አዲስ አበባ ጋዜቦ አደባባይ ጋር ያለ ሕንጻ ያለምንም ሽፋን እየተሠራ ነው:: ዛሬ ጠዋት የብረት ቁርጥራጭ ለጥቂት ነው የሳቱኝ:: የብረት ቁርጥራጮች ከፊትለፊቴ ሲወድቁ ሌላ እንዳይከተል ነዳጅ እንዴት እንደረገጥኩት:: 2002 አካባቢ ይመስለኛል ሰንጋ ተራ ጋር ስልክ ላወራ በቆምኩበት ጠጠሮች ወርደው የፊት የግንባር መስተዋት ሰንጥቀውብኛል:: ከዚያ ማንም የሚጠየቅ የለም:: ምስክር የለ, ካሜራ የለ:: በቃ እንኳንም አላህ አተረፈኝ ብዬ ትቼው ሄድኩ:: ከዚያ በሗላ ግን በሚገነባ ሕንጻ ስር ልቆም ቀርቶ ለማለፍም ይሸክከኛል:: እና ዛሬ ሳልፍ ገጠመኝ::
ተመሳሳይ ነገሮች ሌላም ቦታ ሊኖሩ ስለሚችሉ አደጋ ከማድረሳቸው በፊት ቢታረሙ::
ተመሳሳይ ነገሮች ሌላም ቦታ ሊኖሩ ስለሚችሉ አደጋ ከማድረሳቸው በፊት ቢታረሙ::
👍55
በጣም ብዙ ግብር ከመጣባችሁ ያለው ብቸኛ መፍትሔ ግብሩን የሚያስረሳ ተጨማሪ ገቢ ማ-መንጨት ነው:: ከተሰበርክ የሚጠግንህ መንግሥትም ዘመድም ማግኘት ከbad ነው:: የበለጠ መሾር ነው ያለብህ:: ወንድ ልጅ ፈቃድ ዘግቶ ቦ^ዘኔነትን በራሱ ላይ አያውጅም:: ያለአቅምህ አምስት መቶ ሺህ ብር ካሉህ ይህንን ብር ተራ የሚያደርግ ትጋት ውስጥ መግባት ነው:: ከፍ ሲልም ከፍ ይሉብሃል:: ያው አንተም ሁሌ ከፍ እያልክ ሂድ:: መፍትሔው ይኸው ነው:: ያኔ እራስህ ሕግ አውጪ ባትሆን እንኳ ተርጓሚ ትሆናለህ::
❤33
ንግድ በተለይ ኢምፖርት ላይ ሁሉን Cost 💲 በትክክል ትሠራዋለህ:: ትርፍና ኪሳራህን ቀድመህ ታውቃለህ:: የጉምሩክ እና የገቢዎች ሲቀር:: ይህኛውን ፓርት በጣም በበሉት ሰዎች ነው የምናሰለጥነው:: ቢሆንም ሁሌ ዱዓና ጸሎት ይፈልጋል:: 😃😃
ከሰልጣኞቻችን መካከል ሁለቱን ማለትም የታክስ እና የኢምፖርት ስልጠና የወሰደች እህት ነበረች:: ከዚህ ቀደም ዘውውውው ብላ ገብታ ሲስተሙ በካልቾ ብሏት ባፍንጫዬ ብላው ወደ ስልጠና መጣች:: ምቱ የቱ ጋር እንደሆነ ገባትና ወደ ሜዳው ልትመለስ እንደሆነ አበሰረችን:: እላይ ጉምሩክ ያልኳችሁ ጋር የዕቃ Description አንደኛው የዋጋ ማስሊያ ነው:: አሉሚኒየም እና እንጨት የተደባለቀበት ምርት ቢሆን በየቱ እንደምትይዘው ብቻ ማወቅ ሳይሆን በምን አገባብ ቢመጣ ተወዳዳሪ መሆን እንዳለብህ ማወቅ አለብህ:: ጥሬ ዕቃ ለመጫን አምራች ስትሆንና ኢምፖርተር ስትሆን የ Customs Procedures Code (CPC) ካቴጎሪ ይለይብሃል:: ሰፕላየርህ በጉምሩክ ዳታቤዝ ውስጥ ፍላግድ 🚩ከሆነ ማለትም የሚልካቸው ኢንቮይሶችና አጫጫኖች ችግር ካለበት አንተንም ይነጅስሃል:: ጉምሩክ የትራንዚተር rating ጭምር ያያል:: ትራንዚተርህ በተለያዩ ማምታታቶች ፍላግድ 🚩ከሆነም ያንተንም ታሪክ ያበላሽብሃል:: ኢምፖርተሮቻችን ባለ ሰማያዊ መም (🟦Blue line) መሆን ባይችሉ አረንጓዴ መም (🟩Green line) እንዲሆኑ ማስቻል ነው:: ባለሰማያዊ መም ከሆንክ የኢምፖርተር ዲፕሎማቲክ ደረጃ ነው የሚኖርህ::
