Sidama prison Commission Communication
225 subscribers
3.16K photos
38 videos
30 files
20 links
ሲዳማ ብ/ክ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
Download Telegram
ሥነ-ምግባራዊ ተቋም እንዴት ይገነባል?
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ጠንካራ እና አስተማማኝ ሥነ-ምግባራዊ ተቋም መገንባት ቀጣይነት ያለው ሥራ፣ ግልጽነት እና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ትልቅ ሂደት ነው። ተቋማዊ ብልሹ አሰራርን እና ሙስናን በመከላከል የህዝብ አመኔታን ያተረፈ ተቋም ለመገንባት ወሳኝ ምሰሶዎች አለ።

👉ግልጽ የሥነ-ምግባር መርሆዎች እና ደንቦች ፦
በተቋሙ ውስጥ ምን መደረግ እንዳለበት እና ምን መደረግ እንደሌለበት በግልጽ የሚያስረዱ፣ ለአንባቢ በቀላሉ የሚገቡ የሥነ-ምግባር ደንቦችን እና መመሪያዎችን ማዘጋጀት ተገቢ ነዉ። እነዚህ ደንቦች በወረቀት ላይ ብቻ ተጽፈው ከመቀመጥ ባለፈ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ፣ አመራር እና ለተገልጋዩ ህዝብ በግልጽ ሊታወቁና ሊደርሱ ይገባል።

👉የአመራር ቁርጠኝነትና አርአያነት፦
የላቀ ሥነ-ምግባር የሚጀምረው ከከፍተኛ አመራሩ ነው። መሪዎች ራሳቸው ለህግ እና ለሥነ-ምግባር ደንቦች ተገዢ በመሆን ለሰራተኛው ምሳሌ መሆን አለባቸው። የሥነ-ምግባር መመሪያዎች በሁሉም ሰራተኞች ላይ ከላይኛው አመራር እስከ ታችኛው ሰራተኛ ያለ አድልዎ እኩል ተፈጻሚ መሆን አለባቸው።

👉አሰራርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማገዝ፦
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማስገባት የአድልዎ እና የሙስና ቀዳዳዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይዘጋል። ቴክኖሎጂ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል፣ ፋይሎችን በግልጽ ለማስቀመጥ እና ማን ምን እንደሰራ በግልጽ ለማወቅ ስለሚረዳ ተጠያቂነትን ያሰፍናል።

👉ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ መፍጠርና ስልጠና፦
ሰራተኞች ስለ ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ ስለ ጥቅምና ፍላጎት ግጭት እና ስለ ጸረ-ሙስና ስልቶች ቀጣይነት ያለው ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ። ታማኝነትና ቅንነት የዕለት ተዕለት የሥራ ባህል እንዲሆኑ ተቋማዊ ንቅናቄዎችን መፍጠር።

👉ጠንካራ የሪፖርት ማድረጊያ እና የጥበቃ ሥርዓት፦
ሰራተኞችም ሆኑ ተገልጋዮች ያዩትን ሥነ-ምግባር የጎደለው ድርጊት ወይም ሙስና ያለ ፍርሃት የሚጠቁሙበት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሚስጥራዊ የጥቆማ ሥርዓት መዘርጋት።

መረጃ አውጪዎች ወይም ጠቋሚዎች ከበቀል ወይም ከማንኛውም ጥቃት ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ።

👉ተጠያቂነት እና የማበረታቻ ሥርዓት፦
የሥነ-ምግባር ጉድለት ሲገኝ ፈጣን፣ ግልጽ እና የማስተማሪያ እርምጃ መውሰድ። በታማኝነታቸው እና በላቀ ሥነ-ምግባራቸው የተመሰከረላቸውን ሰራተኞች በማበረታታትና እውቅና በመስጠት ለሌሎች አርአያ እንዲሆኑ ማድረግ።

በአጭሩ፡ ሥነ-ምግባራዊ ተቋም የሚገነባው ጠንካራ መመሪያዎችን በማውጣት፣ አሰራርን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ አመራሩ በተግባር አርአያ ሲሆን እና በሰራተኛው ዘንድ የውስጥ ስብዕና ለውጥ ሲመጣ ነው።(መልካም ቀን ይሁንላችው!!!)
#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር

የግንቦት ወር  (May) በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ግንዛቤ ወር በመባል ይታወቃል። ይህን አስመልክቶት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ሳምንታት በአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን የተዘጋጁ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ ነበር። እንሆ ዛሬ የመጨረሻው መልዕክት ተልኳል👇

አዕምሯችንም ይደክማል!

