ʜᴀʟᴀʟ
11.5K subscribers
778 photos
457 videos
1 file
211 links
خُذ ماشئت ، لا تستأذن بنشر الخير🤍.


Cross @Ifendim
Download Telegram
የአንዳንዶች ጫማ ለሌሎች የመቀመጫ ወንበራቸው ነው😭
😁38
አንዱ ምን አለ
ሴቶች ደስተኛ ሰላማዊ ህይወት እና ረጅም እድሜ ይኖራሉ ለምን መሰላቹ
.
.
.
.
.
ሚስት ስለማያገቡ 😁
😁35🤣7
ወጣቶች ሆይ ተጋቡ! ከከባድ የሥራ ውሎ በኋላ ወደ ሚስት እቅፍ መመለስ ብዙዎች የማያውቁት እረፍት አለው፤ እውነቱን ለመናገር እኔም አላውቀውም፣ ግን አንድ ሰው ሲናገር ሰምቼ ነው።😭
😁45🤣5👍4
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ስለ ዘረኝነት እንዲህ ይላሉ፡-

- ​"የበለጸጉ ሀገራት ነጭ መኪና ሰርተው ጥቁር ጎማ እስካደረጉላት ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም።

- የበለጸጉ ሀገራት የወንጀለኞችን ዝርዝር 'ጥቁር መዝገብ' (Blacklist) እያሉ እስከጠሩ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም።

- ነጭ ቀለም ሰላምን፣ #ጥቁር_ቀለም ደግሞ ጦርነትን እስካመለከተ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም።

- ​ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን እኔ ጥቁር በመሆኔ እኮራለሁ፤ ምክንያቱም በጣም በቀላል ምክንያት ነው... ጥቁር ሰውነቴን በነጭ ሶፍት ነው የምጠርገው።"😅
😁29🔥112👏1
ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም 🙌
18🤣1
ሀቢቢ በልጅነት አግባና ልጅህን ጓደኛህ አርገህ አሳድገዉ


አንተ ባባን እንደምትፈራዉ ልጅህ እንዲፈራህ አትፍቀድ ጓደኛ አርገህ ሲጨንቀዉ አንተን ሚያማክርህ አይነት ወንድ አርገህ አሳድግ ፈጠን በል ✌️🙂
46👍3
لِكُلِّ سَاقِطٍ لَاقِطٌ
~የማይፈለግ ሕይወት~?!
¤
ሰው ዝንባሌ አለው..ፍላጎት አለው...ራሱን እስከ ሞት ድረስ ማቆየት የሚፈልግበት ቅኝት አለው...ይህ ቤተሰብ..^ ማህበረሰብ..ባህል..ሐይማኖት ተባብረው የሚፈጥሩት የሰው ልጅ የተለያየ ቀለም የሚይዝበት ሁኔታ ነው።

ምናልባት አንዱ ሳይፈልግ የሚኖረው ህይወት ለአንድ ምኞት ወይም ፍላጎት ነው። የፍላጎቱን እየኖረ ያለው ሰው ህይወት ደሞ ለሌላኛው መቀመቅ ነው ። ምንም ማረግ አይቻልም። አለም ለዚህ የተፈጥሮ ህግ የተገራች እኛንም በዚህ ቀንበር ጠምዳ የምታስጉዘን ናት።


ግን ደሞ ተፈጥሯችን ለግዞት የተገራ አይደለም። ለጨለምተኝነት... ለእርካታ ቢስነት እጅ የሚሰጥ አይደለም.. መፍትሄ ፍለጋ መማተሩ አይቀርም። ፈላጊዎቹን ተከትለን ስንጓዝ ሁለት አይነት መልክ እናገኛለን።
¤
¤
-∞ አንድኛው ከተፈጥሮ ህግ ጋር ግብግብ እና ትግል የሚደረግበት።
የታሰበ ግን ያልታየ.. የታለመ ግን ያልተጨበጠ ፍላጎት ላይ ለመድረስ በአልሸነፍም ወኔ የሚፋለሙበት ነው..(የማያልቅ ትግል...መጨረሻ የሌለው መዳረሻ ፍለጋ የሚደረግ መባከን)

