ፍቅር እና ስብእና
128 subscribers
3 photos
2 files
4 links
ፍቅር ያሸንፋል
Download Telegram
#ትንሹ ህመም

ነፍሴን ሲያርደዉ አስገምጋሚዉ ድምፅ
የሚገስፀዉ እኔን በጥሩ ስሜን የሚያንፅ
ለጊዜው ሀዘን ቆይቶ ደስታ ዉስጤ ሰፈነ
የጥፋትን ሀቅ ሀጢያትን ከእኔ አመነመነ
ቤት ዉስጥ ሰብስቦ ፍቅርን ወጠነ
ለአንድነቱ ብዙ አምጦ በስቃይ ብዛት
እቅዱ ሰምሮ ሲቃም ቢበዛ አንድ ሆኖለት
በቁጣ ብዛት በፍርሀት ብዛት ብንዘፈዘፍም
ለጊዜው እንጂ ብርድ የመሰለኝ የጥፋት አረም
መንቀሉ እንጂ ሙቀት ይሆናል አይሆን ዘለአለም
መሆኑ ገባኝ አሁን ሲያድነኝ ያኔ ስታመም
እንዳንዴም እኮ መድሀኒት ለኛ ብዙ የሚሰራው
ብዙ ድህነትም የሚያስገኝልን ትንሽ ህመም ነዉ
ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህፃን

በደብተርሽ ምትክ
ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎሂያጅ እግር ስር፤
እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው !!
አፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ
መስኩ ከነጎርፉ ፥
ሰማይ ከነዶፉ ፥ ለጌቶች ተሽጦ
አተር ነው እያሉ፤ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጦሽ
ገና በልጅነት፤ ልጅነት አምልጦሽ፡፡
በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ
በክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው ፤ ለሰው አይሰማ፡
ጠዋት የፎከረ ፤ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸክም ፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡

[ በእውቀቱ ስዩም ]


ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/Human_intellegence
1
''ለምንድን ነዉ የምንኖረው? የህይወት ትርጉሙ ምንድን ነዉ?

እንወለዳለን፥እድለኛ ከሆንን እናድጋለን፥እናረጃለን፥እንሞታለን።

ከእንስሳ የተለዬ ህይወት አይደለም።ልዩነት ቢኖር የሰዉ
ልጅ ስለ መኖር ያለዉ የማሰብ ችሎታ ብቻ ነዉ። ማሰብ ባይኖር ኖር ክፋን ለበጎ ለይቶ ለማወቅ ህሊናችን አይጨነቅም ነበር። ህይወት አጭርና ጅል ነገር ናት!

ግን ታስጨንቀናለች። የጭንቀቱ መሰረት የማሰብ ችሎታችን ነዉ። ሌላ አይደለም። የማሰብ ችሎታችን እፎይታ፥ሰላም፥ዘላለማዊ ፀጥታ! የሰዉ ዘር ሞኝ ነዉ። ጅል ነዉ። ለመኖረዉ
አጭርና ጅል ህይወት፥ ገና ለገና የማሰብ ችሎታ አለኝ ብሎ፥ለእንስሳ ባህሪይዉ የረቀቀ ና የላቀ ትርጉም ሊሰጠዉ ይሞክራል።

መኖር ስቃይ ነዉ። ለማትረባ አጭር ህይወት ብዙ ስቃይ፥ መዋተት፥መጨነቅ፥
መቃተት፥መቡዋጠጥ፥መንጠራራት፥ ትርጉሙ ምንድን ነዉ? ዞሮ ዞሮ ጥሪኝ መቃብር!

ሞት ነዉ ዘላለማዊ ነገር። ሞት ዉበት ነዉ። የሰዉ ልጅ ግብ ነዉ። ግን እንፈራዋለን። ተወልዶ፥አድጎ፥አርጅቶ፥መሞት መኖሩን እያወቅን ሞትን ልናመልጠዉ እንሞክራለን።

እና የሰዉ ልጅ የወል እብደት ምንጩ ይኸዉ ነዉ። በፍርሃት ጥላ ስር የሚኖር ሁሉ በዚህም ሆነ በዚያ
እብድ ነዉ። የእያንዳንዱ ሰዉ የእብደት መጠን ወይም ደረጃ ጠባይ፣ባሕርይ እንለዋለን....''

[ በዓሉ ግርማ ]
👍1
The social media Dilemma
በወንድዬ እንግዳ
#Repost

ጠዋት ስትነሳ ግራ እግርህ ይስራ አይስራ ሳታረጋግጥ መጀመርያ ስልክህን አንስተህ "facebook" ቼክ ታደርጋለህ። ሽንት ቤት ቁጭ ብለህ "Instagram" ላይ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን "scroll" እያደረክ ትኮሞኩማለህ። ስልክህ ካርድ ከሌለው ቶሎ ገዝተህ "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ እስክትጣድ ያንቀለቅልሃል! የሆነ ፅሁፍ ለጥፈህ ምን ያህል "like" እና "comment" እንዳገኘህ ለማወቅ በየደቂቃው "Refresh" እያደረክ ታያለህ። የለጠፍሽው ፎቶ ምን ያህል "like" እንዳገኘ ለማወቅ ያቅበዘብዝሻል። የጠበቅሽውን ያህል "Reaction" ካላገኘ ተበሳጭተሽ ፎቶውን ታጠፊዋለሽ። "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ የምታውቃቸው ሰዎች ለተወሰነ ግዜ ሲጠፉብህ ይጨንቅሃል። ስማቸውን ሳይቀር ፅፈህ ትፈልጋቸዋለህ። ፎቶሽ ላይ ሁል ግዜ "...የኔ ቆንጆ፣ የኔ ልዕልት፣ ስታምሪ.." ምናምን እያለ "comment" የሚያደርግልሽ ልጅ በሆነ አጋጣሚ አዲስ የለጠፍሽው ፎቶ ላይ "comment" ካላደረገ ያሳስብሻል። የለጠፍከው ፎቶ ወይም ፅሁፍ "like" ብዙም ካላገኘ እራስህ "like" ታደርጋለህ። መስሪያ ቤትህ በሰጠህ ኮምፒውተር "facebook" ትጠቀማለህ። ከሰዓት ማስገባት ያለብህ ወሳኝ ስራ እያለ አንተ "tiktok" ላይ ትጣዳለህ። ጠዋት ተነስተህ ወደ ስራ መሄድ እንዳለብህ እያወቅ ማታ ላይ አንድ ሰላሳ ደቂቃ "Tiktok" ልይ ብለህ እስከ ለሊቱ 9 ሰዓት ድረስ ተጥደሃል። በንጋታው ስራ ረፍዶብሃል ወይም "Tiktok" ላይ ለሊቱን ሙሉ ተጥደህ በቂ እንቅልፍ ባለማግኘትህ ምክንያት ጠዋት ታክሲ ውስጥ አንቀላፍተሃል፣ ቀንህ ተጦልቧል። አንድ ቪድዮ "YouTube" ላይ አያለው ብለህ የገባህ ሰውዬ ሳታስበው "30 ቪድዮ" አይተሃል። "Facebook" ላይ ተጀናጅናችሁ፣ የባጥ የቆጡን ሳትተፋፈሩ አውርታችሁ፣ ተዋዳችሁ፣ ሳትገናኙ እዛው "Facebook" ላይ ተጣብሳችሁ በመጨረሻም በአካል ስትገናኙ ተሽኮርምመሃል፣ አፍረሃል፣ መሬት መሬት አይተሃል፣ ተንተባትበሃል። ከጓደኞችህ ጋር ምሳ ለመብላት ተገናኝታችሁ ምግቡ እስኪመጣ በፊት ስለ ውሏቹ፣ ገጠመኞቻችሁ፣ ስለ ቤተሰቦቻችሁ፣ ስለ ስራችሁ ምናምን በሰፊው የምትቀዱ ሰዎች አሁን ሁላችሁም ስልካችሁ ላይ አቀርቅራችኃል። እየበላችሁ ሳይቀር ከስልኩ ጋር የሚበላ ከመካከላችሁ አይጠፋም። ስልክህን አብዝተህ ከመውደድህ የተነሳ ትራስህ ስር ወሽቀኸው ትተኛለህ። መብራት ሲጠፋ መጀመርያ የሚያሳስብህ ምግብ ማብሰል አለመቻልህ፣ ቴሌቪዥን ማየት አለመቻልህ ወይም ጨለማ መሆኑ ሳይሆን ስልክህን ቻርጅ ማድረግ አለመቻልህ ነው። ስልክህ ላይ ተጥደህ በመዋልህ ምክንያት ለሚስትህ የምትሰጣት ግዜ ቀንሷል፣ የምትተኙበት እና የምትነሱበት ሰዓት ተለያይቷል፣ ከልጅህ ጋር የምትጫወትበት ግዜ ወርዳል። ማህበራዊ ህይወትህ ተመቷል። ሰዎችን በአካል አግኝተህ ከምታወራቸው ይልቅ በ "Telegram" ወይም "Messanger" ብታወራቸው ይቀልሃል፣ በአካል መገናኘት ይጨንቅሃል። ጆሮህ ላይ የምትተክለው "Earphone" መገለጫህ እስኪሆን ድረስ ተጣብቆብሃል። የ "Internet' መቋረጥ ሞት እስኪመስልሽ ድረስ ያስጨንቅሻል። ብቻ ምን አለፋህ ስልክህ ህይወት ሆኗል!
አባዬ! ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!


ዓለማችን ካላት ወደ 7 ቢልዮን ከሚገመት ህዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 3 ቢልዮን የሚሆነው ማህበራዊ ሚድያ(facebook, Instagram, snapchat, twitter, tiktok.....) ይጠቀማል። በቅርቡ በ"Netflix" የተሰራ "The Social Dilemma" የሚል ዶክመንተሪ አየሁ። ተራ ዶክመንተሪ አይደለም ጌታዬ! እዚህ ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ግለሰቦች ከባድ ሚዛን ናቸው። "Instagram" መጀመርያ ላይ ሃሳቡ ሲጠነሰስ አብረው የነበሩ ፣ "Twitter" ውስጥ ለአመታት በኢንጅነርነት ያገለገሉ፣ "pintrest" የመጣ ሰሞን ፕሬዝዳንት ሆኖ የሰራ፣ "Facebook" ውስጥ የ "monetization" ክፍል ዳይሬክተር የነበረ፣ "Google Drive"ን የፈጠሩ፣ "Facebook" ላይ ያለችውን "Like button" የሰራ፣ "Google" ውስጥ በዲዛይነርነት የሰሩ ፣" Gmail" መጀመርያ ሲፈጠር አብረው የነበሩ እና የ "Facebook" ስራ አስፈፃሚ(Executive) ቡድን ውስጥ ሳይቀር የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ከነዚህ ከባባድ ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በፍቃደኝነት ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የሚሰሩት ትውልድን ሽባ የሚያደርግ ስራ ስለቀፈፋቸው ተጣልተው ወይ ተባረው የወጡ ናቸው።
የሚያስደነግጥ ነገር!
ሁሉም የሚያወሩት አንድ አይነት ነገር ነው። ምን ይላሉ መሰላችሁ!!
...የቀጠለ

