Seid Al-jeylani
11.3K subscribers
231 photos
59 videos
62 files
176 links
❤️‍🩹 وما من كاتـب إلا سـيفنى ويبقى الدهر ما كتبت يداه
فلا تكتُـب بكفك غير شيء يسـرك في القيامة أن تراه ☘



.


.
For any comment 👇
📧 @Islamic_path_bot
Download Telegram
አንዳንዴ በጀርባህ ላይ የተሸከምከው ከባድ ሸክም ለደህንነትህና ለሕይወትህ መትረፍ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የተሸከምከው ሸክም ምንም ያህል ቢከብድ 'አልሐምዱሊላህ' በል። ምክንያቱም ያ ሁሉ አንተ አሁን ለማታየውና ወደፊት ለሚያገኝህ መልካም ነገር መሆኑን እወቅ።
❤1
★ በሕይወት ውስጥ አንዴ ከሄዱ የማይመለሱ ሦስት ነገሮች።

ጊዜ ፣ ቃል እና አጋጣሚ


★,በሕይወት ውስጥ ልታጣቸው የማይገቡ ሦስት ነገሮች

ሰላም ፣ ተስፋ እና ታማኝነት

★, በሕይወት ውስጥ እጅግ ዋጋ ያላቸው ሦስት ነገሮች

ፍቅር ፣ እምነት እና ባልንጀሮች

★,በሕይወት ውስጥ እርግጥ ያልሆኑ ሦስት ነገሮች

ሕልም ፣ ስኬት እና እድል

★,አንድን ሰው ሰው የሚያደርጉ ሦስት ነገሮች

ጠንክሮ መስራት ፣ ቅንነት እና ጽናት

★,በሕይወት ውስጥ አንድን ሰው ሊያጠፉ የሚችሉ ሦስት ነገሮች

ሱስ ፣ ትዕቢት እና ጭንቀት
ከሰው ጋር መኖር ላደከማቸው ነፍሦች ሁሉ ብቸኝነትን የመሠለ አገር የለም፡፡
👍4
በሰው ሰራሽ ህግጋት እንኳ ጥፋትን አምኖ መቀበልና መጸጸት ከቅጣት ማቅለያ መንገዶች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። ታዲያ በፈጣሪ ፊት ስንቀርብማ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ትርጉም ይኖረዋል። ራሳችንን እንከን እንደሌለብን አድርገን ከማሰብ ይልቅ፣ የሰራነውን ስህተት አምነን በዝቅታ ወደ እርሱ መቅረብ ለይቅርታና ለምህረት ዋነኛው ቁልፍ ነው።

ጌታዬ ሆይ! በእርግጥም አጥፍቻለሁ፤ ወደ አንተም ተመልሻለሁ!
👍2
ወዳጄ ሆይ


ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ።
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌🔖 በመኖርህ ውስጥ ስለኖሩልህ ሰዎች ውለታ ታስባለህ። በአንፃሩ ስለምትኖርላቸው ሰዎች እጣ ፈንታም ትጨነቃለህ። ህይወት ፍቅርን ታስተምርሀለች። በልምድ ጉዞህ ውስጥ ሰውን በማንነቱ መምረጥ ትችላለህ። ማንን መውደድ እንዳለብህም ትገነዘባለህ። በተለያዩ ክስተቶች መሀል የእውነት አንተን የሚወድህ ማን እንደሆነም ታውቃለህ ። ክስተቶች ሰዎችን ያበጥራሉ። ምርጫህን ለይ !!!
❤1
ሶብር



ትግስት የዚህ አለም ሀብት የመጭው አለም ስኬት ናት። አላህ ለታጋሾች ትልቅ ስጦታን ሰጣቸው በገነትም አበሰራቸው።

وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡

''ትግስት ከኢባዳዎች አንዱና ምንዳውም የላቀ ነው። አላህ ትእግስትን ከሶላት ጋር አብሮ በማቆራኘት ጠቅሶታል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡

الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَالصَّابِرِينَ عَلَىٰ مَا أَصَابَهُمْ وَالْمُقِيمِي الصَّلَاةِ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን፣ በደረሰባቸውም (መከራ) ላይ ታጋሾችን፣ ሶላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን (አብስር)፡፡

''ሳትፈተንና መከራን ሳትቀምስ ጀነትን የምታገኝ መሰለህን? አስታውስ! ጀነት ለነዚያ መከራና ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እንዲህ ለሚሉት ናት ።


الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡
አዲስ አፕ ተለቀቀ

🎗 የ አል-ዐቂደቱል ዋሲጢያህ ኪታብ ማብራሪያ

👤የደርሱ አቅራቢ ፡
ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

📗የኪታቡ ይዘት፡ መሰረታዊ የአህሉስ-ሱንና ወልጀመዓን ዐቂዳ የሚያስረዳ አጭር ኪታብ

✍ የኪታቡ ፀሐፊ ፡
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ

🎙88 ኦድዮዎችን የያዘ 448MB

በተጨማሪም

✍በአቡ ፈውዛን አህመድ በፅሁፍ የተዘጋጀውን የሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ አጭር የህይወት ታሪክና

✍ በኢብን ኡሰይሚን የተዘጋጀውን ሙዘኪራ - የአል ዐቂደቱል ዋሲጢያ አጭር ማብራሪያ - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትርጉም ሾል አካቷል

የኪታቡን ማብራሪያ አፕ ሼር ለማድረግ
https://t.me/ustazilyas/1758

ሙሉ የኪታቡን ማብራሪያ ያለ አፕ ለማግኘት
https://t.me/ustazilyas/1499

ለመሰል ስራዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ። ቃሲም አፕ https://t.me/kasimApp

__
@ustazilyas
ለጊዜው ተሸሽጎ የቆየ ማንነት ፍጻሜው ሲቃረብ መጋለጡ አይቀሬ ነው፤ ጭንብል ተለብሶ ቢኖርም እውነተኛው ባሕሪ አንድ ቀን አፈትልኮ ይወጣል። ሰው በሕይወት ዘመኑ ሲያዘወትረው በነበረው ተግባር ላይ ሕይወቱ ያልፋል፤ በዚያው በለመደው ማንነቱም ለፍርድ ይቀርባል። ስለሆነም፣ የነገውን ውርደት ለማስቀረት ዛሬውኑ ራስን መመርመርና መጥፎ አመሎችን ማረም ብልህነት ነው።
🥰2
ምኞት አየለና ቀደሩን አስረሳን፣
ለጥቂት ቀን ፈተና ሰላምን አጣን።

የነገው ሲጨንቀን የዛሬው ሲገፋን፣
የዓለሙ ጌታ መኖሩን ዘነጋን።
🥰3
ራስህ ለራስህ የገባኸውን ቃል ስንቴ እንደካድከው ካስታወስክ ፤ የሰዎች ታማኝ ሆኖ አለመገኘት ብዙ አይገርምህም።
እኔ አልችልበትም...


ለጊዜያዊ ጥቅም ብዬ ቃላቶቼን በውሸት ማር ለውሼ ሰውን ማባበል፣ በሐሰት አሳምኖ ሰውን ከጎን ማቆየት፣ እውነትን ደብቆ ውሸትን ማንገስ፣የሌለ ማንነትን እንደ ጌጥ ተከናንቦ መታየት፣ አዎ እኔ አልችልበትም!

ሰውን አታልዬ በዙሪያዬ ከማሰባሰብ፣ በእውነተኛነቴና በቅንነቴ አጥቼ ከራሴ ጋር በሰላም ብቻዬን ብቀር እመርጣለሁ፡፡
ያለ ቁርአን  ሕይወት ባዶ ናት።
ወላሂ ባዶ።ተማሩት አጣጥሙት።
🥰3
«ቀልብ ዉስጥ አላህን ማውሳት ብቻ እንጂ ሌላ ምንም ነገር የማይሞላቸው ክፍተቶች አሉ። »ይላሉ ኢብኑል ቀይም―ሱብሓነላህ! አልሐምዱ ሊላህ! ላ ኢላሀ ኢልለላህ! አላሁ አክበር!―ማለትን አብዙ።

ከሰብሒ በፊት ጥቂት ቀደም ብሎ ያለው ጊዜ የኢስቲግፋር ነው። ረጋ፣ ሰከን ያለ ወቅት ነው። በሁለት ረከዓ ሶላትም ይሁን በሁለት ዘለላ እንባ ዱዓ ማድረግ መመረጥም መታደልም ነው።
🌹እንኳን አደረሳችሁ🌹

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
وعيد مبارك
أعاده الله عليكم وأنتم في صحة وعافية وإيمان

እንኳን ለ1447 ኛው የዒድ አል_አድሃ  በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!


EID MUBAREK
ኢድ ሙባረክ  🕊
አንዳንዴ መጨከን ግድ ይላል
~
አንዳንድ ዉሳኔዎችን ለመወሰን ጨካኝ መሆን ግድ ይለናል፡፡ ዱንያ ላይ ስንኖር ተወዶ አይደለም እኮ የሚጨከነው፡፡ ካልጨከኑ የሚጠበቀው ፍሬ አይገኝም፤ ከሚታለመው ዉጤት አይደረስም፡፡ በድሎት ላይ ተሁኖ ከድሎት አይደረስምና መጨከን ግድ ይላል፡፡ ምቾት ላይ ተሁኖ ምቾት አይመጣምና መራራ ዉሳኔ መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ኮረኮንች ላይ ሳይሄዱ ከአስፋልት መድረስ የለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ራሣችንን ለመቻል ከሰው መነጠል፣ ዉጤታማ ለመሆን ከአገር መራቅ፣ የኢኮኖሚ አቅማችንን ለማሳደግ ያለ እረፍት መሥራት ግዴታ ይሆናል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ዕውቀታችንን ለማሳደግ እንቅልፍ ማጣት፣ ተሻሽሎ ለመምጣት መሰደድ፣ ከድህነት ለመውጣት ብዙ መሥራት፣ ለመለወጥ መከራን መጋፈጥ፣ ለመጥገብ ሲሉ መርራብ፣ ከፍ ያለ ሰው ለመሆን መዋረድ ግድ ይላል፡፡

አንዳንዴማ እንደገና ለመታደስ መሰበር፣ የተሻለ ነገር ለማግኘት ከታች መነሳት፣ በዘላቂነት ለመዳን መርዝ መጠጣት፣ ቆሞ ለመሄድ ብዙ መታገስ፣ ነገን ለማየት ዛሬን መቸገር፣ በእጅ ያለን ነገር ዋጋ ለማወቅ ማጣት፣ ጠንክሮ ለመውጣት መውደቅ፣ ተነፋፍቆ ለመገናኘት መለያየት፣ ሁሉ ነገር እንደማይዘልቅ ለመረዳት መደሕየት እና ሌላም ሌላም ያስፈልጋል፡፡

ሕይወት እንዲህ ናት፡፡ መቸገር፣ መክሰር፣ መጎዳት፣ መቁሰል፣ የሕይወት አካል ነው፡፡ ይበርደኛል፣ ይርበኛል፣ ይጠማኛል፣ ይቸግረኛል፣ አልቋቋምም፣ አልችልም ... እያሉ ሁሌም እትት ብትት ማለት፤ ከምቾት ክልል ዉስጥ ላለመውጣት ሰበብ መደርደርዉድቀትን ያፋጥናል እንጂ ስኬትን አያመጣም፡፡ ትርፉም ራስን መጉዳት ነው የሚሆነው፡፡ አለመጀገን፣ አለመወሰን፣ መፍራት፣ መግደርደር፣_ መጠራጠር፣ አለመጀመር ዋጋ ያስከፍላል፡፡

ሰንደል ሲያቃጥሉት መልካም ሽቶ ወጣው፡፡ ብረት ሲያቀልጡት ጠነከረ፡፡ የረጋ ዉሃ ሳይሆን ትልቅ ማዕበል ነው ብርቱ ዋናተኛን የሚፈጥረው፡፡ ጀግና በጦርነት መሃል ነው የሚወለደው፡፡ መቃጠልን፣ መቅለጥን፣ መገፋትን አትፍራ፡፡ መከራን ያሳወቀ ጦርነት ጠቀመን፡፡ ችግርን ላስለመደን ስደት ምስጋና ይገባል፡፡ ፅናትን ከነርሱ ተማርን፡፡

ዱንያ የልፋት አገር ናት፡፡ በየቀኑ ከመኝታህ ስትነሳ መጀመርያ ላይ ማስታወስ ያለብህ ሙሉ ቀኑን ብቻ ሳይሆን ዕድሜ ልክህን ልፋት እንደሚጠብቅህ ነው፡፡

~
ከ"ሰባሐል ኸይር " መፅሀፍ  ከገፅ 70 🙌