Hawassa University
33.9K subscribers
11.9K photos
41 videos
237 files
823 links
One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.
Download Telegram
የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የውይይት መድረክ
************//*******
መስከረም 9 ቀን 2016 ዓም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀምን ተከትሎ ባገኘው ውጤትና በ2016 በጀት አመት መሪ እቅዱ ላይ አጠቃላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዘለቀ አርፍጮ የመድረኩን መዘጋጀት አስፈላጊነት አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሌጁ በ2016 ዓ.ም እቅዶቹን በተሻለ አፈጻጸም ለማከናወን ይችል ዘንድ ተጠንቶ በተዘጋጀው መሪ እቅድ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እንደ ግብአት ለመቀበልና ተገቢውን የክለሳ ስራ ለመስራት መሆኑን ተናግረዋል። ዲኑ አክለውም የሚደረግበት ኮሌጁ በ2015 ዓ.ም በነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሰራው የደንበኞች የእርካታ ደረጃ ጥናት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትና ከሪፖርቱ የተገኙ ግብረ መልሶችን በመመልከት በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ: ተገልጋይ ደንበኞችንም በላቀ ደረጃ ለማገልገል ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የማ/ሳ/ስ/ሰ ኮሌጅ የእቅድና መረጃ አስተዳደር አስተባባሪ ዶ/ር ማሙዬ በልሁ በበኩላቸው ውይይቱ በዚህ መልክ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መካሄዱ ባለሙያው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ከማስቻሉም በተጨማሪ ለተግባዊነቱና ውጤታማነቱ በተሻለ ተነሳሽነት እንዲሰራ እንደሚያስችለው ተናግረዋል። ባለፈው አመት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል ብሎም ክፍተት የታየባቸውን እቅዶች ደግሞ በጥልቀት ገምግሞ ተገቢውን ማሻሻያ በማድረግ በተያዘው የበጀት አመት አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የዕለቱ ተሳታፊዎች ቃል መግባታቸውን ዶ/ር ማሙዬ ጨምረው ገልጸዋል።
በማጠቃለያውም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በ2015 ዓ.ም ሁሉም ኮሌጆች በተሳተፉበት የአፈጻጸም ግምገማ ውጤት የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ሶስተኛ ደረጃን ያገኘበት ድል በዕለቱ በጋራ ተከብሯል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬቶች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ድጋፍ ሰጪ አካላት ተሳትፈውበታል።

                        ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
                        ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
የበይነ መረብ ትምህርት (e-learning) ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
***********//**********
መስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ e-learning for Strengthening Higher Education (e-SHE) Initiative" ጋር በመተባበር ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች በበይነመረብ ትምህርት (e-learning) ላይ ስልጠና መስጠት ጀመሯል::

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ e-learning ግብረ-ሃይል አስተባባሪ ዶ/ር ተስፋዬ ባዩ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደገለፁት ስልጠናው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀና ተደራሽ የሆነ የመማር ማስተማር ስርዓትን ለመዘርጋት የታለመ ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሰባቱም ግቢዎች የሚማሩ የተማሪዎች ህብረት ተወካይ ተማሪዎች የሚሳተፉበት መሆኑን ነው:: አስተባባሪው መርሃግብሩ ከስልጠናው በተጨማሪ ለሌሎች ተማሪዎችም የማስተዋወቅ ስራን የሚያካትት መሆኑን ገልፀው እንደ ዩኒቨርሲቲም እስከ ዓመቱ መጨረሻ ይሄንን የበይነመረብ ትምህርት አጠቃቀም ስልጠና ከ12 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ለማድረስ መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