"....የየትኛውም ማህበራዊ ሚድያ የ " Business Model" እንዴት ተጠቃሚዎቻችንን ስክሪን ላይ ማቆየት እንችላለን የሚል ነው! አንድን ተጠቃሚ "Facebook" ወይም "Youtube" ላይ ለማቆየት እና በይበልጥ ትኩረቱን ለመሳብ ምን እናድርግ? የህይወቱን ስንት አመታት ለኛ እንዲሰጠን እናድርግ? የሚለውን ታሳቢ አድርገው ነው የሚሰሩት! እነዚህ "Tech ካምፓኒዎች" ተጠቃሚዎቻቸው "Online" የሚመለከቱትን ማንኛውንም ነገር ያያሉ፣ ይከታተላሉ፣ ይመዝናሉ፣ ያጠናሉ። አንድን ፎቶ ለምን ያህል ደቂቃ ቆም ብለህ እንዳየህ እና የሆነን ቪድዮ እስከ ስንተኛው ደቂቃ ድረስ እንደተከታተልክ ሳይቀር ያውቃሉ! ሲከፋህ ያውቃሉ፣ ሲጨንቅህ ያውቃሉ፣ ስትጓዝ ያውቃሉ፣ ማታ ማታ ምን እንደምታይ ያውቃሉ፣ ቀን ቀን ምን አዘውትረህ እንደምታይ ያውቃሉ። እኛ ከምናስበው በላይ እነዚህ ካምፓኒዎች ጋር ስለኛ ብዙ መረጃ አለ!...."

አባዬ! "Youtube" ልትገዛው ያሰብከውን እቃ መሃል ላይ አስተዋውቆት አስደንግጦህ ያውቃል? የሆነ ልትማር ያሰብለውን ትምህርት በምታየው "Video" መሃል በማስታወቂያ መልክ አምጥቶብህ አልተገረምክም? "Facebook" የዛሬ 10 ዓመት የምታውቀውን እና ከዛ በኃላ አግኝተኸው የማታውቀውን ሰውዬ "people you may know" ላይ ገጭ አድርጎት አይተህ ገርሞህ አታውቅም? "Google" ላይ የሆነ "lipstick" "Search" አድርገሽ ከወጣሽ በኃላ በንጋታው ሌሎች ማህበራዊ ሚድያዎችን ስትከፍቺ የ"lipstick" ማስታወቂያዎች አስሬ እየመጡ አዝገውሽ አያውቁም?
ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

"...አብዛኛዎቻችን የምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚድያ መተግበርያዎች ነፃ ይመስሉናል! ነገር ግን አይደሉም! ለነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች ማስታወቂያ ድርጅቶች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ይከፍላሉ! እኛ ልክ እንደ እቃ(product) ነን! እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የምንወደውን፣ የምንጠላውን፣ የምናደርገውን እና ያቀድነውን ስለሚያውቁ ለነዚህ ማስታወቂያ ድርጅቶች የኛን መረጃ(data) ይሸጡላቸዋል!...በቀላሉ ካሌንደርህ ላይ በቀጣይ ወር መነፅር እንደምትገዛ ከፃፍክ ቀኑ እየቀረበ ሲመጣ ብዙ የመነፅር ማስታወቂያዎች ይመጡብሃል! ኢሜልክ ላይ የሆነ ሃገር የምትሄድበት ትኬት ካለ እዛ የምትሄድበት ሃገር ላይ ያሉ የሆቴሎች ማስታወቂያ ይመጣብሃል!..."

ጌታዬ! "Algorithm" የሚባል ነገር አለ! በአጭሩ አዘውትረህ የምትመለከታቸውን ቪድዮዎች፣ ዜናዎች፣ መረጃዎች እና ፅሁፎች እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች በደንብ ካጠኑ እና ከመዘገቡ በኃላ ማንነትህን የሚያውቁበት መንገድ ማለት
ነው። ለምሳሌ "Youtube" ከፍተህ አንድ ሁለት ቪድዮ ስለ የሆነ ነገር ካየህ በቀጣይ "YouTube" ላይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ተመሳሳይ 100 ቪድዮዎችን " Recommended" ላይ ያመጣብሃል! "Facebook" ላይ ስለ አንድ ጉዳይ በተደጋጋሚ የምታነብ ከሆነ በቀጣይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ብዙ መረጃዎችን ያዘንብብሃል! የአንድ አካባቢ ሰዎችን ጓደኛ ካደረክ በቀጣይ እዛ አካባቢ ያሉ ብዙ ሰዎችን ጓደኛ እንድታደርግ ያመጣልሃል! ለምሳሌ "Tiktok" ላይ ገብተህ ተገላልጠው የሚደንሱ ሴቶችን አንድ ሁለት ቪድዮ ካየህ ከዛ በኃላ "tiktok" ተቆጥረው የማያልቁ ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ያዥጎደጉድልሃል! የ "Tiktok" "Algorithm" ደግሞ ይለያል! ፍላጎትህን ለመለየት አንድን ቪድዮን ለምን ያህል ደቂቃ እንዳየህ ሳይቀር ያሰላሉ!
ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

