊ ክብሩን በታቦር ተራራ ላይ ለሶስት ሐዋርያት ገለጠ ቢሉ?
💡 በተራራ መሆኑ ተራራ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ሶስቱ ሐዋርያት የነገደ ሴም የነገደ ካም የነገደ ያፌት ምሳሌ ለእናንተ ትገባለች ሲል አወጣቸው አንድም
💡 ተራራ የወንጌል ምሳሌ ተራራ ሲወጡ ያስቸግራል ከወጡ በኋሏ ግን ሁሉን ያሳያል ወንጌልም ሲማሯት ታስቸግራሉች ካወቋት በኅሏ ግን ኅጢይቱንና ጽድቁን ለይታ ታሳውቃለች ሲል
👉ለምን በታቦር ተራራ ቢሉ
?
💡ትንቢት ተንግሯልና ይፈጸም ዘንድ
ዳዊት በመዝሙሩ ታቦር ወአርሞንኤም ይትፌስሑ በስመ ዚአከ (ታቦርና አርሞንኤል በስምህ ደስ ይላቸውል) ተብሏልና ) ሁለመናው እንደ ፀሐይ አበራ ብርሃኑም ከታቦር ተራራ ተነስቶ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ታይቷልና እረኞችም ደስታ አርገዋልና ሲል አንድም
💡በከተማ ቢያደርገው አይሁድ ከግርማው አይተው ፈርተው አይስቅሉትማና ሲሸሽግባቸው ነው
KB CREATIVES™
Photo
👉ስለምን ሶስቱን ሐዋርያት መርጦ አወ
ጣ?
💡 ስለ ፍቅራቸው ፤ ስለባለሟልነታቸው ሲል
💡አንድም ይሁዳን ምክንያት ለማሳጣት።
💡እምነት ተስፋ ፍቅር ምስሌ ነውና
ጴጥሮስ = የእምነት
ዮሃንስ = የፍቅር
ያዕቆብ = የተስፋ
እንዚህ ሶስቱ ወደ እርሱ ያቀርባሉና
ሲል
👉ከነቢያት ስለምን ሙሴ ኤልያስን
መረጠ
💡አስቀድሞ ጌታ ሐዋርያትን ህዝቡ እኔን ማን ይለኛል ብሎ ጠይቋቸው ነበርና እነርሱም አንዳድች ከነቢያት አንዱ ተነስቷል ይላሉ አንዳንዶች ኤልያስ ነህ ይላሉ ብለው ነበርና
#እኔ ኤልያስም ሙሴም አየደለሁም የእነርሱ ጌታ ነኝ ሲል ሙሴንም ቀሰቀሰው ኤልያስንም ከብሔረ ህያዋን አመጣው አንድም
💡 ምሳሌ እኔ የህያዋንና የሙታን አምላክ ነኝ ሲል አንድም
💡ምሳሌ ሙሴ የትህትና ኤልያስ የቀናዒነት እነዚህ ሁለቱም የተወደዱ ናቸው ሲል ተነጋግሯ
ቸዋል══════
══════ ❁✿❁
✝ለሐዋርያት ምስጢሩን ክብርን እንደገለጠ ለእኛ አዕምሮውን ልቦውን ማስተዋሉን ይግለጥን እምነትን ተስፋን ፍቅርን ትህትና ቀናኢነትን ያስድርብን✝
- መልካም ደብረ ታቦር -
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✨@KB_Creatives✨