Hawassa University
24.7K subscribers
8.67K photos
33 videos
129 files
716 links
One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.
Download Telegram
ፕሬዚደንቱ አክለውም የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር እንዲሁም በምርምር ስራ ስኬታማ ከሆኑ የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች አንዱ መሆኑንና በዘንድሮው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መውጫና የሙያ ፈቃድ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎቹ መካከል 99.5% ያህሉን ማሳለፉ ለዚህ ማሳያ ሆኖ መቅረብ ይችላል ብለዋል።

የኮሌጁ ቺፍ ኤክሴክዩቲቪ ዳይሬክተር ተ/ፕ/ር አለሙ ጣሚሶ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በኮምፕሪሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታሉ በዓመት ከ18 ሚሊዮን በላይ ለሚሆን የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገልግሎቶቹን በሰብ-ስፔሻሊቲ ዘርፍ በማስፋፋት የካንሰር ጨረር ህክምና፣ የፎረንሲክ እና ስነምረዛ አገልግሎቶችን ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የዛሬውን ምረቃ ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ከ60% በላይ የሚሆኑት የማዕረግ ተመራቂ መሆናቸው እና በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ተመራቂዎች ታሪክ ከፍተኛው ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ውጤት መሳካት የለፉ መምህራን፣ ባለሙያዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የኮሌጁና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ምስጋና እንደሚገባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያም ከየዲፖርትመንቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ ከፍተኛውን ዉጤት 3.95 ያስመዘገበችው ዶ/ር ሶስና ሸለመ የዓመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
You tube: www.youtube.com/@hawassauniversity7400
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
በሶላር ኢነርጂ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።
*//**
የካቲት 18/2016 ዓም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጁ በNORHED II-ReRED ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ በመታገዝ በሀዋሳ ከተማ የህጻናት ማሳደግያ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ለአስራ አምስት ባለሙያዎች በሶላር ኢነርጂ አሰራር ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል::

የኮሌጁ መምህር እና የNORHED II-ReRED ፕሮጀክት አስተባበሪ የሆኑት ዶ/ር ሽመልስ ንጋቱ ስልጠናው ከሲዳማ፣ ኦሮሚያና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወረዳዎች ለተወጣጡና ከሶላር ኢነርጂ ጋር ሙያዊ ግንኙነት ላላቸው ባለሙያዎች በሶላር ኢነርጂ ዝርጋታና ጥገና ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ሽመልስ እንዳሉት ይህ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ሲሆን በቀጣይ በማይክሮ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሰላሳ፤ እንዲሁም በባዮ ማስ ኢነርጂ ደግሞ ሌሎች ስልሳ ሰልጣኞችን ያካተተ ስልጠና ለመስጠት መታሰቡን ተናግረዋል። በማጠቃለያቸውም ውሀና ጸሀይ የተፈጥሮ ሀብቶቻችን በመሆናቸው ይህንን ታዳሽ ሀብት ለኃይል ማመንጫነት በሙሉ አቅም መጠቀም ከተቻለ የሀገራችንን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ለሌሎች አገራት መትረፍ እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።


በሀዋሳ ከተማ የህጻናት ማሳደግያ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ አቶ በዛብህ ሞገስ በበኩላቸው የሶላር ኢነርጂ ከጸሀይ የሚገኝና የተፈጥሮ ኃይልን የሚጠቀም እንደመሆኑ ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ገልጸው በዚሁ ዘርፍ ያለውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመሙላት መሰል ስልጠናዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል። አቶ በዛብህ ማዕከሉ የተመረጠበትን ምክንያት ሲያስረዱም ማዕከሉ መሰል ስልጠናዎችን ለመስጠት የሚያስችል በቂ የሆነ የሰው ኃይልና የመሳሪያ ግብዓቶች ያሉት  በመሆኑ ነው ብለዋል።
የሳይንስ: ቴክኖሎጂና  ሂሳብ ሥልጠና ማዕከል (STEM Center) የስልጠና ሞጁሎችን አስገመገመ::
***//***
የካቲት 18/2016 ዓ.ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ: ቴክኖሎጂና ሒሳብ ሥልጠና ማዕከል (STEM Center) በተመረጡ አምስት የትምህርት ዘርፎች ያዘጋጃቸውን አዳዲስ የስልጠና ሞጁሎች በዘርፉ ምሁራን አስገምግሟል::

