Hasab Today
132 subscribers
521 photos
16 videos
38 files
538 links
View entertainment news and videos for the latest movie, music, News and celebrity headlines on ሀሳብ !

https://youtube.com/@hasab_today?si=Idvx3JBlntxQIcPw

👉 https://linktr.ee/Hasab_Studio?subscribe

Contact :
@Desfil_1
@abuneharon
Download Telegram
ወጣቱ ጄክ ፖል ማይክ ታይሰንን ረታ !


🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️

የአለማችን የምንጊዜም ታላቁ ቦክሰኛ ማይክል ታይሰን ከ 19ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ገነነበት የቦክስ ፍልሚያ ተመልሶ በ 31ዓመታት ከሚያንሰው ጄክ ፖል ጋር ተፋልሟል።

በመላው አለም በርካቶች በተመለከቱት ፍልሚያ የ 27ዓመቱ ጄክ ፖል በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ተጠባቂውን የሁለቱ ቦክሰኞች ፍልሚያ
4.9 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥታ ስርጭት መመልከት ችለዋል።

ካደረጋቸው 5️⃣6️⃣ ፕሮፌሽናል የቦክስ ግጥሚያዎች በ 5️⃣0️⃣ ድል የተቀዳጀው ማይክ ታይሰን ዛሬ
#ሰባተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ወጣቱ ጄክ ፖል በበኩሉ የዛሬውን ጨምሮ ካደረጋቸው 1️⃣1️⃣ ፕሮፌሽናል ግጥሚያዎች በ 1️⃣0️⃣ ድል መቀዳጀት ችሏል።

ማይክ ታይሰን ከፍልምያው በኋላ “ ፖል ጠንካራ ተፋላሚ እንደሆነ አውቅ ነበር በደንብ ተዘጋጅቷል ለማንም ማሳየት ያለብኝ ነገር የለም ባደረኩት ነገር ደስተኛ ነኝ።“ብሏል።

ጄክ ፖል በበኩሉ “ ከማይክ ታይሰን ጋር መፋለም ክብር ነው ፤ እንደጠበቅኩት በጣም ከባድ ፍልሚያ ነበር የቻልኩትን ሁሉ አድርጌያለሁ።"በማለት ተናግሯል።

አሸናፊው ስንት ያገኛል ?

ግጥሚያውን ያሸነፈው ጄክ ፖል የ 40 ሚልዮን ዶላር አሸናፊ ሲሆን ተሸናፊው ማይክ ታይሰን በበኩሉ 20 ሚልዮን ዶላር እንደሚያገኝ ተገልጿል።
የጀርመኑ ቻንስለር ሾልዝ ከሁለት ዓመት በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ ከፑቱን ጋር ተነጋገሩ
የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ዛሬ በስልክ መነጋገራቸዉን የጀርመኑ ARD የተባለዉ የዜና አገልግሎት ዘገበ።


🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️

ለፑቲን ስልክ የደወሉላቸዉ የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ናቸዉ። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች የስልክ ዉይይት ለአንድ ሰዓት የዘለቀ እንደነበርም ተመልክቷል። የጀርመኑ ቻንስለር ኦላቭ ሾልዝ፤ ከፑቲን ጋር በስልክ ሲነጋገሩ የዛሬዉ ከሁለት ዓመት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ ታህሳስ 2 ቀን 2022 ኦላቭ ሾልዝ እና ፑቲን ለመጨረሻ ጊዜ በስልክ ተወያይተዉ እንደነበር ዜና ምንጩ አስታዉሷል።
የጀርመኑ ቻንስለር ሾልዝ ባለፈው የበጋ ወራት ዉስጥ በስዊዘርላንድ እንደተደረገዉ የዩክሬይን የሰላም የመሪዎች ጉባኤ አይነት ሩሲያ ልትሳተፍበት የምትችል ሁለተኛ የዩክሬን የሰላም ጉባኤ ለማካሄድ እየሞከሩ መሆኑን ዜና ምንጩ ዘግቧል። ይሁን እና ጉባኤዉ መቼ እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ቀነ-ቀጠሮ የለም። ስዊዘርላንድ ላይ በተካሄደዉ የዩክሬይን የሰላም ስምምነት ላይ ሩስያ እንድትሳተፍ ምዕራባዉያን ሃገራት ጥረት ቢያደርጉም የሞስኮ መንግሥት የዉይይት መስመሮችን ሁሉ መዝጋቱን ዜና ምንጩ አስታዉሷል።
የሆቴል ሴት ሰራተኞችን ካላስፈላጊ ትንኮሳ ለመከላከል የወጣ የአለባበስ ደንብ !

🗞️ 🗞️🗞️ 🗞️🗞️

ይህ ደንብ ምን ያህል ሴቶችን ካላስፈላጊ ጥቃት ይከላከላል ትላላችሁ?
አስተያየታችሁን ጻፉልን!

የሆቴል ባለሙያዎች የደረት ክፍላቸውን ወይም ከአንገታቸው በታች ያለውን የሰውነት ክፍል ያልሸፈነ ሸሚዝ ቢለብሱ የሚቀጡበት ደንብ ማውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው ከጥቂት ቀናት በፊት እንዳለው ”የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱ እና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ" በደንቡ መሠረት ያስቀጣል።
” የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት“ ለመወሰን የወጣ እንደሆነ የተገለጸው ደንብ “ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶች ለመከላከል” ያቀደ መሆኑ ተገልጿል። ደንቡ “በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ” ጭምር ያቀደ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ “የሆቴል አገልግሎትን ዓለም አቀፍ መስፈርት የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ“ ከዓላማዎቹ መካከል እንደሚገኝበት ተጠቅሷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት ደንቡን የማስፈጸም ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ይህ ደንብ ምን ያህል ሴቶችን ካላስፈላጊ ጥቃት ይከላከላል ትላላችሁ? አስተያየታችሁን ጻፉልን!
👍1
🔵 "የሁለት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ቤተሰብ እንዴት እናስተዳድር?" - የደቡብ ወሎ ዞን መምህራን

🟢
" የሚመለከተው ኮማንድ ፓስቱን ስለሆነ በወረዳ በኩል እንዲፈቱ አነጋግረናል " - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የሚገኙ መምህራን የሁለት ወራት የደመወዝ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው የከፋ ችግር ላይ በመሆናቸው አማረዋል።

ክፍያው ያልተፈጸመላቸው በክልሉ ባለው የሰላም መደፍረስ ሳቢያ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ባለመገኘታቸው ' ሳታስተምሩ ደመወዝ አይከፈላችሁም ' በሚል መሆኑን አስረድተዋል።

" የሁለት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ቤተሰብ እንዴት እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ከዚሁ ትንሽ ደመወዝ ብሶ ባለመከፈሉ ችግር ላይ በመውደቃቸው የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጧቸው በአጽንኦት ጠይቀዋል።

የቀረበው ቅሬታ እንዲቀረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት የዞኑ መምህራን ማኀበር፣ " የሚመለከተው ኮማንድ ፓስቱን ስለሆነ በወረዳ በኩል እንዲፈቱ አነጋግረናል " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

