Information Science and Technology
16K subscribers
270 photos
24 videos
100 files
406 links
Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.
Download Telegram
ስልኬ ስታክ እያረገ አስቸገረኝ መፍትሄዉ ምንድነዉ?
-------------------------------------------------
ስልክዎ ስታክ እያደረገ ካስቸገሮት መነሻ ምክንያቱንና መፍትሄዉን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡፡
--------------------------------------------------------------------------------

ስልኮ ከተለመደዉ በላይ ይዘገያል ወይስ እንዲያ ከናካቴዉ አልሰራም ብሎ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ እንግዲህ ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሾዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡
 ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር
ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡ ስልኮ ላይ ብዙ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች ለምሳሌ ጌሞች ፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ(ኤዲትኢንግ) ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ(ፕሌየሮች) ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን ሶፍሮች ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡

 የስልኮ ዳታ መያዣ(ስቶሬጅ) በፋይሎች መጨናነቅ
በስልኮ ሜሞሪ ላይ ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮች፣ያልጫኑት ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቐት(ሜሞሪ) ያስቀምጡት፡፡

 የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ
ስልኮ ያሉትን ሶፍተዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል ይህም የስልኮን ፐሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ(background play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያደሱት፡፡

 ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት
ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ከች ማፀዳት ተቃሚ ያደርገናል፡፡

 Widgets መጠቀምን ማብዛት
አንድሮይድ ስልኮች ከሚሰጡን የተለየ ጥቅም አንዱ ዊጄትስ ቢሆንም ያን ያህልም የሚሰሩትን ካልገደብን ስልካችንን በማጨናነቅና እንዲቆም (ስታክ) እንዲያደርግ በማድረግ ረገድም ከፍ ያለ ድርሻ ያላቸዉ በመሆናቸዉ ዊጄትስን በመቀነስ ካልሆነም በማጥፋት ስልኮ በየጊዜዉ መቆሙን አላያም መንቀራፈፉን ማስቆም አማራጭ ነዉ፡፡

 ፋብሪካዉ ሲያመርተዉ ወደነበረበት ማሰተካከያ መመለስ(reset factory setting)
የስልኮ ማርጀት አልያም ለብዙ ጊዜያት መጠቀም ስልኮን እንዲቀራፈፍ አልያም በየማሃሉ እንዲቆም ለመሆኑ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ የማስተካከያ(ሴቲንግ) ለዉጦች ወይም አቅጣጫ መጠቆምያ ጂፒስ ኦን ማድረግ(ማብራት) ለስልኮ መንቀራፈፍ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ የስልኮ በመሃል በመሃል መቆም(ስታክ) ሲያጋጥሙ ስልኩ ሲዘጋጅ ወደነበረበት መመለስ (reset factory setting) ችግሩን ሊቀርፍ ይችላል፡፡

 ዎልፔፐር (Wallpaper) መጠቀም
ስልኮ ለዓይን እንዲስብ አልያም በአንድ አንድ አቋራጭ ቴክኒኮች ምክንያት ስልኮ ላይ ላይቭ ዎልፔፐር (Live Wallpaper) መጠቀም አንዱ የአንድሮይድ ስልኮች ገፀ-በረከት ቢሆንም ለስልኮ መዘግየትም ይሁን መቆም(ስታክ ማድረግ) ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ማጥፋቱ መንቀራፈፉን አልያም ሰታክ ማድረጉን ሊያስቆም ይችላልና ይሞክሩት፡፡

 ስልኮ አቧራ ከሞላዉ
የሚሰሩበት ቦታ አልያም የሚዉልበት አከባቢ አቧራማ ከሆነ ስልኮን ማፅዳትና ከተፀዳም በኋላ መልሶ በአቧራ እንዳይሞላ መከላከያ መጠቀም፡፡

ከተጠቀሱት አማራጮች ዉስጥ አንዱን ብቻ መርጦ በመተግበር ሳይሆን ሁሉንም አልያም አብዛዛኛዉን መፍቴዎች በአንድ ላይ በመተግበር ዉጤት ስለሚያስገኝ ከመፍቴዎች ዉስጥ በመምረጥ ሳይሆን ከቻሉ ሁሉንም መፍትሄዎች ስልኮ ላይ መተግበር ካልሆነም የተቻሉትን መከወን እንደመፍተሄ ይሆናል፡፡


