Hasen Injamo
14.1K subscribers
2K photos
50 videos
30 files
234 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
የወለድ ነፃ ባንክ ማለት
ኪስህ ኪሴ
ኪሴ ኪሴ
በባንክ ዙሪያ የምናደርገው ትግል መንግሥት በአንክሮ እየተከታተለው ነው:: ሕዝቡ እየተታለለ እንደሆነ ገብቶታል:: ባልራቁ ጊዜያት የሚታይ ለውጥ እንጠብቃለን::

የወለድ-ነፃ መስኮት እንደ ኩዌስት ኔት ባይታገድ እንኳ መንግሥት ባንኮቹ የሚያስቀሩትን ወለድ ትርፍ አካፍሉኝ ብሎ ሊጠይቅ ይችላል::
#EthiopiaCheck Health Update

የሰሞኑ ጉንፋን- የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው፣ በተጨማሪም እነዚህ ምልክቶች ይታዩበታል:
• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ህመም
• የጀርባ ህመም
• የጡንቻ ህመም
• ምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ኃይለኛ ራስ ምታት
• ፍዝዝ ማለት

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?
ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው። ለምሳሌ ኮሮና ቫይረስ፣ ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ?

• የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
• ሁሌም አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ
• የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
• ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
• ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
• መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ

ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?
 ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ፣ በመቀጠል የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
 ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም
 ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
 ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
 የሕፃናትን ክፍል በደንብ ማፅዳት እና ማናፈስ
 ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
 ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል ::

ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?
 ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
 ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
 ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
 በቂ እረፍት ማድረግ
 የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ
 እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ፣ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም)
ተውሂድንም አስተምራለሁ ብለን ... ሐቅን ካወቅን በሗላ ደግሞ ሰው ምን ይለኛል ብለን ከንፈር ከንፈራቸውን ካየን ይጋጫሉ:: ሐቅ ላይ ቁሙ ተባልን እንጂ ሰውን አቃኑ አልተባልንም:: ቀልቦች በአላህ ጣቶች መካከል ናቸው::
ባለፈው ነሃሴ የወጣውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) መመሪያ ከቀነ ገደቡ በፊት ለማጠናቀቅ ባንኮች ደንበኞቻቸውን እየጠሩ ነው፡፡

ሙሉ መረጃ የሌለው ደንበኛ ከየካቲት በኋላ ሂሳቡ ወደ ኢብባ ይዞራል ተብሏል
.
ባለፈው ነሃሴ 3ኛ ሳምንት ብሄራዊ ባንክ ደንበኛን ማወቅ የሚል እና ህገወጥ የገንዘብ እንቅስቃሴን እና አንቀሳቃሾችን ባንኮች መቆጣጠር የሚችሉበትን መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
.
በመመሪያው መሰረት ባንኮች ቀደም ሲል ሂሳብ ያላቸውን ሆነ የኣዳዲስ ደንበኞችን የተሟላ መረጃ እንዲይዙ የሚያስገድድ ነው፡፡ ይህንን እንዲያጠናቅቁ ኢብባ 6 ወራት ቀነ ገደብ ያስቀመጠ መሆኑ ይታወሳል፡፡
.
ከዚህም ጋር ተያይዞ ባንኮች እንደ መታወቂያ እና ፎቶ ያሉ መረጃዎችን እየያዙ ደንበኞች ሂሳብ በከፈቱበት ቅርንጫፍ እንዲቀርቡ በሞባይል ስልክ አጭር የጽሁፍ መልእክት እና በሚዲያ ማስታወቂያ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
.
በተሰጠው የጊዜ ገደብ የደንበኞች መረጃ የማይሟላ ከሆነ ባንኮች የደንበኞቻቸውን ሂሳብ ለተቆጣጣሪው አካል የማስተላለፍ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን በወቅቱ ካላደረጉ ግን ቅጣት እንደሚከተላቸው መመሪያው ይገልፃል፡፡ በሌላ በኩል ደንበኞች በወቅቱ መረጃቸው የተሟላ እንዲሆን ካላደረጉ ሂሳባቸው ለመንግስት የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ካፒታል
ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ስቴሽን አስመረቀ።
=================================
አዲስ አበባ፣20/04/2014(ኢሚ) በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዲሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ይህ ለምርቃ የበቃው ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደ ከፍታ የሚያመራት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የዚህ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረግ በአሁኑ ወቅት በሃገራችን እየተስተዋለ የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ አንድ እርምጃ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ይህንን ፋብሪካ ለመደገፍ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የፋብሪካው ሊቀመንበር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ካደጉ ሃገራት በርካታ ጫናዎች እየደረሱባት መሆኑ ሃገራችን ወደ ብልጽግና ማማ እየተጓዘች ስለመሆኑ ትልቅ ማሳያ እንደሆነና ይህንን ከፍታዋን በቴክኖሎጂ ማጀብ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን እስከ ዛሬ የጦርነት ሰበር ዜናዎች ስንሰማ ብንቆይም ከዚህ በኋላ ግን በቴክኖሎጂ ረገድ በርካታ ሰበር ዜናዎችን እንሰማለን ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ቻርጅ ስቴሽኖቹ በ15 ደቂቃ ሙሉ ቻርጅ ማድረግ እንደሚችሉና ተሽከርካሪዎቹም በአንድ ጊዜ ቻርጅ እስከ 300 ኪሎሜትር ድረስ መጓዝ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴና ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።
ታህሳስ 20፣2014