" መምሪያ ኃላፊው ጋ ተነጋግረናል። በዚያ በኩል እየገመገሙ መስራት የሚችሉና መምህራን ያልገቡባቸው ትምህርት ቤቶቸ ከሆነ የግድ የማይከፈል መሆኑን፤ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ ግን እንዲከፈል እየተደረገ እንደሆነ ነው " ብሏል።

በትምህርት ቤት ቢገኙም ተማሪ ባለመገኘቱ ብቻ ስላላስተማሩ ደመወዝ እየተከፈላቸው  ቅሬታ ለሚያቀርቡት መምህራን ምላሽ እንዲሰጥ ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ትምህርት መምሪያን አነጋግሩ " ብሏል።

የቀረበውን ቅሬታ በመግለጽ ምላሽ እንዲሰጡ ለሳምንት የጠበቅናቸው የዞኑ ትምህርት መምሪያና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በተጨማሪ፣ መምህራን እያቀረቡት ያለውን የደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ሰምቷል? ስንል ጥያቄ ያቀረብንለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ) ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማኅበሩ ፦

" በአካባቢው ካለው ችግር አንጻር ፎርማል ሆኖ የመጣልን ነገር የለም። ግን በወግዲ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም እስከ ለሁለት ወራት እየተከፈለ አይደለም ከባንክም ከሌላም  ኬዝ ጋር በተያያዘ።

እንደተባለው መምህራን እየተጎዱ ነው። በይበልጥ ጉዳዩ የክልሉን መምህራን ማኅበር ይመለከታል። ፎርማል ሆኖ ወደኛ ቢመጣ ወደ ፌደራል መንግስትም ልንወስደው እንችላለን፡፡

ፎርዛትማተር መንግስት 'የክልሎቹ ማንዴት ነው' ነው የሚለን፡፡ ከዚህ ቀደም የትግራይ ክልል መምህራን መጥተው ያን ያህል ሲንገላቱ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ነበር ለሻይ ሲላቸው የነበረው።

አማራ ክልል አይነት የጦርነት ሁነት ላይ ስለሆነ ፎርማሊ በሕግ አግባብ የሚጠየቅ ድርጅት የለም፡፡ በዚህ ነው የተቸገርነው " ነው ያለው።

በጸጥታው ችግር ትምህርት ቤቶች ስለተዘጉ ሳያስተምሩ ደመወዝ እንደማይፈጸምላቸው እንደተነገራቸው ነው መምህራኑ የሚገልጹት፤ ይህ አግባብ ነው ? በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ የማኀበሩ ፣ " ልክ አይደለም " የሚል መልስ ሰጥቷል።

" ተማሪ እስከመጣላቸው ድረስ አላስተምርም ያሉ መምህራን ካሉ ነው እንጂ መምህራኑ ትምህርት ቤት ቁጭ ብለው ተማሪ እየጠበቁ ነገር ግን በጸጥታ ችግር ተማሪ ካልመጣላቸው ማንን ነው የሚያስተምሩት ? " በማለት ጉዳዩ ልክ ያልሆነበትን ምክንያት በመጠይቅ አስረድቷል፡፡

" ጸጥታውን ማስከበር ያለበት እኮ የመንግስት አካል ነው " ያለው ማኀበሩ፣ " የራሱን ሥራ እንዴት መምህራን ላይ ይጥላል? ትክክል የማይሆነው ይሄ ነው፡፡ መምህራን ትምህርት ቤት ላይ ከሌሉ ትክክል ነው ደመወዛቸው መክፈል አይገባም የት እንዳሉ አይታወቅምና " ብሏል።

" ነገር ግን ማኀበረሰቡ ልጆችን ትምህርት ቤት ልጆቹን አልክም ብሎ ከሆነ መምህራን ደግሞ ትምህርት ቤታቸው ላይ ሆነው እንዴት ነው የማይከፈሉት። ይሄ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን መቱት አይነት ነገር ነውና ትክክል አይደለም " ሲል አክሏል።
የአሜሪካ ብሄራዊ እዳ ከ36 ትሪሊየን ዶላር ተሻገረ !

🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️

ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው የአሜሪካን እዳ በ8 ትሪሊየን ዶላር መጨመራቸው ይታወሳል

የአሜሪካን እዳ የሚመዘግበው ድረገጽን ጠቅሶ አርቲ እንዳስነበበው የአሜሪካ እዳ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ2 ትሪሊየን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።

የልዕለ ሀያሏ ሀገር እዳ ከጥር እስከ ህዳር 2024 በ6 በመቶ መጨመሩና በአራት ወራት ውስጥ በ1 ትሪሊየን ማደጉንም ዘገባው ጠቅሷል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት የሀገሪቱ ብሄራዊ እዳ ከ35 ትሪሊየን ዶላር ማለፉን ያስታወቀው በሀምሌ ወር እንደነበር ይታወሳል።

የአሜሪካ ብሄራዊ እዳ በ2027 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርቷ (ጂዲፒ) 106 በመቶ እንደሚደርስ የኮንግረንሱ የበጀት ጽህፈት ቤት በነሃሴ ወር ያወጣው ሪፖርት ያሳያል።

አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በበኩሉ “አሁን ባለው ፖሊሲ አጠቃላይ የመንግስት እዳው በ2032 ከጂዲፒው 140 በመቶ በላይ ይሆናል” ብሏል።
የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።

የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ።

የታጠቁ የሶሪያ አማጺያን የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።

በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ አማፂያን ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል።

ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።

ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገደዋል።

አማጽያኑ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአላሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆናችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።

አላሳድ ከደማስኮ ወጥተው ሄደዋል ተብሏል።

የፕሬዜዳንቱን ከደማስቆ መልቀቅ ሁለት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

አሁን ላይ አሳድ የት እንደገቡ የሚታወቅ ነገር የለም።

የታጠቁት ተቃዋሚዎች ባወጡት መግለጫ ፤ " ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል " ብለዋል።

" ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም ገልጸዋል።

በሽር አላሳድ ሀገሪቱን ለቀው መጥፋታቸውንም አሳውቀዋል።

አማጽያን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያውን ተቆጣጥረዋል።

አንዳንድ ቪድዮዎች እንዲሁም ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በደማስቆ ጎዳናዎች ሶርያውያን ወጥተው ' ነጻነት ! ነጻነት ! ' እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

እነ ሩስያ ፣ ኢራን ፣ አሜሪካ እና ቱርክ ?

የአገዛዙ ዋነኛ አጋር የሆኑት ሩሲያ እንዲሁም ኢራን ለአሳድ ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ ቢሰነብቱም አገዛዙን ከመፍረስ አልታደጉም።

ሩስያ በዩክሬን በሚያደርገው ጦርነት የተጠመደች ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ እስራኤል በሊባኖስ ሔዝቦላህ ላይ በከፈተችው ዘመቻ ምክንያት ተዳክማለች።

ጦርነቱ ሲባባስ ሞስኮ የሩሲያ ዜጎች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ጥሪ ስታቀርብ ነበር።

በሶሪያ የረጅም አመታት የእርስ በርስ ጦርነት ዋና ተዋናይቷ አሜሪካም ብትሆን ሁኔታውን አይታ ዜጎቿን " በደማስቆ በረራዎች እስካሉ ድረስ " ሶሪያን ለቅቀው እንዲወጡ ስትጮህ ነበር።

ቱርክ በሶሪያ ያሉ አንዳንድ አማፂ ቡድኖችን ትደግፋለች።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለወራት አሳድን ከተቃዋሚዎች ጋር ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ አንዲደርሱ ግፊት ሲያደርጉ ነበር።

ፕሬዜዳንቱ የአማፂያኑን የቅርብ ጊዜ ግስጋሴ እንደሚደግፉ ተናግረው " አሳድ ጥሪዬን ቢቀበል ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር " ብለዋል።

ሶሪያ : እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በተቃውሞ ስትናጥ ከቆየች በኃላ በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ ሰዎች አልቀዋል። ሀገሪቱ እንዳልነበረ ሆናለች። ለሀገሪቱ እንዲህ መሆን የውጭ ኃይሎች አገዛዙን እና አማጽያንን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ድርሻ አላቸው።

መረጃው ከአልጀዚራ፣ ሮይተርስ እንዲሁም ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።
" አሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሶሪያን ለቀው ሸሽተዋል " - ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሀገራቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገለጹ።

ይህን ያሉት ' ትሩዝ ' በሚሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ነው።

" አሳድ ሄዷል " ያሉት ትራምፕ " ጠባቂው በቭላድሚር ፑቲን የሚመራው ሩስያ፣ ሩስያ፣ ሩስያ ! ከዚህ በላይ እሱን (አሳድን) ለመጠበቅ ፍላጎት አልነበረውም " ሲሉ ገልጸዋል።

የትራምፕ ሀገር አሜሪካ በርካቶች ባለቁበት የባለፉት 13 ዓመታት የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ሶሪያ ውስጥ ናት።

ሀገሪቱ ዋና አላማ ብላ የገባችው ' ISIS 'ን ለማፅዳት ቢሆንም በቀድሞ ፕሬዜዳንት ኦባማ ሰዓት " አሳድ መሄድ አለበት / ከአገዛዙ መወገድ አለበት " የሚል አቋም በይፋ ይንፀባረቅ ነበር።

እኤአ በ2013 ኦባማ እስራኤልን ሲጎበኙ ከቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ሆነው " አሳድ መሄድ አለበት አገዛዙ ማብቃት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ፤ የአሳድን ተቃዋሚዎች በቁሳቁስ እና በስልጠና ድጋፍ ታደርግላቸው ነበር።

የፑቱን ሀገር ሩስያ የአላሳድን መንግሥት የምትደግፍ ሲሆን የአገዛዙ ጠላቶች ላይ እርምጃዎችን ስትወስድ ነበር።

#Syria
በጎላን ተራራማ አካባቢ ምን የተለየ ነገር አለ? እስራኤል ቦታውን ለምን ትፈልገዋለች?

🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️ 🗞️

የእስራኤል ኃይሎች በጎላን ተራራማ አካባቢ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ የሆኑ አካባቢዎችን ጨምሮ ሌሎችንም የሶሪያ ግዛቶችን በቁጥጥር ሥር አውለዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የአገሪቱን መከላከያ ኃይል ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ወደሆኑ አካባቢዎች እና "በአቅራቢያ ወደሚገኙ መቆጣጠሪያ ቦታዎች" እንዲገባ ማዘዛቸውን አስታውቀዋል።
ይህም ውሳኔ ጊዜያዊ እንደሆነ እና እስራኤልን ከሶሪያ አማጺያን ጥቃት ለመጠበቅ በሚል መሆኑን ተናግረዋል።
የሶሪያ አማጺያን ፕሬዝዳንት በሻር አል-አሳድን ከሥልጣን ካስወገዱ በኋላ ነው እስራኤል እነዚህን አካባቢዎች የተቆጣጠረችው።
በርካታ የአረብ አገራት ድርጊቱን ኮንነዋል።
ጎላን ተራራማ አካባቢ የሚገኘው ከሶሪያ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ነው። የእስራኤልን ግዛት በሰሜን ምሥራቅ ያዋስናል።
በእስራኤል ወታደሮች ቁጥጥር ሥር ይገኛል።

እአአ በ1967 በስድስት ቀናት ጦርነት እስራኤል በሶሪያ ኃይሎች ከዚህ ተራራማ አካባቢ ጥቃት ተፈጽሞባታል።
እስራኤል በመልሶ ማጥቃት ወደ 1,200 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ቦታ በቁጥጥሯ ሥር አስገብታለች።
በአውሮፓውያኑ 1973 በተደረገው 'ዮም ኪፑር' ጦርነት ሶሪያ ግዛቱን መልሳ ከእስራኤል ለመውሰድ ሞክራ አልተሳካላትም።
በ1974 ሶሪያ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል።
ሁለቱም አገራት ወደ የግዛታቸው 80 ኪሎ ሜትር ርቀው እንዲገቡ ስምምነቱ ያስገድዳል።
የመንግሥታቱ ድርጅት ቦታውን የሚቃኝ ኃይል አሰማርቷል።
በ1981 እስራኤል የጎላን ተራራማ አካባቢን ጠቅልላ በግዛቷ ውስጥ አካተተች። ሰፋሪዎች በቦታው ቤት መሥራት ጀመሩ።
ነገር ግን ይዞታው የእስራኤል መሆኑን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቅና አልሰጠም። ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ግን በ2019 ይዞታው የእስራኤል መሆኑን ተናግረዋል።
እስራኤል ከአጠቃላይ ጎላን አካባቢ ለቃ ካልወጣች የሰላም ስምምነት እንደማይኖር ሶሪያ አስታውቃለች።
እአአ ኅዳር 2024 ላይ እስራኤል ከሶሪያ ጋር የሚለያትን አካባቢ በማለፍ ግንባታ እያደረገች ነው የሚል ቅሬታ በሶሪያ እና በተባበሩት መንግሥታት ቀርቦባታል።

አካባቢው ለምን አስፈላጊ ሆነ?
ሶሪያ የጎላን ተራራማ አካባቢዎችን ከ1948 እስከ 1967 በምትቆጣጠርበት ወቅት በሰሜናዊ እስራኤል አቅራቢያ ጥቃት ለማድረስ ያላት ቁልፍ ቦታ ነበር።
ከእስራኤል አንጻር በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት የሶሪያ መዲና ደማስቆን መመልከት የሚቻለው ከጎላን ተራራዎች ነው።
የሶሪያን ወታደሮች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርም ትጠቀምበታለች።
ሶሪያ በ1973 ጦርነት እንዳደረገችው እስራኤል ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም መከላከል የምትችልበት ሥፍራ አድርጋ እየተጠቀመችበት ነው።
አካባቢው ውሃ የሚገኝበት ቁልፍ ቦታም ነው።
ውሃ ውድ በሆነበት በመካከለኛው ምሥራቅ በጎላን ተራራ የሚገኘው የዝናብ ውሃ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ይገባል።