"...ስራችን የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን ልክ እንደ "ማሽን/ኮምፒተሮች" "program" ማድረግ ነው። ሰዎች አዲስ ማንነት እና ባህሪን እንዲላበሱ ማድረግ ነው። አንተ ለኛ ልክ እንደ የላብራቶሪ አይጥ ነህ። ዓለም ላይ ሁለት ኢንደስትሪዎች ብቻ ተጠቃሚዎቻቸውን "users" ብለው ይጠራሉ። አንደኛው የአደንዛዥ እፅ ኢንደስትሪ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማህበራዊ ሚድያው ኢንደስትሪ ነው። ሌሎች ኢንደስትሪዎች ተጠቃሚዎቻቸውን "Customers(ደንበኞች)" ወይንም "Buyers(ገዢዎች)" ነው የሚሉት!
"Refresh" ባደረክ ቁጥር አዲስ ዜና፣ አዲስ መረጃ፣ አዲስ ፎቶ እንድታይ ነው የሚፈልገው። ምክንያቱም ግባቸው አንተን ከስልክህ አጣብቆ ማቆየት ነው።
እቅዳቸው ተጠቃሚዎቻችን "perfection(ፍፁማዊነት)" እና "Social Approval(ማህበራዊ ተቀባይነት)" እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።አንዲት ሴት ዝም ብላ አንድ የራሷን ፎቶ ምንም ሳትጨምርበት ብትለጥፍ የምታገኘው "like" ያንሳል። ነገር ግን የተለያዩ የውበት መጨመርያ ፊልተሮችን ተጠቅማ ፎቶዋን ብታሳምር፣ ሻዶው ብትጨምር፣ የቆዳ ቀለሟን ፈካ ብታደርግ እና ፊቷ ላይ ያለውን ብጉር ብታጠፋ የምታገኘው "like" እና "comment" ይበዛል። "...ቆንጆ፣ ስታምሪ፣ ከንፈርሽ፣ ፊትሽ..." ምናምን የሚሏት ሰዎች ይጨምራሉ። ግባችን የተወደደች፣ ሰዎች በውበቷ የሚቀኑባት፣ ከሌሎች ጓደኞቿ የተሻለ ተከታይ እና "social approval" ያላት ሴትን መፍጠር ነው። የሚያሳዝነው ልጅቷ ያንን ሁሉ "comment" እና "like" ያገኘችው እሷን ሆና አይደለም! የውሸት/የተጋነነ ማንነትን እንድትፈጥር አድርገናታል። ትክክለኛ መልኳን እና ማንነቷን እንድትጠላው አመቻችተናል! ለዛም ነው ብዙ ሴቶች ጭንቀት እና የአዕምሮ መታወክ የሚያጋጥማቸው። የሚለጥፉትን ፎቶ ለመምሰል ብዙ ሴቶች ቀዶ ጥገና እስከማድረግ ደርሰዋል!ማህበራዊ ሚድያዎች ዋነኛ አላማቸው የተጠቃሚዎችን "Social Media Engagement (ማህበራዊ ሚድያ ቆይታ)" ማሳደግ ነው። በአሁኑ ሰዓት ወደ 214 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች የማህበራዊ ሚድያ ሱሰኞች ሆነዋል። የማህበራዊ ሚድያ ሱስ ከ "Cocaine" ሱስ ጋር አንድ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ "Dopamine" የሚባል የደስታ ስሜትን የሚረጭ ሆርሞን አለ! ሱሰኛ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮኬይን ወይም ሌላ አደንዛዥ እፅን ሲያስቡ አዕምሮዋቸው "Dopamine" ይረጫል፣ ደስታ ይሰማቸዋል። ማህበራዊ ሚድያም እንደዛ ነው! ማህበራዊ ሚድያን ከፍተህ ለማየት እንድትንቀለቀል የሚያደርገህ ወደ ሰውነትህ የሚረጨው "dopamine" ነው! በአማካይ ሰዎች በቀን 2 ሰዓት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚጠቅማቸውንም የማይጠቅማቸውንም ነገር በማየት ግዜያቸውን ያጠፋሉ! ይህ ማለት ከአጠቃላይ እድሜያቸው ድፍን አምስት አመታትን ያባክናሉ ማለት ነው! አሁን ላይ ከሶስት ፍቺዎች ውስጥ አንዱ ከማህበራዊ ሚድያ ሱስ ጋር በተያያዘ ሆንዋል!...." እያሉ ይቀጥላሉ! ከዚህ በላይ ከቀጠልኩ ሙሉ ዶክመንተሪውን መጨረሴ ነው!
ማጠቃለያ!

ይህንን ሁሉ ካወሩ በኃላ እንደ መፍትሄ ከሚያስቀምጧቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱን ላስቀምጥ እና ልውጣ!
"Notification" የሚባል ነገርን "off" ማድረግ! በየደቂቃው ስልክህ ላይ "እንትና አዲስ ፅሁፍ ለጠፋ፣ እንትና አዲስ ፎቶ ለቀቀች፣ እገሌ እንዲህ ሆነ..." እያሉ "Notification" የሚልኩልህ ትኩረትህን ለመሳብ ነው። የቆይታ ግዜህን ለማሳደግ ነው። ያንተን "Algorithm" በደንብ ቀርጥፈው ስለበሉት ነው። አንተ ተቆጣጠራቸው እንጂ እነሱ እንዲቆጣጠሩህ አታድርግ! ማየት ስትፈልግ እራስህ ግባ እንጂ "Notification" አይቆስቁስህ!

ተጨማሪ መፍትሄዎቹን ማወቅ ከፈለጋችሁ ዶክመንተሪውን እዩ
ግሩም አባባሎች

"ያለምክንያት የሚወድህን አምላክ እያሰብክ ያለምክንያት የሚጠሉህን ሰዎች እርሳቸው።"

"እያንዳንዱ ቀን ትንሽ ህይወት ነው ከእያንዳንዱ ህይወት ቀን ጀርባ አዲስ ህይወት አለ፣እያንዳንዱ ጠዋት ትንሽ ወጣት እያንዳንዱ የሌለት እንቅልፍ ትንሽ መሞት ነው።"
አርተር ሾፐን ሀወር


"ፍቅርን ማያዉቁ ሰዎች ፍቅር እዉር ነዉ ይላሉ፤ እኔ እላለሁ አይን ያለዉ ብቸኛ ነገር ፍቅር ብቻ ነዉ፤ ከፍቅር ዉጭ ሁሉንም ነገር እዉር ነዉ።"
ኦሾ

"የተሳሳቱ ሰዎች ሃይማኖትን በተሳሳተ መንገድ ይጠቀማሉ ፡፡ በዚህ ምክንያት ሃይማኖት ለላቀ ተጋድሎ እና ለከፋ መከፋፈል አስተዋጽኦ ያደርጋል ፡፡"
ዳላይ ላማ

"ዛሬን ለሰይጣን ነገን ደግሞ ለእግዚአብሔር አትስጡ።"
ቅዱስ ጎሮጎርዮስ

"ጥሩ ምላስ ስውር ማህተብ ያላት የዘመኑ ሰርተፊኬት ናት"

