🌟ስለ ሾተላይ (Rh-isoimmunization) ማወቅ ያለብን ነጥቦች🌟
በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።
💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።
🌟 ነጥብ
💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም
🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?
👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።
👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።
ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።
👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።
👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።
👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም
☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ
🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል?
👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
☘️ ውርጃ ካጋጠማት
☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ
👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።
💥☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።
👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።
👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።
ዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት - 0911138054
Join the following telegram channel for more https://t.me/DrDawitMOBGYN
@HakimEthio

#የአራስነት_ድባቴ
#Share_it #Postparum_depression
ድባቴ በቀላሉ በምክር፣ በልዩ ልዩ _ አስደሳች ፕሮግራሞች ወይም በቀላል መድኃኒቶች የሚታከም ህመም ነው፡፡ ህክምናውን በቶሎ ካገኘሽ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጤናሽ ተመልሶ ደስተኛ እናት ትሆኛለሽ::
የአራስነት ድባቴ ህመም ከመቶ ሴቶች በአስሩ ላይ ይከሰታል፡፡ የአራስነት ድባቴ የሚከሰተው አንዲት አራስ ከተገላገለች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ ይህ ምልክትና ህመም የሚያጠቃው በአብዛኛው የመጀመሪያ ልጆቻቸውን የተገላገሉ እናቶችን ነው:: ከስነ-ልቦና ህመም ውስጥ አንዱ የሆነው የአራስነት ድባቴ ‹ማትርናለ ብሉ› ተያያዥነቱ ከሴትነትና ከአራስነት ጋር ብቻ ነው፡፡ መነሻውም ‹መልካም እናት ነኝ ወይስ ልሆን አልችልም በሚል የራስ ግጭት ነው፡፡ በአራስነት ድባቴ ተጠቅቻለሁ ብለሽ ካስብሽ ለብቻሽ አታብሰልስይው፡፡ ለቅርብሽ ሰው አውሪው ከባሰም ሐኪምና የስነ-ልቦና ሐኪም እንዲሁም የማህበረሰብ አማካሪ አነጋግሪ፡፡
የህመሞች ሁሉ የመጀመሪያ መፍትሄ በሽታውን በትክክል መለየትና እንደተጠቃሽ ማወቅ ስለሆነ፤ በአራስነት ድባቴ መጠቃት ወይም አለመጠቃትሽን በሚከተሉት ምልክቶች መረዳት ትችያለሽ፡፡
❖ ኃይለኛ ንዴትና ብስጩነት፣
❖ ከዚህ ቀደም ያስደስቱሽ በነበሩ ነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት ወይም መጥላት፣
❖ ተደጋጋሚ የሐዘን ስሜትና እምባ እምባ የሚልሽ ከሆነ፣
❖ ደክሞሽ እንኳን ለመተኛት መቸገር፣
❖ የተጋነነ የስሜት መለዋወጥ (በጣም ደስተኛ እና በጣም ሐዘንተኛ መሆን)፣
❖ ከአራስ ልጅሽ ጋር የመቆራኘት ስሜት ማጣት፣
❖ አብዝተሸ የምትጨነቂ ከሆነና የተጋነነ ስጋት ካደረብሽ፣
❖ ሐሳብሽን በአንድ ነገር ላይ ሰብስበሽ መስራት ከተቸገርሽ፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ምልክቶች ታይተውብኛል ብለሽ እራስሽን የአራስነት ድባቴ ተጠቂ አድርገሽ መውሰድ የለብሽም፡፡ ነገር ግን የድባቴ ምልክቶቹ፡-
1. ከሁለት ሳምንት በላይ ከቀጠሉ፣
2. እየባሱ ከመጡ፣
3. አራስ ልጅሽ ለመንከባከብ አዳጋች ካደረጉብሽ፣
4. የዕለት ተዕለት ተግባርሽ በአግባቡ ለማከናወን አቅም ካሳጡሽ እና
5. አእምሮሽ ልጅሽን ወይም እራስሽን ስለመጉዳት ማሰላሰል ከጀመረ ውለሽ ሳታድሪ ወደ ህክምና ተቋም ሔደሽ ባለሙያ ማማከር ይኖርብሻል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት አንዱ ውስጥሽ ካለ ሐኪም ዘንድ መቅረብ ግዴታሽ ይሆናል፡፡
ስለ ህመሙ መደንገጥ አይጠበቅብሽም፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር በእርግዝና ምክንያት በሚመጣ የኬሚካል መዛባት የሚከሰት ነውና፡፡

#Mental_Health #Awareness_Month
https://www.facebook.com/100002933256142/posts/7618202538287446/?mibextid=PYmHZq6NeoFKAokE

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የማህፀን በር ካንሰር ምንድነው?
