National ID Program - Ethiopia
56.4K subscribers
617 photos
98 videos
233 links
Identity is the new collateral!
መታወቅ ለመተማመን።
ለማንኛውም ጥያቄ:- id.et/help
Download Telegram
Congratulations to our own Yodahe Zemichael for being named one of Okta’s Identity 25, recognizing global leaders in digital identity!

See the whole list here: https://www.okta.com/resources/datasheet-the-identity-25/

#DigitalID #Innovation #ፋይዳለኢትዮጵያ
10ኛ ዙር የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለስደት ተመላሾችን እና ፍልሰተኞችን በቦሌ ሚካኤል እና ቃሊቲ ጣቢያዎች ላይ ተጨማሪ የምዝገባ ማሽኖችን ወደ ሥራ በማስገባት ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ እያከናወኑ ይገኛሉ።

በአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እየተመራ ያለው ይሄ ምዝገባ ፤ በተጨማሪም በጣቢያው ውስጥ ለተመላሾች ፋይዳን በመጠቀም የሲም ካርድ እና ሌሎች አገልግሎት እንዲያገኙም እየተደረገ ነው።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #አካታች #ፋይዳለሁሉም #DigitalID
የፋይዳ ልዩ ቁጥር ካልደረሰዎት ወይም ከጠፋብዎት ደግመው መመዝገብ አያስፈልግዎትም።

ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ ሲስተሙ ማንነትን በልዩ ሁኔታ ለመለየት የሚወስድበትን ጊዜ በማስረዘም ልዩ ቁጥርዎ በጊዜው እንዳይደርስዎ ያደርጋል።

የፅሁፍ መልዕክት ካልደረሰዎ ወይም ከጠፋብዎ *9779# ላይ ጥሪ በማድረግ ወይም የፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ "Fayda ID" በመጠቀም የፋይዳ ቁጥርዎን ወደ ስልክዎ ይላኩ።

መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp እንዲሁም ከአፕ ስቶር https://apps.apple.com/app/fayda-id/id6740314990 ላይ በማውረድ ይጠቀሙ ፣ የፋይዳ አገልግሎቶችን በቀላሉ ያግኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ብሉስካይ
ፋይዳን ለትምህርት ቤት ምዝገባ

ለመጪው የትምህርት ዘመን በመንግስትም ሆነ በግል የትምርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደም ሁኔታ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ወላጆች ከ 5 አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ተማሪዎችን ከወዲሁ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡

የፋይዳ ቁጥር ከጠፋብዎ ወይም ካልደረስዎ *9779# ይደውሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለተማሪ #መታወቅ #DigitalID
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መታወቅ ለመተማመን!
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከት እንዲሁም የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

መታወቅ ለመተማመን!

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID
በፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ " Fayda ID" ምን አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp እንዲሁም ከአፕ ስቶር https://apps.apple.com/app/fayda-id/id6740314990 ላይ በማውረድ ይጠቀሙ ፣ የፋይዳ አገልግሎቶችን በቀላሉ ያግኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID #InclusiveID
ፋይዳን ለፖስፖርት

ከሰኔ 1 ፣ 2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ዋና ሰነዶች ውስጥ በማካተት አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት @ICS_Ethiopia ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል።

በመሆኑም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ የፋይዳ ልዩ ቁጥራቸውን በመያዝ ፣ QR ኮዱን በወረቀት አትመው ፣ ዲጂታል ኮፒውን በ "Fayda ID” application በኩል ይዘው ወይም ትክክለኛውን QR የያዘ ሌላ አማራጭ ተጠቅመው ይዘው በመምጣት ብቻ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

አገልግሎቶች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በመተሳሰራቸው አንድ ወጥ ደረጃ ያለው እና የተናበበ መረጃ በብሔራዊ ደረጃ እንዲኖረን በማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ሙሉ መግለጫውን id.gov.et/news ላይ ያገኙታል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID #fayda
የውይይት ጥሪ

ረቡዕ ሚያዝያ 29 ቀን ከቀኑ 8:30 - 10:30 ሰዓት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ የሚደረገው የኦንላይን ውይይት መድረክ ላይ በዚህ ሊንክ https://zoom.us/j/92025143191?pwd=YdlyextNuOcheHtQ3NpLVAnhI6ivUv.1 በመግባት ይሳተፉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳመታወቂያ #DigitalID
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዝግጁ ነዎት?

የፊታችን እሁድ ግንቦት 3 የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በመዲናችን ለሚያካሔደው የፋይዳ ሩጫ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

በነጻ የሩጫ ቲሸርት ለመሸለም የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከታተሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳሩጫ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክX | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ብሉስካይ
የፋይዳ ለኢትዮጵያ ሩጫ የፊታችን እሁድ ይካሔዳል።

ከ20,000 በላይ ተሳታፊዎች የሚኖረው የ5 ኪ.ሜ የፋይዳ ሩጫ ግንቦት 3፣2017 እንደሚካሄድ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሙሉ መግለጫዉን : id.gov.et ላይ ያገኙታል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳሩጫ #DigitalID
ይመልሱ ፤ ይሸለሙ!

ጥያቄ 1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገብ የሚቻለው ከስንት አመት ጀምሮ ነው?

በትክክል በመመለስ በመዲናችን ልዩ የሆነ "ፋይዳ ለኢትዮጵያ" የጎዳና ላይ ሩጫ ላይ ለመሳተፍ ዕድል ያግኙ።

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና ከአዲስ አበባ ስፖርት ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እና የማህበረሰቡን የዲጂታል ብሎም ስፖርታዊ ንቃት ለመጨመር ይረዳ ዘንድ 3 ግንቦት 2017 ዓም የሩጫ ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

በአስተያየት መስጫ ላይ መልሱን በትክክል ለፃፉ የተወሰኑ ዕድለኞች የሩጫ ቲ-ሸርት እንሸልማለን።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ፋይዳሩጫ #DigitalID
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፋይዳ ለኢትዮዽያ ሩጫ ግንቦት 3 የአካል ጉዳተኞችን ውድድር ጨምሮ ከ25,000 በላይ ተሳታፊዎችን የተለያዮ ውድድሮችን በማካተት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ኩራት ይሰማናል።

ቁልፍ ባለድርሻ አካል ለሆኑት ከአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፣ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ፣ እንዲሁም ስትራቴጂክ አጋር ድርጅት ለሆኑት ኢትዮ ቴሌኮም ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ስኬት ባንክ ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት እንዲሁም ፕሮግራሙን በቀጥታ ስርጭት ሲይስተላልፉ ለነበሩት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንክ ኮርፖሬት እና አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።

በፋይዳ ይታወቁ ፣ በፋይዳ ይገልገሉ ፣ በፋይዳ ይዘምኑ!!!

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #አካታች #DigitalID
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Just 5 days to go!

Are you ready for the most impactful identity conversation of the year #ID4Africa?
See you in Addis Ababa in May 20-23 for a line up of panel and programs that will shape the future of digital identity.

For more on the program: https://id4africaevents.com/

#DigitalID #ID4Africa2025
#MeetInEthiopia
"ፋይዳ ብዝኀ ማንነት ላላት ኢትዮጵያ አስፈላጊ ነው" የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ

በዛሬው እለት በአማራ ክልል በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አተገባበር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ። በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እና ያለው ጠቀሜታ እንዴት ወደ መሬት አውርዶ መሰራት እንዳለበት ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መሥተዳድሩ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ ሀገር በርካታ ጥቅሞችን ያስገኛል ያሉ ሲሆን ፣ ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትስስርን በመፍጠር የመንግሥት እና የዜጎችን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር የሚረዳ ነውም ብለዋል።

በመድረኩም ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሰተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አሕመዲን መሐመድ ፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርዓያሥላሴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ አሁን ላይ እየተተገበረ ያለውን የምዝገባ ሒደት ምን እንደሚመስል አንስተው ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር በቀጣይ መደረግ ስላለባቸው እና መወሰድ ስለላባቸው እርምጃዎች ላይ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተነጋገረዋል።

#ፋይዳለኢትዮዽያ #መታወቅ #DigitalID
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ፋይዳ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ ነው።" ክቡር ጠ/ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በኢቢኤስ ቴክቶክ ሾው ላይ

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #አካታች #DigitalID