አካባቢው ለም የሆነው፣ እንስሳትም የሚጠጡት ውሃ የሚያገኙት ከዚሁ አካባቢ ነው።
እስራኤል ከ1967 በፊት ወደነበረው ይዞታዋ ትመለስ የሚለው የሶሪያ ጥያቄ በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም እንዳይወርድ ምክንያት ሆኗል።
ይህ ከሆነ ሶሪያ በገሊላ ባሕር ምሥራቃዊ ዳርቻ ይዞታ ይኖታል። እስራኤልም ንጹህ የመጠጥ ውሃ ምንጭ ታጣለች።
ይህን ባሕር እስራኤላውያን ኪናሬት ሲሉት አረቦች ቲቤሪየስ ይሉታል።
እስራኤል ድንበሩ ወደ ምሥራቅ እንዲገፋ ትሻለች።
እስራኤላውያን አገራቸው የጎላን ተራራማ አካባቢን ይዛ እንድትቆይ ይፈልጋሉ።
በቦታው ማን ይኖራል?
በ1967 ጦርነት አረብ ሶሪያውያን የጎላን ተራራማ ሥፍራ ነዋሪዎች ከቦታው ሸሽተዋል።
አሁን በአካባቢው ከ30 በላይ የእስራኤል ሰፋሪ ይዞታዎች ይገኛሉ።
20 ሺህ ነዋሪዎች እንዳሉ ይገመታል።
ከ1967 ጦርነት በኋላ እስራኤል በአካባቢው ግንባታ ጀምራለች።
ሰፈራው በዓለም አቀፍ መርህ ሕገ ወጥ ነው።
ሰፋሪዎቹ የሚኖሩት ወደ 20 ሺህ ሶሪያውያን ከሚኖሩበት አቅራቢያ ነው።
ከሶሪያውያኑ አብዛኞቹ የድሩዝ ጎሳ አባላት ናቸው። ጎላንን እስራኤል ስትቆጣጠር ቦታውን ጥለው አልወጡም።

እስራኤል በጎላን ተራራማ አካባቢ ምን ትሠራለች?
የሶሪያ ወታደሮች ከጎላን ተራራማ አካባቢዎች መውጣታቸውን ተከትሎ እስራኤል ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ የሆነውን አካባቢ በቁጥጥር ሥር አውላለች።
"ዘላቂ አካሄድ እስከምንዘረጋ በጊዜያዊነት ቦታውን እንደ መከላከያ ሥፍራ ኃይላችን ይይዘዋል" ብለዋል ኔታንያሁ።
"በሶሪያ ካለው አዲስ ኃይል ጋር ሰላም ማውረድ እና የጉርብትና ወዳጅነት መመሥረት ነው ፍላጎታችን። ይህ ካልሆነ ግን እስራኤል እና ድንበሯን ለማስጠበቅ ማንኛውንም እናደርጋለን" ሲሉም አክለዋል።
በሶሪያ በኩል የወጡ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት እስራኤል በደማስቆ እስከ 25 ኪሎ ሜትር ዘልቃ ገብታለች።
እስራኤል ግን ያን ያህል ርቀት ኃይሏ አለመጓዙን ትናገራለች።
የአረብ አገራት እስራኤልን እየወቀሱ ነው።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "የሶሪያን ግዛት በቁጥጥር ሥር ማዋል ነው። ይህም የ1974 ስምምነትን ይጥሳል" ብለዋል።

እስራኤል ግን በሶሪያ ያለው መንግሥት ስለወደቀ በ1974 የተደረሰው ስምምነት አሳሪ አይደለም ትላለች።
በለንደን ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር ጊልበርት አካር "እስራኤል የጥቅምት 7 ዓይነት ጥቃት በሶሪያ በኩል እንዳይከሰት ለመከላከል ነው ትላለች። በይዞታ ሥር ባለው ድንበር በኩል ሌላ ኃይል እንዳይጠጋ ለማስቆም ነው ዕድሉን የተጠቀመችው" ይላሉ።
እስራኤል ወደ ሶሪያ ግዛት መግባቷ ለወደፊት በሶሪያ ከሚኖረው መንግሥት ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር እንደሚያስቸግርና "እስራኤል የከፋ ቀን ቢመጣ በሚል ዕሳቤ ነው የምትንቀሳቀሰው። ይሄም አፍራሽ ነው" በሚል እንድትታይ እንደሚያደርግ ያክላሉ።
ብዙ ተንታኞች የእስራኤልን ማብራሪያ አሳማኝ አድርገው አልተቀበሉትም።
ለንደን ባለው የተንታኞች ስብስብ 'ቻተም ሐውስ' የሚሠሩት ፕሮፌሰር ዮሲ ሜክልበርግ "ሶሪያ በስምምነቱ አልገዛም አላለችም። እስራኤል ደኅንነቷን ለማስጠበቅ የወሰደችው ቅድመ ጥንቃቄ ነው። ግን ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ምንም አሳማኝ ምክንያት የለም" ይላሉ።
ለንደን ባለው ሌላ ስብስብ 'ሮያል ዩናይትድ ሰርቪስ ኢንስቲትዩት' የሚሠሩት ዶ/ር ሀይ ሄይለር "የሶሪያ አማጺያን የጎላን ተራራማ አካባቢዎችን መልሰው የመውሰድ ዕድላቸው ጠባብ ነው። በአገር ውስጥ ጉዳይ ይጠመዳሉ። ከእስራኤል ጋር አዲስ ግጭት ውስጥ መግባትንም አያስቡም" ይላሉ።
በሶሪያ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች እና ሚሳዔሎች ላይ ጥቃቶች መፈጸሟን እስራኤል አረጋገጠች