👩⚕️👩⚕️👨⚕️
💉 ይህ የካንሰር ዓይነት ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) በተሰኘ ረቂቅ ተህዋስ አማካኝነት የሚከሰት ነው፡፡
💉 ተዋህሱ የማህፀን በር ህውሳትን በመወረር ጤናማ ያልሆነ ዕድገትና ብዜትን እያስከተለ ወደ ሌሎች አካላት ክፍሎች በመሰራጨት የሰውነትን ተለምዶአዊ ተግባር በማወክ የብዙ ሴቶችን ህይወት በመንጠቅ የታወቀ ነው፡፡
💉 ይሁን እንጂ በሽታው ስር ሳይሰድ በምርመራ ከተደረሰበት ታክሞ መዳን ይችላል፡፡
👁️የቅድመ ካንሰር ምርመራና ህክምናው
💉 የማህፀን በር ካንሰር መስፋፋት በጣም አዝጋሚ በመሆኑ ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ በሽታው ተባብሶ ለህይወት አስጊ ከመሆኑ በፊት ታክሞ መዳን ይችላል፡፡
💉 የማህፀን በር ካንሰር መኖር ያለመኖሩን ለመለየት የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋሉ፡፡
- በመሆኑም የምርመራው ውጤት የቅድመ ካንሰር ምልክት ከላይ በህክምና መዳን ይቻላል፡፡
💉 ይህ የህክምና ዓይነት ከራዮቴራፒ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የማህፀን በር ካንሰር ከመከሰቱ በፊት 90 በመቶ በላይ ይከላከላል፡፡
💉 ስለዚህ ከ30-49 ዓመት የሆናቸው ሴቶች ወቅታዊና ተከታታይ ምርመራ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
👁️ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ የሆኑ እነማን ናቸው?
💉 ማንኛውም የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽማ የምታወቅ ሴት ሁሉ ለማህፀን በር ካንሰር ዋነኛ መንስኤ ለሆነው ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ የመጋለጥ አጋጣሚ ሊኖራት ይችላል፡፡
💉 ይሁን እንጂ
o ከ20 ዓመት ዕድሜ በታች የግብረ ስጋ ግንኙነት መጀመር፤
o ከተለያየ ወንዶች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ፤
o ከተለያዩ ሴቶች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ የወንድ ጓደኛ ያላቸው ሴቶች፤
o በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነት በሽታ በመቋቋም ኃይል መቀነስ ያጋጠማቸው ሴቶች፤
o ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ የመከላከል አቅምን የሚቀንስ መድኃኒት የሚወስዱ ፤
o በአባላዘር በሽታዎች የተያዙ፤
o ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች ይበልጥ የተጋለጡ ናቸው
👁️ስር የሰደደ የማህፀን በር ካንሰር የህመም ስሜቶችና ምልክቶች
💉 የቅድመ ካንሰር ምርመራ በወቅቱ ካልተደረገ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች የህመሙ ተጠቂ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
💉 የማህፀን በር ካንሰር ሥር እስኪሰድ ድረስ ምንም ዓይነት ስሜትና ምልክት ሳይኖው 15-20 ዓመት ሊቆይ ይችላል፡፡ ከተባባሰ በኋላ ግን ከግብረስጋ ግንኙነት በኋላ ደም በብልት ይፈሳል፡፡ ይህ ክስተት የወር አበባ ባቋረጡ ሴቶች (የዕድሜ ምክንያት) ላይም ይከሰታል፡፡ ከዚህም ሌላ ያልተለደመ የማህፀን ፈሳሽ በብዛት ይፈሳል፡፡
💉 በሽታው እየተባባሰ ሲሄድም የማህፀን አካባቢ ህመም ይኖራል (ሕመም በግብረ ስጋ ግንኑነት ጊዜ ሊሰማ ይችላል)፡፡
ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱ የህመም ምልክቶች ካሉ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ ይገባል፡፡
በእውነተኝነት እና ታማኝነት ሁሌም ስለመልካም ጤናዎ እንተጋለን!