"መስታወቱን መስበር ከፊቱ የቆመውን እውነት አይቀይረውም"

" ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና "
አቡነ ሺኖዳ

"ህይወትህ ቀላል እንዲሆንልህ አትፀልይ፡፡ ጥንካሬ እንድታገኝ ፀልይ እንጂ፡፡ በአቅም ልትሰራው የምትችለውን ነገር ለማግኘት አትፀልይ፡፡ ልትሰራው ካሰብከው ነገር ጋር የሚመጣጠን ሀይልን እንድታገኝ ፀልይ፡፡ከዚያ አስደናቂው ነገር 'የሰራህው ስራ' ሳይሆን 'አንተ' ትሆናለህ፡፡"
ፊሊፕ ብረክስ

."በዓመቱ ውስጥ ምንም ሊከናወን የማይችልበት ቀን ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡ አንደኛው ትናንት ሌላኛው ደግሞ ነገ ይባላል ፡፡ ዛሬ ለመውደድ ፣ ለማደግ እና ከሁሉም በላይ ለመኖር ትክክለኛው ቀን ዛሬ ነው።"
ዳላይ ላማ
ሰዎች እቅዳቸውን በሚገባ ለማሳካት ራሳቸውን መቆጣጠር እና መምራት ይኖርባቸዋል፡፡

ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ፍላጎትን እና እቅድን ባለማጣጣም እንዲሁም መመሪያቸውን በአግባቡ ባለመተግበራቸው የቀን ውሏቸው እና የሕይወት ስኬታቸው ወጣ ገባ ይሆናል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ራስን የመቆጣጠር እና የመምራት አቅምን ለማሳደግ የሚጠቅሙ 10 ምክሮችን አቅርበናል፡፡

1. በተግባር የሚገለፅ አመለካከት
ራስን ማየት በነጻነት የምንሰራቸውን ስራዎች ሃላፊነት እንድንወስድባቸው ያደርገናል፡፡
በመሆኑም ሊተገበር የሚችል አስተሳሰብን ማስፈን እና አስቀድሞ አቅዶ የዕለት ውሎን መምራት ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
ይህም ራስን በራስ ለማረም ይረዳል፤ ያልተፈለገ ጭንቀት እንዳያጋጥም ያደርጋል፡፡

2. ግብ ማስቀመጥ
አንድ ሰው ሲኖር የሕይወት ግብ ሊኖረው ይገባል፤ ግቦች ደግሞ ምርጫን ይወስናሉ፤ ግብን በውል ለይቶ ያስቀመጠ ሰው ያሳካዋል፡፡
የተዘበራረቀ ግብ ያለው ሰው ደግሞ ለቀውስ ይጋለጣል፤ ይህ ደግሞ ለጭንቀት እና ለሌላ ህመም ይዳርጋል፡፡
በመሆኑም በጊዜ የተገደበ፣ የተመጠነ፣ ሊለካ እና ሊሳካ የሚችል ግብን ማስቀመጥ ራስን ለመቆጣጠር እና ሕይወትንም በዚሁ መልክ ለመመራት አቅም ይፈጥራል፡፡

3. ራስን መገምገም

ራስን መገምገም ከተወሰነ ጊዜ በፊት የተከናወኑ ድርጊቶችን ወይም ስራዎችን መልሶ በማየት ምላሽን ለአዕምሮ መመገብ ነው፡፡
የተቀመጠውን የሕይወት ግብ ለማሳካት ቀድሞ የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም በቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ለማካተትም ይረዳል፡፡ይህ ዓይነቱ ተግባር ሰዎች ባህሪያቸውን ራሳቸው እንዲያርሙ ያግዛቸዋል፡፡

4. መነቃቃት
ሰዎች አንድ ዓላማ ባስቀመጡ ቁጥር ያንን ለማሳካት የራስ ተነሳሽነት እና ትጋት ያድርባቸዋል፡፡
ይህ እንዲሆን ደግሞ የተቀመጠው የሕይወት ስኬት ግብ እና የእለት ውሎ አቅጣጫ ለስራ የሚያነሳሳ እና ቁርጠኝነትን የሚጨምር ጥቅም ሊኖረው ይገባል፡፡
ሰዎች የግቡ ስኬት ተደምሮ ውጤት እንደማይኖረው ካወቁ የስራ መነቃቃታቸው ይቀዘቅዛል፤ ስለሆነም የሚቀመጠው ግብ መነቃቀትን የሚፈጥር መሆን አለበት፡፡

5. በራስ መተማመን
መነቃቃትን ወደ አዕምሮ ለማምጣት በራስ መተማመን መኖር አለበት፤ በራስ መተማመን ለዓላማ ስኬት ዓቢይ መንገድ ነው፡፡
ሰዎች በራሳቸው ካልተማመኑ የሕይወት ስኬት ግቡን አይመታም፤ ይህ ደግሞ ራስን መቆጣጠር እና መምራትን ማጎልበት አልተቻለም ማለት ነው፤ በእጃቸው ያለውን ቀሪ ስራ ለማሳካት ይከብዳቸዋል በተጨማሪም ጭንቀትን ያመጣባቸዋል፡፡
በመሆኑም በርካታ ችግሮች ሊያጋጥሙ ቢችሉም እንኳ በራስ የመተማመን መንፈስ እቅድን ማሳካት ተገቢ ነው፤ ጥቀሙም ራስን የመምራት ጥበብን እስከ ማጎልበት ይደርሳል፡፡