መንግስት በነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ሊያነሳው ነው፡፡

ከ6 ወር የዝግጅት ጊዜ በኋላ መንግስት በነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ከተመረጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችለው የዋጋ ማስተካከያ የአሰራር ሥርዓትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አፅድቋል፡፡

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በኢኮኖሚው እና በህብረተሰቡ ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር በመንግስት እየተወሰነ እና ቁጥጥር እየተደረገበት ሲሰራ መቆየቱን ምክር ቤት አስታውሷል፡፡

ሆኖም የሀገሪቱን ወቅታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ፤የህብረተሰቡን የኑሮ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሀገር ውስጥ ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የአለም አቀፉን ዋጋ በሚያንፀባርቅ መልኩ እየታየና እየተከለሰ ወደ ሸማቹ እንዲተላለፍ ባለመደረጉ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ እዳ በዋጋ ማረጋጊያ ፈንዱ ላይ እየተከማቸ ይገኛል ተብሏል፡፡

እየሰፋ የመጣውን በፖሊሲ ያልተደገፈ የነዳጅ ድጎማ ከተመረጡ ተሽከርካሪዎች በሂደት ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችል የዋጋ ማስተካከያ ጥናት በማድረግ የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን ለመተግበር የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ተዘጋጅቶ ቀርቧል ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

የውሳኔ ሀሳቡን በዛሬው እለት ያፀደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከስድስት ወር የዝግጅት ምዕራፍ በኋላ ተፈፃሚ እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል፡፡
ለጠቅላላ ዕውቀት ሴቭ አድርጉት:: ሙሉ መረጃውን እያየን እንለጥፋለን::
በኦንላይን የጉምሩክ አገልግሎት እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባትም ሆነ ከአገር ለማስወጣት የሚፈልግ ግለሰብ ግብዓት ሊሆኑት የሚችሉ መረጃዎችን የይለፍ ቃል እና ፓስወርድ ሳያስፈልግው ማግኘት ይችላል።

ማንኛውም ሰው የይለፍ ቃል ሳያስፈልግው ከኮሚሽኑ Trade Portal የሚያገኛቸው መረጃዎች

ሊከፈል የሚገባ የቀረጥና ታክስ መጠን ለማወቅ

ተጠቃሚው https://customs.erca.gov.et/trade/ የሚለውን በሚጠቀምበት ዌብ ብሮውዘር ላይ በማስገባት በጉምሩክ ሲስተም (TPM) የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን TAX SUMULATOR የሚለውን በመጠቀም እና የሚጠየቁ አስፈላጊ መረጃዎችን ብቻ በማስገባት Calculate የሚለውን ቁልፍ በመጫን ሊከፈል የሚገባውን የቀረጥና ታክስ መጠን ማወቅ ይችላል፤

የዕቃዎችን የታሪፍ ኮድ መግለጫ እና የታሪፍ ምጣኔ ለማወቅ

ተጠቃሚው https://customs.erca.gov.et/trade/ የሚለውን ዌብ ብሮውዘር ላይ በማስገባት በጉምሩክ ሲስተም (TPM) የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን SEARCH TARRIF የሚለውን በመጠቀም የታሪፍ ኮድ (HS code)፣ መግለጫ (Tarrif Description) እና የታሪፍ ምጣኔ (Tariff Rate) ማግኘት ይቻላል፤