#አላትዮን ጠቅላላ ሆስፒታል
ስልክ 0993 20 5272
0917 24 2224

ከማህፀን ውጭ እርግዝና(ectopic pregnancy) ምንድነው?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የሴት ልጅ ማህፀን የተለያዪ ክፍሎች አሉት።እነዚህም
✅የማህፀን ግድግዳ(uterine cavity)
✅የማህፀን ቱቦ(fallopian tube)
✅የማህፀን ጫፍ(cervix)
✅እንቁላል አምራች(ovary) ናቸው።
ታዲያ የወንድ ዘር እና የሴት እንቁላል የሚገናኙት የማህፀን ቱቦ(fallopian tube) ውስጥ ነው።በዚህ ቦታ ላይ የመጀመሪያው ፅንስ ይፈጠራል።ይህ የተፈጠረው ሽል(Blastocyst) ወደ ማህፀን ግድግዳ ጉዞ በማድረግ የማህፀን ግድግዳ ላይ ሄዶ ይጣበቃል።ይህ የጉዞ ሂደት እስከ 5 ቀናት ይፈጃል። የፅንስ እድገትም በዚህ ይቀጥላል።
ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ይህ ሂደት በተለያየ ምክንያት ሲስተጓጎል የተፈጠረው ፅንስ እድገቱን በዛው ጠባብ በሆነችው የማህፀን ቱቦ(fallopian tube) ውስጥ ያደርጋል። ይህም ከማህፀን ውጭ እርግዝና ይባላል። ይህም ትቦው እንዲፈነዳ ሊያደርግ ይችላል።ከ95% በላይ የሚሆነው ከማህፀን ውጭ እርግዝና በዚህ ትቦ ውስጥ ይፈጠራል።
ከ1.5-2%የሚሆኑ ሴቶች ከማህፀን ውጭ እርግዝና ያጋጥማቸዋል።
አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸው?
ከ50% በላይ የሚሆኑት ከማህፀን ውጭ እርግዝና የሚያጋጥማቸው ሴቶች ምንም አይነት አጋላጭ ምክንያት የላቸውም።
ዋና ዋና አጋላጭ ምክንያቶቹ
1.ከዚህ በፊት ከማህፀን ውጭ እርግዝና አጋጥሟት ከነበረ
2.የማህፀን ኢንፌክሽን
3. 3 ወይም ከዚያ በላይ ውርጃ
4.እድሜ ከ40 በላይ
5.በማህፀን ውጥ የሚቀበር የወሊድ መከላከያ
6.ሲጋራ ማጨስ
7.ከ5 በላይ የወሲብ ጓደኛ
ምልክቶች
1.የወር አበባ መቅረት
2.የታችኛው የሆድ አካባቢ እና የወገብ ህመም
3.በብልት በኩል ደም መፍሰስ
4.በድንገት ራስን መሳት
5.የደም ማነስ ምልክቶች
የህክምና አማራጭ
1.ክትትል ማድረግ
2.ሰርጀሪ መስራት
3.በመድሀኒት እንዲከስም ማድረግ
የወር አበባ እንደቀረ አልትራሳውንድ በመታየት የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል።

"የደም ማነስ"
አማርኛ | Afaan Oromo
ሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስ ሜጋሎብላስትስ የሚባሉት ባልተለመደ ሁኔታ ትላልቅ ቀይ የደም ሴሎች በመኖራቸው የሚታወቅ የደም ማነስ አይነት ነው።
የሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስ ምልክቶች ድካም፣ ድክመት፣ ማዞር፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የገረጣ ቆዳ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መቻቻልን ያጠቃልላል። ሌሎች የተለመዱ ምልክቶች ምላስ መቁሰል፣ ክብደት መቀነስ እና በቆዳ እና በአይን ላይ ቢጫማ ቀለምን ሊያካትቱ ይችላሉ።
በጣም የተለመደው የሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስ መንስኤ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎችን ለማምረት አስፈላጊ የሆኑት የቫይታሚን B12 ወይም ፎሊክ አሲድ እጥረት ነው።
ይህ ጉድለት በተመጣጣኝ የአመጋገብ ስርዓት, በተመጣጣኝ የአመጋገብ ችግሮች, በአንዳንድ መድሃኒቶች ወይም አንዳንድ የሕክምና ሁኔታዎች ምክንያት ሊከሰት ይችላል. ሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስን ለመከላከል በቫይታሚን B12 እና ፎሊክ አሲድ የበለጸጉ ምግቦችን መጠቀም አስፈላጊ ነው. እነዚህም የወተት ተዋጽኦዎች፣ ሥጋ፣ የዶሮ እርባታ፣ ዓሳ፣ የተመሸጉ እህሎች፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች እና ጥራጥሬዎች ያካትታሉ።
ሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስ በደም ስርጭቱ ውስጥ ሜጋሎብላስትስ የሚባሉት ባልተለመደ ሁኔታ ትላልቅ ቀይ የደም ሴሎች በመኖራቸው የሚታወቅ የደም ማነስ አይነት ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ለቀይ የደም ሴሎች ምርት አስፈላጊ የሆነው የቫይታሚን B12 ወይም ፎሊክ አሲድ እጥረት ነው።
የሜጋሎብላስቲክ የደም ማነስ ሕክምና ዋናውን መንስኤ ማስወገድን ያካትታል. ይህ በተለምዶ የሚከተሉትን ያጠቃልላል
1. ቫይታሚን B12 ወይም ፎሊክ አሲድ ማሟያ፡- እንደ ጉድለቱ መጠን በጡንቻ ውስጥ የቫይታሚን ቢ12 ወይም የአፍ ፎሊክ አሲድ ተጨማሪዎች መርፌዎች የጎደለውን የቫይታሚን መጠን ለመሙ
2. የአመጋገብ ማስተካከያ፡- በቫይታሚን ቢ12 እና ፎሊክ አሲድ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ድክመቶችን ለመቆጣጠር ይረዳል። ምንጮቹ ስጋ፣ ዓሳ፣ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ እንቁላል እና ቅጠላማ አትክልቶች ይገኙበታል።
3. ማላብሶርሽን ጉዳዮችን መፍታት፡- የቫይታሚን B12 ማላብሶርሽን መንስኤ በሆነበት ጊዜ፣ የዕድሜ ልክ ወርሃዊ የቫይታሚን B12 መርፌ ሊያስፈልግ ይችላል።
Hir’inni dhiigaa megaloblastic gosa hir’ina dhiigaa seelii dhiiga diimaa guddaa haala hin baratamneen megaloblasts jedhamu jiraachuu isaatiin kan beekamudha.
Mallattoon hir’ina dhiigaa megaloblastic kan jedhaman dadhabbiin, dadhabbii, garaan namaa mar’achuu, hafuura kutuu, gogaan isaa diimaa ta’uu fi sochii qaamaa dandamachuu hir’achuudha. Mallattoowwan biroo kanneen mul’atan arrabni nama dhukkubsuu, ulfaatina qaamaa hir’isuu fi gogaa fi ija irratti keelloo ta’uu danda’u.
Sababni hir’ina dhiigaa megaloblastic baay’inaan mul’atu hanqina vitaamin B12 ykn folic acid kan seelii dhiiga diimaa fayya qabeessa ta’e uumuuf barbaachisaa ta’e dha. Hanqinni kun sababa nyaata gaarii hin fudhanne, rakkoo malabsorption, qoricha tokko tokko ykn haala fayyaa tokko tokko irraa kan ka’e uumamuu danda’a. Hir’ina dhiigaa megaloblastic (megaloblastic anemia) ittisuuf nyaata vitaamin B12 fi folic acid baay’ee qabu nyaachuun barbaachisaadha. Isaan keessaa oomishaalee aannani, foon, qamadii, qurxummii, midhaan jajjaboo, kuduraalee baala magariisaa fi loomii kan dabalatudha.
Hir’inni dhiigaa megaloblastic gosa hir’ina dhiigaa seelii dhiiga diimaa gurguddaan haala hin baratamneen, megaloblasts jedhaman, dhiiga keessatti argamuun kan beekamudha. Yeroo baayyee hanqina vitaamin B12 ykn fooliik asiidii kanneen seelii dhiiga diimaa oomishaniif barbaachisoo ta'an irraa kan dhufudha.
Wal’aansi hir’ina dhiigaa megaloblastic sababa bu’uuraa furuu of keessaa qaba. Kunis akkaataa idileetti:
1. Vitamin B12 ykn folic acid supplementation: Hanqina isaa irratti hundaa’uun, hamma vitamin B12 ykn folic acid dabalata afaaniin fudhatamu maashaa keessaa lilmoodhaan lilmoodhaan fudhachuun hamma vitaaminii hir’ate guutuuf ajajama.