ሌሎች መሰል ጥያቄዎች ካሎት በፌስቡክ ፔጃችን ኮመንት ያርጉልን አልያም ኢንቦክስ ያርጉልን፡፡ እርስዎን በመርዳትዎ ደስታ ይሰማናል፡፡

ይህን ፖስት ከወደዱት Like & Share
https://youtu.be/e7LSYCQkTfs
+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +
የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::
ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::
እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::
ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::
ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::
ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::
ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::
የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::
ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?
እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::
ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
5G ቴክኖሎጂ እንዴት ይሰራል? *******
የ 5G ቴክኖሎጂ የ አምስተኛው ትውልድ የሞባይል ቴክኖሎጂ ሲሆን የዲጂታል ዓለሙ የሚፈልገውን ፈጣን ግንኙነት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ ያራመደ ቴክኖሎጂ ተደርጎም ይወሰዳል። የ 5G ቴክኖሎጂ የመረጃ መለዋወጫ ፍጥነትን አሁን ካለው የ4G ቴክኖሎጂ ከ10 እስከ 100 የተሻለ እጥፍ እንደሚልቅ ይገምታል። ይህም ማለት የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን እስከዛሬ ከነበረው የm/s ፍጥነት ወደ g/s ያሳድገዋል ማለት ነው።
ኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሃሪሽ ክሪሺናስዋሚ እንዳሉት “ የ 5G ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አሁን ባለው የኔትዎርክ ፍጥነት መተግበር ያልቻልናቸውን ከፊተኛ የሆነ የኔትዎርክ አቅምን የሚጠይቁ መተግበሪያዎችን እንድንጠቀም ያስችለናል ለምሳሌ በ ጊጋ ባይት ደረጃ ያሉ ተንቀሳቃሽ መስሎችን በሰከንድ ከኢንተርኔት ማውረድ ያስችለናል እንድሁም እንደ ቨርችዋል ሪያሊቲ መተግበሪያና ሰው አልባ መኪኖችን ላይ ለፈጣን የመረጃ ዝውውር መጠቀም ያስችለናል”። በተጨማሪም ዘመኑ እየፈጠራቸው ያሉ ቴክኖሎጂዎች ማለትም እንደ አጉመንትድ ሪያሊቲ እና ሰው አልባ መኪኖች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ፍጥነትን ይሻሉ ስለሆነም የ5G ቴክኖሎጂ የመረጃ የመዘግየት ሂደንት ወደ 1 ሚሊ ሴኮንድ ዝቅ ማድረን አላማ አድርጎ ተነስቷል ይህ ማለት ተንቀሳቃች መሳሪያዎች መረጃን የ1 ሴኮንድ 1/1000 ባነሰ መለዋወጥ ያስችላቸዋል።
ባለፉት ትውልዶች ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙት የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረርን እንደ ሬድዮ ሞገድ ባሉ ቴክኖሎጂዎች በመሆኑ የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ በከፍተኛ ሁኔታ የኔትዎርክ መጨናነቅን ይፈጠርበታል፡፡ ስለሆነም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የሆነ የራድዮ ሞገድ ከመጠየቁም በላይ በ ሴንቲሜትር የሚለካውን ወደ ሚሊሜትር ሞገድ ዝቅ ማድረግ አስፈልጓል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ቀድመን ከምናውቀው ትልልቅ የሆኑ የኔትዎርክ ምሰሶዎች በላይ በማይፈልጉ የህንጻዎች አናት እና በመብራት አስተላላፊ ምሰሶዎች ላይ ሊገጠሙ የሚችሉ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎቹ አዲስ የግንኙነት መንገድ የክፈቱ አስብሏቸዋል። ነገር ግን እነዚህ የሞገድ አይነቶች ሌሎች ተግዳሮቶች አጋጥሟቸዋል ከነዚህም መካከል ሞገዶቹ በዛፎችና በህንጻዎች ከመዋጥ አልዳኑም። ነገር ግን እነዚህ በመጠናቸው አንስተኛ የሆኑ የኔትዎክ አስተላላፊዎች ለአዳዲስ የምርምር ስራዎች መፈጠር ጉልህ አስተዋጾ ነበራቸው። የ አምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ የመፈጠር ምክንያትም ናቸው። የአምስተኛው ትውልድ ኔትዎርክ (5G) ቀድሞ በነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ በመጠን አነስተኛ የሆኑ አንቴናዎችን በመጨመር እንዲሁም የማስተላለፍ አቅማቸውን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ መላላኪያ ፍጥነትን በመጨመር የተፈጠረ ሲሆን የመረጃ መዘግየትን በእጅጉ ቀንሷል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በተጨማሪም በፊት ከነበሩት የኔትዎርክ አስተላላፊዎች ያነሰ የኤሌክትሪክ ሃይል መጠቀማቸውም ልዩ ያደርጋቸዋል።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
ኮምፒውተር ወይም ላፕቶፕ ከሞባይል ወይም ከታብሌት ጋር በማገናኘት መቆጣጠር ወይም እንተርኔት መጠቀም ፣ ኮምፒውተርዎ መዝጋት መልዕክት መለዋወጥ እንደሚችሉ ያቃሉ? በጣም ቀላል እና በጎጉል አማካኝነት በተሰራው ጎጉል ክሮም ዴስክቶፕ ኮንትሮል በሚባል ሶፍትዌር በመጠቀም አሁኑኑ በማጋናኘት ከፈለጉት ኮምፒውተር ጋር በማስተሳሰር ግዜዎ ይቆጥባል የኮምፒውተርዎ ድህንነት ይጠብቃል። ይህንን ቪድዮ በማየት በቀላሉ ይጠቀሙበት።
https://youtu.be/TaBAITkWTXA
🌹🌹🌷🌷🍄🍄⛄️⛄️⛄️⛄️🍄🍄🌷🌷🌹🌹
ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
🔍🔍🔍🔍🔍▬▬ Share ▬▬🔎🔎🔎🔎🔎
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
በሦስት መንገድ ወይም ዘዴ ስልክ ሲደውሉ ቁጥሩን እንዴት እንዳይታይ ማድረግ ወይም መደበቅ እንችላለን?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉👉phone setting
👉👉👉phone code
👉👉👉google chrome