🗞️ 🗞️ 🗞️

እስራኤል በሶሪያ ያሉ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች እና ሚሳኤሎች 'ጽንፈኞች' እጅ እንዳይገቡ በሚል በአየር ጥቃት እያወደመች መሆኗን አረጋገጠች።
የበሻር አል አሳድ መንግሥት መውደቁን ተከትሎ በተለያዩ በሶሪያ ክፍሎች የሚገኙ ስትራቴጂያዊ የጦር መሳሪያዎችን ለማውደም በመቶወች የሚቆጠሩ የአየር ጥቃቶችን እስራኤል ፈጽማለች።
በተጨማሪም በአገሪቱ የባሕር ኃይል መርከቦች እና ይዞታዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ውድመት ማድረሷ ተገልጿል።
ከእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው 15 የጦር መርከቦች ቆመው የነበሩባቸውን አል ባይዳ እና ላታኪያ በተባሉ የሶሪያ ወደቦች ላይ የሚገኙ የባሕር ኃይል ትጥቆች ላይ ጥቃት ፈጽሟል።
ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት ላታኪያ በተባለችው ወደብ በተፈጸመው ከፍተኛ ጥቃት የመርከቦች ቃጠሎን እና ወደቡ ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክቷል።
በመላው ሶሪያ ከ350 በላይ የአየር ጥቃቶችን መፈጸሙን የገለጸው የእስራኤል መከላከያ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ወደ ሆነው ቀጣና ኃይሎቹን ያስገባ ሲሆን፣ የጎላን ተራራ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚገኝ አንድ በሶርያ ዙሪያ የሚሠራ የሰብዓዊ መብት ተቋም ባሰባሰበው መረጃ መሠረት ባለፈው እሁድ የሶሪያ አማጽያን ወደ መዲናዋ ደማስቆ መግባታቸውን ተከትሎ የእስራኤል መከላከያ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች 310 የአየር ጥቃቶችን ፈጽሟል ብሏል።
የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ኢዝራኤል ካትዝ ጥቃቶቹ ለአገራቸው ስጋት የሆኑ ስትራቴጂክ የጦር መሣሪያዎችን ለማውደም መሆኑን ገልጸው፣ የሶሪያን የባሕር ኃይል ለማውደም የተካሄደው ዘመቻን "ትልቅ ስኬት ነው" ብለውታል።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል እንዳስታወቀው በጥቃቶቹ የአየር ኃይል ሰፈሮች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ ፀረ አውሮፕላን መሳሪያዎች እና የጦር መሳሪያ ማምረቻ ስፍራዎችን ጨምሮ በርካታ በዋና ከተማዋ ደማስቆ፣ ሆምስ፣ ታርቱስ እና ፓልሜራ ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
በተጨማሪም ጥቃቱ የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘኖች፣ የተተኳሽ ማከማቻዎች እና "በርካታ" ከባሕር ላይ የሚወነጨፉ ሚሳዔሎች ተመትተዋል ተብሏል።
እስራኤል በሶሪያ ላይ ይህንን ጥቃት የምትፈጽመው "መሳሪያዎቹ በጽንፈኞች እጅ እንዳይወድቁ" ለመከላከል ነው ብላለች።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የበሻር አል አሳድን መንግሥት ለገረሰሰው ሃያት ታህሪር አል ሻም ቡድን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት "ኢራን ሶሪያ ውስጥ ድጋሚ ለመቋቋም የምትሞክር ከሆነ ምላሽ ለመስጠት እንገደዳለን" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራቸው የምትፈጽመው ጥቃት ራስን ለመከላከል መሆኑን በማስረዳት፣ ነገር ግን ከአዲሱ የሶሪያ ኃይል ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚፈልጉም ቀደም ሲል ገልጸው ነበር።
" የኑሮ ውዶነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል "


ተቃዋሚ ፓርቲዎች

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ (ኮከስ) ምን አለ ?

- የመድረክ
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
- የኅብር ኢትዮጵያ
- የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
- የኢሕአፓ ... ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ በወቅታዊ ሁኔታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል።

ኮከሱ ምን አለ ?

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከሱ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር በእጅጉ ኮንኗል።

በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ " የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ ዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዙ ነው " ብሏል።

ይህም ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረገን ነው ሲል ወቅሷል።

" ፖለቲካችን የተለመደውን የአፈናና አግላይነት፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ጠቅላይነት አጠናክሮ ቀጥሏል " ያለው ኮከሱ " የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአጃቢነት፣ ህዝብ ከአገልጋይነት ያለፈ የፖለቲካ መብታቸውን የማንሳት ህገመንግስታዊ መብት ተነፍጓቸው በወንጀል ተቆጥሮባቸው ፀጥ-ለጥ ብለው እንዲገዙ ተፈርዶባቸው በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ናቸው " ብሏል።

ኢኮኖሚው ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ተሸጋግሮ ለተለያዩ የልማት መሰረተ ልማት አውታሮች ሊውል የሚችል የዓመታዊ በጀት ከፍተኛውን ድርሻ ለጦርነትና ጸጥታ ማስከበር ግብዓቶች እንዲውል ተደርጓል ሲል ወቅሷል።

" ልማትና ዕድገት ከቀለም-ቅብ ያለፈ መሰረት እንዳይኖረው ተገደናል " ሲልም አክሏል።

" የኑሮ ውድነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " ሲልም ገልጿል።

ኮከሱ " ማኅበራዊ ህይወታችን በሥራ አጥነት፣ መፈናቀል፣ የማኅበራዊ ተቋማት መዳከምና የአገልግሎት መቋረጥ ወይም መቀንጨር፣ የሠራተኞች ብሶት መገለጫቸው ከሆነ ውሎ አድሯል " ብሏል።

" በየአቅጣጫው የሚነሱት ጥያቄዎችም የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው " ሲል ገልጿል።

" ከትምህርትና ጤና አገልግሎት ተቋማትና ሠራተኞች የሚሰማው ጩሄት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " ሲልም አመልክቷል።

ኮከሱ፦

- " ግጭትና ጦርነትን እያስፋፉ - የይስሙላ አግላይ የምክክርና ውይይት ስብከት ሊቆም ይገባል " ብሏል። " መንግስት / ገዢው ፓርቲ / ከማስመሰል ተላቆ ራሱንና የአገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ለሁሉን አካታችና አሳታፊ ተዓማኒና በባለድርሻ አካላትና አስፈጻሚዎች ተቀባይነት ያለው ሃቀኛ የምክክር ፣ ድርድር ፣ ውይይት መድረክ እንዲያመቻች ሽግግሩ በመጨናገፉ የቀጠለውና የተስፋፋው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።

- የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ማጠናከር ዓላማና ተልዕኮ ይዞ ፤ የገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ያቋቋሙት የጋራ ምክር ቤት ከተቋቋመበት ዓላማና ተልዕኮ እየራቀ የገዢው ፓርቲ ታዛዥ ጉዳይ ፈጻሚና አስፈጻሚ እንዲሆነ ጫና እየተደረገበት ነው " ብሏል።

- " የፖለቲካ ድርጅቶች ሃሳብ መለዋወጫ እንዲሆን የመሠረቱትን የጋራ ምክር ቤትን ብልጽግና ቀስ በቀስ በስልታዊውና በሚታወቀው የኢህአዴግ አካሄድና ዘዴዎች አሽመድምዶታል " ሲል ገልጿል።

- " ህወሓት መር የነበረው ኢህአዴግ ይሠራቸው የነበሩት ዕመቃዎች፣ ጥሰቶች፣ ተንኮልና ደባዎች፣ አስርጎ የማስገባትና የመከፋፈል ሤራዎች፣አሁን በወራሹ ብልጽግና ደምቀውና ጎልተው ያለድብብቆሽና ይሉኝታ እየተደገሙ ነው " ሲል ወቅሷል።

- " ብልጽግና በአደባባይ ኃሳብን በነጻነትና ያለመሸማቀቅ የመግለጽ መብት መከበርን ቢሰብክም በተግባር ግን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በአዋጅ፣ በመመሪያና ደንብ እያፈነ ይገኛል " ሲል ከሷል።

