የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከሐረሪ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሔዱ።
በመድረኩም በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ክቡር አቶ ጌቱ ወዬሳ "ፋይዳ ዜጎች ወጥ የሆነ ማንነት እንዲኖራቸው በማስቻል የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና የዜጎችን እርካታን ለማሳደግ የሚያስችል ነው" ብለዋል።
የፋይዳ መታወቂያ ከፍተኛ አመራሮች ፋይዳ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እና ነዋሪዎች በዲጂታል መንገድ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ የሚያመቻች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማስተሳሰር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀዋል።
ክቡር አቶ ጌቱ የሀረሪ ክልል አመራሮች እና ማህበረሰቡ የፋይዳ ትግበራን በመደገፍ በአጭር ግዜ ወስጥ የክልሉን ነዋሪ መዝግቦ ማጠናቀቅ እንደሚገባ በአፅኖት ገልፀዋል።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳመታወቂያ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከት እንዲሁም የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
መታወቅ ለመተማመን!
#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID
መታወቅ ለመተማመን!
#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID
በድሬዳዋ አስተዳደር ሁሉንም ነዋሪ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የምዝገባ ዘመቻ እና የነዋሪነት መታወቂያ የትስስር መርሃ ግብር ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ ከተቋማት የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት፣ የከተማ እና የገጠር ወረዳዎች ስራ አስፈፃሚዎች እና የማስተባበሪያ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩም የድሬዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ “ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ ሀገር ከያዝናቸው እና ከምንተገብራቸው የልማት እቅስቃሴዎች አንዱ ነው” ብለዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ድሬዳዋ ከተማን ስማርት ሲቲ ከማድረግ አንጻር የተለያዩ የዲጂታል ስርዓቶችን በማልማት ለነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ተደራሽ ለማድረግ ከሚሰራው ስራ አኳያ የድሬዳዋ የነዋሪነት መታወቂያን ዲጂታል ማድረግ አንዱ ነው።

በፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ " Fayda ID" ምን አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp እንዲሁም ከአፕ ስቶር https://apps.apple.com/app/fayda-id/id6740314990 ላይ በማውረድ ይጠቀሙ ፣ የፋይዳ አገልግሎቶችን በቀላሉ ያግኙ።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID #InclusiveID

ፋይዳን ለፖስፖርት
ከሰኔ 1 ፣ 2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ዋና ሰነዶች ውስጥ በማካተት አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት @ICS_Ethiopia ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል።
በመሆኑም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ የፋይዳ ልዩ ቁጥራቸውን በመያዝ ፣ QR ኮዱን በወረቀት አትመው ፣ ዲጂታል ኮፒውን በ "Fayda ID” application በኩል ይዘው ወይም ትክክለኛውን QR የያዘ ሌላ አማራጭ ተጠቅመው ይዘው በመምጣት ብቻ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
አገልግሎቶች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በመተሳሰራቸው አንድ ወጥ ደረጃ ያለው እና የተናበበ መረጃ በብሔራዊ ደረጃ እንዲኖረን በማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ሙሉ መግለጫውን id.gov.et/news ላይ ያገኙታል።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID #fayda

በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ለዚህ ቁርጠኝነታቸን አንዱ ማሳያ የሆነውን የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከልን ዛሬ መርቀናል።
ይኽን አዲስ ማዕከል የሚገልጡ ሶስት ቁልፍ አላባውያን አሉ። የቆየ እና የተጎዳ ህንፃን ወደ ዘመናዊ እና ሥነውበታዊ ደረጃው ለሥራ ከባቢ አስደሳች ወደ ሆነ ህንፃ መለወጡ አንዱ ነው። አገልግሎቶችን ለመሰተር እና ለማቀናጀት በሀገር ውስጥ የለማ ሶፍትዌር በሥራ ላይ መዋሉ ብሎም በታደሰ አመለካከት ብቁ እና ክብር የሞላበት አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች መዘጋጀታቸው ሌሎቹ አላባውያን ናቸው። 12 ተቋማት በአንድ ጣሪያ ሥር 40 የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት የጀመሩ ሲሆን ይኽም ዜጎች ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡ እና አገልግሎቶችን በተሻለ ውጤታማ መንገድ ለማግኘት ያግዛል።
እንደዚህ ያሉ ሥርዓቶችን ማበልፀግ ለዜጎች የተለያዩ የአገልግሎት ርካታ መታጣቶች ምላሽ በመስጠት በሂደት ለሰፊው ማኅበረሰብ ርካታ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል። የዛሬው ምረቃ ትልቅ ርምጃ መራመዳችንን ያሳያል። ኢትዮጵያ በዚህ ማዕከል ላይ ጨምራ እና አስፋፍታ ለዜጎች ሁሉ የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥን ታረጋግጣለች።