የe-SHE Initiative አስተባበሪ አቶ ሙሉነህ አጥናፉ በበኩላቸው ስልጠናውን ሲሰጡ እንደተናገሩት በሀገራችን አሁን እየተተገበረ ያለው የትምህርት ስርዓት ሂደት በርካታ ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን እና ከዚህ በመነሳት ያለንበት ዓለም የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ተማሪዎችንም መምህራንንም የዲጅታል ቴክኖሎጂና የቋንቋ ክህሎቶቻቸውን በማጎልበት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በመታገዝ ትምህርቱን በቀጥታ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ስልጠናው መዘጋጀቱን አብራርተዋል:: የፕሮግራሙ ዓላማም እንደሀገርና እንደዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለማድረግ፣ የተማሪዎችንና የመምህራንን አቅም ለመገንባት፣ የመልቲ ሚዲያ
ስቱዲዮዎችን ለመገንባት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ጠቀሜታውም ትምህርትን ለማዘመን፣ መማር ማስተማሩን ተደራሽና አካታች ለማድረግ፣ በአግባቡ መተግበር ሲጀምርም የሀገርንና ዩኒቨርሲቲዎችን ገፅታና እይታ እንደሚጨምር፣ የተማሪዎችን ወጪ እንደሚቀንስ፣ የመምህራንን ገቢ እንደሚያሳድግ እና በርካታ የስራ ዕድሎችንም እንደሚከፍት ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ቀናቶችም ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና መምህራኖች ጋር ይሄንን የቀጥታ ኢ-ትምህርትን የተመለከተ ውይይት እንደሚካሄድና ቀጣይ አቅጣጫዎችም እንደሚቀመጡ ታውቋል፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
ማስታወቂያ ለሀዩ የማ/ብ ሞዴል 2ኛ ደ/ት/ቤት ተመዝጋቢዎች
**********//**********
መስከረም 10 ቀን 2016 ዓም

የ8ኛ ክፍል እና የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ላለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ከዛሬ መስከረም 10 - 12/2016 ዓም መሆኑን እንገልፃለን:: ከተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያላችሁና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ ስኮላርሺፕ የተሰጣችሁ 10 (5 ሴትና 5 ወንድ) ተማሪዎች ከዚህ ጋር የተያያዘው ደብዳቤ ላይ የተገለፀውን ሂደት ተከትላችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*************
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
ማስታወቂያ ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ተመዝጋቢዎች
*********//*********
መስከረም 11 ቀን 2016 ዓም
በዘንድሮ የትምህርት ዘመን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ለመከታተል የተመዘገባችሁ በሙሉ ከዚህ በላይ የተገለፀውን ሂደት እንድታሟሉ እናሳስባለን::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ያገኙን ቢፈልጉ:-
*************
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
A Team from MoE hold discussion with HU officials on e-SHE project implementation
**********//***********
In collaboration with international and national partners, the Ministry of Education is implementing a five-year project named "e-Learning for Strengthening Higher Education" (e-SHE) which has an overall aim of enabling the 50 public universities teach their courses in blended and online modalities. The project is anticipated to: improve educational quality, increase access to higher education, and create more access to teach international students.

To this end, a team of professionals and project managers from MoE held a discussion session with HU officials on ways of the e-SHE project implementation of cloud-based e-learning platforms for the fifty universities, and the work in progress to establish five Multimedia Studios including one for Hawassa University. It was also pointed out that the project has a target of training 35,000 instructors on online teaching and equipping 800,000 students with
digital learning skills.

In 2023, the e-SHE project has a plan to train 336 instructors from Hawassa University in Master class for online teaching (MCT) from Arizona State University, and a total of 12,304 students are targets to get trained in Student suits – a digital literacy training. The team explained that the MCT training will enable instructors to teach online, to develop quality digital course contents, and give instructors an opportunity to undertake further Training of Trainers (ToT) and become certified trainers for future MCT trainings offered locally.

Dr. Ing. Fisiha Getachew, Vice President for Academic Affairs of HU extended his gratitude to the visitors and MoE for designing this timely project aimed at empowering the actors in Ethiopian academia.

Hawassa University
Ever to Excel!

Contact us via:
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: ccmd@hu.edu.et
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa