Hawassa University
25.3K subscribers
8.74K photos
34 videos
150 files
725 links
One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.
Download Telegram
የነገ መሪዎችን ማበርታትና ማንቃት ላይ ያተኮረ መርሃግብር በሀዋሳ ታቦር ከ/ሁ/ደ/ት/ቤት ተካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በEUPE (Enabling university peace education) ፕሮጀክት ስር "የነገ መሪዎችን ማበርታት፤ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት" እና "ሰላም የእድገት ሁሉ ስር ነው።" በሚል መሪ ቃል ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ለታቦር ከ/ሁ/ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የማህበራዊ ምግባር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የገቨርናንስና ልማት ጥናት ት/ቤት ኃላፊ የሆኑትና በእለቱ ስልጠናውን የሰጡት መ/ር ዳኜ ጥላሁን ቀደም ሲል መሰል ስልጠናዎች በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ብቻ ተገድበው የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረቱን ከታች ባሉ የትምህርት እርከኖች ላይ ወደሚገኙ ተማሪዎች እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለሰላም መረጋገጥ ኃላፊነት የሌለበት አንድም አካል አለመኖሩን የገለጹት አሰልጣኙ የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት ተማሪዎች ላይ የሚሰራው ስራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የሁለተኛ አመት የህግ ተማሪ የሆነችው የፕሮግራሙ አስተባባሪ ትምህርት ሽብሩ ስለሰላም አስፈላጊነትና አይተኬነት በመረዳት ስልጠናው ከትምህርት ቤቱ ለተወጣጡ 50 ተማሪዎች መዘጋጀቱን ተናግራለች። ሀገር የእያንዳንዱ ትውልድ አሻራ ውጤት መሆኗን ያነሳችው ተማሪ ትምህርት የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለችና ሰላሟ የተጠበቀ ሆና ማየት የምንሻ ከሆነ በመጪው ትውልድ ላይ ያለመታከት ልንሰራ ይገባል ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች።

በት/ቤቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ወራሽ ባሽላ እንዲሁ ስልጠናው ስለሰላም የነበረውን ግንዛቤ ያሻሻለ መሆኑን ገልጾ በቀጣይም የሰላም አምባሳደር በመሆን የተካፈለውን እውቀት ለጓደኞቹ በማጋራት በት/ቤቱ ግቢና በአካባቢው ተጽዕኖ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግሯል።
ሀዩ በሲዳማ ክልል መልጋ ወረዳ ለተደራጁ የወጣት ማህበራት የተሻሻለ ዝርያ የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩት ድጋፍ አደረገ።
*//***
ግንቦት 30/2016
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሲዳማ ክልል መልጋ ወረዳ ለተደራጁ የወጣት ማህበራት 1,200 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩቶች አቅርቦ ያስጀመረውን ሥራ ያለበትን ሁኔታ ለባለድርሻ አካላት አስጎበኘ::

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ መንደሮች አንዱ በሆነው መልጋ ወረዳ ወጅግራ ከተማ ያለውን የተቀናጀ የዶሮ እርባታ ስራ ለባለድርሻ አካላት ለማስጎብኘት ዛሬ በተካሄደው የመስክ ውይይት የወረዳውና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የመልጋ ወረዳ አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሳሙኤል ኩሌሎ ወረዳው በአንድ ኢንተርፕራይዝ አምስት ወጣቶችን ካደራጀ በኃላ የሀዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስልጠና በመስጠት: የአንድ ቀን ጫጩቶችን ለአርባ ቀናት አርብተው ለህብረተሰቡ ገበያ እንዲያቀርቡ ለማስቻል ማህበራቱን ወደስራ ማስገባቱን ገልጸው የዶሮ ጫጩትና የመኖ ድጋፍ እንዲሁም ያልተቋረጠ ሙያዊ ድግፍ በማድረግ ውጤታማ ሥራ መስራቱን አመስግነዋል:: ከዚህ በፊት ተሞክሮ ያልተቻለውን በማስቻሉ ዩኒቨርሲቲው ትልቅ የስኬት መንገድ እንዳሳየ የገለፁት አስተዳዳሪው በቀጣይነትም በትብብር የመስራት ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ዩኒቨርሲቲው የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ ገልፀው በራሱ የግብርና ኮሌጅ በኩል የተፈለፈሉትን የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የአንድ ቀን ጫጩቶች ለተለያዩ ማህበራት የሚያደርገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉም
ባለድርሻ አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል:: "እኛ የምንሰጠው የመነሻ ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረው የማስፋፊያ ሥራውን ከክልሉ እና ከወጣቶች ይጠበቃል እንጂ ወጪና ገቢውን በእውቀት እያስተዳደሩ መቀጠል ካልቻሉ ውጤት አይኖርም" ያሉት ዶ/ር አያኖ ለስራ አጥ ወጣቶች ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው ያለውን አቅም በአግባቡ ተጠቅሞ የአንድ ቀን ጫጩት ማቅረብ ላይ ለክልሉ ጭምር ለማድረስ ጠንክሮ ይሰራል ብለዋል::

