Seid Al-jeylani
10.3K subscribers
241 photos
61 videos
62 files
178 links
❤️‍🩹 وما من كاتـب إلا سـيفنى ويبقى الدهر ما كتبت يداه
فلا تكتُـب بكفك غير شيء يسـرك في القيامة أن تراه ☘



.


.
For any comment 👇
📧 @Islamic_path_bot
Download Telegram
የኢማን መዳከም ምልክቶች፦
* አዛን እየሰማህ ምላሽ አለመስጠትህ።
* የፈጅር ሶላት አምልጦህ ግድ የለሽ መሆንህ።
* ቁርኣንን ትተህ (ርቀህው) ሳለህ አለመፍራትህ።
* መልካም ነገር ስትነፈግ ግድ የማይሰጥህ መሆንህ።
* ከመልካም ጓደኞች ስትነጠል (ስትርቅ) እረፍት ማጣት አለመሰማትህ።
* ወንጀልን ሰርተህ አለማዘንህ።
* የዕለት ተዕለት የቁርኣን እና የአዝካር ዊርድ የሌለህ መሆንህ።
ተጠንቀቅ!
ሞት ቅርብ ነው፤ የሚመጣውም በድንገት (ሳይታሰብ) ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቁርዓን ቲላዋ
#أحمد_بن_طالب

ለምትወዱት ሰው ሼር አድርጉለት🙌
https://t.me/QuranForQalb
https://t.me/QuranForQalb
🚫 በሶስት ነገር ጊዜ ከማባከን ተጠንቀቅ !

➖ ባለፈ ነገር በመፀፀት አይመለስምና !
➖ ራስህን ከሌላ ጋር በማወዳደር አይጠቅምህምና !
➖ ሁሉንም ለማስደሰት በመሞከር አይቻለረምና !
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
① መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ  እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ  ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ)  የአላህ መልእክተኛ  እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
❤2
ያ ረብ! የኔ ባልኾነ ነገር ላይ ልቤን አታንጠልጥልብኝ፣ዓይኔም የኔ ያልኾነን አይከጅል፣በማላገኘው ነገር ላይ ሀሳቤ አይበታተን።
👍2
​ኢላሂ...
እኛ ሁላችንም ፈላጊዎችህ ነን። ሀብታሙም በውስጡ ድሃ ነው፤ ጤነኛውም በውስጡ ደካማ ነው። ያገኘውም ያጣውም፣ የተማረውም ያልተማረውም፣ ትልቁም ትንሹም... ሁላችንም በአንተ ፊት እኩል ድሆችና ያንተ እገዛ የሚያስፈልገን ፍጥረታትህ ነን። የውስጣችንን የማይነገረውን ምስጢር፣ ማንም የማያይልንን ስውር ስብራትና ጭንቀት የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ።

ኢላሂ...
◈​ያጣውና የቸገረው... ከአንተ ሰፊ ሲሳይ ስጠው።

◈​የታመመውና በአልጋ ላይ ያለው... በፈውስ እጅህ ዳስሰው።

◈​ልቡ የተሰበረውና የተገፋው... አንተ መጠጊያ ሁነው።

◈​መንገዱ የጠፋበትና የጨለመበት... ብርሃንህን አብራለት።
🔷 ጓደኛህ ማን መሆን እንዳለበት ከወዲሁ እወቅ

ኢማም ማሊክ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :-

"ቃላቱ እውቀትን ከሚጨምርልህ ፣ ተግባሩ ወደ መጨረሻው አለም ከሚጠራህ ሰው ጋር መቀመጥ አለብህ። ቃላቱ ከሚያደናግርህ ፣ ሀይማኖቱ ጉድለት ካለበት እና ተግባሩ ወደዚህ አለም ከሚጠራህ ሰው ጋር ከመቀመጥ ተጠንቀቅ"

ترتيب المدارك ١/٤٤٢
👍1
ነቢዩ ሙሳን عليہ السلام
እና ተከታዮቻቸውን ከበዳዩ ፊርዐውን ግፍ ያዳነውና ባህሩን ያለመርከብ በሰላም ያሻገራቸው አላህ
سبحانہ وتعالى
ከሁሉም ዓይነት የዱኒያና የኣኺራህ
ሃሳብ፣ ጭንቀትና ስጋት እራሳችን፣ ቤተሰብና ኡመታችንን በሙሉ ይገላግለን
ሀገራችንም ሰላም ያድርግልን
ከሁሉም በፊት እራስህን አስተካክል!!
———
ኢብኑ ቁዳመህ አል-መቅዲሲይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-