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን -የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት)

ብዙዎቻችን የአካላችንን ድካም በቀላሉ እንረዳዋለን ለምሳሌ እግራችን ሲደክም እንቀመጣለን፣ ትከሻችን ሲዝል ደግሞ ጋደም ብለን ለማረፍ እንሞክራለን። ነገር ግን አዕምሯችን የሰውነታችን ሁሉ መሪ ሆኖ 24 ሰዓት ያለእረፍት እንዲሠራ እናስገድደዋለን። አዕምሮ ልክ እንደ አካላችን ካልተንከባከብነውና ተገቢውን እረፍት ካልሰጠነው መድከሙ የማይቀር ነው።

በየቀኑ በኑሮና በሥራ ሩጫ ውስጥ ስንሆን አዕምሯችን " ደክሞኛል፣ እረፍት እፈልጋለሁ! " እያለ በተለያየ መንገድ ድካሙን ይገልፃል።

አንዳንዴ በእንቅልፍ ማጣት፣ አንዳንዴ የማተኮር አቅም በማጣት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለምክንያት ቶሎ በመበሳጨትና በስሜት መለዋወጥ ሊገለፅ ይችላል።

ታዲያ እነዚህን ምልክቶች እንደ ቀላል አይቶ ችላ ማለት ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል። የአዕምሮ ጤናን መጠበቅ የሚጀምረው ራስን ከማድመጥና ለራስ ጊዜ በመስጠት ነው።

ለአዕምሯችን ጊዜ መስጠትና ማሳረፍ ስንል ምን ማለታችን ነው?

- በቂ እንቅልፍ ወስደን አዕምሯችን ራሱን እንዲያድስ እድል በመስጠትና ከመተኛታችን በፊት ከስልክና ሶሻል ሚዲያ በመራቅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲያርፍ ማድረግ።

- ብቻችንን ከመብሰልሰል ከሰዎች ጋር ተገናኝቶ የውስጥን ጫና እና ጭንቀት ማውራት፤ ስሜትን ለምናምነው የቅርብ ሰው ወይም ለባለሙያ በማጋራት የአዕምሮን ሸክም በማውረድ።

- ከዕለት ተዕለት ጩኸት ራቅ ብሎ በንጹህ አየር እና በተፈጥሮ መካከል ጥቂት ደቂቃዎችን በማሳለፍ እንዲሁም ከአደንዛዥ እፆች ፣ ከጫት እንዲሁም ከአልኮል ጊዜያዊ መጠለያነት በመራቅ የአዕምሮን ጤና መጠበቅ እና መንከባከብ እንችላለን።

ምስጋና ፦
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላለፉት ሳምንታት በአዕምሮ ጤና ላይ ግንዛቤ ለመስጠት ሙያዊ ፅሁፎችን አዘጋጅተው ሲያቀርቡ ለቆዩት የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ለሆኑት ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን ከልብ የመነጨ ምስጋና ያቀርባል።

#የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር
#MentalHealthAwarenessMonth

@tikvahethiopia
የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እግርኳስ ቡድን የክልል ሴክተር መ/ቤቶች ሻምፒዮን ሆነ::

የአምናው የክልል መ/ቤቶች ሻምፒዮን የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት የክልሉን ኮንስትራክሽን ቢሮን 1:0 በሆነ ውጤን የዘንድሮውን የሴክተር መ/ቤቶች ዋንጫ ለሁለተኛ ግዜ በማንሳትና በተጨማሪም:-

የፀባይ ዋንጫን

የዉድድሩ ምርጥ አሰልጣኝ

የዉድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ

የዉድድሩ ምርጥ ተጫዋቾች በማስመረጥ የውድድሩን ዋንጫዎች ሁሉ በመውሰድ የአመቱ ምርጥ ቡድን መሆናቸውን አስመስክረዋል::


ግንቦት 30/2018 ዓ,ም
👍1