|| INAS ﷺ ||
649 subscribers
183 photos
15 videos
884 links
۞ ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው።

ISLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL ©
FOR CROSS :- @hayatiiii12
Download Telegram
ዱንያ ለስራ ናት እንጂ ለውጤት አይደለችም፤ ውጤቱ ያለው አኼራ ዘንድ ነው። በምድር ላይ ያለህ ግዴታ መትጋት እንጂ ውጤቱን መወሰን አይደለም።
نَحْنُ عَلَيْنَا العَمَلُ، وَعَلَى اللهِ التَّمَامُ🤩

🌙ረመዳን 2

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች
~
① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣
② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣
③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣

④ ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣
⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣
⑥ ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣

⑦ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣
⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ)
⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣

(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣
(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣
(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣

(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣
(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣
(15) ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣

(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣
(17) በዒሻእ ሶላት ላይ እየተዘናጉ አሳልፎ ዘግይቶ መግባት፣
(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣

(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣
(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣
(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣

(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)
(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣

(24) አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣
(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣
(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ

©: ኢብኑ ሙነወር

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2
ሰሑር ሲሆን የሰፈራችሁ መስጂድ ትዝ የሚላችሁና ኢፍጣር ሲሆን ሁሉንም የምታስታውሱ፣ እረፉ!

ሰሑር እየበላችሁ አዛን ሲል «የኛ መስጂድ ገና አላለም!» ብላችሁ መብላታችሁን ትቀጥላላችሁ።

ኢፍጣር ላይ ሲሆን ግን የእናንተ ሰፈር መስጂድ አዛኑ ቢዘገይም፤ የሩቅ ሰፈር መስጂድ አዛን ስትሰሙ ታፈጥራላችሁ።

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
«በሌሎች ስህተት አትደሰት። ምናልባትም በአላህ እገዛ አንተ ራስህ ትናንት ይሆናል ከዚህ ስህተት የወጣኸው። አላህ ወደፊት በዚህ ስህተት እንደማይፈትንህስ ምን ዋስትና አለህ⁉️ ይልቅ ዱዓእ አድርግ!»

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2
የጉዞ ሻንጣህ በከበደ ቁጥር ጉዞህ አድካሚ ይሆናል፣ የዱንያ ጭንቀትህ በበዛ ቁጥርም ልብህ ይዝላል! ሸክምህን ለ አላህ ስጥ እና ቀለል ብለህ ተጓዝ።
اِسْتَعِنْ بِاللّٰهِ وَلَا تَعْجَزْ🤗

🌙ረመዳን 3

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
🌙 ረመዿን - ቀን 4⃣፡ ከሚስክ ሽቶ የሚበልጠው የአፍህ ጠረን
====================
📓 እነሆ 4ኛውን ቀን ጾመን እየዋልን ነው። ጾሙ አራተኛ ቀኑ ላይ ሲደርስ፣ የሰውነታችን ድካም፣ የጉሮሯችን መድረቅ እና የሆዳችን ባዶ መሆን በደንብ መሰማት ይጀምራል። በዚህ ወቅት ብዙዎቻችን ድካሙ ሊያሸንፈን ይሞክራል።

ነገር ግን... ዛሬ አንድ ልብን የሚያረጥብና ተስፋን የሚያለመልም አስደናቂ የአላህ ቃል (ሐዲሠል ቁድስ) ላካፍላችሁ። ይህን ስታነቡ፣ ረሃባችሁ ወደ ደስታ፣ ጥማታችሁ ወደ እርካታ ይቀየራል!

💎 «ፆም ለኔ ነው፤ ዋጋውንም እኔው ነኝ የምከፍለው!»

አላህ 👆 አብዛኛዎቹን መልካም ሥራዎች ምንዳቸውን (አጅራቸውን) በቁጥር አስቀምጦልናል (ከ10 እስከ 700 እጥፍ)። ጾም ሲሆን ግን ቁጥሩን አንስቶ፣ «ሒሳቡን ለኔ ተዉት፤ እኔው ራሴ ነኝ የምሸልመው!» ይለናል።