“እራስህን ከማስተካከልህ በፊት ሌሎችን በሚያስተካክል ነገር ከመወጠር busy ከመሆን ተጠንቀቅ!። ውስጥህን በማስተካከልና ከሚወገዙ ባህሪያት በማፅዳት ተወጠር!፣ እላይህን ከማስተካከልህ በፊት ለዱኒያ ከመጓጓት፣ ከምቀኝነት፣ ከይዩልኝ፣ በራስ ከመደነቅ ውስጥህን አፅዳ!።” [ሙኽተሶር ሚንሃጁ'ል ቃሲዲን ገፅ 20]
👍1
የማይበጀኝን መንገድ ስመርጥ፣ እኔን ለማዳን ሲል እቅዴን የሚያበላሽብኝ እርሱ ምንኛ መሐሪ ጌታ ነው!

አሁንም እዝነትህን የኔ ጌታ።
❤2
❝አላህን በማያስደስት መንገድ የተጀመረ መጀመሪያ፣ ፍጻሜው ባለቤቱን አያስደስተውም።❞
ከማንም ምንም አለመጠበቅ

ከአንገት እንጂ ከአንጀት የሚያወራ ቁምነገረኛ ሰው በጠፋበት በዚህ ዘመን፤

ካንተ ጋር ቃል ገብቶ ዘወር ብሎ ከሌላ ጋር የሚደራደር በሞላበት በዚህ

መጣሁ ብሎ ቀረሁ እኮ ማለት እጅግ ተራ ነገር በሆነበት በዚህ ወቅት፤

ብቻ በአጠቃላይ መልካም እሴቶች እየተሸረሸሩ ባሉበት ዘመን ሕይወታችሁን ቀጥ አድርጋችሁ ለራሣችሁ ኑሩ እንጂ ወደ ሰዎች ብዙ አትመልከቱ፡፡ ማንንም አትጠብቁ፤ ከማንም አትጠብቁ። ብዙዎቻችን ወደኋላ ያስቀረን መጠበቅ ነው፡፡ መጠበቅ ያደኅያል፣ መጠበቅ ከሰው ያስከጅላል፣ መጠበቅ አላህን ያስረሳል፣ መጠበቅ ያሰንፋል፣ ልብን ያንጠለጥላል፣ ሞራልን ይሰብራል ... አንዳንድ ጊዜ መጠበቅ መልካም ቢሆንም ግና ፍፁም በሆነ መልኩ ሰው ላይ በመደገፍ መሆን የለበትም።

ነብዩ ዩሱፍ ዐ.ሰ. ለአላህ አደራህን አምላኬ ማለት የነበረባቸዉን ነገርእረስተው ከእስር ለተፈታው ባልደረባቸው እንዳትረሳኝ አሉት፡፡ ግና እሱ ጉዳያቸዉን ረሳ፡፡ አላህ ግን አልረሣቸዉም።

አባታችን ሊሞትልን ነው ብለው የአባታቸውን ሀብት ለመውረስ ሲጠብቁ ስንቶች ድሆች ሆነው ሞተዋል!

ያገባኛል / ታገባኛለች ብለው ሲጠብቁ ስንቶች ተከዳን ብለው እሪ ብለዋል፡፡

በርግጠኝነት መጠበቅና _ በርሱ ላይ እራሣችንን ልንጥል የምንችለው አምላካችንን አላህን (ሱ.ወ.) ብቻ ነው፡፡ እሠጣለሁ ብሎ ቃሉን የማያጥፍ፣ እመጣለሁ ብሎ የማይቀር ከርሱ ወዲያ ማን አለ!!።
❤2👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ
በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡

يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ
ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡

إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»

[سورة الشعراء]
ኢላሂ!