2. Sirreeffama nyaataa: Nyaata vitaamin B12 fi foolikii asiidiitiin badhaadhe fudhachuun hir’ina jiru to’achuuf gargaaruu danda’a. Maddoonni isaanii foon, qurxummii, qamadii, oomishaalee aannani, hanqaaquu fi kuduraalee magariisa baala qaban ni argamu.
3. Dhimmoota garaachaan xuuxamuu dhabuu vitaaminichaa furuu: Haalota xuuxamuu dhabuun vitaamin B12 sababa ta’e keessatti, ji’a ji’aan vitaamin B12 umurii guutuu lilmoodhaan argachuun barbaachisaa ta’uu danda’a.
Reference:
1 Harrison' s principle of internal medicine 20th & 21st edition
Dr Wondu Belayneh Dejen

መውለድ አለመቻል ብዙ ጥንዶችን የሚያጋጥም ችግር ነው። መካንነት መንስኤዎቹን መረዳት፤ እርዳታ ለመፈለግ እና መፍትሄዎችን ለማግኘት ወሳኝ የመጀመሪያ እርምጃ ነው።
የመካንነት ምክንያቶች እዚህ ናቸው:-
ለወንዶች፡-
፩. ዝቅተኛ የወንድ የዘር መጠን ወይም ጥራት፡- የወንድ የዘር ፍሬ አመራረት ወይም ጥራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ማርገዝን ሊያደናቅፉ ይችላሉ። በሆርሞን መጠን ላይ የሚከሰቱ ለውጦች የወንድ የዘር ፍሬን ይጎዳሉ።
፪-በወንድ ዘርፍሬ/testis ዙሪያ ያሉ እንደ varicocele ያሉ ሁኔታዎች፣ የወንዱ ዘር ጤና ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
፫. የሆርሞኖች መዛባት፡- የሆርሞን መጠን ለውጦች የወንድ የዘር ፍሬን ምርት እና ጥራትን ሊጎዱ ይችላሉ።
፬- የአኗኗር ዘይቤዎች፡- ማጨስ፣ አልኮል ማብዛት እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት የማርገዝ እድል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።
ለሴቶች:**
፩. የኦቭዩሽን ችግር፡ እንደ ፖሊሲስቲክ ኦቭሪ ሲንድረም (PCOS) ያሉ ሁኔታዎች የእንቁላልን በመደበኛነት መለቀቅን ሊያውኩ ይችላሉ።
፪. የፎልፒያን ቲዩብ (የማህጸን ቱቦ) ጉዳት፡- የማህፀን ቱቦዎች መዘጋት ወይም መጎዳት የወንድ የዘር ፍሬ ወደ እንቁላል እንዳይደርስ ይከላከላል።
፫. የማህፀን ሁኔታዎች፡- እንደ የማህፀን ዕጢ ያሉ ጉዳዮች ወይም በማህፀን ውስጥ ያሉ ያልተለመዱ ችግሮች እርግዝና በማህፀን መትከል እና በተፈጠረ እርግዝና ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
፬. እድሜ፡- ሴቶች እድሜያቸው እየጨመረ በሄደ ቁጥር በተለይም ከ35-40 በኋላ የመጸነስ እድል በተፈጥሮ ይቀንሳል።
በተጨማሪም የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች፣ የሕክምና ሁኔታዎች (እንደ የስኳር በሽታ ወይም የታይሮይድ መታወክ) እና የአካባቢ ሁኔታዎች (ለመርዛማ ኬሚካሎች መጋለጥ ያሉ) ሁሉም በመራባት ውስጥ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ።
እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ለዚህ ችግሮች ተጠቂ ከሆነ፣ ብቻዎን እንዳልሆኑ ይወቁ። የማህጸን እና ፅንስ ባለሙያዎችን ማማከር ወይም ድጋፍ መፈለግ ለችግሩ ጠቃሚ መፍትሄ ያመጣል።
የምርመራ እና የሕክምና አማራጮች በቅርቡ ይለጠፋሉ።
ዶ/ር ወንዱ በላይነህ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት -
0913764264
Hawassa
Join the following telegram channel for More https://t.me/wondubelayne

መንታ ሲረገዝ መታወቅ ያለባቸው ነገሮች፡-
፩:-መንታ እርግዝናው ምን አይነት አርግዝና እንደሆነ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። አንደኛ የመንታ ዓይነት ከአንድ እንቁላልና ከአንድ የወንድ ዘር ፍሬ የተፈጠረ ሲሆን፤ ከተፈጠረ በኋላ ለሁለት ተከፍሎ መንታ ይሆናል። ከአንድ እንቁላልና ከአንድ የወንድ ዘር ፍሬ የሚፈጠረው የመንታ ዓይነት አንድ አይነት ፆታ፣ የደም አይነት እና መልካቸውም የሚመሳሰል ይሆናሉ።
ሁለተኛ የመንታ አይነት ደግሞ ከሁለት እንቁላል እና ከሁለት የወንድ ዘር ፍሬ ተዋህዶ የተለያዩ ልጆች የሚፈጠሩበት ነው። እንደዚህ አይነት መንታዎች የተለያዩ የደም ዓይነት፣ የተለያየ ጾታ፣ የተለያየ መልክ ሊኖራቸው ይችላል።
፪:-መንታ እርግዝና ሲከሰት ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር፡- አደገኛ የእርግዝና ምልክቶች የሚባሉት ነው። መንታ ያረገዘች እናት ለነዚህ ለአደገኛ የእርግዝና ምልክቶች ተጋላጭ ናት። አደገኛ የእርግዝና ምልክት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡- ሃይለኛ ራስ ምታት፣ የእይታ በሽታ ብዥታ፣ ጊዜው ሳይደርስ ምጥ መምጣ፣ ከምጥ በፊት እንሽርት ውሃ መፍሰስ፣ ደም መፍሰስ እና የልጅን እንቅስቃሴ መቀነስ ናቸው። እነዚህ ምልክቶች ከተከሰቱ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ እና ሳወቅ ያስፈልጋል።
፫:-አንድ መንታ ያረገዘች እናት ማድረግ ያለባት ነገር ፡- ከአቅም በላይ የሆነ ስራ መስራት የለባትም፤ ሁለተኛ ለረጅም ጊዜ መቆም የለባትም።
፬:- አንድነት መንታ ያረገዘችው እንዴት መውለድ አለባት የሚለውን እንመልከት፡- አቀማመጡ ጥሩ ከሆነ እና ከዚህ በፊት በኦኘሬሽን ያልወለደች ከሆነች በክምና ተቋም አመጣ መውለድ ትችላለች። ነገር ግን በፊት በኦኘሬሽን የወለደች ከሆነች ወይም ደግሞ የመጀመሪያው ልጅ በመቀመጫው የመጣ ከሆነ በኦኘሬሽን መውለድ ይኖርባታል።
፭:- ሌላው አመጋገብ ነው። በእርግዝና ወቅት የሚጠበቅ የኪሎ መጨመር ይኖራል። ይህም ኪሎ መጨመር አንድ ካረገዙት በላይ 2 ወይም መንታ ያረገዙ እናቶች የተሻለ ኪሎ መጨመር ይጠበቃል።
፮:-በእርግዝና ክትትል ወቅት ከሚሰጡት ነገሮች ውስጥ አንዱ አይረን የሚባለው መድሀኒት ነው። አይረን ቀይ የደም ሴል መጠንን ለመገንባት ይረዳል። ደም ማነስ እንዳይኖር ያደርጋል። አይረን በተጨማሪ የልጅ አእምሮ እድገት ላይ አዎንታዊ ተጽኖ ይኖረዋል። ስለዚህም መንታ ያረገዘች እናት ተጨማሪ አይረን ያስፈልጋታል። ለዚህም በአካባቢዎ ባሉ የጤና ተቋማት በመሄድ ግንዛቤዎች በመውሰድ እና ህክምናና እንዲሁም ጥቆማ በማድረግ በማናገር የተሻለ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

Forwarded from Wondu Belayneh
ሴፕሲስ/Sepsis ምንድ ነው?
