ISLAMIC SCHOOL
12.5K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.08K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀልብ ላለው ሰው ትልቅ ምክር ከሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ!!!:

ምንም የሚጠቅም ነገር ሳታገኝና ሳትሰራ ጊዜህ ካለፈ፣ እድሜህም ዝም ብሎ ከገፋ፣ የጊዜን በረካ ከተነፈግክ ይህ የአሏህ ቃል አንተንም አግኝቶህ እንዳይሆን ተጠንቀቅ!
ﻭَﻟَﺎ ﺗُﻄِﻊْ ﻣَﻦْ ﺃَﻏْﻔَﻠْﻨَﺎ ﻗَﻠْﺒَﻪُ ﻋَﻦْ ﺫِﻛْﺮِﻧَﺎ ﻭَﺍﺗَّﺒَﻊَ ﻫَﻮَﺍﻩُ ﻭَﻛَﺎﻥَ ﺃَﻣْﺮُﻩُ ﻓُﺮُﻃًﺎ
<< ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ >>

አንዳንዱ ሰው አሏህን በተመስጦ ሳይሆን ዝም ብሎ በማነብነብ ብቻ አሏህን ይዘክራል። ይሄ ምንም አይጠቀምም። አሏህን በቀልብ አለማስታወስ በስራም ላይ በጊዜም ላይ በረካ ያሳጣል። ነገሩ ሁሉ የተምታታ እስኪሆንበት ድረስ። አንዳንዴ ምንም ነገር ሳይሰራ ረጅም ሰአት ያሳልፋል። ነገር ግን ነገሮችን ከአላህ ጋር ያደረገ ሰው በሁሉም ተግባሩ በረካን ያገኛል።

ተፍሲሩ ሱረቱል ካህፍ
[ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ]

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረመዳንና የለውጥ ክፍሎቹ

እንኳን ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የረመዳን ወር ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ታላቅ ወር ነው፡፡ ረመዳን ለአጠቃላይ ማንነታችን ነፍስን ለማስተካከልና ለማረቅ ውድ የለውጥ አጋጣሚም ነው፡፡ ይህ የተላቀ ወር የለውጥ ክፍሉ በፆም ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ እውነተኛ የአላህ ፍራቻን ያጎናፃፋል፡፡ሙስሊሞች ከፆሙና ከያዘው ሀይማኖታዊ ፋይዳ አንፃር የመንፈሳዊና የስነምግባር ከፍታ የሚገኝበት ወር እያሉ ይሰይሙታል፡፡
የለውጥ ክፍሎቹ ከሁኔታ ወደ ሁኔታ፣ ከግለሰብ ወደ ግለሰብ፣ከቦታ ወደ ቦታ፣ ከባህሪ ወደ ባህሪ ልዩነት ሲኖረው በአጠቃላይ ሙሉ የለውጥ ክፍሎችን ይዳስስልናል፡፡

1- ሙስሊም ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት

በዚህ የተቀደሰ ወር አንድ ባሪያ ከፈጣሪው አላህ ጋር የሚኖረው ግንኙነት እጅግ ከፍ ብሎና ልቆ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ቀረቤታ በዚህ ወርም ሆነ በተቀሩት ወራትም የሚቀጥልና ግዴታ ነው፡፡ የረመዳን ጌታ የተቀሩት ወራትም ጌታ ነውና፡፡ የአላህን ትእዛዛትን መፈፀም ሆነ ከእርሱ ጋር ያለውን ቀረቤታ ለአንድ ወር ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ይህ የለውጥ መንገድ ቀጣይነት ያለውና ዘወትር ትእዛዝን በመፈፀም የታጀበ ነው፡፡ይህ ጉዞ ዘውታሪነትን አንዲላበስና እስከእለተ ፍፃሜ መቃረቢያ እንዲሰነብት ደረጃ በደረጃ የሚያበቃው ነው፡፡
فعن عائشة – رضي الله عنها – أنها قالت: سئل النبي – صلى الله عليه وسلم -: أي الأعمال أحب إلى الله؟
 قال: ((أدومُها وإن قل))
 አዒሻ(ረዐ) በዘገበችው ሀዲስ ላይ እንዲህ ትላለች፡፡ መልእክተኛው(ሰዐወ) ተጠየቁ፡ የትኛው ስራ ነው ወደ አላህ የተወደደ ?            እንዲህ ሲሉ መለሱ፡ (ዘውታሪ የሆነው…ትንሽ እንኳ ቢሆን!)

2- ሙስሊም ከነፍሱ ጋር ያለው ግንኙነት

የረመዳን ወር ነፍስን ለመታደግ፣ እርሷን ለመተሳሰብ፣ወደ መልካም ቦታ ለመግራት መልካም የለውጥ አጋጣሚ ነው፡፡ ለውጥ የሚጀምረው ነፍስን ከማስተካከል ነው፡፡ ያለባትን ስህተት ለማስተካከል ሁልጊዜ የሚቀጥልና ተከታታይ ልማድ ሆኖ የሚቀር ክትትል ያስፈልጋታል፡፡ ይህ ክትትል ግለሰቡን ወደ ተሻለ መስመር ያደርሰዋል፡፡
يقول الحسن البصري – رحمه الله – : “المؤمن قوَّام على نفسه، يحاسب نفسَه لله – عز وجل – وإنما خفَّ الحسابُ يوم القيامة على قومٍ حاسَبوا أنفسَهم في الدنيا، وإنما شقَّ الحساب يوم القيامة على قوم أخَذوا هذا الأمرَ من غير محاسبة”.
ሀሰን አልበስሪ (ረዐ) እንዲህ ይላሉ፡ ሙእሚን የራሱ ነፍስ ላይ ብርቱ ነው፤ ለአላህ ብሎ ነፍሱን ይተሳሰባል፤በዚህ አለም ላይ ነፍሳቸውን የተሳሰቡ ሰዎች አላህ(ሱወ) ነገ (የውመል ቂያማ) ሂሳባቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ ነፍሳቸውን ከመተሳሰብ የተዉ(የተዘናጉ) ሰዎችን ደግሞ አላህ ሂሳባቸውን ያከብድባቸዋል፡፡

3- ሙስሊም ከቤተሰቡና ከቅርብ ዘመዶቹ ጋር ያለው ግንኙነት

ሰዎች በበርካታ ጉዳዮቻቸው ተወጥረው በሚገኝበት በዚህ ጊዜ የዘነጉት ነገር ቢኖር ዝምድና ነው፡፡ቤተዘመድን ለመጠየቅና ለመንከባከብ ይህ ወር እጅግ ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ረመዳን በዝምድና መካካል ቀጣይነት ያለውን ትስስር የሚጀመርበት ታላቅ ወር ነውና ተጠቀምበት፡፡ ይህ የነብዩ ሀዲስ ብቻውን የሚበቃን ይመስለኛል፡፡
حديث النبي – صلى الله عليه وسلم – عن الرحم، حيث قال: ((إن الله خلَق الخلْق، حتى إذا فرغ من خلقه، قالت الرحم: هذا مقام العائذِ بك من القطيعة، قال: نعم، أما ترضين أن أَصِل من وصلك، وأقطع من قطعك؟ قالت: بلى يا رب، قال: فهو لك))،
 قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم -: فاقرؤوا إن شئتم: ﴿ فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ ﴾ 
 አቡሁረይራ (ረ.ዐ) በዘገበው ሀዲስ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፣ “አላህ ፍጥረትን ሰርቶ ሲጨርስ ‘ረሂም’ (ዝምድና) ወደ አላህ መጥታ ቆመች፤ አላህ (ሱ.ወ) ‘ምንሆነሽ ነው’ ሲላት ‘ዝምድናን ከሚያበላሹ (የዝምድናን ገመድ ከሚበጥሱ) በአንተ እጠበቃለሁ’ አለች። አላህም (ሱ.ወ) ‘አንቺን የሚቀጥል ችሮታዬን ባደርግለት፣ የሚቆርጥሽን ችሮታዬን ብከለክለው ይበቃሻል ወይ?’ ሲላት ‘አዎን ጌታዬ ሆይ!’ አለች። አላህም (ሱ.ወ) ‘ይህንኑ አድርጌልሻለሁ’ አላት።”
አቡሁረይራ ዘገባዉን ቀጥሎ፣ “ብትፈልጉ ይህን የቁርአን አንቀፅ አንብቡ፣ “በምድር ላይ ስልጣን (ሀይል) ቢሰጣችሁ በምድር ላይ ሀፂያትን ባስፋፋችሁ እና ዝምድናን ባበላሻችሁ ነበር?!”ማለታቸውን ዘግቧል። (ቡኻሪ ዘግበውታል)

4- ሙስሊም ከማህበረሰብ ጋር ያለው ግንኙነት

ይህ የእርስ በእርስ ግንኙነት ከሌሎች ግንኙነቶች አንፃር እጅግ እይታው ከፍ ያለ ሲሆን እያንዳንዱ እንቅስቃሴም በተግባር የሚገለፅ ነው፡፡ሙስሊሞች በማህበረሰባዊ ስራዎች ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባው ተሳትፎ ከፍተኛ ሊሆንም ተገቢ ነው፡፡በማህበረሰባዊ ግልጋሎቶች ላይ መከባበር፣መረዳዳትን ያጠቃለለ ስራዎች የሚሰሩበት የለውጥ ክፍል ነው፡፡

إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡አልሁጁራት 49፤10
ويقول رسول الله – صلى الله عليه وسلم -: ((مثل المؤمنين في توادِّهم وتراحمهم وتعاطفهم مثل الجسد، إذا اشتكى منه شيء تداعى له سائر الجسد بالسهر والحمى)) 
መልእክተኛው(ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ “ሙስሊሞች እርስ በርስ መዋደዳቸው፣ በእዝነታቸውና በርህራሄያቸው እንደ አንድ ሰውነት ናቸው። አንዱ የሰውነት ክፍል የታመመ እንደሆነ ሌላው የሰውነት ክፍል በትኩሣት እና ያለ እንቅልፍ በማደር ይታመማል” (ቡኻሪና ሙስሊም)

5- ሙስሊም ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር

ይህ ማህበረሰባዊ ለውጥ ከስብከት በዘለለ መልኩ በተግባር እንዲገለፅም ኢስላም ያዛል፡፡ ከሌሎች ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር የማህበረሰባዊ ስራዎችን አለመተግበር ከኢስላማዊ መርህ ጋርም ያጋጫል፡፡አንድ ሰው ሁልጊዜም ቢሆን ጉጉቱ መልእክተኛውን(ሰዐወ) መከተልና እርሳቸውን መምሰል ይኖርበታል፡፡ መልእክተኛው(ሰዐወ) ደግሞ ከሙስሊሙም ጋር ሆነ ሙስሊም ካልሆኑ የማህበረሰቡ አካሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት በጥበብና በእዝነት ብሎም በመልካም ግሳፄ የታጀበ ነው፡፡ይህም ትልቅ ተግባር የኢስላም መንፈሱም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ አነህል 16፤125
ويقول رسول الله – صلى الله عليه وسلم : ((فوالله لأنْ يَهدِيَ الله بك رجلاً، خير لك من أن يكون لك حُمْر النَّعَم))
ነብዩ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ በጌታዬ እምላለሁ አንድን ሰው ወደ እውነተኛ
ው መንገድ መምራት የቀያይ ግመሎች ባለቤት ከመሆን የተሻለ ነው፡፡
እነዚህ የለውጥ ክፍሎች ላይ በፅናት መታገልና መበራታት እንዲሁም ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት የአዎንታዊነትን አዲስ ገፅ መክፈት ነው፡፡ ከረመዳን ትምህርት ቤት እነዚህን ሙሉ የለውጥ ክፍሎች ለመሰነቅ እንዘጋጅ!
አላህ በሰላም ያድርሰን…….

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መልካም_ሚስት
#ሚስት ተጠየቀች ለምንድነው ባልሽ ይህን
ያክል የሚወድሽ?
ካንቺ ውጭ ሌላ ሴት የማያየው?
፦ እንደህ አለች ሚስት
* እርግጥም ይህን ያህል ቆንጆ ሴት አይደለሁም
፦ ነገር ግን ባሌ ባአንድች ነገር ካስከፋኝ ይቅር እለዋለሁ
#ወደኔ አዝኖና ተክዞ ሲመጣ የሆነውን ሁሉ
አይኑን እያየሁ በትኩረት አዳምጠዋለሁ
#ወደቤት ሲመጣ ፈገግ ብዬ ቆሚ
እጠብቀዋለሁ
#ብዙ ገንዘብ ከሰጠኝ በጣም አመሰግናለሁ
#ትንሽ ገንዘብ ከሰጠኝ ደግሞ እብቃቀዋለሁ
እንድህ ነው አላህ ና እረሱል ያዘዙኝ አለቻ
( ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)

🌷#እህቴ ሆይ አንቺም የሷ አይነት ሴት ሁኒ ። ዱኒያዊ ጀነትሽ ያምርልሽ ዘንድ።

#አላህ እኛንም ከመልካሞቹ ያድርገን።
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
➠ዊትር ሰላት!

1)ትርጉሙ፦ ዊትር (وتر) የሚለው ቃል ጎዶሎ ቁጥር ( odd) እንደማለት ነው ለምሳሌ 1; 3; 5; 7... የመሳሰሉ ቁጥሮች ዊትር ሲባሉ 2;4 ;6... የመሳሰሉ ቁጥሮች ደግሞ ሸፍእ (شفع) ይባላሉ።
➠በመሆኑም የዊትር ሰላት ማለትበነዚህ ጎዶሎ ቁጥሮች የሚያበቃ ሰላት ማለት ነው።

2)ግዴታ ነው ወይስ ሱና?