~ ባንተ ታውቀን ባንተ ከሚያምፁት አታድርገን፣ለሰው ጠቁመን ተቃራኒውን ከሚጓዙ አታድርገን፣ በአፍ ቀርበውህ በተግባር ከሚርቁህ አታድርገን፣ በምላስ ከሚያመልኩህ በልቦና ከሚሸሹህ አታድርገን፣አለባበሣችንን እንዳሳመርክ ዉስጣችንን አሳምርልን!
ኢማም ፉደይል ቢን ዒያድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"ሙእሚን ንግግሩ ጥቂት ነው፣ ሥራው ግን ብዙ ነው። ሙናፊቅ ደግሞ ንግግሩ ብዙ ነው፣ ሥራው ግን ጥቂት ነው።"

እንዲሁም እርሳቸው (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"ከጁምዐ እስከ ጁምዐ ድረስ የተናገረውን ቃል በጥንቃቄ የሚቆጥር ሰው አውቃለሁ።
"
ትልቁ ኪሳራ ማለት...ጀናዛው ላይ ሊሰገድበት ብቻ ተብሎ መስጊድ የገባ ሰው ነው።
ልትቀበር ተብላ በከፈን ጊዜ ብቻ ሒጃቧን ፀጉሯን የሸፈነ ሴት ናት።ጌታዬ ሆይ በዲንህ ላይ አጽናን።መልካም መመለስን ወዳንተ መልሰን።
🥰1
ኢላሂ...ፍጡራን ሁሉ ቢወዱኝም ሆነ ቢጠሉኝ ግድ የለኝም፤ የእኔ ትልቁ ጭንቀት በአንተ ዘንድ ያለኝ ስፍራ ብቻ ነው። ኢላሂ! ሰዎች ከሚያዩት ውጫዊ ማንነቴ ይልቅ በአንተና በእኔ መካከል ያለውን አሳምርልኝ!
👍3❤2
ወንጀል ከሰራህ በኋላ ምንም እንኳን ትንሽ ገንዘብ ቢሆን ሰደቃ ስጥ፤ ምክንያቱም ሰደቃ የኃጢአቱን መጥፎ ተጽእኖና መዘዝ በአላህ ፈቃድ ታስወግዳለች።

— ሸይኽ ዐብዱስሰላም አሽ-ሹወይዒር
❤3
በቢሊዮን ከሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች መሃል ሙስሊም ሆኖ መገኘትን የመሰለ ታላቅ ጸጋ ይዞ ማማረር እንዴት ይሆናል? ሙሊም ከመሆን በላይስ ምን ፀጋ አለ!?

ኧረ አልሐምዱ ሊላህ እንበል!
❤2
ያለ ስራ ምኞት ቂልነት ነው ።

قال يحيى بن معاذ -رحمه الله - :

أعظمُ الاغترَار: التمادِي في الذنُوبِ
معَ رجَاء العَفْو مِن غير ندامَة ،
وتوقّع القُرب من الله بغير طاعَة ،
وانتظَار زرْع الجنّة بِبَذر النار ،
وطلَبُ دَار المطيعينَ بالمعاصِي ،
وانتظار الجزاء بغير عمَل ،
والتمنّي علَى الله مَعَ الإفرَاط.

تزكية النفوس(١١٤).

🔷  የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ የተባሉ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላሉ :-

" በጣም ትልቁ መታለል በወንጀል መዘውተር ነው ። ያለ ፀፀት የአላህን ምህረት , መከጀል
ትእዛዙን ሳይፈፅሙ ወደ አላህ ለመቃረብ መጠበቅ , የእሳት ዘር እየዘሩ የጀነት ፍሬ መጠባበቅ , ወንጀል እየሰሩ የአላህን ታዛዦች ሀገር መፈለግ , ያለ ሥራ ምንዳ መፈለግ ,
ምንም ሣይሠሩ በአላህ ላይ ተስፋ ማድረግ " ናቸው ።
አንዳንዶቻችንም ምንም የማይጠቅም የእርዳታ ጩኸት ይጮኻሉ።
አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿قال رَبِّ ارْجِعُونِ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا ۖ وَمِنْ وَرَائِهِمْ بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ﴾
እንዲሁም አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿وَأَنْفِقُوا مِنْ مَا رَزَقْنَاكُمْ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَا أَخَّرْتَنِي إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُونَ مِنَ الصَّالِحِينَ﴾
እንዲሁም አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي﴾
ስለዚህ ገና ዕድሜ እያለን ሳለ፣
እንመከር፣ እንለወጥ።
❤1