-  " ሽግግር በሌለበት የሽግግር ፍትህ ውዳሴ " ከንቱ ነው በማለት ከመንግስት/ የገዢ ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ጠይቋል። በመንግሥት አደራጅነት የሚቋቋም የሽግግር ፍትህ ተቋም ከዚህ በፊት ከተቋቋሙትና ያለውጤትና ሪፖርት ከተበተኑት ኮሚሽኖች የተለየ ውጤት አይጠበቅም ብሏል። ለአካታች፣ አሳታፊና ተዓማኒ የሽግግር ሂደትና ተቀባይነት ያለው ህጋዊ የፍትህ ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ እንዲተገበርና ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል።

- " የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና የዲሞክራሲ አጋሮች እየተበረታቱ ሳይሆን እየተሸማቀቁ ነው " ብሏል።

-  " ዕለት ከዕለት የገዥው ብልጽግና አምባገነዊነትና አማቂነት እየጎላና እየተበራከተ ነው የመጣው " ያለ ሲሆን " የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መጥቶ ተኮማትሯል። " ሲል ገልጿል። " በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ነፃነትና ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና በመግለጫዎች እንዲወሰን ተደርጓል " ሲልም ወቅሷል። " ሠላማዊ ሠልፍ ለመጥራት መዘጋጀት፣ ህገመንግሥት የሚፈቅደው መብት ሆኖ ሳለ- ያሳስራል፣ ለከፋም ጉዳት ይዳርጋል " ብሏል።

- " በገዥው የብልጽግና ፓርቲ ሹመኞች፣ ሃላፊነት በጎደለው ፍላጎትና ውሳኔ፣ በዋና ከተማችን ‹የኮርደር ልማት› በሚል የተጀመረው የመኖሪያና ንግድ ቤቶችንና ህንጻዎችን በማፍረስ ህዝብን በማፈናቀል ለከፍተኛ ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቀውስና ለጎዳና ተዳዳሪነት አጋልጧል " ብሏል። " ይህ ኅብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ከፖለቲካ ገለልተኛ ሙያዊ ጥናት ውጪ የሚደረገው ዜጋ አሰቃይ  እርምጃ ወደ ክልል ከተሞች እየተዛመተና ሥቃዩን በመላ አገሪቱ እያዳረሰ ነው " ሲል ተቃውሟል። " ግቡ ለቀጣዩ ምርጫ የቅስቀሳ ግብዓት ነው " ብሏል።
" የኮርደር ልማት በገዥዎች የረጅም ጊዜ አብሮነታቸውና ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቁርኝታቸው የማይፈለገውን የማኅበረሰብ አባላት ማፈናቀልና መበተን ስለሆነ ሥራው ያለምንም ተጠያቂነት፣ በማናለብኝነት መንፈስ፣ በጥድፊያ እየተካሄደ ነው " ሲል ወቅሷል።

- " በርካታ የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ወደ ጎን ተብለዋል። ውዱን የአገርና ህዝብ ሃብት ከመንገድ ስፋትና፣ ህንጻ መቀባትና ሣር መትከል አልፎ ለቤተመንግሥት ግንባታ ጭምር እየዋለ መሆኑ ለዜጎች ህይወትና ኑሮ ደንታ ማጣት- ኢሰብዐዊነት ነው " ሲል ወቅሷል።

ኮከሱን መንግስትን " ጦርነትን እንደ መግዣ ሥልቱ እየተጠቀመ ነው " በሚል ወቅሶ እንዲህ አይነት መንግሥት " የሠላምና ልማት ጠንቅ ነው " ብሏል።

" አገሪቱ ከገባችበትና ካለችበት እጅግ አሳሳቢና ፖለቲካዊ ማህበረ-ኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንድትወጣ፣ በየአቅጣጫው ከሚሰማውና ህዝባዊ የህልውና ጥያቄ፣ ከሚታየው የትጥቅ ትግል መፍትሄ ለመስጠት ተኩስ ቆሞ ሃቀኛ፣ ሁሉን-አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ ለማውረድ ተዓማኒ ውይይት/ምክክርና ድርድር እንዲደረግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ሩሲያ በቀይ ባህር ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ከሱዳን ጋር መስማማቷ ተገለጸ

********

ሩሲያ በቀይ ባህር ላይ ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ጥያቄ ካቀረበች ስድስት ዓመት ሞልቶታል

ሩሲያ በቀይ ባህር ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ከሱዳን ጋር መስማማቷ ተገለጸ።

ሩሲያ ከቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር መንግሥት ጋር በቀይ ባህር ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ተስማምታ ነበር።

ይሁንና በሱዳን ያጋጠመው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሩሲያ ይህን ወታደራዊ ማዘዣ እንዳትገነባ እክል ፈጥሮባት ቆይቷል።

አሁን ላይ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ ዩሱፍ በሩሲያ ጉብኝት አድርገዋል።

ሚንስትሩ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር በሞስኮ ተወያይተዋል።
ሚንስትሩ አሊ ዩሱፍ በሞስኮ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ "ሩሲያ ከሱዳን ጋር ባላት ስምምነት መሰረት በቀይ ባህር ወታደራዊ ማዘዣ ትገነባለች፣ ይህን ስምምነት እንዳይተገበር የሚከለክል ነገር ምንም የለም" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሱዳን ካለባት የእርስ በርስ ጦርነት ጫና በተጨማሪ በቀይ ባህር ላይ ባላት ቁልፍ ቦታ የሀያላን ሀገራት ሀይል ፍትጊያ አደጋ ተደቅኖባታል።

ከዚህ ባለፈም ሱዳን የወርቅ ማዕድን ሀብታም መሆኗ ምዕራባዊያን እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ትኩረትን ትስባለች።
👍1
#ድፍድፍ_ነዳጅ 📈

እስራኤል በኢራን ላይ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ከ2020 በኋላ በቀን ውስጥ በዚህ ደረጃ ሲጨምር ከፍተኛው ነው ተብሏል።

አሁን ያለው ውጥረት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ መቆራረጥ እንዳይፈጥር ተሰግቷል።

በጥቃቱ መክንያት በዓለም ገቢያ ፈጣን እርምጃዎች እየተስተዋሉ ነው። የአክሲዮን ገቢያዎች ተዳክመዋል፤ ባለሀብቶች እንደ ወርቅ፣ ስዊስ ፍራንክ እና የጃፓን የን ያሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ወደሆኑ ንብረቶች እየተጣደፉ ነው።

ተንታኞች ውጥረቱ ተባብሶ በዚሁ ከቀጠለ ሁኔታው ​​የዓለምን የኃይል ገበያ የበለጠ ሊያናጋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ቀጣዮቹ 72 ሰዓታት ይህ ዋጋ በዚሁ ለመቀጠሉ ወይም ለመባሱ ወሳኝ ሰዓታት ናቸው ተብሏል።