6. ተስፋን መሰነቅ
ተስፋ ሰዎች ልቦናዊ አቅም በመፍጠር የሕይወት ጉዟቸው የተሳካ እንዲሆን የማስቻል አቅም አላት፡፡
በሂደት የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን በመጋፈጥ ለግባቸው ስኬት ወደ ፊት እንዲራመዱም መሪውን ታስጨብጣለች፡፡
የግሪኩ ፈላስፋ ፕሌቶ “አንድ ነገር ብቻ ተስፋ አድርግ እሱንም በሚገባ አሳካው” ብሎ ነበር፡፡ስለዚህ ሰዎች ራስን በመቆጣጠር ያስቀመጡትን አንድ ዓላማ በልኩ ለመፈፀም ተስፋ የግድ ያስፈልጋቸዋል፡፡

7. ጫናዎችን ማስወገድ
አንዳንድ ጊዜ ያልተፈለጉ ፍላጎቶች ሕይወትን ለመምራት በሚደረገው ጥረት ላይ ያልተፈለገ ጫና ይፈጥራሉ፡፡
ስለዚህ እነዚህን የፍላጎት ቅጥ ማጣት ጫናዎችን በመቅረፍ የሕይወት ስኬት ጉዞን ወደፊት ማስቀጠል ይገባል፡፡

8. ለምን እና እንዴት የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ
በሕይወት ውስጥ ለምን የሚለው ጥያቄ በአጠይቆቱ ሩቅ ለማሰብ እና ስራን የሚከናወንበትን ዓላማ አውቆ ለማከናወን ይጠቅማል፡፡

በሌላ በኩል እንዴት የሚለው ጥያቄ ደግሞ ሩቅ የታሰበውን ግብ የማሳኪያ መንገዶችን ለማፈላለግ ፋይዳ አለው፡፡
ጀርመናዊው ኒቼ በአንድ ወቅት “በለምን ጥያቄ ላይ የተመሰረተ ህይወት ያለው ሰው እንዴት የሚለውን ጥያቄ በተግባር እየመለሰ ለህይወቱ ትርጉም ያለውን ስራ ይሰራል” ብሎ ነበር፡፡
👍3
😔😔😔 የሰው ዋጋው ስንት ነው?😢😢😢

ዛሬ ጠዋታ ወደስራ ሳመራ በአይኔ ያየውትን አሳዛኝ ክስተት ላካፍላችሁ፡፡ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ጠዋትና ማታ ዝናብ መመታት የተለመደ ነው፡፡ ጠዋት እንደወትሮዬ ከትራንስፖርት እንደወረድኩ ወደ መስሪያ ቤቴ የምታደርሰኝን የ5 ደቂቃ የእግር መንገድ በፍጥነት መራመድን ተያይዣለው፡፡

ትንሽ እንደተጓዝኩ ግን መገናኛ ድልድዩ ስር ብዙ ትራፊክ ፖሊሶች እና ብዙ ፖሊሶች በድንጋጤና በወከባ ቆመው ተመለከትኩ፡፡ ብዙ ትራፊኮችን በመመልከቴ እና በቦታው ብዙ የቆሙ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማየቴ ነገሩ ከህገ-ወጥ ጭነት ጋር የተያያዘ ነው ስል አሰብኩ፤ ግን በጣም በትልቁ ተሳስቼ ነበር፡፡

ወደ እነሱ እንደተጠጋውም በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው አስከሬን በአይኔ አየው፤ ለዛውም እንደ እንሰሳ ተቀጥቅጦና ተወግቶ ተገድሎ ደሙ ሙሉ መሬቱን ሸፍኖ፡፡ እርግጠኛ ባልሆንም በቦታው የነበሩ ፖሊሶችና ትራፊኮች ከውሃ መውረጃ ትቦ ውስጥ አውጥተን ካነበብነው መታወቂያው ላይ አገኘን ባሉት መረጃ ተማሪ ነው አሉ፡፡ ግን የትኛው ትቦ ውሃ መውረጃ እንደሆነ አላወኩም መሬት ላይ ከጎኑ ወድቆ የተገኘ የላፕቶፕ ቦርሳም አለ፡፡

ብቻ ይሄ ሰው ወጣትም ይሁን ሽማግሌ፤ ህፃንም ይሁን አዋቂ፤ በጨለማ ተገሎ እንደ እንሰሳ መሬት ላይ ተጥሎ ስጋውን ዝናብ ሲደበድበው አድሯል፡፡

ይህን ሰው በግፍ የገደሉት የሰይጣን ሙሽሮች ምንም የተለየ ምክንያት ይኑራቸውም አይኑራቸውም ክቡር የሆነውን የሰው ነፍስ ያጠፉት ለምድራዊ ጥቅም ፣ ቁስ ወይም ገንዘብ ሲሉ ነው፡፡

እውነት ግን የሰው ዋጋው ስንት ነው?

የሰው ነፍስ በደቂቃ ከሚጠፋ ገንዘብ ታንሳለችን?

የሰው ነፍስ ከአንድ ስማርት ፎን ታንሳለችን?

የሰው ነፍስ ወድቆ ከሚሰበር ኮምፒውተር አንሳ ነውን?

ኧረ እንደው ሲጀምር የሰው ልጅ ከምንስ ጋር በምን መለኪያ ይወዳደራል?

#ውድ ሰዎቼ ጠባቂ አንድ #አምላክ ቢሆንም እራሳችንም የተቻለንን ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለብን #ይሰማኛል፡፡ ኪሳችን ውስጥ ያለን 50 ብር ለመውሰድ ሊገለን ጩቤ የሚያወጣ ወሮ በላ ያለበት #ዘመን ላይ ደርሰናልና በግዜ ወደየቤታችን #እንግባ፡፡ ወንድማዊ ምክሬ ነው፡፡ ፈጣሪ ማስተዋል የሚችል #አእምሮን ለሁላችን #ይስጠን፤ እንደቀልድ በየሜዳው ደማቸው የሚፈሰውን እህት እና ወንድሞቻችን ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት አምላክ ያኑርልን፡፡

#ጳ_ው_ሎ_ስ 😢😢😢
"ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"