ለሚያውቁት እና ለማያውቁት ሰው ስልክ መደወል አለብዎት? ችግር የለም ፣ በተቀባዩ ስልክ ላይ ቁጥር እንዳይታይ እና ስልክ ደውለው በስውር እንዴት ያወራሉ ፡፡ እንዴት ነው የማደርገው ብለውስ? ቀድሞውኑ ስለራስዎ አስበው ያውቃሉን? ነገር ግን በስልክ ውስጥ ብዙ ልምድ ስለሌለ፣ እንዴት መቀጠል እንዳለብዎ አያውቁም? ገብቶኛል. ስለዚህ ይህንን እናድርግ ፣ ጥቂት ጊዜዎችን ነፃ ጊዜ ለራስዎ ወስደው ይህንን ቪድዮ በማየት ፣ የግል ወይም ፕራይቬት ቁጥር ማድረግ ወይም መደበቅ እንደሚቻል ሥስት ዘዴ ተጠቅመን እናያለን ቀላል ነው።
📱📱📱📱ሼር📱📱📱📱
https://youtu.be/JZv8hzIKCBo
የአንድሮይድ ሞባይል ተጠቃሚ የሆናችሁ ሁለት ነገሮችን ማወቅ ያለባችሁ
1.👉👉👉👉ለፈለግነው አፕልኬሽን ኖትፊኬሽን በቁጥር ብዛት እንዲያሳየን እንዴት ኢንኤብል ወይም ኦን እናደርጋለን
2.👉👉👉👉 ፎን ሴቲንግ ተጠቅመን ማንም ሰው ማየት የለበትም የምንላቸውን አፕሊከሽኖች እንዴት እንደብቃለን ለዚህ ቡዙ ምክንያት አለን ልጆች አሉ ብላ ብላ --------
https://youtu.be/ZqnmUxM2sPg
በክትባት ልንከላከላቸው የምንችል በሽታዎች
>>>>>>>>>>>>>>>>>>በክትባት ልንከላከላቸው የምንችል በሽታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ
● የማህጸን በር ካንሰር
● ኮሌራ
● ዲፍቴሪያ
● ሄፓታይትስ ቢ
● ኢንፍሉዌንዛ
●የሳንባ ነቀርሳ
● ኩፍኝ
● ጀሮ ደግፍ
● ፐርቱሲስ
●የሳንባ ምች
● ፖሊዮ
●የእብድ ውሻ በሽታ
● ሮታ ቫይረስ
● ሩቤላ
● ቴታኑስ
● ታይፎይድ
● ጉድፍ
● ቢጫ ወባ
ለማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ኤችፒቪ ክትባት በመባል ይታወቃል ። ይህ ክትባት ዕድሜያቸው 11 አመት ወይም 12 ዓመት የሆኑ ልጆች እንዲወስዱ ይመከራል። ነገር ግን ከ 9 እስከ 26 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችም ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ። ነፍሰጡር ሴቶች ክትባቱን መውሰድ የለባቸውም።
Source፦ጆይ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ
▬▬ Share ▬▬▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለባችሁ 10 ወሳኝ ነገሮች
1ኛ :- ያለንበትን ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልከውን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላክዋን ከፍተን location የምለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::
2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የምለውን እንነካለን ከዛ passcode የምለወን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::
3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንደይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የምለዉን እንነካለን ከዛ
ከዛ when using mobile data -OF-አድርጉት ::