¤[ሌላኛዎቹ ደሞ ወደ ፈጣሪያቸው መንገድ የገቡ ናችው... ወደ መለኮታዊው ዓለም የሰመጡ.. ከራሳቸው ፍላጎት ለጌታቸው ፍላጎት ራሳቸውን ያስገዙ... በሚያልሙት ሳይሆን በተገኙበት ላይ ፍቅርን ለመዝራት ብሎም ለማጨድ የሚኳትኑ ፀኣዳ ነፍሶች ናቸው...
¤
በእነዚህ አለም ጉዳያቸው ወደ አላህ...ንግዳቸው ከአላህ...ሚደገፉትም በርሱ... ሚጽናኑትም በርሱ... የሚመኩትም በርሱ ብቻ ነው... የነሱ ውበት የአላህ ግኝነት ላይ የተመሰረተ ነው..እርሱ የተጠራበት እርሱ የተወሳበት እርሱ የተላቀበት ሁሉ ለእነሱ ውበት ያዘለ አለም ነው...ፍጡርን በፈጣርያቸው አሸንፈው ያደመቁ ፅገሬዳዎች ናቸው.. ሲጀምሩ 'አላህ ያለበት ሁሉ ውብ ነው' የሚለውን ሐረግ በቃል አምነው ነው። ሲደርሱ እየኖሩት ነው... ቃሉ ህይወታቸው ነው...የሚነገር ሳይሆን የሚታይ ነው... 'አልሐምዱሊላህ' ሲሉ 'ከአንተ ከሆነ ወድጄዋለሁ' የሚልን መልዕክት በውስጡ አዝሎ ነው... እነዚህ ከ እውነት ጋ ሳይሆን ከፍላጎታቸው ጋ ትግል የገጠሙት ናቸው...እውነቱ የአላህ ፍላጎት መሆኑ የገባቸው ..!

ምን ላይ ነን?!
5😭2👍1
.


አድጌም እስካሁን ድረስ የዚህን ነገር ስም አላወቅኩትም፤ ምንድነው ስሙ?🥲
😁241
s/one said፦ ባለትዳሮች ላጤዎችን ያሉበትን ችግር ቢያዩ ለይሉን ሙሉ ለምስጋና ሰላት ይቆሙ ነበር አለ አንዱ¡

ላጤዎች ቻሉት😅
🤣211
ከንግግርህ የበለጠ ተግባርህ ሰዎችን ወደ ሂዳያ ይመራል...
22❤‍🔥8👍2🥰2💯1🏆1
..


የአንድ አመትን ዋጋ ማወቅ ከፈለግክ ከጓደኞቹ ተለይቶ አንድ አመት ትምህርት የደገመን ሰው ጠይቅ። የአንድ ወርን ዋጋ ማወቅ ከፈለግክ ከ 9 ወር በፊት ልጇን የወለደችን እናት ጠይቅ። የአንድ ሳምንትን ዋጋ ማወቅ ከፈለክ በቴክኒክ ችግር ምክንያት ጋዜጣውን ያላሳተመ ድርጅትን ጠይቅ። የአንድ ሰአትን ዋጋ ማወቅ ከፈለክ ፍቅር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ጠይቅ። የ1 ደቂቃን ዋጋ ማወቅ ከፈለክ ባስ ያመለጠውን ሰው ጠይቅ።
በዚህም የጊዜ ጥቅምን መረዳት እንችላለን..

ከመፅሀፍ የተወሰደ
20🍓4💯1
ስም አልተራም😭
🤣29🤔4❤‍🔥2
2000090436955081
ይደመጥ 💔
💔14
ሁሌም በጣም ከሚገርሙኝ የቁርዓን ምዕራፎች መካከል አንደኛው (ሱረቱል አዲያት) ነው። አላህ እዚህ ሱራ ላይ እንዲህ ብሎ በፈረሶች ይምላል...

                                                  وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحًا
                          
እያለከለኩ ሯጭ በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡

አላህ የማለው ዝም ብለው በቆሙ ፈረሶች አይደለም፤ በከፍተኛ ሩጫ ከመጋለባቸው የተነሳ ደረታቸው ተቃጥሎ ማለክለካቸው በደንብ እስኪሰማ ድረስ በሚተጉ ፈረሶች ነው።
                                              
فَالْمُورِيَاتِ قَدْحً
ሸኮናቸው እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤

ፍጥነታቸውና ጥንካሬያቸው እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ፣ ኮቴያቸው ከመሬት እና ከድንጋይ ጋር ሲጋጭ ብልጭታን ወይም እሳትን በሚፈጥሩ ፈረሶች...
                                                 
                                                          فَالْمُغِيرَاتِ صُبْحًا
                                  
በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤

​እነዚህ አላህ የማለባቸው ፈረሶች ለጨዋታ አይደለም እንደዛ በፍጥነት የሚሮጡት በጦርነት መካከል ውስጥ ሆነው ነው። ስለዚህ አደጋ ላይ መሆናቸውን ያውቃሉ።

                                                         فَأَثَرْنَ بِهِ نَقْعًا
                                   
  በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤

ከሩጫቸው ብዛት በቦታው ላይ አደገኛን አቧራ ቀስቅሰው ፈረሶቹ የሚተነፍሱት አየር እራሱ ከአቧራ ጋር የተቀላቀለ በሆኑ።

                                                  فَوَسَطْنَ بِهِ جَمْعًا                      
   በጠላት ክብ መካከል ገብተው በተጋፈጡት እምላለሁ፤

አደገኛ መሆኑን እያወቁ...ሞት መኖሩን እያዩ በጠላት ጦር መሃል ሰንጥቀው በሚገቡ ፈረሶች ይምላል። አላህ በነዚህ ፈረሶች ከማለ ብኋሏ ቀጣዩ አንቀፅ ላይ እንዲህ ይላል...