# በህይወት እስካለህ:-
:
ልትሳሳት ፣ልትወድቅ ትቸላለህ ፣
:
ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣
:
ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ፣ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣
:
በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣
:
ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።:"
:
☞በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።
:
መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።
:
አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል።
:
ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል።
:
ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
:
ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም።
:
☞ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር!
:
☞ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
:
# አንድ ነገር ልንገራችሁ!
:
~>በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል
:
~>መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል
:
~>ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል
:
~>ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል።

"ሁሌም ጥሩ ሁን ጥሩ ነገር ይገጥምሀል"።

# ስብሀት ገብረ እግዚአብሔር #
👍3
ጨዋታ.....🤡

አንዳንዴ የሰጠነዉ ለፍቅራችን ቦታ
ሆኖ ስናገኘው ለየቅል ለአንዳፍታ
ብዙ አጋነነዉ ለሰው እስኪሰለች
እርግጠኛ ሆነን አዉርተን ለሰዎች
ሁሉም እስኪገረም ጭኖ እጁን በአፉ ላይ
ለፍቅራችን ቦታ ሰጥተን ከሞት በላይ
ጥርጥር ሳይገባን ለነሱ ያለን እምነት
ሰዉ ሁሉ ቢያማልን ስንላቸው ዉሸት
ከአልማዝ ከእንቁ በላይ ስንሳሳላቸዉ
ልፋታችን እነሱ በመዳብ ቀይረው
ምንም ሳንጠረጥር ሳይገባን ቅሬታ
አደረጉት እኮ ፍቅርን ጨዋታ።

ፅጌሬዳ አስናቀዉ
እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣
ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡››

[ በፍልስፍና መደመም - ገፅ 40 ]
ተቃራኒ ኑሮ .....😊 / 😞

ሁለት ሰዎች አሉ ተቃራኒ የሆኑ
ካንዱ ደስታ ሲሆን አንዱ የበዛ ሀዘኑ
አንደኛው ሞልቶለት ፍላጎቱ ብዙ
ሁሉም ተትረፍርፎ የበዛ መዘዙ
ቄንጠኛ መኪና ቄንጠኛ አለባበስ
ዉድ ዉድ እቃዎች ሁሉንም ሲያዳርስ
መስጠት ያላወቀ መቀበልን ብቻ
ዉስጡ ሰላም ያጣ ያነፀዉ ጥላቻ 😡
ሁልጊዜ የሚኖር ለገንዘቡ ብቻ🤑
በዛዉ ልክ ደግሞ ይሄኛው ድሀ አለ
የቀን ገቢ ዉሎዉ ለምግብ ያልዋለ
ቀኑን የሚጀምር ጌታን አመስግኖ
ህይወቱን የሚኖር በስራ መንኖ
የእሱ ሀብት ድሎታዉ ፈጣሪ የቸረዉ
የጤና ሀብተኛ ሁን ብሎ የመረቀዉ
ታዲያ ያኛው ለምን ጤና የጎደለው???
ሁሉንም አግኝቶ የበዛለት ተድላዉ
ያሻውን አድርጎ ያማረውን በልቶ
ትንሽ ደበር ሲለው ራሱን አዝናንቶ💆‍♂💆
ሲያሻዉም ተኝቶ 😴
ታዲያ ለምን ከዛ ድሀ ከተባለው
ሁሉም ተሳክቶለት ጤና የጎደለው?
ቄንጠኛ አኗኗሩ ጤናን ካልመለሰ
ፍቅር ካላመጣ ህመም ካባባሰ💘
ምን ያደርግለታል 🤔
ምንስ ሀብት ኑሮ ከዚህ የበለጠ 🤷‍♀
መሆኑን አያውቅም
እሱ ካልኖረ ሁሉም የቀለጠ
ዉስጣዊ ሰላሙን ከሆነ የሚያሳጣው
ሀዘኑን አብሶ ህመም የሚያመጣው 🤢
ከሆነ ገንዘቡ
ከሱ የበለጠ ሁሉን ነገር ይጣዉ🙅

ፅጌሬዳ አስናቀዉ
አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል!!

ገበሬው በአቅራቢያው ያለ ጃምቦ ቤት በቀን አረቄ በጃንቦ ይጨልጣል።
አንድ ሌላ የሚያውቀው ሰው ይመጣና ይጠይቀዋል
" በዚ የስራ እና የምርት ሰዓት ግን እዚ መጠጥ ቤት ምን ታደርጋለህ?"
ገበሬው ጭንቅላቱን እያወዛወዘ
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ይላል።
ሰውዬው ወንበር ስቦ እየተቀመጠ ገበሬውን ይጠይቀዋል
"ወዳጄ ምን ሆነህ ነው ንገረኝ፣ሲያወሩት ይቀላል"
"እሺ ካልክ...!" ብሎ ገበሬው ይጀምራል
"እሄውልህ ዛሬ ጠዋት ተነስቼ ግብርና በብድር የሰጠንን ነጯን ላም እያለብኩ
ነበር። አንድ እቃ እንደሞላው ግራ እግሯን አንስታ የታለበውን በሙሉ ደፋችው"
"እሺ ግን ይሄ እኮ ታድያ ብዙ አያስከፋም ለዚህ ሁኔታም አይዳርግም "ይላል
ሰውየው
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ብሎ ገበሬው አሁንም ይተክዛል
...ጭማሪ አረቄም ያዛል።
"እሺ ከዛስ ምን ሆነ" ሰውየው አለሳልሶ ለማረጋጋት ይጠይቃል
ገበሬው እየጠጣ ንግግሩን ይቀጥላል
" ከዛ ያው ግራ እግሯን ከ አንዱ ቋሚ ጋር አሰርኩት"
"ከዛስ....?"
"ከዛማ ድጋሚ ተቀምጬ ማለብ ጀመርኩ....በሌላ እቃ ሞልቼ እንደጨረስኩ ቀኝ
እግሯን አንስታ ድጋሚ የሞላውትን እቃ ደፋችው"
ሰውዬው ከት ብሎ ስቆ "እንዴ ድጋሚ?" ይለዋል
ገበሬው አሁንም
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል " ይለዋል።
"ከዛስ ምን አረክ?" ሰውዬው በጉጉት ይጠይቃል።
"ያው ከዛ በጣም ተማርሬ ቀኝ እግሯንም ከሌላ ቋሚ ጋር አስሬ ማለብ
ጀመርኩ...የሚያሳዝነው ይቺ የተረገመች ላም ይሄኛውን በጥንቃቄ እንደጨረስኩ
በጭራዋ ደፋችው"
"ያሳዝናል በእውነቱ "አለ ሰውዬው ጭንቅላቱን እየነቀነቀ።
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ብሎ ጭንቅላቱን በሃዘኔታ ይነቃንቃል
አሁንም ገበሬው
"ከዛስ?" ሰውዬው የገበሬው ችግር መጨረሻው አጓጉቶታል
"ከዛማ ሌላ ገመድ ፈልጌ ስላጣው ቀበቶዬን ፈትቼ ጭራዋን አስሬ እንደጨረስኩ
ሱርዬ ወለቀ፣በዝች ቅጽበት ሚስቴም ወደውስጥ እየገባች ነበር"
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።"
👍1
የተግባር ሰው ሁን!

"ስፖርት መስራት እጀምራለሁ፣ አንድ መፅሀፍ በሳምንት አነባለው፣ በጠዋት እነሳለው፣ ራሴን አሻሽላለው" ብለህ ካሰብክ ቆየህ ፤ ግን መቼ ነው ወደ ተግባር የምትገባው? ሁልጊዜ ሰኞ ሲመጣ ወይ ወሩ ሲያልቅ፣ ወይ አመቱ ሲፈፀም ማቀድ አልሰለቸህም?

ወዳጄ ምግብ የበላ እንጂ ለመብላት ያሰበ አይጠግብም እኮ! መድሀኒቱን የዋጠ እንጂ ስለ መድሀኒቱ አብዝቶ ያወቀ አይድንም እኮ! ማወቅ ማሰብ ማቀድ አሪፍ ቢሆንም ተግባር ከሌለው ግን በዜሮ ነው ሚባዛው! ስለዚህ አንዱን ዕቅድ አሁኑኑ ጀምረው! ዳይ ወደ ተግባር!

የተግባር ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
@Yemuu
. 人 ★* 。 • ˚* ˚ 🌙
. (_ _) * RAMADAN * ★
. ┃口┃ * KAREEM *
. ┃口┃★ * ***. . *˛•
. ┃口┃★ * •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃. ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. 三_三三三三三

𝚓𝚘𝚒𝚗 & 𝚜𝚑𝚊𝚛𝚎
ወዳጆቼ ፍቅር ማለት እንዲህ ነው…እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋትና በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ነው በቃ ፍቅር እንዲህ ሲሆን ነው ትክክለኛ ስሜቱ የሚታወቀው😍
" አንድን መርከብ የሚያሰጥመው በዙርያው ያለው ውሃ ሳይሆን ወደ ውስጡ የሚገባው ውሃ ነው ። አንተም በዙርያህ በሚከቡ መጥፎ ድርጊቶች ሳይሆን ውስጥህ እንዲገቡ በፈቀድክላቸው ማንነቶች በማይረባ አመለካከት መስጠምህም ሆነ በመልካምነት ወንዝ ላይ መንሳፈፍህ ሁሉቱም ባንተ ይወሰናል ። የከበበህ ሁሉ ሳይሆን ውስጥህ እንዲገባ የፈቀድክለት ነው ጥፋትህንም ኑረትህንም የሚወስነው "
​​🌺🌺🌿#የፍቅርሽ_ትንታ🌿🌺🌺

በረቀቀ ጥበብ በረቀቀ ሚስጥር
ያለምንም ስስት ያጎረሺኝ ፍቅር

ጨጓራዬን ትቶ ልቤ ላይ በማረፍ
በፍቅር ትንታ ዘውትር ስንደፋደፍ

ይሻለኛል ብዬ ከዛሬ ከነገ
ጀርባዬን ባስመታም ይባስ እያደገ

ሊለቀኝ አልቻለም የፍቅርሽ ትንታ
ውሀም ብጠጣበት ጠዋትና ማታ።
የመጠቁ ሀሳቦች
፨፨፨

"ጎበዝ ሰው ለጥያቄዎች በሚሰጠው መልስ ይታወቃል። ብልህ ሰው ግን በሚጠይቀው ጥያቄ ይመዘናል።"


"ድርቅ የተፈጥሮ ምክንያት አለው። ርሀብ ግን ሁሌም የተዛባ ፖለቲካዊ መስመርና ፖሊሲ ውጤት ነው። "


"...ሞኝ አትሁን! ፍቅር፣ ወሲብ፣ ምናምን ቀድሞ የተዘጋጀ ቀመር የለውም። የምክንያትና የሎጂክ ጣጣም አያውቅ። ድንገት ብቅ ይላል፣ ሀሴት አዝንቦልህ መልሶ ይሰወራል። እንደገና ትናፍቀዋለህ። ይሄንን የተፈጥሮ ሕግ እንኳንስ አንተ የፍቅር አማልክት ሊለውጡት አይችሉም ።..."


"ምሥጢር በትክክል ምሥጢር የሚሆነው የአንተ እስረኛ ሲሆን ነው። ሌላ ሰው ጆሮ ከደረሰ ግን አንተ የምሥጢርህ እስረኛ ትሆናለህ!..."


"የሚኖሩለት ዓላማ አለ ማለት ከእንስሳዊ ተፈጥሮ እየወጡ...እየራቁ...አየመጠቁ መሄድ ማለት ነው ። "

ምንጭ የሱፍ አበባ
ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው
👍15