4ኛ :- የለክነዉን message ከደረሰ ቦኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የለነክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የምለውን Also delete receive የምለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት
6ኛ :- በተላይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፈ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከምሰጠን የመልክ ምርጫ የፍለግነዉን እንመርጣለን ::
7ኛ :- ቴሌግራም የሉ ፅፎች አልነበብ እየሎት ተቸግረዋል ማለት ፍደሎችሁ አንሰዉ ለዓይን አልተይ ከለ ፍደሎቹሁን ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
አዎ በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፍለግነዉን ያህል ትልቅ ማድርግየ ይቻላል ::
8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የምለውን ነክተን create new channel የምለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፍለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::
9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራፍ ጉሩፒ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ የለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የምለውን እንነካለን ከዛ create new groupጠ የምለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፍለግነዉን የጉሩፒ ስም እናስገባለን ::
10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የምለውን በመንካት የፍለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
🌹🌹🌷🌷🍄🍄⛄️⛄️⛄️⛄️🍄🍄🌷🌷🌹🌹
ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
🔍🔍🔍🔍🔍▬▬ Share ▬▬🔎🔎🔎🔎🔎
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
🌹🌹🌷🌷🍄🍄⛄️⛄️⛄️⛄️🍄🍄🌷🌷🌹🌹
ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
🔍🔍🔍🔍🔍▬▬ Share ▬▬🔎🔎🔎🔎🔎
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
#ሰለ_imo_ማወቅ_ያለባችሁ_ስምንት_ወሳኝ_ነገር .
ሰለ imo ማወቅ ያለብን ስምንት ወሳኝ ነገሮች ...
በመጀመሪያ imo ማለት ምን ማለት ነዉ
imo :- ማለት ፈጣን የሆነ የመልዕክት መላዋዉጫ በተጨማሪ ኔቶርክ /በዳታ የሚሰራ ቴክኖሎጅ ነዉ ...
በተጨማሪ ሰንዳዋዉል ከዳዋዩም ከተደወለለትም ሰዉ እኩል ብር ሚበላ ቴክኖሎጅ ነዉ
በIMO ላይ ማወቅ ያለብን ስምንት ነገሮች
👉1ኛ እኛ online ላይ መሆናችንን ለመደበቅ ከፈለግን ሰዉ እንዳያውቅ ከፈለግን ...
በመጀመሪያ imo እንከፍታለን ከዛ ከኢሞዉ ከታች ሦስት መስመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ privacy አንዴ እንነካለን ከዛ last seen ሰንነካ ሦስት አማራጭ ያመጣል ከነዛ አማራጮች no body የሚለውን እንነካለን ከዛ online መሆናችን አይታወቅም ።