ስልጠናው በተተዋወቀ በሰዓታት ውስጥ ደህና ሄዷል:: ዝርዝሩ ከስር::
👇🏼👇🏼👇🏼

❤13
Hasen Injamo
ንግድ በተለይ ኢምፖርት ላይ ሁሉን Cost 💲 በትክክል ትሠራዋለህ:: ትርፍና ኪሳራህን ቀድመህ ታውቃለህ:: የጉምሩክ እና የገቢዎች ሲቀር:: ይህኛውን ፓርት በጣም በበሉት ሰዎች ነው የምናሰለጥነው:: ቢሆንም ሁሌ ዱዓና ጸሎት ይፈልጋል:: 😃😃 ከሰልጣኞቻችን መካከል ሁለቱን ማለትም የታክስ እና የኢምፖርት ስልጠና የወሰደች እህት ነበረች:: ከዚህ ቀደም ዘውውውው ብላ ገብታ ሲስተሙ በካልቾ ብሏት ባፍንጫዬ…
''IMPORT from A to Z''
ለ 3 ቀናት ኅዳር 8 -10 ጠዋት
ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
1. በድርጅቱ ድረ-ገጽ
www.hab.et/register
ወይም
2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
———
Withhold የምታደርጉ ድርጅቶች ቀንሳችሁ ክፈሉና የዊዝሆልድ ደረሰኙን ይዛችሁልን ምጡ::

www.hab.et
Register – HAB Management and Technologies
❤6
የኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎርማት በግል መንቀሳቀስ ነው:: በጋራ እሠራለሁ ብለህ ከተነሳህ ትርፉን ብቻ ሳይሆን ዋና ብርህን ከእነጓደኝነትህ ጭምር ርሳ:: በጋራ ጀምረህ ከምትቋሰል በብሩ እምብርት እስኪገለበጥ ብትበላበት ይሻላል:: ቢያንስ ጮማ ገደ^ለው ይባላል:: ከወንድምህ ጋር ስትሠራ እንኳ ጥንቃቄ ይፈልጋል:: ምክንያቱም የናት ያባት ወንድምህ ... እናቷ ከሩቅ ምስራቅ አባቷ ከሩቅ ምዕራብ እህል ውኃ አገናኝቷቸው የወለዷት ቡኒ ሚስት ሊያገባ ይችላል:: እህትህም የሆነ ፋስ የመሰለ ጠረንገሎ ወስዶ አጫውቷት በአባትህ ክምር ካልተጫወትን ቢሉስ! በጋራ ሲሠሩ የሚያዋጡ የተወሰኑ ሥራዎች አሉ:: ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል::
__
በጀማዓ ሠርተህ ትርፍ ሲገኝም በጀማዓ ነው የምትካፈለው:: ኪሳራ ሲመጣ በጀማዓ ከሠራህ አትጎዳም የሚል ፈሪ አይጠፋም:: አንዳንድ ድርጅት ለያውም ብሔራዊ ባንክ የሚቆጣጠረው ሆኖ በ30 ሺህ አባላት ተቋቁሞ መቶ ሚሊዮን አትርፎ ይጨፍራል:: አንዳንዱ ኢንቨስተር ግን ለብቻው ሠርቶ ለልጁ ሰርግ ጥሎሽ የአንድ ቢሊዮን ብር ቼክ ብጥስ አድርጎ እንደ ቀልድ ይሠጣል::

❤43
ከሰሞኑ ጋዜቦ ጋር የብረት ቁርጥራጭ ለጥቂት ስቶኝ ነበር ብዬ የፖሰትኩት ሕንጻ የደሕንነት መጠበቂያ ሽፋን ለብሷል:: እናመሰግናለን:: ንብረታችሁ ይባረክ::
👍56