የምርምርና ቴክ/ሽ/ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በበኩላቸው ሀዩ በተመረጡ ጭብጥ ተኮር ዘርፎች ማለትም በሰብል ልማት፣ እንስሳት እርባታ፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ትምህርት እና ስነ-ምግብ ዘርፎች በርካታ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በወረዳው የሚገኙ ወጣቶች በዶሮ እርባታ ዘርፍ ተደራጅተው ለመስራት ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በወረዳው የስራ እድል ፈጠራ ቢሮ የአንድ ቀን ጫጩትና የዶሮ መኖ ድጋፍ እንድናደርግ በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ሙያዊ ስልጠና ጨምረን ድጋፍ በማድረጋችን የአካባቢውን አየር ንብረት መቋቋም የሚችሉ 1,200 የዶሮ ዝርያ ጫጩቶችን በራሳችን ባለሙያዎችና መፈልፈያ ማሽን አምርተን ለውጤት በቅተናል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር አደገ አየለ የዶሮ እርባታ ዘርፉ በርካታ ወጣቶችን በአንድ ጊዜ በማሳተፍ የስራ እድል ፈጠራን የሚጨምር ከመሆኑ ባሻገር የህብረተሰቡን የአመጋገብ ሁኔታ ከማሻሻል አንጻር ውጤታማ ሆኖ መገኘቱን ገልጸዋል። ቢሮው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲና በወረዳዎች መካከል እየተደረገ ያለው ጠንካራ የትብብር ስራ እንደ ሀገር ትኩረት የተሰጠው የሌማት ትሩፋት ዕቅድን ለማሳካት የሚያስችል ሰፊ ዕድል እየፈጠረ እንዳለ ይገነዘባል ሲሉ ኃላፊው አክለዋል።

በማህበር የተደራጁት ወጣቶች ስለተደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያመሰገኑ ሲሆን በስራቸው ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል:: በውይይቱ ማጠቃለያ በብዛት እንደ ከባድ ተግዳሮት የሚነሳው የዶሮ መኖ ጥያቄ የሚመለስበትን መንገድ እንደሀገር እና እንደምርምር ተቋም ጠንክረን መፍትሄ ልናበጅለት ይገባል ሲሉ ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ለሁሉም ባለድርሻ አሳስበዋል::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
His Excellency Ambassador Dr. Markos Tekle gives Public lecture at HU
*//*
June 8/2024
College of Law and Governance in collaboration with office of Vice President for Research &Technology Transfer, HU, organized a public lecture by his Excellency Amb. Dr. Markos Tekle Rike, Deputy Head of Mission at the Ethiopian Embassy in Juba, South Sudan, on the theme, "Grand strategy in the changing world: Analyzing the Complexities and Adaptations in Modern Geopolitics", on June 7, 2024 at AU Hall.

Dr. Emebet Bekele, Director General at OERC of HU, briefly presented a short biography of the ambassador where she mentioned that he served as Ethiopian Ambassador to Japan and Egypt. He also served as State Minister for Ministry of Foreign Affairs and as Executive Director of the Foreign Service Training Institute. Dr. Markos also worked as a Lecturer and Dean of the College of Social Sciences at Hawassa University before joining the foreign service.
In his lecture, Dr. Markos broadly explained the historical development and role of 'Grand Strategy' in the comprehensive national planning indicating its importance and prospects for Ethiopia to design and implement successful grand strategy. He also boldly indicated the overall influence of grand strategy in the changing global structure, technological advancement, environmental and nontraditional influences and cultural and ideological influences. In addition he has indicated the determining force of grand strategy on military, economic, diplomatic, information, domestic and foreign policy strategies at large.

Hawassa University
Ever to Excel!

Our Social Media Platforms:
***
Website: https://www.hu.edu.et
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa