የልቦና ውቅር (ማይንድሴት) ትምህርት አስፈላጊነትና ምንነት ላይ ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን ስልጠና እየተሰጠ ነው
----------------------------------------
ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን ከደቡብ ኮርያ በመጡ አስልጣኞች የማይንድሴት ትምህርት አስፈላጊነትና ምንነት ላይ ስልጠና እንዲሁም በደቡብ ኮሪያ የአዲስ መንደር ግንባታ ንቅናቄ ላይ የተመሰረተ የልምድ ልውውጥ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም እየተካሄደ ነው::
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ ሲናገሩ በማይንድሴት ትምህርት አስፈላጊነት ላይ እንዲሁም ደቡብ ኮሪያዎች በለውጥ ላይ ያላቸውን ልምድ ሊያካፍሉን በሀገሪቱ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች እኛን መርጠው በመምጣታቸው እጅግ እናመሰግናለን ብለዋል:: ፕሬዚደንቱ እንግዶቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ ተሳታፊዎችም ካገኘነው ትምህርትና ተሞክሮ በመነሳት እራሳችንና ተቋማችንን ለመጥቀም መጣር ይኖርብናል በማለት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን አመሰራረትና የእድገት ጉዞ አጭር ገለፃ አቅርበዋል፡፡

የስልጠና ቡድኑን ይዘው የመጡት የመንግስት አማካሪ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በመክፈቻው ላይ እንደተናገሩት በዛሬው ዕለት እዚህ የተገኙበት ዋናው ምክንያት "እኛ በ1950 እና 60ዎቹ አካባቢ የነፍስ ወከፍ ገቢያችን ከደቡብ ኮሪያ የሚበልጥ የነበርን ወደ ኋላ ቀርተን ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ውስጥ ደቡብ ኮሪያዎች አድገው ኢኮኖሚያቸው ዓለምን እንዲመራ እንዴት ቻለ? እኛንስ ምን ጎተተን? ምንድነው የጎደለን? ማነው ይሄንን የለውጥ አስተሳሰብስ የሚወስደው?" የሚለውን ለመማማርና ልምድ ለመቅስም ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በዚህ ትምህርት የተነቃቃና ከራሱ አልፎም ወደ ሌላው የሚያሰርፅ መሆን እንዳለበት ጠቅሰዋል:: አምባሳደሩ አክለውም ይህ የማይንድሴት ሃሳብ አንደኛ ተቋማዊ እንዲሆን በሁለተኛነትም አለም አቀፋዊ ሆኖ ተደራሽ እንዲሆን ነው የምንፈልገው በማለት ሃሳቡም ከራሳችን አልፎ በተቋማችን እና በትውልዳችን ሰርፆ የመጪው ዘመን ትውልድ የሚቀየርበት እንዲሆን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር ዶ/ር ቾይ ኦይ ቹል ይሄንን ስልጠናና ልምድ ልውውጥ በዋናነት በዩኒቨርሲቲያችሁ ለመስጠት የተገኘነው በዩኒቨርሲቲው ያለው የሰው ኃይል ያለው ተነሳሽነት ሃሳቡን ከመቀበል ባሻገር ለሌሎችም ለማስረፅ ተነሳሽነት ያላችሁ በመሆናችሁ ሲሆን የእናንተ አያት ቅድመ አያቶቻችሁም ከሰሜን ኮሪያ ጋር በነበረን የእርስ በእርስ ጦርነት 6037 የክቡር ዘበኛ ዘማቾችን ልካችሁልን ጀግንነታችሁን አሳይታችሁናልና እናመሰግናችኃለን በማለት ለእድገት ፀር የሆነውን የእርስ በርስ ግጭቶችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ እና ያሏችሁ ሃብቶች ላይ ማተኮር አለባችሁ ሲሉ ለተሳታፊዎች ደቡብ ኮሪያ ከነበረችበት ድህነት አሁን ወዳለችበት ብልፅግና እንደደረሰች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በቀጣይም በቀረበው ትምህርት ላይ ውይይት ከተካሄደ በኃላ በከሰዓት በሚኖረው ፕሮግራም በደቡብ ኮሪያ የአዲስ መንደር ግንባታ እንቅስቃሴ ላይ የልምድ ልውውጥ ተደርጎ ጥያቄና አስተያየት ተቀብለው እያብራሩ ነው፡፡

ንግሥት ፉራ ዘመኗን የዋጀች ንግሥት… ለተጨማሪ መረጃ…https://mylibrarianship.wordpress.com/2022/08/22/amazing-some-people-around-the-city-are-yet-to-know-about-furra-sumuda-etc-better-to-know-latter-than-never/
21st Century Library & Information Science Network
ንግሥት ፉራ ዘመኗን የዋጀች ንግሥት
In April, ETV journalist visited us with a view to do a documentary based on Queen Furra. The final programme was aired this week. Amazing some people around the city are yet to know about Furra, S…
NASA Engineer Develops Tiny, High-Powered Laser to Find Water on the Moon...See more...https://mylibrarianship.wordpress.com/2022/08/24/nasa-engineer-develops-tiny-high-powered-laser-to-find-water-on-the-moon/
21st Century Library & Information Technology Network
NASA Engineer Develops Tiny, High-Powered Laser to Find Water on the Moon
Berhanu Bulcha shows off his terahertz laser technology in his lab at NASA’s Goddard Space Flight Center in Greenbelt, Md. Credits: NASA/Michael Giunto Finding water on the Moon could be easier wit…