🌟መስከረም የሴፕሲስ ግንዛቤ ወር ነው! 🌟
ሴፕሲስ ሰውነት ለበሽታ ከፍተኛ ምላሽ ሲሰጥ የሚከሰት ከባድ የጤና መታወክ ችግር ነው። ከተለያዩ ኢንፌክሽኖች ማለትም ከሳንባ ምች፣ ከሽንት ቱቦ ኢንፌክሽኖች አልፎ አልፎም ከቀላል ኢንሼክሽን ሊነሳ ይችላል። ሁሉም ሰው ለአደጋ ተጋጭ ነው፤ ነገር ግን አንዳንድ ምክንያቶች የተጋላጭነትን ይጨምራሉ። ለምሳሌ የእድሜ መግፋት፣ እንደ ስኳር በሽታ ወይም ካንሰር ያሉ ሥር የሰደዱ ህመሞች እና የበሽታ መከላከል ስርአቶች መዳከም ናቸው።
ምልክቶቹን ቀደም ብለው ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። እንደ ሀይለኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ፈጣን የልብ ምት፣ ግራ መጋባት/confusion፣ የመተንፈስ ችግር እና ከፍተኛ ህመም ወይም ምቾት ማጣት ያሉ ምልክቶች ይኖሩታል። እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው እነዚህን ምልክቶች ከታዩ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ይኖርበታል።
ምርመራው ብዙውን ጊዜ የደም ምርመራዎችን እና የኢንፌክሽን ምንጭን ለመለየት ሌሎች ሂደቶችን ያካትታል። ሕክምናው አንቲባዮቲክስ እና በሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ድጋፍ ሰጪ እንክብካቤዎችን ያጠቃልላል።
ግንዛቤን ማሳደግ ህይወትን ለማዳን ይረዳል! እራሳችንን እና ማህበረሰቦቻችንን ስለ ሴፕሲስ እና ስለ ጉዳቶቹ እናስተምር። አንድ ላይ ሆነን ለውጥ ማምጣት እንችላለን! 💙 #ሴፕሲስግንዛቤ #ህይወትንያድናል #ጤናትምህርት
ዶ/ር ወንድ በላይነህ የጽንስና የማህፀን ሐኪም
@Wondubelayneh
+251913764264
@Drobs_gyne

#የማህፀን በር ካንሰር አራቱ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ምንድናቸው?
የማኅጸን ካንሰር ምልክቶች
፩-ከወሲብ በኋላ የሴት ብልት ደም መፍሰስ።
፪-ከማረጥ በኋላ የሴት ብልት ደም መፍሰስ።
፫-ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ውሃ የበዛ እና ጠንካራ ሽታ ያለው ወይም ደም ያለበት።
፬-በጾታዊ ግንኙነት ወቅት የማህፀን ህመም ወይም ህመም።
የማኅጸን ካንሰር ምልክቶች
፩-ከወሲብ በኋላ የሴት ብልት ደም መፍሰስ።
፪-ከማረጥ በኋላ የሴት ብልት ደም መፍሰስ።
፫-ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ውሃ የበዛ እና ጠንካራ ሽታ ያለው ወይም ደም ያለበት።
፬-በጾታዊ ግንኙነት ወቅት የማህፀን ህመም ወይም ህመም።
የማህፀን በር ካንሰር ምንድነው?
የማኅጸን በር ካንሰር በማህፀን በር/ጫፍ ላይ የሚከሰት የካንሰር አይነት ሲሆን ይህም የማህፀን የታችኛው ክፍል ነው። ይህ የካንሰር አይነት በተለይ ለብዙ አመታት በዝግታ ያድጋል። ብዙውን ጊዜ የማኅጸን አንገት ዲስፕላሲያ/dysplasia በሚታወቁት የማኅጸን cell ለውጦች ውስጥ ይከሰታል።
እነዚህ ላይ የተጠቀሱት ለውጦች ወደ ካንሰር ሳይቀየሩ፣ በሚደረጉ የቅድመ ካንሰር ምርመራዎች ሊገኙ እና ወደ ካንሰር ሳይቀየሩ በህክምና ማስወገድ ይቻላል።
ስለዚህ ቅድመ ካንሰር ምርመራን ልምድ ማድረግ ይኖርብናል።
ሁለት አይነት የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራዎች አሉ።
#አንደኛው ከሃያ አንድ ዓመቷ ጀምሮ በሦስት ዓመት ልዩነት ከማህፀን በር ናሙና እየተወሰደ ምርመራ የሚደረገው ነው። ሰላሳ አመት ከሞላት በኋላ ደግሞ በየአምስት ዓመቱ ከHPV ምርመራ ጋር ይካሄዳል።
#ሁለተኛው ዓይነት ከ35 ዓመቷ ጀምሮ በየ አምስት ዓመቱ የሚደረግ ምርመራ ነው። የዚህኛው አይነት ምርመራ ምርመራው እየተደረገ ችግሩ ከተገኘ ወዲያውኑ ህክምና የሚሰጥበት ነው።
በነዚህ በሁለቱ ቅድመ ካንሰር ምርመራዎች ችግሩ ወደ ካንሰር ሳይቀየር መለየትና ማከም ይቻላል።
ነገር ግን ብዙዎች ይህንን ቅድመ ካንሰር ምርመራ
ስለማያደርጉ ሁኔታው ወደ ካንሰር ከተቀየረ በኋላ ነው ወደ ህክምና የሚመጡት።
ካንሰሩ ከተከሰተ በኋላም፣ ደረጃው ሳይጨምር፣ ህክምና ማግኘት የመዳን አጋጣሚውን ይጨመራልና፤ ቀጥለው ያሉትን የማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች ከተከሰቱ ወደ ህክምና ተቋም መሄዱ መከራል።
#የማህፀን በር ካንሰር አራቱ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ምንድናቸው?
የማኅጸን ካንሰር ምልክቶች
፩-ከወሲብ በኋላ የሴት ብልት ደም መፍሰስ።
፪-ከማረጥ በኋላ የሴት ብልት ደም መፍሰስ።
፫-ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ውሃ የበዛ እና ጠንካራ ሽታ ያለው ወይም ደም ያለበት።
፬-በጾታዊ ግንኙነት ወቅት የማህፀን ህመም ወይም ህመም።
Share it!!!
ለሰዎች ይደርስ ዘንድ አጋሩት!!!
Dr. Wondu Belayneh, Obstetrician and Gynecologist.
+251913764264
https://t.me/drObs_gyne

ስለ ማህፀን ጫፍ ካንሰር
1. በ አለም ላይ በየ 2 ደቂቃ አንድ እናት በ ማህፀን ጫፍ ካንሰር ምክንያት ህየወቷ ያልፋል።
2. በአለም ላይ 4 ኛው ገዳይ ካንሰር ሲሆን በ አገራችን ደግሞ ሁለተኛው ሴቶችን ገዳይ ካንሰር ነው።
3. ከ 90 % በላይ የሚሆነው የማህፀን ካንሰር የሚከሰተው HPV በሚባል ፣ በ ግብረስጋ ግንኙነት ግዜ ተላላፊ በሆነ ቫይረስ አማካኝነት ነው።
4. HPV ቫይረስን አንድ ልጃገረድ የግብረ ስጋ ከመጀመሯ በፊት ( ከ 9 - 14 ዓመት ዕድሜ ያሉ ) ፣ ፀረ HPV ክትባት በመከተብ ከ ቫይረሱ የወደፊት ተጠቂነት ነፃ መሆን ትችላለች።
5. የማህፀን ጫፍ ካንሰር ከመፈጠሩ ከ አመታት በፊት ቅድመ ምርመራ በማድረግ ለህመሙ ተጋላጭ መሆናቸውን ሴቶች ማወቅ ይችላሉ ፣ በተጨማሪም ቅድመ ህክምና በማድረግ ሙሉ ለሙሉ ከ ካንሰሩ ነፃ መሆን ይቻላል።
6. በ ኢትዮጵያ ውስጥ በ ዓመት በመኪና አደጋ ከሚሞተው የሰው ቁጥር ይልቅ በ ማህፀን ጫፍ ካንሰር አማካኝነት የሚሞቱት የሴቶች ቁጥር ይበልጣል።
እንደ ፈረንጆቹ በ 2020 ዓ.ም ብቻ ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 4100 ሰዎች በ መኪና አደጋ ሲሞቱ ፣ 5300 የሚሆኑ እናቶች ደግሞ በ ማህፀን ካንሰር ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።
7. የማህፀን በር ካንሰር ሙሉ በሙሉ መከላከልና ማስወገድ የሚቻል ህመም ነው። ይህም ፀረ HPV ካንሰር በመከተብና ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ ይቻላል።
8. እንደ ፈረንጆቹ ከ2018 ጀምሮ እስከ ባለፈው ጥር ወር ድረስ በተደረገ የፀረ HPV ክትባት ዘመቻ 13 ሚሊዬን ታዳጊ እንስቶች በአገራችን ለመከተብ ተችሏል።
NB:- ፋና ሬዲዮ የቀጥታ ስርጭት ከነበረኝ ቆይታ የተቀነጨበ።
It was a nice session @Fanastudio
Dr. Reta Tizazu
#Read #Share