➠ሀነፍዮች ዊትር ግዴታ ነው ይላሉ ነገር ግን ከማስረጃ አንፃር ስናየው ዊትር ግዴታ እንዳልሆነና ነገር ግን በጣም የጠነከረ ሱና የተወደደ ተግባር መሆኑን እንረዳለን።የአብዛኛዎቹ ኡለሞች አቋምም ይህ ነው
➠ግዴታ እንዳልሆነ ከሚጠቁሙ ማስረጃዎች መሀከል የአላህ መልእክተኛ ﷺ ግዴታ የሆኑ ሰላቶችን በሚያስተምሩባቸው አጋጣሚዎች አምስት ወቅት ሰላትን ሲጠቅሱ ዊትርን ግን አለመጥቀሳቸው ነው
➠ግዴታ ባይሆንም ግን በጣም የጠነከረ ሱና ነውና አንድ ሰው ሊተወው አይገባም

ኢማም አህመድ እንዲህ ይላሉ

"ዊትርን ሰላትን የተወ ሰው መጥፎ ሰው ነው ምስክርነቱን ሊቀበሉት አይገባም"

3)የሚሰገድበት ወቅት

➠የዊትር ሰላት የሚሰገደው ከኢሻ ሰላት በሗላ ጀምሮ ሱብሒ አዛን እስኪል ድረስ ባለው ወቅት ነው።
ማስረጃውም የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው

((አላህ በዊትር ሰላት አቆያቹ አላህ ከሰላተል ኢሻ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ አደረገላችሁ))📚ቲርሚዚ 425

4)በላጩ ማዘግየት ነው ወይስ በጊዜ መስገድ?
➠ለሊት እነሳለሁ ብሎ ለሚል ሰው ወደ ለሊቱ ማብቂያ ማዘግየቱ ይወደድለታል። ምክንያቱም ያ ወቅት አላህ ወደ ሰማአዱንያ ወርዶ ማነው የሚጠይቀኝ የምሰጠው? የሚልበት ወቅት ነው።
➠ለሊት ላይ መነሳት ለሚከብደው ሰው ግን ሳይተኛ በፊት ዊትር መስገዱ ይወደድለታል።

ማስረጃው

የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው

"በለሊቱ መጨረሻ አልቆምም ብሎ የፈራ ሰው በለሊቱ መጀመሪያ ዊትር ያድርግ በለሊቱ መጨረሻ እቆማለሁ ብሎ ያለሰው በለሊቱ መጨረሻ ይቁም የለሊቱ መጨረሻ ሰላት የሚጣዱበት ነው በላጭም ነው))📚 ሙስሊም 755

5)ትንሹ የዊትር ቁጥር ስንት ረከአ ነው
➠አነስተኛው ዊትር አንድ ረከአ ነው
ማስረጃውም

የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው

((ዊትር አንድ ረከአ ነው ከለሊቱ መጨረሻ))📚ሙስሊም 752

➠ በመሆኑም አንድ ሰው ሁለት ሁለት ረከአ እያደረገ የለይል ሰላትን የፈለገውን ያክል ከሰገደ በሗላ በመጨረሻ አንድ ረከአ ዊትር ይሰግዳል
➠ወይም ደግሞ ሌላ ምንም የለሊት ሰላት ሳይሰግድ አንድ ረከአ ዊትር ብቻ ቢሰግድም ይችላል
6)ሌሎች የዊትር አሰጋገዶች አሉ?

አዎ እነሱም
1) ሶስት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል
➠ሶስት ረከአ ሲሰግድ ሁለት አይነት አሰጋገዶች አሉ
አንደኛው፦ ሶስቱንም ረከአ አከታትሎ በመሀል ተሸሁድ(አተህያቱ) ሳይቀመጥ በመጨረሻ ላይ ብቻ አንድ ተሸሁድ ቀርቶ ያሰላምታል
ሁለተኛው፦ ሁለት ረከአ ሰግዶ ያሰላምትና እንደገና አንድ ረከአ ሰግዶ ያሰላምታል
➠ሶስት ረከአ ሲሰግድ ከፍቲሀ በሗላ በመጀመሪያው ረከአ (( ሰቢህ ኢስመረቢከ)) የሚለውን ሱራ በሁለተኛው ደግሞ ((ቁልያ አዩሀል ካፊሩን)) በሶስተኛው ረከአ ደግሞ ((ቁልሁወላሁ አሀድን)) ቢቀራ ይወደድለታል።
2)አምስት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል
➠ተሸሁድ ሚቀመጠው በመጨረሻ ላይ አንዴ ብቻ ነው መሀል ላይ ምንም ተሸሁድ አይቀመጥም
3)ሰባት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል
➠በዚህም ግዜ ተሸሁድ ሚቀመጠው በመጨረሻ ላይ አንዴ ብቻ ነው መሀል ላይ ምንም ተሸሁድ አይቀመጥም
4)ዘጠኝ ረከአ ዊትር መስገድም ይችላል
➠በስምንተኛው ረከአ ላይ ተሸሁድ ይቀራና ይነሳል ከዛህም በዘጠነኛው ረከአ ተሸሁድ ብሎ በዛው ያሰላምታል።ሁለት ተሸሁድ ይቀራል ማለት ነው።
➠በነዚህ ሁሉ የዊትር አሰጋገዶች ላይ ሀዲስ ስለመጣ አንድ ሰው የቀለለውን መርጦ መተግበር ይችላል።
➠አንዱን አንድ ቀን ሌላውን ደግሞ ሌላቀን ቢጠቀም ይበልጥ ይወደድለታል