መሞት አይቀርም መልካም ስራና ዝና ግን አብሮ አይቀበርም፡፡
*********************
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሐኪምና መምህር ለነበሩት እና በነሃሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በድንገት ህይወታቸው ያለፈውን ዶ/ር ሙሉቀን ታምራትን ለማሰብ ኮሌጁ የደም ልገሳ፣ ችግኝ ተከላ እና የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓቶች ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ባልደረቦቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸው እና ተማሪዎቻቸው በተገኙበት አካሂዷል፡፡
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አንተነህ ጋዲሳ በፕሮግራሙ መክፈቻ ባልደረባችን ዶ/ር ሙሉቀን ታምራት በዩኒቨርሲቲያችን ከተማሪነት ጀምሮ በመምህርነት፣ በምርምር ስራዎችና ሰዎችን በፍቅር፣ በርህራሄና በትጋት በማከም በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ በኩላሊት ሕክምና በደቡብና ሲዳማ ክልሎች ብቸኛው ስፔሻሊስት በመሆኑ የሕክምና ሙያውን በብቃት ሲወጣ የነበረ በታካሚዎቹ፣ በተማሪዎቹ እና በእኛ ባልደረቦቹ የሚወደድ የነበረ ሲሆን በዶ/ር ሙሉቀን ድንገተኛ ሞት የተሰማን ሃዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለፅኩኝ በዛሬው ዕለት ይሄንን ፕሮግራም ስናዘጋጅ እሱን ለማመስገን እና ለመዘከር እንዲሁም ሁላችንም የእሱን አርአያ በመከተል በሙያችን የተሰጠንን አደራ በአግባቡ እንድወጣ አደራ ለማለትና እሱ የጀመራቸውን ውጥኖች አርአያውን ተከትለን ከዳር እንድናደርሳቸው የበኩላችንን እንድንወጣ ለማሳሰብ ነው ብለዋል፡፡

በሕ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ መምህርና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ክንዴ ውብሸት እንደገለፁት ዶ/ር ሙሉቀንን ከማስተማር አንስቶ ህይወቱ ድንገት እስካለፈችበት በባልደረባነት ለበርካታ ዓመታት የማውቀው ሲሆን ከጠቅላላ ሐኪምነት ተነስቶ በኩላሊት ሕክምና ስፔሻላይዝድ በማድረግ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይ በደቡብና ሲዳማ ክልሎችና ከአጎራባች ኦሮሚያ ክልል በበሽታው የሚሰቃዩ ታካሚዎችን ደከመኝና ሰለቸኝ ሳይል የሚያገለግል ታታሪ ሐኪም፣ በተማሪዎቹም የሚወደድ እና ባለብሩህ አእምሮ ተመራማሪና ዕሩቅ ሃሳቢ የነበረ ነገር ግን በአጭሩ የተቀጨ ባልደረባ መሆኑ ታውቋል፡፡ አክለውም እሱን በማጣችን ብናዝንም በዛሬው ፕሮግራም የእሱን አርአያ በመከተል የደም ልገሳ በማድረግ የበርካቶችን ሕይወት ለመታደግና እሱን በመዘከር ለሌሎች ባለሙያዎችናተተኪዎች አርአያነቱን ለማስረፅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሟች ዶ/ር ሙሉቀን አባት አቶ ታምራት ሎንሰቆ በበኩላቸው ልጄ በምድር ላይ የቆየባቸው ሰላሳ አምስት ዓመታት ጥቂት ቢሆኑም አንድ ሰው ኖረ የሚባለው ለሌሎች ሲተርፍ ነው የሚለውን መርሁ በማድረግ ለበርካቶች ከፈጣሪ በታች በሕክምና ሙያው ሲደርስላቸው፣ ተተኪዎቹን ሲያስተምር፣ ሲመራመር፣ ሙያውን ለማሳደግና ተደራሽ ለማድረግ ሲጥር መቆየቱን በመገንዘብ እሱን ለማሰብ የተማረበትና ያገለገለበት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕ/ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዚህን መሰል ፕሮግራም በማዘጋጀቱ ልባዊ ምስጋና እያቀረብኩኝ ደስታ በወርቅ ሽልማት ብቻ ሳይሆን በሞትም መኖሩን እና “መሞት አይቀርም መልካም ስራና ዝና አይቀበርም” የሚለውን በልጄ ተግባሮች አይቻለሁኝ ብለዋል፡፡ ባለቤቱ ወ/ሮ አይዳ ታደለም ይህ ፕሮግራም በእሱ ስም በመዘጋጀቱ እያመሰገንኩኝ በተለይ ስሙን ጠርተው ለማይጠግቡት ልጆቻችን አባታቸው በጣም ጥሩ፣ ምስጉንና ታታሪ እንደነበር የምናሳያቸው ሕያው ምስክርና ታሪክ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙም በተያዘለት ዕቅድ መሰራት የደም ልገሳ፣ ችግኝ ተከላ እና የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓቶች ተደርገው መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በ2014ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
----------------------------------
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም የኮሌጁ ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ግምገማና ውይይት አካሂዷል፡፡
የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ ሲናገሩ ኮሌጃችን ከመማር ማስተማር፣ ከምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በእውቀት፣ በአስተሳሰብና አመለካከት ላይ እየሰራና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም ግንዛቤ የመፍጠርና ማሳደግ፣ የተለያዩ ምሁራንን ከተለያዩ ቦታዎች በመጋበዝ ስለ ሰላም አስፈላጊነት፣ በጦርነቱ ወቅትም በተለይ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ወታደሮችና የጤና ባለሙያዎችን ከስነ-ልቦና ጋር በተያያዘ ስልጠና የመስጠት እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ እና በዜና አውታሮች የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችን እንዴት መለየትና መከላከል እንደሚቻል፣ የኮሌጃችን ምሁራንም በተለያዩ ሚዲያዎች በመጋበዝ ለማህበረሰቡ ሃሳቦችን በማካፈል እና በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ እንደ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም በርካታ ስራዎች ሲሰራ የቆየ ቢሆንም አፈፃፀማችንን በመፈተሽና ድክመቶቻችንን ነቅሰን በማውጣት በቀጣይ እንዳይደገሙ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ይኖርብናል ብለዋል፡፡ ዲኑ አክለውም በዚህ ውይይት ዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ እንደመለየቱ የዩኒቨርሲቲው አዲሱ የ2015 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ምን እንደሚመስል በመፈተሽ ኮሌጃችንም የራሱን ዕቅድ እንዴት ማዘጋጀት እንዳለበት፣ በ2015 ዓ.ም በሚጀመረው የመውጫ ፈተና አዘገጃጀት ላይ፣ በቀጣይ የ12 ክፍል ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ፈተና የሚወስዱ በመሆኑ ፈታኝ መምህራን፣ ለዓይነ-ስውራን አንባቢ እና ቆጣሪ መምህራንን ምልመላ

ማድረግ፣ አዳዲስ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከዩኒቨርሲቲው የመጡ ወይም የተሻሻሉ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ እና የ2015 ዓ.ም በጀትን በማሳወቅና አጠቃቀም ላይ በሰፊው ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
የፕላን እና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ የዩኒቨርሲቲው አዲሱን የ2015 ዓ.ም መሪ ዕቅድን ሲያቀርቡ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በተልዕኮ ልየታ መሰረት ከምርምር ዩኒቨርሲቲ አንዱ እንደመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እና መለኪያና መመዘኛዎቹንም በመዘርዘር አዲስ ዕቅድ የላከልን በመሆኑ ከዚያ በመነሳት አዲስ መሪ ዕቅድ መዘጋጀቱን እና የትኩረት አቅጣጫዎቹም ሳይሸራረፉ መወሰዳቸውን አብራርተው ኮሌጆችም ከዚህ በመነሳት ማቀድ እንዳለባቸው እንዲሁም ወደፊትም የዩኒቨርሲቲውም ሆነ የኮሌጆች አፈፃፀም የሚገመገመው በተቀመጡት መመዘኛዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በፕሮግራሙም በኮሌጁ ዲን የተነሱ ነጥቦች ላይ ግምገማና ውይይት ተደርጎባቸው በታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ላይ በተሳታፊዎች አስተያየት ተስጥቶባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የ2014ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሄደ፡፡
-------------------------------
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሂዷል፡፡ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በዕለቱ ውይይቱን ሲከፍቱ በኮሌጃችን በአካዳሚክ፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፍ በዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ሲሆን በዕቅዳችን ላይ ተቀምጠው ያላከናወንናቸውን ተግባራት እና ክፍተቶቻችንንም በመለየት በቀጣይ እንድተገብራቸው የዚህ መሰሉ ግምገማ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ዲኑ አክለውም በዚህ ዓመት በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን የመማር ማስተማሩንና የምርምር ስራዎቻችንን በስኬት የተከናወን በተለይ በትብብር የፕሮጀክት ስራዎች ስኬታማ ከመሆናቸው በላይ ከኖርዌይና ስውዲን መንግስታት በተገኘው ድጋፍ በታዳሽ ኃይል ላይና መሰረተ-ልማትን የማሟላት እንዲሁም ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ መደረጉን እና በፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ የተሻልን የነበር ቢሆንም በመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች የመዝለቅ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆንና ፕሮጀክቶችን ወደ በዘላቂነት እንዲቀጥሉ አለማድረግ ላይ ክፍተቶች ስላሉብን በቀጣይ የተማሪዎች ምደባ ላይ በመስራትና ዝቅተኛ ውጤት ላመጡትም ተጨማሪ የማስተማር ዕገዛ ለማድረግ እና ለመደገፍ እንዲሁም የተፈራረምንባቸውን የተብብር ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ማድረግ ላይ በርትተን እንሰራለን ብለዋል፡፡