የዕቃው ትራንዚት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማወቅ

ተጠቃሚው https://customs.erca.gov.et/trade/ የሚለውን ዌብ ብሮውዘር ላይ በማስገባት በጉምሩክ ሲስተም (TPM) የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን T1 SEARCH የሚለውን በመጠቀም የመንገድ ወረቀት ሪጅስትሬሽን ቁጥር (T1 registration number) ወይም የኮንቴይነር ቁጥር በማስገባት ትራንዚቱ (T1) ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መከታተል ይቻላል፤

ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ወይም ወደ ውጭ ለመላክ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ዝርዝር ለማግኘት

ተጠቃሚው በጉምሩክ ሲስተም (TPM) የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን TRADERS INTERACTIVE GUIDE የሚለውን በመጠቀም እና አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት ዕቃዎችን ለማስገባት (Import) ወይም ወደ ውጭ ለመላክ (Export) የሚያስፈልጉትን አስፈላጊ የሆኑ አባሪ ሰነዶችን ዝርዝር ማግኘት ይቻላል፤

በጉምሩክ ዲክላሪስዮን ላይ የሚገኙ ኮዶችን ዝርዝር መግለጫ ለማግኘት፤

ተጠቃሚው በጉምሩክ ሲስተም (TPM) የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን Traders Assistance on Codification የሚለውን በመጠቀም በጉምሩክ ዲክላራሲዮን ላይ የሚገኙ ኮዶችን ዝርዝር መግለጫ ማግኘት ይቻላል፤

የሀገራት የምንዛሬ መጠን

ተጠቃሚው በጉምሩክ ሲስተም (TPM) የመነሻ ገጽ (Home Page) ላይ ያለውን EXCHANGE RATE የሚለውን በመጠቀም የተለያዩ ሀገራት የወቅቱን የምንዛሬ መጠን ማግኘት ይችላል፤

በደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት
በደንበኞች ትምህርት ቡድን ለግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎት የተዘጋጀ
በጣም ገርሞ የሚገርመው:-
ነቢያችን ﷺ ሲወደሱ ቢድዓ ሽርክ እያሉ የሚንጫጩ አንጃዎች ነቢያችን ﷺ ሲሰደቡ ግን ለማወደስ ይሰባሰባሉ:: "ፊዳከ, ነቢይይዬዬዬዬዬ, እርርርሪሪሪይ" ይላሉ:: ሰልፍ ይጠራሉ:: ግጥም, ነሽ-እዳ, ድራማ በያይነቱ ያቀርባሉ:: ቆይ ቆይ አብረን ለማወደስ የግድ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ መሰደብ አለባቸው እንዴ?
ገንዘብ ሲጠርባቸው "እባካችሁ ነቢዩ ሙሐመድን ﷺ ስደቡልን" ብለው ስፖንሰር የሚያደርጉ ያስመስልባቸዋል::
ልዩነታቸውን ግር ለሚላችሁ
- ቢሰደቡም ባይሰደቡም ነቢያችን ﷺ የሚያወድስ ሱፊያ ነው::
- ሲሰደቡ ብቻ ጠብቆ የሚያወድስ ኢኽዋንይ ነው::
- ቢሰደቡም ባይሰደቡም ዝም የሚል ወሀቢይ ነው::
የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ሥርዓት ይፋ ሆነ

ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ) የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት ማስተዳደሪያ ሥርዓትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ሥርዓቱ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አዲስ ፍቃድ ማውጣት፣ ዓመታዊ ፍቃድ ማደስ፣ አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ማስመዝገብ፣ የጉዞ መርሃ ግብርን ማሳወቅ፣ የድንበር ተሻጋሪ መታወቂያዎችን መስጠት እና የተሽከርካሪዎችን የጉዞ ርቀትና ጭነት ማሳወቅ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በመርሃ ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሹመት ግዛው (ዶ/ር) እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የገቢና ወጪ ጭነቶችን በማጓጓዝ ረገድ የተሽከርካሪ ድርሻ 90 ከመቶ በላይ የያዘ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ተጨማሪ በጀቱ ለሀገር ደህንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግስት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ በጀቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ፣ መንግስት በሚሰበስበው ገቢ አሁን ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አስቸጋሪ በመሆኑ እንዲሁም የተጨማሪ ወጪ ፍላጎትን በበጀት ሽግሽግ ማስተናገድ አዳጋች በመሆኑ ነው፡፡

የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንደ ጸደቀ በቀጥታ ስራ ላይ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ሸሪዐ Vs ጦሪቃ
===✿❀====
ኢልም Vs ማዕሪፋ
====✿❀=====
*
ዲኑን (እስልምናን) በክብ ቅርፅ (Circle) 💿 ብንመስለው... ሸሪዐ የክቡ ዙሪያ (The circumference) ማለት ነው... ማዕከሉ (The center) 💚 💕አሽረፈል ኸልቅﷺ ናቸው.... ጠሪቃዎች ደግሞ ከውጭኛው የክቡ ዙሪያ ወደ መሀከሉ የሚወስዱ መስመሮች (Radius) ናቸው... በመሀከሉ (through the center) የማያልፉ መስመሮችን እንዘንጋቸውና እንቀጥል...
*
ያሉበት መስመር በመሀከሉ (through the center)🎯 እስካለፈ ድረስ... ያሉበት ቅርበት ቢለያይም... በመስመሩ ላይ ያሉ ሀሉም ነጥቦች በመስመሩ (ራዲየስ) አማካይነት ... ከመሀከሉ ጋር የተገናኙ ናቸው... መሀከሉ ሁሉንም ነጥብ ይቆጣጠራል... የዲን ማዕቀፍ ድንበር አለው... ሐላሉም ግልፅ ተደርጎ ተቀምጧል ሐራሙም ግልፅ ተደርጎ ተቀምጧል ... ከክቡ ዙሪያ ውጭ ያለው ክልክል ነው... በክቡ ውስጥ ባለው ግን ሁሉም ካለበት አንፃር ልክ ነው ... በዚህ መጠን በማዕቀፉ ውስጥ የተለያዩ አተያዮችን (Perspectives) እኩል ልክ ሆነው ይገኛሉ....
*
ኢልም የዙሪያውን ክብ ሲወክል ማዕሪፋ ደግሞ መስመሩን (ራዲየሶቹን) ተከትለው ያሉ ነጥቦችን ይወክላል ... ይበልጥ ወደ መሀከሉ የቀረበ ... ማዕሪፋውም በዛው መጠን የረቀቀ እና የመጠቀ ይሆናል... የጦሪቃ መንገድ ውስጡ ሸሪዐ ነው ማለት ይኸው ነው... ክቡን ደግሞ ወደ ድቡልቡል ክብ (Sphere) ከፍ ካደረግከው እና ጥልቀት ከጨመርክለት ንፅፅሩ በኢልም እና በሲረል አስራር መሀከል ይሆናል...
(Fuad Yasin)
ህብረተሰቡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ
**********************

ህብረተሰቡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማውን
• በቀጥታ ስልክ 0111300340 ወይም 9988
• በፋክስ ቁጥር 0111233007
• በኢ-ሜል dialoguecommission@gmail.com
በinfo@hopr.gov.et ወይም
• በአካል በምክር ቤቱ መረጃ ስክሪን መስጠት የሚችል መሆኑን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 1 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የዕጩ ኮሚሽን አባላትን ከህዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማህበራት እንደሚቀበል ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሰረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበያ ጽ/ቤት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መሥፈርቶችም፡-
1/ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ፤
2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን በእኩል ዓይን የሚያይ፤
3/ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፤
4/ ለአገራዊ መግባባት ጉልህ አስተዋፅዖ ሊያበረክት የሚችል፤
5/ መልካም ሥነ-ምግባርና ስብዕና ያለው፤
6/ በሕዝብ ዘንድ ዓመኔታ ያለው፤
7/ በከባድ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት፤
8/ የኮሚሽኑን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ብቃት ያለው፤
9/ ሙሉ ጊዜውን ለኮሚሽኑ ስራ ለማዋል ፍቃደኛ የሆነ የሚሉት መሆናቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ጥቆማ የሚሰጥበት ቅጽ በምክር ቤቱ ድረገጽ www.hopr.gov.et ላይ የሚጫን መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