                                                    إِنّ
الْإِنسَانَ لِرَبِّهِ لَكَنُودٌ

                             ሰው ለጌታው በእርግጥም ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
¤
አላህ ከዚህ አንቀፅ በፊት ስለ ብርቱ ፈረሶችን ምሳሌ አድርጎ ከጠቀሰ ብኋላ፣ ለምንድነው ስለኛ ስለሰው ልጆች ባህሪ መናገር የፈለገው? ምክንያቱም የማለባቸው ፈረሶቹ ይሄንን ሁሉ መስእዋትነት የሚከፍሉት ለሚመግባቸው ለሚንከባከባቸው አሳዳሪያቸው ነው። ለዛ ውለታም ያላቸውን ታማኝነት ያለ ፍርሃት ሞትን እስከመጋፈጥ ድረስ በመሄድ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ። የሰው ልጅ ግን በእርሱ ላይ ያለውን የአላህን ፀጋ ይረሳል።
በአጠቃላይ ይህ ሱራ በሁለት ተቃራኒ የታማኝነት አይነቶች ላይ እንድናሰላስል ያደርገናል። በአንድ በኩል ለጥቂት ምግብና እንክብካቤ ሲል እስትንፋሱ እስኪቆራረጥ ድረስ የሚሮጥ፣ ኮቴው እሳት እስኪያወጣ የሚጋልብና ወደ ጦርነት መሃል ሰንጥቆ በመግባት ለአሳዳሪው ያለውን ታማኝነት በተግባር የሚያሳይ "ፈረስን" እናያለን። ​በሌላ በኩል ደግሞ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን መለኮታዊ ጸጋዎች እየተመገበ፣ ነገር ግን ለፈጣሪው ምስጋና ቢስ ስለሆነው "የሰው ልጅን" እናገኛለን።

በመልካም መንገድ ወደ አላህ የምንመለስ እና ካመሰጋኝ ባሮቹም የምንሆን ያድርገን። አሚን!
30
<<.....ድከመቴን የማታጎላብኝ፤ መውደዷ የማይወላውል፣ እንደምወዳት ማስረጃ የማታስስ፣ ተዝረክርኬ ዝንጥ እንዳልኩ የምታሰማኝ፤ ሕመሜ የሚያማት፤ ስኬቴ ከሁሉ በላይ የሚያስፈነድቃት፣ ነገሬን ሁሉ ጉዳዬ ነው የምትል፤ እንደምወደድ እስትንፋሴ ዓለም ላይ ካረፈ ጀምሮ እያሳየች የመሰከረችልኝ።

እምወደድ እንደሆንኩ ልቤ ላይ ያሰረጸችልኝ፤ መወደድን የሚያክል ምንም በረከት እንደሌለ በምርቃት እና በዱዐዋ ያሰማችኝ።
¤
ጥንካሬዋን ፈተና የማይበግረው፤ በደል ሆነ መከፋት የማይሽረሽረው ትሕትና የተላበሰች፣ በየቀኑ ስለልጇ ከአምላኳ ጋ የምታወራ አመስጋኝ፣ ስጉ ፍጥረት ናት።
¤
እስክንጠግብ የማይርባት፤ አሟት በድካም የምታሳብብ፤ እየረገመችን የምትጸልይልን፣ አንደበቷ ከእውነቷ ጋ የማይገጣጠም ድብቅ ፍጡር ናት።

ፍላጎቷን አሽሻ፣ የምትፈልገውን አጣጥላ ለምንወድው ነገር ፍላጎቷን የሰዋች፣ስኬታችን ከኛ በላይ የናፈቃት፥ ለልጆቿ ቸር፣ ለራሷ ስስታም ናት።
እናት🖤
26🥰9
መች ነው ግን ቀን በሄደ ቁጥር ወደሞት መቅረባችን ሚገባን😢
በተቃራኒውኮ ከሞት እየራቅን ነው ሚመስለው ስራችን በሙሉ
😢363
من جد وجد ومن زرع حصد



حَسْبِيَ اللَّهُ لَآ إِلَهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ

አዝካር እንዳይረሳ 🙌
14
ውሸታም መሆኔን እወቁልኝ ሰውን በሐሰት ስወነጅል ነበር እኔ ሚመስለኝ cool የሆንኩ ነበር ለካ ፋራ ነኝ
🤣15🏆4🤷‍♀3🤝1