በግምገማው መድረክ በስነ-ሕይወት: ፊዚክስ: ኬሚስትሪ: ሒሳብ እና ሮሆቦቲክስ ትምህርቶች ላይ ስልጠና ሊሰጥባቸው ታስቦ የተዘጋጁ አዳዲስ ሞጁሎች በዩንቨርሲቲው የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ቀርበዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት  በ2008 ዓም የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በተለይም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች በማሠልጠን የጎለበተ ዕውቀት እንዲኖራቸው ለማስቻል ታስቦ የተቋቋመው የሳይንስ: ቴክኖሎጂና ሒሳብ ስልጠና ማዕከል አሁን ከዩኒቨርስቲው አልፎ ለአከባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ከ7ኛ እስከ 10ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች ላይ አትኩረው የተዘጋጁት እነዚህ የማሰልጠኛ ሞጁሎች ተማሪዎች ዓለም በቴክኖሎጂው ዘርፍ የደረሰበትን የዕውቀት ደረጃ እንዲገነዘቡና ራሳቸውን በመገምገም በትምህርት ዘርፍ የሚጠብቃቸውን ውጣ ውረዶች በብቃት በመወጣት የወደፊት ትልማቸውን በረዥሙ እንድያቅዱ የሚያግዝ መሆኑን ም/ፕሬዚደንቱ አስረድተዋል።

የማዕከሉ ዳይሬክተር  ዶ/ር ዮናስ ሹኬ በበኩላቸው ከዩኒቨርስቲው በተመረጡ ምሁራን በአምስቱ የትምህርት መስኮች ከ9-10ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጁት እነዚህ የማሰልጠኛ ሞጁሎች ከዚህ ግምገማ በኃላ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ታትመው ስራ ላይ የሚውሉ እንደሆነ ገልፀዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት
በቀጣይም በኤሌክትሮ ማግንቲዝም እና በኦፒትክስ ትምህርቶች ላይ ሞጁሎች ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ መጀመሩ እና በሀዋሳ ከተማና አካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገጽ በሚለቀቁ ማስታወቂዎችና በየትምህርት ቤቶች በሚደረጉ ጥሪዎች አማካይነት ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በሚኖራቸው ጊዜ ተጠቅመው በክፍል ውስጥ የቀሰሙትን ትምህርቶች ተግባራዊ ልምምድ ለማድረግ የሚያግዛቸው መሆኑን አብራርተዋል። ለአንድ ቀን በተዘጋጀው ኘሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ምሁራንና የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሮቦትክስ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የፓናል ወይይት ተካሄደ።
**//***
የካቲት 18/2016 ዓ.ም
"የሀገር ግንባታ መሠረታዊያን: አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የፓናል ዉይይት አካሂዷል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በመክፈቻ ንግግራቸዉ ኢትዮጵያ ረጅም የዘመነ መንግስት ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም ገና የሀገረ መንግስት ግንባታዋ ያልተጠናቀቀበት ሀገር መሆኗን ጠቁመው ነገር ግን በጋራ ቆመዉ፣ በጋራ ሞተዉ ሃገራቸዉን የታደጉ ኩሩ ዜጎችን ያፈራች፣ በዓለም ላይ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት እና የጥቁር ህዝቦች ድል ምልክት እንደሆነች የአድዋን ድል ማስታወስ በቂ መሆኑን ገልፀዋል።

የመጀመሪያዉ ጥናት አቅራቢ በሕ/ገ/ኮሌጅ የአካዳሚክ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን ዶ/ር ንጉስ በላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ የሰዉ ዘር መገኛ፣ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት፣ ብቸኛ በቀኝ ገዥዎች ያልተገዛችና ነፃነቷን ያስከበረች እንዲሁም ሌሎች በርከት ያሉ ማህበራዊና ኃይማኖታዊ ትሩፋቶች ያሏት ሀገር መሆኗን በመጥቀስ በሌላ በኩል ደግሞ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በድህነት፣ በፓለቲካ አለመረጋጋትና በአካባቢያዊ ግጭቶች አሳሯን ያየች አሁንም በዚሁ አዙሪት ዉስጥ የምትገኝ ሀገር መሆኗን ገልፀዋል። ዶ/ር ንጉስ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለችግሮቿ አንዱ ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት ያስተዳደሯት መሪዎች ሀገሪቷን ለመገንባት የሄዱበት የሀገር ግንባታ (Nation Building) ጉዞው ከሀገረ መንግስት ግንባታ (State Building) ጉዞ አንፃር ወደኋላ የቀረ መሆኑን በጥናታዊ ፅሁፋቸው ገልፀዋል። የዶ/ር ንጉስ ፅሁፍ "ሃገራዊ እሴቶች" በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