ሀሁ ቲዩብ Hahu Tube
69 subscribers
8 photos
5 links
#ታሪክ
#ወግ
#ባሕል
#ወቅታዊ ነገሮች
#በሁሉም _ቻናላችን_ይዳሰሳሉ

👉 ቴልግራም ቻናላችን
https://t.me/Hahu_Tube

👉 ፌስቡክ ገፃችን
fb.me/hahutube.ethiopia

👉 ዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/channel/UCMwvnofSCxwxSwB54RrdWdw
Download Telegram
Channel photo updated
ጠቃሚ ምክር ለእርስዎ!

ይሄን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት እንደ ማንበብ ነው!
🔺በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

🔺ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።

🔺የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።

🔺ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።

🔺የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።

🔺ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።

🔺ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።

🔺ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።

🔺እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።

🔺ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።

🔺በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።

🔺የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።

🔺ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!

🔺መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።

🔺ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።

🔺ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።

🔺ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።

🔺ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

🔺የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !!

🔺ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

🔺ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ
አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።

🔺እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

🔺የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

🔺 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

🔺 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ?

👉 ቴልግራም ቻናላችን
https://t.me/Hahu_Tube

👉 ፌስቡክ ገፃችን
fb.me/hahutube.ethiopia

👉 ዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/channel/UCMwvnofSCxwxSwB54RrdWdw
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/Hahu_Tube
አዲስ ነገር በቅርብ ቀን
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡- ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡- ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/Hahu_Tube
ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/Hahu_Tube
ዜጎቻቸው ቆንጆ የሆኑ የ50 ሀገራት ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን፤
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተቀምጣለች

የዓለማችን 50 የቆንጆዎች ሀገር ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መረጃን በመጠቀም ይፋ የሆነው የዓለማችን የውበት ደረጃ ሕንድን በቀዳሚነት አስቀምጧል።

አማላይነት፣ ውብ፣ ለአይን ማራኪነት እና አካላዊ ቁንጅናን በዋነኛ መስፈርትነት እንደተጠቀሙ ሜይል ኦንላየን ዘግቧል።

ይህ ቴክኖሎጂ የሁለቱንም ጾታዎች ለውበት ማወዳደሪያነት የተጠቀመ ሲሆን ደረጃውን ለማውጣትም አማካይ ነጥብ ወጥቶላቸዋል ተብሏል።

በዚህ መስፈርት መሰረትም ሕንድን በዓለማችን የውበት ደረጃ በአንደኝነት ሲያስቀምጥ
አሜሪካን በሁለተኝነት
ስዊድንን በሶስተኝነት አስቀምጧል።
ጃፓንን አራተኛ
ካናዳን አምስተኛ
ብራዚል ስድስተኛ፣
ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ዩክሬን እና ዴንሜርክ እስከ 10ኛ ድረስ ያሉትን ደረጃዎች እንደያዙ ተገልጿል።

ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችው ኢትዮጵያ በቁንጅና ከዓለም በ32ኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጥ ሌላኛዋ አፍሪካዊ ሀገር ግብጽን ደግሞ በ44ኛ
ደረጃ ላይ ማስቀመጡን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

ጾታዎችን ነጣጥሎ በተሰጠው ደረጃ መሰረትም በሴቶች ውበት ሕንድ፣ ጃፓን እና ስዊድን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያሉ ደረጃዎችን ይዘዋል።

በወንዶች አማላይነት ደግሞ የብሪታንያ ወንዶችን በቀዳሚነት ሲያስቀምጥ ሕንድ በሁለተኝነት እንዲሁም ጣልያንን በሶስተኝነት አስቀምጧል።

ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/Hahu_Tube
በረዶ በአዲስ አበባ
#በፖሊስ_እየተፈለገ_ነው !!

ስሙ ሞጣ ቀራኒዩ ወይም ማማሩ ይባላል
አይደለም ሄቨን እናቷም ትደፈር ሲል በህፃናት ሞት #ተሳልቆ ነበር
ቤቱን ለቆ ስልኩን ዘግቶ ተደብቆ ይገኛል
ከአሜሪካ ህግ ማምለጥ የለም የእጁን ያገኛል

ሚስቱም ተጨንቃለች
___ትዕግስት ሃብተወልድ የሞጣ ሚስት ክሱ ላይ ሚስቱም በተባባሪ ተከሳለች ወጥታ በይፋ መናገር አለባት::
ሞጣ የተባለ ነውረኛ አሁን ቲክቶኩ ላይ ያሉትን ቪዲዮዎች በሙሉ አጥፍቷል::

እኛ ግን video አውርደነዋል ስራችን ቲክቶኩን ማዘጋት ሳይሆን እሱን በህግ የበላይነት አፉን ማዘጋት ነው:: አይቀርም!

ፍትህ ለህፃናት
ፍትህ ለሄቨን