ሁለት ዓይነት የኢምፖርት cost 💲💲 ስሌት አለ:: አንደኛው የኢምፖርተሩ ሲሆን ይህም በደቂቃዎች ውስጥ ትርፍና ኪሳራ ለማስላት የሚያስችል Lazy-man calculation 🧮 ነው:: ስልጠናም ላይ እዚህኛው ላይ ነው የምናተኩረው:: ይህ በእጅ, በእርሳስ, በሞባይል, አለፍ ሲልም በ Excel ሊሰላ የሚችል ነው:: በምንም አስላው ሲስተሙ ያው ነው:: ሁለተኛው ከጉምሩክ ጀምሮ እስከ ገቢዎች ኦዲት, ከአካውንታንት እስከ ባንክ ሪፖርቶች የሚመለከቱት እና ሰነዱ እስከ 10 ዓመት አርካይቭ መገኘት ያለበት ነው:: ይህ ለነጋዴው ትእግስት አይሆንም:: ቢሆንም ግን ሁለቱም ሳይጋጩ መናበብ አለባቸው:: በዌብ ፖርታል ሠርተነዋል:: ግን ለነጋዴው አይመችም:: ስለዚህ ሁለቱንም ያጠቃለለ Excel ነበር የምንሰጠው:: አሁን በጣም አዘምኘዋለሁ:: ስለዚህ ከፊታችን የኢምፖርት ስልጠና ቀን ጀምሮ ይለቀቃል:: ቀድማችሁ የሰለጠናችሁም በተቻለ መጠን ለመላክ እሞክራለሁ:: አብሽሩ ለሰልጣኝ ክፍያ የለውም:: ብችል ደግሞ ለቀድሞ ሰልጣኞች በዙም ባብራራላችሁና ደስ ባለኝ:: ያው ልትጭኑ ስትመጡ የከበዳችሁ ፓርት ካለ እናየዋለን::
(ፎቶ:- የኢምፖርት ዋጋ ማስሊያ ዝርዝር ገጽ መግቢያ)
(ፎቶ:- የኢምፖርት ዋጋ ማስሊያ ዝርዝር ገጽ መግቢያ)
❤8
Hasen Injamo
ሁለት ዓይነት የኢምፖርት cost 💲💲 ስሌት አለ:: አንደኛው የኢምፖርተሩ ሲሆን ይህም በደቂቃዎች ውስጥ ትርፍና ኪሳራ ለማስላት የሚያስችል Lazy-man calculation 🧮 ነው:: ስልጠናም ላይ እዚህኛው ላይ ነው የምናተኩረው:: ይህ በእጅ, በእርሳስ, በሞባይል, አለፍ ሲልም በ Excel ሊሰላ የሚችል ነው:: በምንም አስላው ሲስተሙ ያው ነው:: ሁለተኛው ከጉምሩክ ጀምሮ እስከ ገቢዎች ኦዲት, ከአካውንታንት…
👆🏾👆🏾
እየሞላ ስለሆነ ግቡ
''IMPORT from A to Z''
ለ 3 ቀናት ኅዳር 8 -10 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register
ወይም 2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
እየሞላ ስለሆነ ግቡ
''IMPORT from A to Z''
ለ 3 ቀናት ኅዳር 8 -10 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register
ወይም 2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
www.hab.et
Register – HAB Management and Technologies
❤3
ቲክቶክ ግን ሲጨንቅ ወላሂ:: ስክሮል እያደረግህ ሳትፈልግ መጦዝ ነው:: ፌስቡክ እኮ አይንቀዠቀዥም:: ዓይንን አይወሰውስም:: በቀልምና በምስል ተንቀልቅሎ ልብህን አያስገድድብህም:: ቲክቶክ የግድ የሆነ መልእክት ያላችሁ ሰዎች እንደ ካካ ጣል አድርጋችሁና ውኃ ደፍታችሁ ማለቴ logout ተጭናችሁ መጥፋት ነው:: ኮሜንትና ኢንቦክስ ዘግቸዋለሁ:: ስክሮል ስታደርግ ውለህ ምን እንደተማርክ የት እንደዋልክ ይጠፋብሃል::
😢61
የምትሸጡትን እቃ
ቀድማችሁ ለዩ
=======
