📚አስደናቂ ታሪኮች በጳውሎስ📚
112 subscribers
247 photos
8 videos
8 files
160 links
Download Telegram
የሰው ልጅ ሌላውን እውቀት ሁሉ ሲማር ሰው ለመሆን ግን አንዳች የተማረው ነገር የለም። ይሁንና ሰው መሆናቸውን በማወቃቸው ደግሞ ሰዎች ለራሳቸው በሚፈጥሩት ኩራት አንዳች ስኬትን አላተረፉም። ነገር ግን ሰዎች በማወቃቸው ሊኮሩበት የሚገባ አንድ ነገር ቢኖር ሳይማሩት ያወቁትን ሰው የመሆን እውቀት ነው።
ብሌይዝ ፓስካል
2,4.7
በታላቁ ፀሀፊ Eckohert Tolle ''The Power of Now'' በሚለው መፃህፉ ላይ አብርሆትን ሲገልፅ እንዲህ ሲል ይነበባል።
Enlightenment is not only the end of suffering and of continuous conflict within and with out, But also the end of the dreadful enslavement to incessant thinking. በእኔ ግርድፍ ትርጉም እንዲህ ማለቱ ነው።
አብርሆት ወይም መንቃት(መገለጥ) ማለት የስቃይ ማብቂያና ከራስና ከውጭ ጋር ያለውን የማያቋርጥ ግጭት መቋጫ ብቻ አይደለም። መንቃት ወይም አብርሆት ከሚያስጠላ ባርነት ወደ ማያቋርጥ አሳቢነት እድገት ነው።
የሰው ልጅ ከእስር ተፈትቶ ነፃ ሆኖ ባያውቅም፤ እስራቱን ሲፈራ ይኖራል። የማሰሪያችን ገመድ ይርዘም ወይም ይጠር፤ ይጠበቅ ወይም ይላላ ይሆናል እንጂ ሁላችንም እስረኞች ነን። በባህል ታስረናል፤ በእምነት ታስረናል፤ በወግና ዕሴት ስም ታስረናል፤ በልምድና በድግግሞሽ እውነት በመሰለን ባልተፈተሸ እውቀት ታስረናል፤ ግዑዝ ገንዘብን በማምለክ ታስረናል፤ ተንኮልና ክፋትን በማሰብ ታስረናል፤ ምቀኝነት እውነት እንዳናይ አስሮናል፤ ዘረኝነትና ግለኝነት በእውነታ በሌለ የቅዠት ከፍታ ላይ ሰቅሎ በትምክህተኝነት አስሮናል፤ ራስ ወዳድነት ፍቅር የሌለበት ባዶነት ውስጥ አስሮናል። ከዚህ በላይ እስርን በመፍራት የውሸት ካባ ውስጥ ታስረናል።
ዓፄ ቴዎድሮስ

ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ (ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፮ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.)[1] ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ።

ቴዎድሮስ ጥር ፮ ቀን ፲፰፻፲፩ ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን ተዳሩ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በኒህ ተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ፫ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሥ ካሳ - ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ።
ሥርዓተ ንግሡ የዘመነ መሳፍንት መቃብር በመሆን የዘመናዊ ኢትዮጵያን ታሪክ "ሀ" በማለት ጀመረ። ዓፄ ኃይለ ስላሴ እስከ ፈጸሙት ድረስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ሥራም በዚሁ ወቅት ተጀመረ። ዓፄ ቴዎድሮስ ሰሜናዊ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አንድ ለማድረግ የሞከሩት፣ አጠቃላይ በታሪክ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ክፍል ነበር - ለዚህም ዋቢ ወደ ወሎና ወደ ሸዋ ያደረጓቸው ዘመቻወች ይጠቀሳሉ።