📜 ታላቁ ሰሃባ አቡ ሁረይራ ➡️ እንዳስተላለፉት ነብዩ ⏩️ እንዲህ ብለዋል፡-
"የአደም ልጅ ሥራ ሁሉ ይባዛለታል፤ አንዱ መልካም ስራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ይባዛል። አላህ 👆 እንዲህ አለ፡- «ጾም ሲቀር! ጾም ለኔ ነው፤ ምንዳውንም (ያለ ገደብ) እኔው ራሴ ነኝ የምከፍለው! (ባሪያዬ) ስሜቱንና ምግቡን የተወው ለእኔ ብሎ ነውና!»"
[አል-ቡኻሪይ፡ 1894 እና ሙስሊም፡ 1151 ዘግበውታል]



🎁 አላሁ አክበር! የዓለማቱ ጌታ «እኔ ራሴ ነኝ የምሸልመው» ካለ፣ ሽልማቱ ምን ያህል ታላቅና ጣፋጭ እንደሚሆን አስቡት!

🌸 በተጨማሪም ነብዩ 👑 በዚሁ ሐዲሣቸው ላይ አንድ ልብን የሚሰብር እውነታ ተናግረዋል፡-

«ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! የጾመኛ ሰው የአፉ (የሆድ ባዶነት) ጠረን፣ አላህ ዘንድ ከሚስክ (ከምርጥ ሽቶ) ጠረን የበለጠ ያማረ ነው!»


ወዳጄ ሆይ! ባዶ ሆድ መጥፎ ጠረን እንደሚያመጣ የታወቀ ነው። ሰዎች ይህንን ጠረን ሊጸየፉት ይችላሉ። ነገር ግን ጌታህ አላህ ዘንድ፣ አንተ ለእርሱ ብለህ የተራብከው ረሃብ ያመጣው ጠረን፣ ከዓለማችን ውድ ሽቶ (ከሚስክ) በላይ ይወደድለታል።

ምክንያቱም ያ ጠረን የፍቅር፣ የታዛዥነት እና የኢኽላስ ምልክት ነውና!

ስለዚህ ዛሬ ጉልበትህ ሲዝል፣ ከንፈርህ ሲደርቅና ሆድህ ሲጮህ አትከፋ፤ ይልቁንም «ያ አላህ! ይህንን ድካሜን ላንተ ብዬ ነውና የተቀበልኩት፣ አንተም በጀነትህ አስደስተኝ!» በለው።

🚀 የዛሬ ሥራ:
ድካምን በፈገግታ ማሳለፍ፡
ዛሬ ጾም አደከመኝ ብለህ ፊትህን አታጨፍግግ። ጌታህ ላንተ ያዘጋጀልህን ማለቂያ የሌለው ሽልማት እያሰብክ በደስታና በፈገግታ ዋል!

አጅርን ማሰብ (ኢሕቲሳብ)፡
ሆድህ ሲርብህ፣ «አላህ ሆይ! ይህንን ረሃብ የጀነት በር በሆነው 'አር-ረያን' ለመግባት ሰበብ አድርግልኝ» እያልክ ራስህን አደፋፍር።

መልካም ንግግር፡
የአፍህ ጠረን አላህ ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነው ሁሉ፣ ከአፍህ የሚወጣው ንግግርም (ዚክር፣ ቁርኣን እና ቆንጆ ቃላት) የሚያምር ይሁን።

🤲 አላህ ሆይ! በምድር ላይ ላንተ ብለን የተጠማነውን ጥማት፣ ነገ በጀነት ውስጥ ከነብዩ ⏩️ እጅ ከሚጠጣውና ዳግም ከማያስጠማው የከውሠር ምንጭ እንድንጠጣ ሰበብ አድርግልን። ጾማችንን ያለ ገደብ ከምትመነዳቸው ምርጥ ባሮችህ ተርታ አስገባን። አሚን!

📌 ይህ መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ ተስፋ እንዲሆን ሼር በማድረግ አጅሩን ይካፈሉ።

#ረመዿን_4 #የፆመኛ_ሽልማት #አር_ረያን #ተስፋ

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
«የኔ ፍቅር... በቃ አሁን ረመዳን ገብቷል፤ ስለዚህ አናወራም፣ አንደዋወልም። ኢንሻአላህ ከረመዳን በኋላ እንገናኛለን!»

💬ይህች አረፍተ ነገር የረመዳን ፆም መግባቱን ተከትሎ በብዙ ወጣቶች ዘንድ የምትሰማ 'የጊዜያዊ ስንብት' ቃል ነች።በነገራችን ላይ ይህ ዓይነቱ ድርጊት ተውበት ሳይሆን፣ ለወንጀል የተሰጠ የዕረፍት ጊዜ ነው የሚባለው።

✔️ምክኒያቱም ወደ አላህ  የምናደርገው እውነተኛ ተውበት ተቀባይነት እንዲኖረው ከተቀመጡት መስፈርቶች አንዱና ዋነኛው «ዓዝም» ነው። ዓዝም ማለት ዳግም ወደዚያ ወንጀል ላለመመለስ በልብ የሚደረግ ጽኑ ውሳኔና ቁርጠኝነት ነው። ነገር ግን «ለአንድ ወር ላቁምና ከረመዳን በኋላ እቀጥላለሁ» የሚል ሀሳብ ካለ፣ ገና ከመነሻው እውነተኛ ተውበት አላደረግንም ማለት ነው።

✔️ረመዳን ሲመጣ ሀራም የነበረው ግንኙነት፣ ሸዋል ሲገባ ሀላል አይሆንም። የረመዳን ጌታ የሆነው አላህ  የሸዋል፣ የሻዕባን፣ የሙሀረምና የሌሎችም ወራት ሁሉ ጌታ ነው። አላህን መፍራት  ያለብን በረመዳን ብቻ ሳይሆን በሁሉም የህይወታችን እስትንፋሶች ውስጥ ነው።

«ከረመዳን በኋላ እንቀጥላለን»ብለን ቀጠሮ ስንይዝ፣ ከረመዳን በኋላ በህይወት ለመቆየት ምን ዋስትና አለን? ሞት መቼና የት እንደሚመጣ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው። በሀራም ቀጠሮ ላይ እያለን፣ ወንጀልን በልባችን እያሰብን ሞት ቢመጣስ? በአላህ ፊት በምን ፊት እንቆማለን?

❤️ውድ እህቴ! በአላህ መንገድ ያልመጣ፣ ኒካህ  የሌለው ግንኙነት የቱንም ያህል ጣፋጭ ቢመስልም መጨረሻው ፀፀት ነው። ለአንቺ ከልቡ የሚያስብ ወንድ በሀራም መንገድ አያገኝሽም። በአንፃሩም ውድ ወንድሜ፣ የምትወዳትን እህት በሀራም መንገድ እያነጋገርክ የአላህን ቁጣ አታተርፍ። እውነተኛ ፍቅር ማለት የምትወደውን ሰው ከእሳት መጠበቅ እንጂ በጋራ ወደ እሳት መጓዝ አይደለም።

ስለዚህ ምን እናድርግ?
ይህ የተባረከ ወር ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ነው። ይህን የሀራም ግንኙነት «ለረመዳን ብቻ» ብላችሁ ሳይሆን ―ለአላህ ብላችሁ― ሙሉ በሙሉ አቋርጡት። ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናበቱት። ስልኮቻችሁን ዝጉ፣ ከሀራም የሚያገናኛችሁን መንገድ ሁሉ ጥረጉ።

ሀራምን ነገር ለአላህ ስትሉ ስትተው፣ አላህ ከጠበቃችሁት በላይ የሆነን ሀላል ትዳር፣ የልብ እርጋታን፣ እና በረካን በህይወታችሁ ላይ ያዘንብላችኋል። ንጹህ የሆነው የረመዳን ፆማችሁ በሀራም ቀጠሮ አታበላሹት።

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2
በጣም አስቸጋሪው የሂሳብ አሰራር
አላህ የሰጣችሁን በረከቶች መቁጠር
ነው...❤️‍🩹

وإن تعدوا نعمة الله لا تحصوها

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
3
እንደማያየን አድርገን ወንጀል
እየሰራን እንዳላየ አድርጎ የሚምር
ጌታ እኮ ነው ያለን

ما أجملك يارب 🫶❤️‍🩹

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
3
.
አባት የልጁ ሰርግ እለት ለልጁ ባል
እንዲህ ሲል አደራ አለው...

«ልብህ የተቀየረ ጊዜ የማትወዳት ጊዜ ከመጣ እንዳትጎዳት ልጄን እንድመልስልኝ»

ስለ አባት ፍቅር ነው የማወራው!!!🤌🥹

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
3
•በነገረችን ላይ…የዓጅዋ (የመዲና) ተምር ከምግብነቱ ባሻገር ታላቅ ፈውስና መድኃኒትነት ያለው መሆኑን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አስተምረውናል።

عن سعد بن أبي وقاص رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ تَصَبَّحَ بِسَبْعِ تَمَرَاتٍ عَجْوَةً، لَمْ يَضُرَّهُ ذَلِكَ الْيَوْمَ سُمٌّ، وَلَا سِحْرٌ» (رواه البخاري ومسلم)
ከሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ እንደተላለፈው፤ የአላህ መልእክተኛ () እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡-
«ማንም ሰው በየዕለቱ ጠዋት (በባዶ ሆዱ) ሰባት የዓጅዋ ተምሮችን የተመገበ፣ በዚያን ቀን መርዝም ሆነ ድግምት (ሲሕር) አይጎዳውም።»
📚(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

✔️ኢማሙ ኢብኑል አሲር ስለ ዓጅዋ ምንነት ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል፡-

«ዓጅዋ ወደ ጥቁረት የሚያደላ የተምር ዓይነት ሲሆን፣ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመዲና ከተማ በገዛ እጃቸው ከተከሉት (የተምር ዛፍ የተገኘ) ነው።» ይላሉ።

✔️የመዲና ዓጅዋ ተምርን በተለይም ጠዋት ላይ 7 ፍሬ መመገብ ሱና ከመሆኑም በላይ፤ በመርዝ ለሚመጣ አካላዊ ህመምም ሆነ በሲሕር ለሚመጣ መንፈሳዊ ጥቃት አስተማማኝ መከላከያና መድኃኒት ነው።

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2
የአላህ ችሮታ ልክ እንደ ባህር ነው፤ አንተ ብቻ ባዶ እጅህን ይዘህ በዱዐ ቅረበው። የሰበረህን አለም ትተህ፣ ለሚጠግንህ ጌታ የውስጥህን ንገረው።
فَوض أمركَ لله، فهو جابرُ القلوبِ ومُعطي السائلين🩶

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2
ሰበር ዜና¡
~
ዓለም ሁሌም የምታወራው አዲስ ነገር አላት። ፖለቲካው፣ ትንታኔው፣ ወሬው... መቼም አያልቅም። ስልካችንን እና ቴሌቪዥናችንን ባበራን ቁጥር፣ ዓለም አሁን ካልሰማናት የምትፈርስ ይመስል በየደቂቃው በዜና ታጣድፈናለች።

ግን እዚህ ግርግር ውስጥ ምን ያህል ውድ ጊዜያችንን እያቃጠልን እንደሆነ አላስተዋልንም። የሌሎችን "ሰበር ዜና" ለመስማት ስክሪን ላይ ስናፈጥ፣ የራሳችን ዕድሜ በዝምታ እያለቀ የራሱን የሞት "ሰበር ዜና" እያቀረበልን ነው።

ወዳጄ... አእምሮህን ከሚያደነቁረው ከዚህ ሁሉ ጫጫታ ራስህን አግልል። የልብህን እርጋታ ቀስ በቀስ ከሚሰርቀው የሚዲያ ሱስ ራቅና ስክሪንህን ዝጋው።

ቁርኣንህን አንሳ። ጊዜው በፍጥነት እየሮጠ ነው። እነዚህ የተከበሩ የረመዷን ቀናት በቶሎ ያልፋሉ፤ ወይም ደግሞ ቀናቶቹ ሳያልቁ አንተ ታልፋለህ።ጊዜህን ተጠቀምበት፤ ቀናቶቹ የተቆጠሩ ናቸውና!
أياماً معدودات....

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
👍1
የረመዷን  መልዕክቶች


መች ተወለድክ?» አሉት። «በረመዷን» አለ።

በእርግጥ ውልደት ሁለት ዓይነት ነው። አንዱ ይታወቃል። ሌላኛው የመንፈስ ልደት ነው። የኢማን፣ የየቂን፣ የተውበት ውልደት ነው። የመጀመሪያው ውልደት የስኬት ምልክት አይደለም። እድለኛም እድለቢስም ይወለዳል። ሁለተኛው ግን የዱንያም ሆነ የአኺራ ስኬት ጥንቅር ፣ የከፍታ ውጥን፣ የደስታ ህይወት ጅምር ነው።

ረመዷን ራሳችንን ከወንጀል አጥርተን የምንወለድበት ወር ነው! ቀደር ያረገዘው፣ አላህ ደስተኛ ያደረገው እድለኛ የሚወለድበት ቀጠሮ!  ድካም አለው። ነገርግን ልፋታችን ሁሉ አይባክንም። ቅድስና ያለው 'ነፍሳችን' የሚወለድበት ብስራት ነውና ስቃዩን ሁሉ እንታገሳለን። በሌሊቱም በቀኑም እንበረታለን። አላህም ይረዳናል!ነገርግን በረመዷን ካልተወለድን ረመዷናችን የውሸት ምጥ ነው ማለት ነው! ህመምና ስቃይ፣ ረሀብና ጥማት ብቻ! አላህ ኸይሩን ይወፍቀን።