ኢምፖርት ቢዝነስ ቀላል እንዳይመስላችሁ:: ከፍተኛ ውድድር እና ከፍተኛ መጭ^በርበር ያለበት ሰፈር ነው:: በየትኛውም stages ላይ ገንዘብ ከመክፈላችሁ በፊት የሰዎቹን ማንነት አጣሩ:: ለማንም ሰው ይህንን ያህል ብር አለኝ ምን ልሥራ ባትሉ ይመከራል:: አትመካከሩ እያልኩ አይደለም:: ብር ጋር ሲደርስ ጠንቀቅ ማለት ነው:: ገራሚ ትርፍ ካሳዩዋችሁ ችግር አለ:: በዚህ ብር ምን ልጫን? ተብዬ በተደጋጋሚ እጠየቃለሁ:: እንዲህ ለሚለኝ ሰው "ሲጀመር ይህ ያህል ብር እንዴት እዚህ ጋር ደረሰ? ምን ሠርተህ ነው ያመጣኸው?" ነው ልለው የምችለው:: ምክንያቱም ሥራን የሚያውቅ ሰው ምን ልጫን አይልም:: ቢልም ዋነኛ ሥራ መጫን ሳይሆን መሸጥ መቻል ነው:: የማትሸጠውን ዕቃ እንዴት ልትጭነው ነው? ንግድ ፈቃድ ከማውጣት ጀምሮ መዘጋጀት ይፈልጋል:: ዛሬ የጫንከው እቃ ሰነድ እስከ 10 ዓመት ማስቀመጥ አለብህ:: ይህንን ለመሸሽ በሌላ ሰው ማለትም በኪራይ ንግድ ፈቃድ መጫን የራሱ ሪስክ አለው:: ሁሌ መጠያየቅ ሁሌ መረጃ ማነፍነፍ የግድ ይላል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈርተህ ከቆምክማ አበቃልህ:: ገብተህ መታገል ነው:: የባሕሩን ጥልቀት በአንድ እግርህ ለካ::

❤35
ኢምፖርተር የሚሆነው እቃውን መሸጥ የሚችል ሰው ብቻ ነው:: <<ብቻ>> የሚለው ቃል ስጠቀም እርግጠኛ ሆኜ ነው:: ከመርካቶ ሳሪስ ወስደህ ለመሸጥ ትልቁ ልፋት ከመርካቶ ማምጣቱ ሳይሆን ላልታወቁ ለወደፊት ዓመታት ሳሪስ ላይ ከደንብ, ከደንበኛና ከተወዳዳሪ ጋር ታግለህ አትርፈህ ሽጠህ ቅርንጫፍ ለመክፈት መቻል ማለት ነው:: ኢምፖርተር ከመሆንህ በፊት የግድ ኮንሲዩመሮችህን ማለትም እቃህን የሚገዙህ ተጠቃሚዎችህን ማወቅ አለብህ:: ዘው ብለህ ገብተህ እቃ ካመጣህ "አሕያ ያረጀበት ሰው" ትሆናለህ:: አሕያህን አታ^ርደው, አትጭነው, አትጥለው ነገር ይሆንብሃል:: ላስፈራራችሁ ሳይሆን ትልቁ ሥራ ያለው ቻይና ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው:: መሸጥ ከቻልክ ሌላው ቀላል ባይባልም ከባድ አይደለም:: ካልኩለሱ እዚሁ እኛው ሀገር ነው:: እዚያ እኮ የእቃ ውቅያኖስ ነው ያለው:: ከውቅያኖሶች ወይም ወንዞች ጨልፈህ መምጣቱን አያሳስብህ:: እኛ አለን:: ካንተ ግን ሁለት ነገር እንፈልጋለን:: መሸጥ መቻል እና መነሻ ካፒታል:: ከካፒታልህ ጋር ንክኪ አይኖረንም:: በስንት እንደምትሸጠው አናውቅም:: ያንተ ምስጢር እና ሀጃ ነው::
(ምሥጢርህን መጠበቅ ዋነኛ ካፒታላችን መሆኑንም ማስታወስ ያስፈልጋል)
(ምሥጢርህን መጠበቅ ዋነኛ ካፒታላችን መሆኑንም ማስታወስ ያስፈልጋል)
👏16
ዛሬ ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ? በሚል ርዕስ Live ይኖረናል:: ቀጣይ ሲስተሙ በዚህ እየከፈለን ስለሆነ ጎራችንን ለመለየት ይረዳናል:: ሲስተሙ እየቆለፈና እያጠበበ ነው::
🔥19