👉 2ኛ chat እያደረግን እኛ የምንፅፍዉን ሳንልክም እየፃፈን እየለ የሚነበብ ከሆነ ማለት send ሳንልም እየፃፈን እየለ የምንፅፍለት ሰዉ የሚያነብ ከሆነ ...
በመጀመሪያ setting ላይ ትገባላችሁ ከዛ privacy የምለውን አንዴ ትነካላችሁ ከዛ real time chat የሚለዉን ላይ ቦዶ ተዉት አታብሩት ወይም አታረሙ ባዶውን ተዉት ከዛ እየፃፈን እየለ አይነበብም ማለት ነዉ ።
👉 3ኛ የሚላክልን ፎቶም ቪድዮም በ imo ላይ ብቻ እንዳይቀመጥ በሚሞሪያችን እንዲገባ ከፈለግን ...
በመጀመሪያ setting ላይ እንገባለን ከዛ ወድ ታች ወርደን storage የሚለውን አንዴ እንነካለን ከዛ store photo አንዴ ንኩት በተጨማሪ store video የምለውንም አንዴ ንኩት በአጭሩ ራይት አድርጉት ከዛ በ imo የምለክልን ሁሉም ወደ ሚሞሪያችን ይገባል ማለት ነዉ ።
ማስጠንቀቂያ:- ይህንን ካደረግነው ማንኛውንም ፎቶና ቪዲዮ ወደ ስልካችን ስለሚወርድ ዳታ የምንጠቀም ከሆነ ብር ስለሚቆርጥ ይጠንቀቁ!
👉 4ኛ የተላላክነዉን ፅሁፎች ሁሉንም delete ለማድረግ ከፈለግን ...
በመጀመሪያ setting ላይ እንገባለን ከዛ ወዳ ታች ወርደን delete all chat history የምለዉን አንዴ እንነካለን ከዛ የተፃፀፈነዉ ሁሉም delete ይሆናል ማለት ።
👉 5ኛ በ imo ሲደዉልልን የደወል ጥረ ለመቀየር ከፈለግን ማለት ringtone ለመቀየር ከፈለግን...
በመጀመሪያ setting ላይ እንገባለን ከዛ ወዳታች ወረድ ብለን ringtone የሚለዉን አንዴ ነካ ታደርገላችሁ ከዛ አማራጭ ያመጣል የተለያዩ ሙዝቃዎችን ከነዛ ዉስጥ አንዱን መረጣችሁ ነካ ታደርገላችሁ ማለት ነዉ ከዛ በ imo ሲደወል እኛ የመርጥነዉ ጥረ ይጣራል ማለት ነዉ ።
👉 6ኛ የ imo ስማችንን ለመቀየር ከፈለግን ...
በመጀመሪያ setting ላይ እንገባለን ከዛ imo account setting ላይ እንገባለን ከዛ አንዴ እንነካለን ከዛ request name የምለዉን አንዴ ነክተን የፈለግነውን ስም ፅፈን ok እንላለን ከዛ ስማችን ይቀየራል ማለት ነዉ ።
👉 7ኛ የኢሞ አካውንት delete ለማድርግ ከፈለግን ሙሉ በሙሉ imo መጠቀም ካልፈለግን delete ለማድረግ ከፈለጋችሁ ...
በመጀመሪያ setting ላይ ትገባላችሁ ከዛ imo account setting ላይ ገብታችሁ ከሉት አማራጮች delete imo account የሚለውን አንዴ ነካ እናርገለን ከዛ ስልክ ቁጥራቹሁን አስገቡ ይላል ከዛ ታስገባላችሁ ከገባቹሁ ቦኃላ delete ይሆናል ማለት ነዉ ።
👉8ኛ :- block ለማድረግ ከፈለግን እኛ የልፈለግነዉን ሰዉ block ለማድረግ ከፈለግን..
በመጀመሪያ block ለማድረግ የፈለግነዉን ሰዉ ፎቶዉን አጥብቀን እንይዛለን ከዛ profile የሚለዉ ይመጣል ከዛ እሱን አንዴ ነካ እናደርጋለን ከዛ መጨረሻ ላይ block የሚል ፅሁፈ አለ እሱን አንዴ እንነካለን ወይም እናበራለን ከዛ የልፈለግነዉ ሰዉ ከ imo ከኦሞችን ይጠፈል block ይሆናል
ማሳሳቢያ ፦ በፅሁፍ ዉስጥ setting ያልኩት የኢሞዉን ዉስጥ የለዉን setting ነዉ እንጅ የስልኩን setting አይደለም ።
🌹🌹🌷🌷🍄🍄⛄️⛄️⛄️⛄️🍄🍄🌷🌷🌹🌹
ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
🔍🔍🔍🔍🔍▬▬ Share ▬▬🔎🔎🔎🔎🔎
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q