በዘመነ ንግሣቸው ዓፄ ቴዎድሮስ አገሪቱን የሚያሻሽሉ ሥርዓቶችን ለአገራቸው አስተዋውቀዋል። ከነዚህም ውስጥ፡ ባርነትን የሚያግድ አዋጅ፣ የመጀመሪያው መንገድ ግንባታ፣ የሥርዓተ ንዋይና የፖለቲካ ሥርዓቱን በማዕከላዊ መንገድ ማዋቀር፣ የባላባት የተከፋፈለ "ሁሉ-በሁሉ-ጦርነት ሥርዓት"ን በማስቀረት ብሔራዊ ውትድርናን ማስተዋወቅ ይጠቀሳሉ። በዘመነ መሳፍንት እንደልባቸው ይፈልጡ ይቆርጡ በነበሩ ባላባቶች ዘንድ እኒህ ለውጦች እጅግ የተጠሉ ሆኑ። በ፲፰፻፶ ዓ.ም. ብዙወቹ ባላባቶች አመጽ ማነሳሳት ጀመሩ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርስት የነበረውን መሬት ለገበሬወች በማከፋፈላቸው ከሃይማኖት መሪወች ጋር ተጣሉ። ይህን ተከተሎ በየቦታው አመጽ በሚነሳበት መካከል አውሮፓውያን ሚሲዮኖችም ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተነሳሳ አለመግባባት ምክንያት በዓፄው ታሰሩ።
በመጋቢት ወር ፲፰፻፷ ዓ.ም ላይ የእንግሊዝ መንግሥት በሮበርት ናፒየር የሚመራ፣ በጊዜው እጅግ ግዙፍ የተባለ ኃይልን አሰናድቶ አውሮፓውያን እስረኞችን ለማስፈታት ጦር ላከ። መጋቢት ፭ ቀን ፲፰፻፷ ዓ.ም ይህ ጦር በመቅደላ ምሽግ ላይ በሚገኘው፣ በአመጽ በተዳከመ የንጉሱ ጦር ላይ ጥቃት አደረሰ። በውጊያው መሃል ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁ እስከመጨረሻው አሻፈረኝ በማለት በሽጉጣቸው እራሳቸውን ገድለው በጀግንነት አለፉ። ዓፄ ቴዎድሮስ ያሰቡትን ለውጦች በሙሉ በተግባር ቢፈጽሙ ኖሮ በእርግጥም ታላቅና የሰለጠነ ሀገር መሪ ሊሆኑ ይችሉ እንደነበር ታሪክ ተመራማሪወች ይስማማሉ። ዕቅዳቸው በዚህ መልኩ ቢሰናከልም፣ እጅግ ድንቅ መሪ፣ የተዋጣላቸው ወታደርና የተባበረች ዘመናዊ አገር ራዕይ አብሳሪ እንደነበሩ ያሰሯቸው አውሮጳውያን ሳይቀር ሳይመሰክሩ አላለፉም።

የዙፋን ስማቸው «ቴዎድሮስ»ን የወሰዱት ከፍካሬ ኢየሱስ ከተገኘ ትንቢት ነበረ። በዚያው ትንቢት በኩል፣ በዓለም መጨረሻው ክፍለ ዘመን፣ ተወዳጁ፣ የጥንቱ ዘመን ንጉስ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ተነስቶ አገሪቱን ለ፵ ዓመታት ይገዛል የሚል ነበር። "ቴዎድሮስ" የሚለው ስም ከግሪክ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም «ጤዎስ ዶሮስ»፣ 'የአምላክ ስጦታ' ማለት ነው።
የግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን

ďżź

በ ፳ኛው ምእት ሁለተኛው ሩብ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያን ከልጅ ኢያሱ በኋላ መምራት ጀመሩ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ሕብረት መቋቋም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

የኢትዮጵያ ነጻነት በጣልያን ወረራ ከ ፲፱፻፴፮ (1936) እስከ ፲፱፻፵፩ (1941) እ. ኤ. አ. ድረስ ቢጠቃም በጀግኖችዋ መከታ ተጠብቋል። በአዚህ ጥቃት ጊዜ ዓፄ ኃይለሥላሴ በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ. ኤ. አ. በሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) ፊት የሚታወስ ንግግር በአማርኛ አደረጉ። ይህ ንግግር በዓለም ታዋቂ አደረጋቸው። እንዲሁም በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ.ኤ.አ. በ ታይም (Time) መጽሄት «የዓመቱ ሰው» አስባላቸው። ጣልያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መሳተፍ ስትጀምር ፣ እንግሊዝ ከኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ጋር ኢትዮጵያን ነጻ አወጣች። ግን እስከ ፲፱፻፵፫ (1943) እ. ኤ. አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር። በ ፲፱፻፵፪ (1942) እ. ኤ. አ. ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባርነት እንደ ተከለከለ አወጁ።

ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ጀግና ሆነው ቢታዩም ፣ የ ፲፱፻፸፫ (1973) እ.ኤ.አ. ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ፣ የምግብ ዕጥረትና የድንበር ጦርነቶች ተቃውሞ አስነሱ። ከዚያም በ ፲፱፻፸፬ (1974) እ. ኤ. አ. በሶቪየት ሕብረት የተደገፈውና በመንግስቱ ኃይለ ማርያም የተመራው ደርግ (ደርግ ማለት ኮሚቴ ማለት ነው) ዓፄ ኃይለ ሥላሴን ከስልጣን አስወረደ።
ዞስካለስ የተባለው የአክሱም መሪ ኔሮን ቄሳር በነገሰበት ዘመን(ከ ፶፬ እስከ ፷፷ ዓ.ም በ 1 ኛው ክ/ዘ ነው። ዞስካለስ የመጀመሪያው ታሪክ የሚያውቀው (ታሪክ ከ primary source አንፃር) ኢትዮጲያዊ መሪ የነበረ ሲሆን ነጋዴው ዞስካለስ በሚል ስሙ ይታወቃል። ይህ ንጉስ ግዛቱ እስከ በርባሪ (በርበራ) የሚደርስ ሲሆን የግሪክ ቋንቋን ደህና አድርጎ የሚናገር ፤ የግሪክን ስልጣኔ በአባሩ ያስገባ ገንዘብ በጣም የሚወድ ንጉስ እንደነበር 'ፔርፕል ዳማትሬ ኤርትሬ (ትርጒሜው የኤርትራ ባህር ዙሪያ) በሚል አርዕስት ሮማውያን የተውት ፅሁፍ ያትታል።
በቀጣይ... ኢትዮጲያ እስካሁን ያየችው ስርዓተ መንግስት (dynasty/ Empire) የሚያትት ፅሁፍ እንደምለጥፍ ቃል በመግባት ልሰናበት። ቸር ጊዜ ተመኘሁ።
2,4.7
ለበለጠ ኢትዮጲያዊ የታሪክ ፅሁፎችን ለማግኘት ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ በመንካት ተቀላቀሉ።
@ytopnhistory
አዲስ ፡ አበባ (ወይም ባጭሩ «አዲስ») ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ (1879) ፡ ዓ.ም. ፡ ፍልውሃ ፡ ፊን-ፊን ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተ ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ፡ ዋና ፡ ከተማ ፡ ስትሆን ፡ በተጨማሪ ፡ የአፍሪካ ፡ ሕብረት ፡ መቀመጫ ፡ እንዲሁም ፡ የብዙ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅት ፡ ቅርንጫፎችና ፡ ሌሎችም ፡ የዓለም ፡ የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ፡ ልዑካን ፡ መሰብሰቢያ ፡ ከተማ ፡ ናት። ራስ-ገዝ ፡ አስተዳደር ፡ ስላላት ፡ የከተማና ፡ የክልል ፡ ማዕረግ ፡ ይዛ ፡ ትገኛለች። አብዛኞቹን ፡ የሀገሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ የሚናገሩ ፡ ክርስቲያኖች ፡ እና ፡ ሙስሊሞች ፡ የሚኖሩባት ፡ ከተማ ፡ ናት። ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በ2500 ፡ ሜትር ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ የምትገኘው ፡ ከተማ ፡ በግምት ፡ 2,757,729 ፡ በላይ ፡ ሕዝብ ፡ የሚኖርባት ፡ በመሆኗ ፡ የሀገሪቱ ፡ አንደኛ ፡ ትልቅ ፡ ከተማ ፡ ናት።

ከተማዋ ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ በመረጡት ፡ ቦታ ፡ ማለትም ፡ በፍል ፡ ውሐ ፡ አካባቢ ፡ ላይ ፡ በባላቸው ፡ በዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ፡ ተቆረቆረች። የሕዝቧ ፡ ብዛት ፡ በያመቱ ፡ 8% (ስምንት ፡ በመቶ) ፡ እየጨመረ ፡ አሁን ፡ አራት ፡ ሚሊዮን ፡ እንደሚደርስ ፡ ይገመታል።

ከእንጦጦ ፡ ጋራ ፡ ግርጌ ፡ ያለችው ፡ መዲና ፡ የአዲስ ፡ አበባ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ መገኛ ፡ ሆናለች። ይህም ፡ በመስራቹ ፡ የቀድሞው ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ ስም ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ ይባል ፡ ነበር።
እያንዲንዱ ቀን ትንሽ ህይወት ነው፣ ከእያንዲንዱ ቀን ጀርባ አዲስ ህይወት አለ፣ እያንዲንዷ ጠዋት ትንሽ ወጣት ናት፣ እያንዲንዷ የሌሊት እንቅልፍ ትንሽ መሞት ናት፡፡

አርተር ሻፕንሃር
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 28 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.