ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፋይዳን የሚዳስስ የምክክር መድረክ አካሄደ።
*//*
መጋቢት 29/2018 ዓ/ም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ፣ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም እና ለሃገር ብልጽግና ያለው ፋይዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ መጋቢት 28/2018 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ አካሂዷል::
በውይይት መድረኩ ላይ የሲዳማ ክልልና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የገዥውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የም/ት/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ትንታኔዎችን በማቅረብና ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ ውይይቶችን በማመቻቸት ረገድ ያለውን ሚና አብራርተው በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ላይም የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ ለመቀጠል መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ምርጫ የዜጎች የውሳኔ ሰጪነት መብት የሚረጋገጥበትና የሀገር ግንባታ ሂደት መሰረት የሚጣልበት ወቅት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ታፈሰ በተለይም ምሁራንና ተማሪዎች በምርጫ ሂደት ላይ ያላቸው ግንዛቤ መዳበሩ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እድገትና ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ተጠሪ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዋነኛ መገለጫና ህዝባዊ ውክልና የሚረጋገጥበት መድረክ መሆኑን ጠቁመው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከቀደሙት በበለጠ መልኩ ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። አቶ አብርሃም አክለውም ምርጫው በሁሉም ተሳታፊዎች ዘንድ ተዓማኒ ሆኖ እንዲያልፍ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መላው ህዝብ በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው አሳታውሰዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎች በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ፕሮፌሰር ዘለቀ አርፍጮ እና በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ምህረት ዳናንቶ አማካኝነት የቀረቡ ሲሆን፣ በምርጫና በሀገር ግንባታ መካከል ስላለው ጥብቅ ትስስር ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል::
በመድረኩ በተነሱት አጀንዳዎች ላይ ተሳታፊዎች በዝርዝር ተወያይተው ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ከሰነዘሩ በኋላ ውይይቱ ሀገራዊ ምርጫውን በጋራ መግባባት ለማጠናቀቅ በመስማማት ማጠቃለያውን አግኝቷል።
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተደራጁ ያሉ ዘመናዊ ቤተ-ሙከራዎችን ጎበኙ።
*//*
መጋቢት 30/2018 ዓ/ም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ባለፉት ሁለት ዓመታት ተገንብተው ከጀርመን መንግስት በተገኘ የዘመናዊ መሣሪያዎች ድጋፍ ማስፋፊያ እየተደረገባቸዉ ያሉ ቤተ-ሙከራዎች የደረሱበትን ደረጃ ለመገምገም ያለመ ጉብኝት አድርገዋል።
በኢንስቲትዩቱ የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ መምህር በሆኑት ዶ/ር ተወልኝ ከበደ አማካኝነት ከጀርመን አገር የተገኘውን ከ2.1 ሚሊዮን ዩሮ (ሶስት መቶ ሰማኒያ ሚሊዮን ብር ገደማ) የሚጠጋ ዋጋ የሚያወጡ እና ለስምንት ቤተ-ሙከራዎች ማሟያ የሚሆኑ የቁሳቁስ ድጋፍ ተገኝቷል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ይህ ፕሮጀክት መምህራን ከመንግስት በጀት ባሻገር በራሳቸው ጥረት ለሀገር ትልቅ ሀብት ማምጣት እንደሚችሉ ማሳያ ስለመሆኑ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ ቤተ-ሙከራዎች ግብዓት የሚሆን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የቢሮ ዕቃ አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም አክለዋል።
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ምህረት ዳናንቶ በበኩላቸው ጉብኝቱ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና በቀጣይ የሚታዩ ክፍተቶችን በከፍተኛ አመራሩ ድጋፍ ለመሙላት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
የቤተ-ሙከራዉ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፣ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ወራት ውስጥ የጀርመን አምባሳደርና የሚመለከታቸው ሚኒስትሮች በተገኙበት በታላቅ ሥነ-ስርዓት እንደሚመረቅ በፕሮጀክቱ አማካኝነት የቁሳቁስ ድጋፉን ያስገኙት ዶ/ር ተወልኝ ከበደ አመልክተዋል።