አጫጭር መልዕክቶች ሼር ከማድረግ አይቆጠቡ


SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
ደብዳቤ!
----
የናፈቅከኝ፣ ስመጣ በደስታ የተቀበልከኝ፣ የረህመቱ እና የምህረቱ ወር... ረመዷን ነኝ።

የመጣሁት ትላንት ይመስል ነበር፤ ዛሬ ግን የጉዞዬን ማጠናቀቂያ እያሰናዳሁ ነው። በቅርቡ እሄዳለሁ! ቀኖቼ እያለቁ፣ ሰዓታቶቼ እየተሟጠጡ ነው።

ያ ዐብደሏህ! በእነዚህ አብረን ባሳለፍናቸው ቀናት መልካም ሰርተህብኝ ከሆነ አላህን አመስግን። ሌሊቱን ቆመህ፣ ቁርአኑን አንብበህ፣ ፆሙን በኢማን ፆመህ፣ አቅምህ የፈቀደውን ሰደቃ ሰጥተህ ከሆነ… አልሀምዱሊላህ በል። የቂያማ ቀን ጌታዬ ፊት ስቆም፣ «ያ አላህ! ይህ ባሪያህ በእኔ ምክንያት እንቅልፉን ትቷል፣ ምግቡን ትቷል፣ ማረው!» ብዬ በኩራት እመሰክርልሀለሁ።

ግን ደግሞ... በቸልተኝነት አሳልፈኸኝ፣ ሞባይልህ ላይ አፍጥጠህ፣ እንቅልፍ አብዝተህ፣ ወይም በዱንያ ሀሳብ ተውጠህብኝ ከሆነ... አሁንም ጥቂት ቀናት ቀርተውኛልና እባክህን ተመለስ። የጌታህ በሮች አሁንም ክፍት ናቸው። እኔ ከመሄዴ በፊት በእንባ ታጥበህ ንፁህ ሁን።

ምን አልባት... ቀጣይ አመት ላታገኘኝ ትችላለህ!
ባለፈው አመት አብረውኝ የነበሩ፣ አብረውኝ ያፈጠሩ፣ አብረውኝ የሰገዱ ስንት ሰዎች ዛሬ ከኔ ጋር የሉም። ቀዝቃዛው መቃብር ውስጥ ገብተዋል። ቀጣዩ አመት እኔ በድምቀት እመለሳለሁ፤ አንተ ግን ከምድር ገፅ ተሰናብተህ፣ በነጭ ጨርቅ ተከፈነህ፣ አፈር ልብሰህ ይሆናል። ስለዚህ፣ ይህን የመጨረሻ ቀኖቼን ልክ ዳግም እንደማታገኘኝ አስበህ ተጠቀምበት። የመጨረሻዬ ነው ብለህ ስገድ፣ የመጨረሻዬ ነው ብለህ አልቅስ!

አደራ ኢማንህን ጠብቅ!
እኔ ስሄድ መስጊዶችን ባዶ አታድርጋቸው። እኔ ስሰናበት ቁርአንህን አቧራ አታልብሰው። እኔ የአንድ ወር እንግዳህ ነበርኩ፤ አላህ ግን የዘላለም ጌታህ ነው። የረመዷን ጌታ፣ የሸዋልም፣ የሌሎችም ወራቶች ጌታ ነውና ከእኔ በኋላም በአላህ መንገድ ላይ ፅናት ይኑርህ።

አደራህን... ጌታዬ ፊት ስቆም የምመሰክርልህ እንጂ የምመሰክርብህ አታድርገኝ።

✒️ከ አላህ እንግዳ – ረመዷን!

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
"ፈረሶች በውድድር ላይ ሳሉ መጨረሻ ሲቀራርቡ ድልን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

የረመዿን አቀባበልህ የማያምር ከነበረ፤ አሸኛኘትህን አሳምረው።

ስለዚህ፣ ፈረሶች ከአንተ የበለጠ ብልህ አይሁኑ! ሥራዎች በመጨረሻዎቻቸው ነው የሚገመገሙት።" 
- ኢብን አልጃውዚ

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2
እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በመላው ዓለም ለምትገኙ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን በሙሉ፦ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን። አላህ ጾማችንንና ዱአችንን ይቀበለን።

ዒድ ሙባረክ!