7)ቁኑት
➠ቁኑት የሚባለው ዊትር ሰላት ላይ በመጨረሻው ረከአ ከሩኩእ ከተነሳን በሗላ ሱጁድ ሳኖርድ በፊት የሚደረግ ዱአ ነው
➠ዊትር ላይ ቁኑት የተወደደ ተግባር ነው ነገር ግን ግዴታ አደለም።
➠አንዳንዴ እያለው አንዳንዴ ቢተወውም ችግር የለውም ዘወትር ቢለውም ችግር የለውም
🖋ኻሊድ ሙሀመድ (አቡ ሱለይማን)
ረመዳን 1440 ዓመተ ሒጅራ

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላት ከሰገዱ ቡኋላ መስገጃዎ ላይ መፅናት ምን ያህል አጅር እንደሚያስገኝ ያውቃሉን?

የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ከእናንተ መካከል አንዳቹ ሰላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለ እና ውዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዱለታል። "አላህ ሆይ! ወንጀሉን ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት።" ይላሉ።"
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

☞ ኢብኑ በጣል(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እጅግ ብዙ ወንጀል ያለበት ያለ ብዙ ልፋት ወንጀሉን አላህ እንዲያራግፍለት የሚፈልግ ሰው ካለ፦ መላኢካዎች እርሱ ላይ የሚያደርጉት ዱዓእና ኢስቲግፋር ይበዛለት ዘንድ ሰላት ከሰገደ ቡኋላ መስገጃው ላይ በመፅናት እድሉን ይጠቀም።"
••••ሼር እንዳይረሱ••••


•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸

🦋...............🍃🌹🍃..................🦋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ስትቀርበው ለራቀህ አትጨነቅ ምክኒያቱም 'ውድ ነገር " ያለቦታው እርካሽ ነው እና"

"ስታምነው ለከዳህ አትጨነቅ ምክኒያቱም " ታማኝ "በመሆንህ አሸንፈሃል እና"

"ስትፈልገው ባጣኸው ነገር አትጨነቅ" ምክኒያቱም" እርሱ አንተን ሲፈልግ ታገኘዋለህ እና"

"ስትወደው ለጠላህ አትጨነቅ ምክኒያቱም" ስንት ምርጥ ሰወች አንተን እሚወዱ አሉና"

"ስላልሆነው ነገር አትጨነቅ ምክኒያቱም" ገና ከዚህ በኅላ እሚሆን ብዙ ነገር አሉና"

" አጣዋለሁ ብለህ ያላሰብከውን ብታጣ አትጨነቅ ምክኒያቱም" አገኘዋለሁ ብለህ ያላሰብከውን ታገኛ ለህ እና "

"ያሰብከው ሳይሆን ቢቀር አትጨነቅ ምክኒያቱም" አሏህዬ ያላሰብከውን ይሰጥሃል እና"

"እናልህ ወዳጆ አትጨነቅ እንተ ለሁሉም ተፈጠርክ እንጅ ሁሉም ለአንተ አልተፈጠረም"

"አሏህዬ ለአንተ እሚያስፈልግህን ያውቃል" ያሰብከውን አስጥሎህ ያላሰብከውን ይሰጥሀል እና "

"ስላለፈው ብዙ አታሰላስል ' ስለወደ ፊቱ አብዝተህ አትጨነቅ ከዚህ ይልቅ ዛሬን ጠበቅ አድርግ" አትጨነቅ!!

("እችም ቀን ታልፍ እና ድሮ ትባላለች ስአቷ ታልፍ እና ታሪክ ትባላለች") በደስታ "እለፋት ነገም ሌላቀን ነው "ህይወትህ ተስፋ አላት.......

•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸

🦋...............🍃🌹🍃..................🦋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሱብሀነላህ
ከአቡ ሁረይራህ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ይላሉ፡-
“ከበኒ ኢስራኢል (ህዝቦች) አንድ ወንጀል የሚያበዛና ሌላ በዒባዳ (በአምልኮ) ላይ የሚታገል ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ዒባዳ ላይ የሚታትረው ያንኛውን ሁሌ ወንጀል ላይ ስለሚመለከተው ‘ተው’ ይለዋል፡፡ የሆነ ቀን ወንጀል ላይ አገኘውና ‘ተው’ አለው፡፡
(ወንጀለኛው): ‘ተወኝ (እባክህ) በጌታዬና በእኔ መሀል አትግባ! በእኔ ላይ ተቆጣጣሪ ሆነህ ተልከሀል?’ ሲል መለሰለት፡፡ ያንኛው በዚህን ጊዜ፡
‘ወላሂ! አንተን አላህ አይምርህም!! ወይም አላህ አንተን ጀነት አያስገባህም’ አለ፡፡
የሁለቱም ሩሕ ተወሰደ (ሞቱ፡፡) ከአለማቱ ጌታ ዘንድ ተገናኙ፡፡ ለዚያ ታታሪ ሰውም (አላህ) እንዲህ ሲል ጠየቀው፡-
‘በእኔ ላይ (እንደማልምረው) አዋቂ ነበርክ?! በእጄ ላይ ባለውስ ቻይ ነበርክ?!’
ለወንጀለኛው፡- ‘ሂድ በእዝነቴ ጀነት ግባ’ አለው፡፡ ያንኛውን ደግሞ ‘ወደ እሳት ውሰዱት’ አለ፡፡”
አቡ ሁረይራ - ረዲየሏሁ ዐንሁ ከዚህ ሐዲሥ በመቀጠል እንዲህ አሉ፡- “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! በርግጥም ዱንያ አኺራውን የምታጠፋ ንግግርን ተናገረ፡፡” [ሶሒሕ ኢብኑ ሒባን፡ 5712]
……………………………………………..
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም-ነገሮች
በመጀመሪያ የዚህን ሐዲሥ መልእክት ምን ያክል እናውቀዋለን? ምን ያክልስ አደጋው ይታየናል? ምን ያክልስ ጥንቃቄው አለን? ከዚህ ጥፋት ያለንስ ርቀት ምን ያክል ነው?
1. በሐዲሡ እንደተገለፀው
1.1. አንደኛው ሰው ወንጀል የሚያበዛ ነው፡፡ በዚያ ላይ ምክር አልተቀበለም፡፡
1.2. ሁለተኛው ሰው ዒባዳ የሚያበዛ ነው፡፡ በዚያ ላይ ከመጥፎ ለመመለስ የሚመክር አስተማሪ ነው፡፡
2. ውጤቱ ግን አስደንጋጭ ነው፡፡ ወንጀለኛው ወደ ጀነት፣ ዓቢዱና መካሪው ወደ እሳት!!!
3. ምክንያቱ ደግሞ፡-
3.1. የመጀመሪያው ወንጀሉ ከሺርክ በታች እስከሆነ ድረስ ከአላህ መሻት ስር ነው፡፡ “አላህ የሚያጋራበትን አይምርም፡፡ ከዚያ በታች ያለውን ግን ለፈለገው ይምራል” ማለቱ አይዘንጋ፡፡ ስለዚህ ሰውየው የተማረው ስላላጠፋ ሳይሆን በአላህ እዝነት ነው፡፡ “ሂድ በእዝነቴ ጀነት ግባ” እንዳለው ይታወስ፡፡
3.2. ሁለተኛው በማያገባው ገብቶ “ይህን አያደርግም” እያለ በአላህ ላይ እየማለ ነው፡፡ ይህን ወንጀለኛ ይምረዋል ወይስ አይምረውም የሚለውን የሚያውቀው ባለምህረቱ ብቻ ነው፡፡ ስልጣኑም ችሎታውም የሱው ነውና፡፡ ስለዚህ አቶ ዐቢድና መካሪ የአላህን ሐቅ ነው እየተጋፋ ያለው፡፡
4. ከሳሽ ማን ነው?!
በቂያማ ቀን ታዲያ የዚህ ሰውየ ከሳሽ የሆነው ያ ወንጀል የሚያበዛው አካል አይደለም፡፡ እህሳ ከሳሹም ዳኛውም የአለማቱ ጌታ አላህ ነው!! አያስፈራም?! “በእኔ ላይ (እንደማልምረው) አዋቂ ነበርክ?! በእጄ ላይ ባለውስ ቻይ ነበርክ?!” ሲል አፋጠጠው፡፡
5. ቀይ መብራት!
እንዳቅሚቲ በዲን ላይ የምትታትረው ወንድሜ ሆይ! እንዳቅሚቲ ሸሪዐውን ለመተግበው ተፍ ተፍ የምትይዋ እህቴ ሆይ! የምናውቃትን ከማስተላለፍ ባለፈ፣ ስለ ሰዎች መፃኢ እድል ከመዳፈር በእጅጉ ልንቆጠብ ይገባል፡፡ ይሄ ሐዲሥ እጅግ አስፈሪ የሆነ መልእክት ነው የያዘው፡፡ ድንበር ማለፍ በዲን ስም ስለተፈፀመ ከተጠያቂነት አያተርፍም፡፡ አላህ መጨረሻችንን ያሳምረው፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 16/2009)
•┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸

🦋...............🍃🌹🍃..................🦋
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀልብ ላለው ሰው ትልቅ ምክር ከሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ!!!:

ምንም የሚጠቅም ነገር ሳታገኝና ሳትሰራ ጊዜህ ካለፈ፣ እድሜህም ዝም ብሎ ከገፋ፣ የጊዜን በረካ ከተነፈግክ ይህ የአሏህ ቃል አንተንም አግኝቶህ እንዳይሆን ተጠንቀቅ!
ﻭَﻟَﺎ ﺗُﻄِﻊْ ﻣَﻦْ ﺃَﻏْﻔَﻠْﻨَﺎ ﻗَﻠْﺒَﻪُ ﻋَﻦْ ﺫِﻛْﺮِﻧَﺎ ﻭَﺍﺗَّﺒَﻊَ ﻫَﻮَﺍﻩُ ﻭَﻛَﺎﻥَ ﺃَﻣْﺮُﻩُ ﻓُﺮُﻃًﺎ
<< ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋውን ፍላጎቱንም የተከተለውን ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ >>

አንዳንዱ ሰው አሏህን በተመስጦ ሳይሆን ዝም ብሎ በማነብነብ ብቻ አሏህን ይዘክራል። ይሄ ምንም አይጠቀምም። አሏህን በቀልብ አለማስታወስ በስራም ላይ በጊዜም ላይ በረካ ያሳጣል። ነገሩ ሁሉ የተምታታ እስኪሆንበት ድረስ። አንዳንዴ ምንም ነገር ሳይሰራ ረጅም ሰአት ያሳልፋል። ነገር ግን ነገሮችን ከአላህ ጋር ያደረገ ሰው በሁሉም ተግባሩ በረካን ያገኛል።

ተፍሲሩ ሱረቱል ካህፍ
[ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ]

┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸

🦋...............🍃🌹🍃..................🦋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉 _*አንተ እውቀት ፈላጊ ሆይ እነዚህ ነገሮች ላይ ካልተገኘህ የት ነው መገኛህ?!*_
*أين موقعك ياطالب العلم ؟*

👉አንደኛው ሶፍ ላይ የሚገኙት ተራ ሰዎች ከሆኑ
إذا كان أهل الصف الأول في المسجد (عوام)..!!
👉ጁምአ ቀን በመጀመሪያዋ ሰአት ገብተው የሚገኙት ተራ ሰዎች ከሆኑ
وأهل الساعة الأولى لصلاة الجمعة (عوام)..!!
👉ከመግሪብ እስከኢሻእ መስጂድ ተቀምጠው ሶላት የሚጠባበቁት ተራ ሰዎች ከሆኑ
والذين يرابطون بين العشاءين (عوام)..!!
👉ከፈጅር ሶላት ቡሀላ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ዚክር የሚያደርጉት ተራ ሰዎች ከሆኑ
والذين يذكرون الله في مُصلاهم بعد صلاة الفجر حتى تطلع الشمس (عوام)..!!
👉የዱሀን ሶላት የሚሰግዱት ሰጋጆች ተራ ሰዎች ከሆኑ
والذين يصلون ركعتي الضحى (عوام)..!!
👉አላህን በብዛት የሚያስታውሱትና የጧት የማታ ዚክሮችን የሚይዙት ተራ ሰዎች ከሆኑ
والذين يذكرون الله كثيراً، ويلتزمون أذكار الصباح والمساء (عوام)..!!
👉በቀን መቶ ግዜ ነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት የሚያወርዱት ተራ ሰዎች ከሆኑ
والذين يلزمون الصلاة على النبي ﷺ مئات المرات في اليوم (عوام)..!!
👉በየቀኑ አንዳንድ ጁዝእ ቁርኣን መቅራትን ተለምዶቸው ያደረጉት ተራዎች ከሆኑ
والذين يحافظون على قراءة جزء من القرآن كل يوم (عوام)..!!
👉ሙታንን የሚያዘጋጁት በነሱም ላይ የሚሰግዱት ቀብር የሚምሱት ሙታንን የሚቀብሩት ተራ ሰዎች ከሆኑ
والذين يجهزون الأموات ويصلون على الجنائز ويحفرون القبر ويدفنون الاموات (عوام)..!!
👉አብዘሀኛው ሰደቃ ሰጪ በወጪዎች የሚሯሯጠው ተራዎች ከሆኑ
وأغلب المتصدقين والمسارعين في الانفاق (عوام)..!!

አንተስ የት ነህ
*فياترى أين أنت ؟؟*

*ومن تكون إذاً أنت ؟؟!
ታድያ ያንተ መገኛ የት ይሆን የትኛው መልካም ስራ ላይ ልትሳተፍ ነው _ያቺ አስደንጋጭ ቀን ከመድረሷ በፊት ለሷ የሚሆንህን አሁን አከማች_

┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸

🦋...............🍃🌹🍃..................🦋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍎الحثُّ والتَّرغيبُ في استعمالِ السِّواك🍏ِ

የመፋቂያ ሸሪዓዊ ድንጋጌ

መፋቂያ ወይም ሲዋክ ይባላል

💥 ትርጉሙ:- "ከአራክ እንጨትና ከመሳሰለው ተወስዶ መጥፎ ጠረንና የምግብ ቅሪትን ከአፍ ለማስወገድ ጥርስን ለማጽዳት የሚያገለግል ነው፡፡"