ኢራን በቀን እስከ 3.3 ሚሊዮን በርሜል ታወጣለች፣ ይህም ከዓለም አቀፍ አቅርቦተለ 3 በመቶውን ይሸፍናል።

Source: BBC , CNBC
#ኢራን #iran🇮🇷 #iranian
አይበለውና በኤሌክትሪክ አደጋ የተያዘ ሰው ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንደሚኖርብዎት ያውቃሉ? ⚠️
ኤሌክትሪክ ጠቀሜታው የላቀ ቢሆንም በጥንቃቄ ጉድለት በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ ለሞትም ይዳርጋል፡፡ ታዲያ ሁሌም እራስዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በኤሌክትሪክ ቢያዝ ወዲያውኑ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ህይወቱን ሊያድን የሚችልበት አግባብ አለ።
⛔️ አይበለውና በኤሌክትሪክ አደጋ የተያዘ ሰው ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንደሚኖርብዎት ያውቃሉ?
✅ የኤሌክትሪክ ምንጭን ማጥፋት ወይም ቆጣሪ ብሬከር መመለስ
ይህ የመጀመሪያውና ዋነኛው እርምጃ ሲሆን፤ የቆጣሪ ብሬከሩ የት እንዳለ ካወቁ በፍጥነት ማጥፋት እና የኤሌክትሪክ ፍሰት መቆሙን ሲያረጋግጡ ብቻ ወደ ተጎጂው መቅረብ፤
✅ ኤሌክትሪክን ወዲያውኑ ማጥፋት ካልቻሉ ተጎጂውን ከኤሌክትሪክ ምንጭ ለማራቅ ደረቅ እና ኤሌክትሪክ የማያስተላልፍ (non-conductive) ነገር ይጠቀሙ፤
✅ በፍፁም ባዶ እጅዎን ወይም እርጥብ ነገርን አይጠቀሙ!
ለምሳሌ:- ደረቅ የእንጨት ዘንግ፣ የፕላስቲክ መጥረጊያ እጀታ፣ ወፍራም ጋዜጣ ወይም መጽሐፍ፣ ወይም የጎማ ምንጣፍ መጠቀም ይችላሉ።
✅ ተጎጂውን አይንኩ! በኤሌክትሪክ የተያዘ ሰው ሰውነታቸው ሊያስተላልፍ ይችላል፤
✅ የኤሌክትሪክ ንዝረት የቆዳ ላይ እና ውስጣዊ ቃጠሎ ሊያስከትል ስለሚችል የተቃጠለውን ወይም የተጎዳውን የሰውነት ክፍል በቀዝቃዛ (በረዶ ባልሆነ) ውሃ በማቀዝቀዝ ንጹህና ደረቅ በሆነ ጨርቅ ይሸፍኑት።
✅ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ወደ ህክምና ተቋም ይደውሉ፤
ያስታውሱ‼️
የኤሌክትሪክ አደጋ የሚያስከትል ሁኔታ ሲመለከቱም አደጋው ከመድረሱ በፊት በአቅራቢያዎ ካለ የተቋማችን የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በአካል ወይም በጥሪ ማዕከሉ 905 እና 904 በመደወል አልያም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ያሳውቁ!
የእርስዎ ደህንነት ቀዳሚ መሆኑን አይርሱ❗️
እራስዎን ከአደጋ ይጠብቁ❗️
ኤሌክትሪክን በቁም ነገር ይዩት🚫
#Safety_First_Always - #ሁልጊዜም_ቅድሚያ_ለጥንቃቄ⚠️
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
የአማራ ክልላዊ መንግሥት እና የአፋሕድ ሥምምነት ከማስረሻ ሰጤ ያለፈ ነው?

*******

በአማራ ክልላዊ መንግሥት እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል ማስረሻ ሰጤ የተፈራረሙት “ዘላቂ የሰላም ሥምምነት” ጥያቄ በርትቶበታል። ማስረሻ ሥምምነቱን የፈረሙት አፋሕድ ከአመራርነት እንዳገዳቸው ባሳወቀ በቀናት ልዩነት ነው። የፋኖን እንቅስቃሴ እና የአማራ ክልልን ፖለቲካ የሚከታተሉ አጥኚዎች ሥምምነቱ ከግለሰብ ያለፈ እንዳልሆነ ይተቻሉ።

የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አረጋ ከበደ ትላንት በአዲስ አበባ ቅንጡ ሆቴል ከማስረሻ ሰጤ ጋር በተፈራረሙት ሥምምምነት ከፍ ያለ ተስፋ ሰንቀዋል። በክልሉ ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲስ በፋኖ አመራርነት ስማቸው ከሚነሳ ግለሰብ ጋር ሥምምነት ሲፈረም የመጀመሪያው ነው።

በኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ በሚደረግበት ወቅት ክልሉን የመምራት ኃላፊነት ከይልቃል ከፋለ የተረከቡት አቶ አረጋ ሥምምነቱ ከተፈረመ በኋላ “ተወያይተን እና ተደራድረን በክልላችን እና በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ቆርጠን ተነስተናል” ሲሉ ተናግረዋል።

የቀድሞው የተዋጊ ሔሊኮፕተር አብራሪ ማስረሻ ሰጤ ሥምምነቱን ከመፈራረማቸው በፊት ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴም ይሁን ከድርጅቱ አባልነት እንደታገዱ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አስታውቆ ነበር። እስክንድር ነጋ በሰብሳቢነት የሚመሩት አፋሕድ ማስረሻ ሰጤ እና መሥፍን አባተ የተባሉ ሌላ አመራር “ከየትኛውም ተቋም ጋር ተገናኝተው በድርጅቱ ስም በግል እንዲናገሩ ውክልና ተሰጥቷቸው እንደማያውቅ” ኅዳር 20 ቀን 2018 ገልጿል።

የድርጅቱ መግለጫ ከወጣ ከአምስት ቀናት በኋላ ግን ማስረሻ በአፋሕድ ስም ሥምምነቱን ፈርመዋል። ሥምምነቱን ከፈረሙ በኋላ “ወደ ጫካ የወሰዱን የተለያዩ የሕዝብ ጥያቄዎች ነበሩ” ያሉት ማስረሻ ጥያቄዎች የሚመለሱበት የጊዜ ሰሌዳ መቀመጡን ተናግረዋል። ማስረሻ “በሒደት አሁን የሚመለሱ በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛ ጊዜ እና በረዥም ጊዜ የሚመለሱ ብለን በሦስት ከፍለን ተወያይተን ተስማምተናል” ሲሉ ተደምጠዋል።

ዶይቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሰብሳቢ እስክንድር ነጋን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይሁንና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተሰራጨ የድምጽ መልዕክት አቶ እስክንድር አፋሕድ “ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በየትኛውም ጊዜ በየትኛውም ቦታ” ከመንግሥት ጋር ተደራድሮ እንደማያውቅ ገልጸዋል።

ሥምምነቱ የተፈረመው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ሰልማ ማሊካ ሐዳዲ እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ምክትል ዋና ጸሀፊ ሞሐመድ አብዲ ዋሬ በተገኙበት ነው። የአፍሪካ ኅብረት “የሥምምነቱን ተግባራዊነት እና በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሰላም ለመደገፍ ቁርጠኛ” እንደሆነ አስታውቋል። ሥምምነቱን “የደፋር እርምጃ” ያለው ኢጋድ “የቀሩት ታጣቂ ኃይሎች” ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

ሥምምነቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ በፌድራል መንግሥት እና በአማራ ክልል ቢወደስም የፋኖን አደረጃጀት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቅርብ የሚከታተሉ ፖለቲከኞች እና የጸጥታ ጉዳዮች አጥኚዎች ግን ውኃ የሚያነሳሆኖ አላገኙትም።

በእርግጥ ሥምምነቱን ፈረሙ የተባሉት ማስረሻ ሰጤ ያልተማከለ አደረጃጀት ያላቸው የፋኖ ኃይሎች ከመንግሥት ጋር መዋጋት ከጀመሩ በኋላ ስማቸው ከሚጠቀስ አመራሮች መካከል ናቸው።

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት ማስረሻ “እንደ ጎጃም ፋኖ ተወካይ” ተደርገው ይቆጠሩ እንደነበር ፖለቲከኛው መስፍን አማን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። “የጎጃም ፋኖን ከመሠረቱት፣ እንቅስቃሴውን መጀመሪያ ከመሩት ሰዎች አንዱ እሱ ነበር። በውጊያ አመራር ሰጪ ነው” ያሉት መስፍን “ትልቅ ቦታ ነበረው” ሲሉ አስረድተዋል።

ዶይቼ ቬለ ሐሳባቸውን የጠየቃቸው የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ጥናት ባለሙያ በበኩላቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ማስረሻ ስለሚመሯቸው ታጣቂዎች ብዛት ስለተቆጣጠሯቸው ቦታዎች ግልጽ መረጃ አለመኖሩን ገልጸዋል። በአቶ ዘመነ ካሴ የሚመራውን የፋኖ ቡድን “የሚቃወም” በምሥራቅ ጎጃም ዞን መርጡለ ማርያም አካባቢ “ደጋፊ አለኝ” ከሚል የዘለለ መከላከያ ሠራዊትን ከመሳሰሉ የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ስላደረጓቸው ውጊያዎች ተጨባጭ መረጃ አለመስማታቸውን ስማቸውም ሆነ የሚሰሩበት ተቋም እንዳይገለጽ የጠየቁት ባለሙያ አስረድተዋል።

“ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የትኛውን አንጃ ነው ሲመራ የነበረው? ምክንያቱም ቡድኖቹ ይታወቃሉ። ሸዋ አለ፣ የወሎ አለ፤ የጎንደር አለ። ጎጃም ላይ ያለው በጣም በጣም ትንሽ ነው” የሚሉት ባለሙያው “አለ ከተባለ” በማስረሻ ሰጤ እንደሆነ ይሞግታሉ። “በጎጃም ትልቅ ቦታ ያለው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ወይም የእነ ዘመነ ቡድን ነው” በማለት አስረድተዋል።
አዲስ የፈጠራ ውጤት፡ በመኪና ወንበር ላይ የሚገጠም የሄልሜት ቅርጽ ያለው ኤርባግ (Airbag) ይፋ ሆነ


አንድ የቻይና የመኪና መለዋወጫ አምራች ኩባንያ የተለመደውን የኤርባግ አሰራር በመቀየር በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነና በመኪና ወንበሮች ላይ የሚገጠም የራስ ቁር(ሄልሜት) ቅርጽ ያለው የደህንነት ከረጢት ይፋ አደረገ። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በትራፊክ አደጋ ወቅት የተሳፋሪዎችን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ሲሆን አሰራሩም ካለው የተለመደ የኤርባግ ቴክኖሎጂ በእጅጉ የተለየ ነው።

ይህ የኤርባግ ስርዓት በአደጋ ወቅት የተሳፋሪውን ራስ፣ አንገት፣ ትከሻ እና የአከርካሪ አጥንትን ሙሉ በሙሉ በመሸፈን የሚከፈት ሲሆን ከጎን በኩል ካሉ ኤርባጎች ጋር በመቀናጀት ተሳፋሪውን እንደ ሄልሜት ከበው በመያዝ ከከባድ ጉዳት ይከላከላል። ይህም በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከሚሰነዘር ግጭት ይልቅ ተሳፋሪውን በአራት አቅጣጫዎች በመደገፍ የተሻለ ጥበቃ እንዲያገኝ ያስችለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ስርዓቱ ከመኪናው አሽከርካሪ ረዳት ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ዘመናዊ ሴንሰሮች ያሉት ሲሆን እነዚህም ሴንሰሮች አደጋ በሚከሰትበት ቅጽበት የተሳፋሪው ወንበር ተኝቶ እንደሆነ በመለየት በጥቂት ሚሊሰከንዶች ውስጥ ወንበሩን ወደ ትክክለኛ አቀማመጥ በራሱ የመመለስ ብቃት አላቸው።

ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ይህ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁዋዌ እና በቼሪ ኩባንያዎች የጋራ ፕሮጀክት በሆነው ሉክሲድ ቪ9 (Luxeed V9) ሞዴል መኪና ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፈጠራ በመኪና ደህንነት ዘርፍ ላይ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ የታመነ ሲሆን በተለይም የራስና የአንገት ጉዳቶችን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
ይህ ‘ኢንቨስትመንት’ እውነት ነበር… ወይስ ታላቅ ማጭበርበር?”

🚨 ሰበር ዜና…

#Ethiopia_news #hasab_today

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት መስራችን እና “ጥቅም በመጋራት” በሚል የተወያዩ ታዋቂ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ፖሊስ እንደሚገልጸው፣ እነዚህ ተጠርጣሪዎች የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅቱን በተጋነነ እና ባልተገባ መልኩ በማስተዋወቅ ሕገወጥ መንገድ ገንዘብ ማሰባሰብ ተጠርጥረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ በዚህ ሂደት ውስጥ “ተጋሪ” በመሆን እንደተሳተፉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎች እና የማስታወቂያ ባለሙያዎችም ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

በፖሊስ መረጃ መሠረት፣ ከ1200 በላይ ዜጎች በዚህ ማጭበርበር ተጎድተዋል፣ እና የደረሰው የገንዘብ ጉዳት 1.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ከተጎጅዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ፣
95 ሺህ ብር እንደ ቅድመ ክፍያ፣
285 ሺህ ብር እንደ “ታክስ”፣
እንዲሁም 130 ሺህ ብር ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር በሚል ምክንያት
ከእያንዳንዱ ሰው እስከ 1.365 ሚሊዮን ብር ድረስ መቀበላቸው ተገልጿል።

አሁን ግን፣ በ19 ዓይነት የተለያዩ ወንጀሎች ላይ ምርመራ ተጠናቆ፣ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ፖሊስ ህዝቡን ከእንደዚህ ያሉ “ፈጣን ትርፍ” ተብለው የሚቀርቡ ኢንቨስትመንቶች እንዲጠንቀቅ ጠርቷል።

እንዲህ ያሉ ኢንቨስትመንቶች በእውነት ይሰራሉ ወይስ ማጭበርበር ናቸው?”
🔥1