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው?

እውነተኛ ፍቅር ከስሜትና ከመሳሳብ የዘለለ ነው። ጽኑ የሆነ ቁርጠኝነትን፣ መተሳሰብን፣ መከባበርንና መስዋዕትነትን የሚያካትት ነው። እውነተኛ ፍቅር የጊዜን ፈተና የሚቋቋምና በሕይወት ውጣ ውረድ የማይናወጥ ነው።

የእውነተኛ ፍቅር መገለጫዎች:

እውነተኛ ፍቅር የሌላውን ሰው መልካም ጎን ብቻ ሳይሆን ድክመቱንም ጭምር መቀበልን ያካትታል። ፍጹም የሆነ ሰው የለምና፣ የምንወደውን ሰው ጉድለት እንደ ጉድለት ሳይሆን እንደ ማንነቱ አካል አድርገን ስንቀበል ፍቅራችን እውነተኛ ይሆናል።

የሌላውን ስሜት መረዳትና አብሮ መኖር የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ ነው። የምንወደው ሰው ሲደሰት አብረን መደሰት፣ ሲከፋ ደግሞ አብረን ማዘንና መጽናናትን መስጠት ያስፈልጋል።
በመተማመን ላይ ያልተመሠረተ ፍቅር እውነተኛ ሊሆን አይችልም። የምንወደውን ሰው ማመን፣ ለእርሱም ታማኝ መሆን የፍቅር መሰረት ነው።

እውነተኛ ፍቅር የሌላውን ሰው ክብር መጠበቅና ለሃሳቡ ቦታ መስጠትን ያካትታል። ምንም እንኳን በሃሳብ ባንስማማ እንኳ ለሌላው ሰው ክብር መስጠትና ሃሳቡን ማዳመጥ አለብን።

ለእውነተኛ ፍቅር ሲባል አንዳንድ ነገሮችን መተውና መስዋዕት መሆን ሊያስፈልግ ይችላል። ለምሳሌ፣ የምንወደውን ሰው ለማስደሰት ጊዜያችንን መስጠት፣ ወይም ደግሞ ከእርሱ ጋር ለመኖር ሲባል ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ሊያስፈልግ ይችላል።

እውነተኛ ፍቅር በችግር ጊዜ እርስ በርስ መደጋገፍን ይጠይቃል። የምንወደው ሰው ሲወድቅ እጅን ሰጥተን ማንሳት፣ ሲሳካ ደግሞ አብረን መደሰት ያስፈልጋል።
እውነተኛ ፍቅር ሁለቱም ሰዎች በግንኙነታቸው ውስጥ እንዲያድጉ ያበረታታል። አብረው መማርን፣ አዳዲስ ነገሮችን መሞከርንና የተሻሉ ሰዎች ለመሆን መጣርን ያካትታል።

ማንም ሰው ፍጹም ስላልሆነ፣ በግንኙነት ውስጥ ስህተት ሊፈጠር ይችላል። እውነተኛ ፍቅር ስህተትን ይቅር ማለትና ወደፊት መጓዝን ያስተምራል።
እውነተኛ ፍቅር ጊዜን ይፈልጋል። ግንኙነታችንን ለማሳደግና ለማጠናከር ጊዜን መስጠት ያስፈልጋል።

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትቶህ የሄደን ይሂድ ተወው። ማን እንደሚጎዳ እናያለን። ስላንተ ግድ የሌለዉን ለሰከንድ እንኳን ጊዜ አትስጠው፣ ሞኝ አትሁን። እንደማይገባው እያወቅክ ከፍ ያረግከው እንደሆን የሰው ልጅ ልኩን ይረሳል።

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
1
ወዳጅ የማይፀናበት፣ መሠለቻቸት የበዛበት ዘመን ነዉና አንዳንድ ጊዜ ብቸኝነትንም አስቀድማችሁ ተለማመዱት።

SHARE 💫
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ያበረታቱን።
╔════════════╗
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||
    JOIN: || INAS ISLAMIC ||

    ♡ㅤ            ❍ㅤ                ⌲ 
   ʟɪᴋᴇ        ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         sʜᴀʀᴇ‌‌
2👍1