💥 ሸሪዓዊ ሑክሙ፦ "ጥብቅ የነቢዩ ﷺ ሱንና ነው፡፡"

የመፋቂያ ጥቅሞች፦

ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሓመሁሏሁ ዛዱል መዓድ በተሰኘው ኪታቡ (4ኛው ሙጀለድ/ገፅ፥323) ላይ እንዲህ ብለው ነበር ያስቀመጠው

1-يطيب الفم
🍏 አፍን ያጸዳል
2-يشد اللثة
🍏 ድድን ያጠነክራል
3-يقطع البلغم
🍏 አክታን ይቆርጣል
4-يجلو البصر
🍏 ዐይን ያጠራል
5-يذهب بالحفر
🍏 የጥርስ መቦርቦርን ያስወግዳል
6-يصحح المعدة
🍏 ሆዳችን ጤናማ እንድሆን ያደርጋል
7-يصفي الصوت
🍏 ድምጽን ያጠራል
8-يعين على الهضم
🍏 አላስፈላጊ ውፍረትን ያስወግዳል
9-يطرد النوم
🍏 እንቅፍን ያባራል
10-ينشط للقراءة
🍏 ለቂርኣት ያነቃቃል
11-ينشط للصلاة
🍏 ለሶላት ያነቃቃል
12-ينشط للذكر
🍏 ለዚክር ያነቃቃል
13-يرضي الرب
🍏 የአላህን ውዴታ ያስገኛል፤
14-يعجب الملائكة
🍏 መላኢካን ያስደስታል
15-يكثر الحسنات
🍏 ምንዳን ያበዛል

💥 መፋቂያ መጠቀም በየትኛውም ወቅት ሱና (የተወደደ) ነው፡፡ ፆመኛም ጠዋትም ይሁን ከቀትር በኋላ ጥርሱን ቢፍቅ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ﷺ ጥርስን በመፋቅ ሲያነሳሱ አንዱን ወቅት ከሌላው አልለዩም፡፡

ሁኖም መጠቀሙ በጣም የጠበቀ ሱንና የሚሆኑባቸው ቦታዎች እንደሚከተሉ ቀርቧል፦

1 - በዉዱእ ጊዜ

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡፡

"لَوْلَا أَنْ أَشُقَّ عَلَى أُمَّتِي لَأَمَرْتُهُمْ بِالسِّوَاكِ عند كُلِّ وضوء"
ٍ
‹‹ኡመቴ ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ዉዱእ ወቅት ሰዋክን እነዲጠቀሙ ባዘዝኳቸው ነበር፡፡›

2 - በሶላት ጊዜ

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:-

"لَوْلَا أَنْ أَشُقَّ عَلَى أُمَّتِي لَأَمَرْتُهُمْ بِالسِّوَاكِ مَعَ كُلِّ صَلَاة"

‹ ኡመቴ ላይ ማጥበቅ ባይሆንብኝ ኖሮ በያንዳንዱ ሶላት ወቅት ሰዋክን እነዲጠቀሙ ባዘዝኳቸው ነበር፡፡›

3 - ወደ ቤት በሚገባበት

عَنِ الْمِقْدَامِ بْنِ شُرَيْحٍ ، عَنْ أَبِيهِ قَالَ : سَأَلْتُ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا ، قُلْتُ : (( بِأَيِّ شَيْءٍ كَانَ يَبْدَأُ النَّبِيُّ ﷺ إِذَا دَخَلَ بَيْتَهُ ؟ قَالَتْ : بِالسِّوَاكِ ))

‹‹ነቢዩ ﷺ ወደ ቤታቸው በሚገቡበት ጊዜ አስቀድመው ምን ያደርጉ እንደ ነበር ዓእሻን ጠይቄ፣በሰዋክ ነው አሉኝ፡፡››

4 - ከእንቅልፍ ሲነቃ ፡-

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُما ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ : ((كَانَ لَا يَنَامُ إِلَّا وَالسِّوَاكُ عِنْدَهُ، فَإِذَا اسْتَيْقَظَ بَدَأَ بِالسِّوَاكِ))

"የአሏህ መለዕክተኛ ﷺ ሲተኙ ከጥጋቸው አድርገው ይተኙ ነበር ሲነሱ ጥርሳቸውን በማፅዳት ይጀመራሉ"

5 - ቁርኣን በሚቀራበት ጊዜ

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:-

" طيبوا أفواهكم بالسواك، فإنها طرق القرآن "

"አፋችሁን ለቁርኣን አጽዱ፡፡"

لا نسمح بالحذف عن المنشور

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

┈┈┈┈•✿✿•┈┈┈┈•
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸

🦋...............🍃🌹🍃..................🦋