HT useful perspectives
73 subscribers
12 photos
2 files
5 links
Always challenge ur self
Believe in ur self
Dont waste ur time
Dont fear of change
Do it now before its late
Work hard
Failure is lnevitable
Download Telegram
'ቅድም' እና 'በኋላ'

"በጊዜ ውስጥ ትናንት የትዝታ፣ ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው። ካመለጠ ትናንት...ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል። ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሰለ የማይደገም... ተመልሶም የማይመጣ... ላንድ አፍታ ለቅጽበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወር...በትናንትና በነገ መሃል የተሸነቆረ እንቁ ነው። የዛሬ ምስጢሩና ጉልበቱ ያለው ደግሞ 'አሁን' ላይ ነው። 'ቅድም' እና 'በኋላ' ግን ያለቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትናና የነገ ሽርፍራፊዎች ናቸው።"


ዶክተር ምህረት ደበበ✍️


Join us👇👇👇👇👇
@HTperspective
የረቀቁ ሀሳቦች
(osho views)

🔱ምን ይዞ እንደሚመጣ ለማይታወቀው መጪው ጊዜ መፈንጠዝና በምኞት ፈረስ መጋለብ ካላቆማችሁና፣ ትናንትናንና ነገን ትታችሁ ዛሬን መኖር ካልጀመራችሁ ነፃ አትወጡም። ነፃነት አሁን እዚህ ናት።
ያለህበት ጊዜ ብቻ ናት እውነት ህልውና ያላት። መጪው ጊዜ ምኞትህ፣ ያለፈውም ጊዜ ትዝታህ ነው። ህልውና የላቸውም።
የአሁኑን ጊዜ በንቃት ማሳለፍ ንቃተ ሂሊናህና ካለፈውና ከመጪው ጊዜ ሰብስበህ በአሁኑ ጊዜ ላይ ማትኮር ማለት የነፃነትን ጣዕም ማወቅ ነው።


🔱ብዙ ጊዜ ትወድቃላችሁ። ይህ ለክፉ አይሰጥም። እንደገና ተነስታችሁ ቁሙና ዳግም ያለመውደቅን ተማሩ። የበለጠ ንቁ። ስህተት መስራታችሁ አይቀርም ፣ ግን አንድ ስሄተት ደግማችሁ አትስሩ። ይህን የምላችሁ ሰው ጥበብን የሚያገኘው በዚህ መልኩ ነው።
አጭር ሆናችሁ አትቅሩ። የምትችሉት ርቀት ላይ ለመድረስ ሞክሩ። ሊያኮራ የሚችለውን ብቃት ይዞ ያልተፈጠረ ማንም ሰው የለም። አንድን አዲስና ውብ ነገር የመውለድ፣ህላዊን የበለጠ የማበልፀግ ብቃትን ሳይዝ የተፈጠረ ሰው የለም።


🔱አንተ ትክክል መሆን አለመሆንህን ለማወቅየህሊናህ እና የድርጊትህ እንጂ የሌሎች ሰዎች ድጋፍና ምስክርነት አያሻህም ። ትክክለኛውን እንጂ አብዛኛውን ለመሆን አልተፈጠርክም። ትክክል ባትሆን እንኳን መቶ በመቶ የሌላ ሰው ቅጂ አትሁን።"

ውስጣዊ ማንነቱ የተከፋፈለ ግለሰብ በአብሮነት የማይስማማ ማህበረሰብን ይፈጥራል፤ንቃተ-ህሊና ያለው ግለሰብ ያልተከፋፈለ ውስጣዊ ማንነት ሲኖረው የተዋሃደ ማህበረሰብንም ይፈጥራል።ንቃት የሌለው ማንነት ለዘላለማዊ ሙት ነውና
ንቁ!!!!**


🔱አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ እንደማሰብ መርዘኛ ነገር የለም ሰውን የግል የማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው ከእንዲህ አይነቱ ስሜት ቢያንስ ጥላቻ ይሻላል በጥላቻ ውስጥ ውሸት የለም ከዚያ በላይም ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል
የሰውን ልጅ ግን የግል የማድረግ ፍላጎት ፈጽሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው ፍቅር ማለት ሞት ነው።

🔱መላው አለም እኔን መቃወሙ አያስጨንቀኝም። ዋናው ነገር ተሞክሮዬ ተቀባይነትን ማግኘቱ ነው። ምን ያህል ሰዎች ከኔ ጋር እንደሆኑ ለማወቅ ቁጥራቸውን አልመለከትም። ትኩረት የማደርገው በተሞክሮዬ ተቀባይነት _ የሌላ ሰው ቃላትን እንደበቀቀን እየደገምኩ መሆን አለመሆኔን ወይም የምናገራቸው ነገሮች ከገዛ ራሴ የመነጩ መሆን አለመሆናቸው ላይ ነው። ንግግሬ በገዜ ራሴ ተሞክሮ ውስጥ ከሆነ፤ የደሜ፣ የአጥንቴና የመቅኔዬ አካል ከሆነ፣ መላው አለም በአንድ ወገን ሊሆን ቢችል እንኳን፣እኔ ትክክል ነኝ። እነሱ ግን ተሳስተዋል። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም። እኔ ትክክል መሆኔ እችዲሰማኝ የእነሱ የድጋፍ ድምፅ አያስፈልገኝም። የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙት ብቻ ናቸው።


🔱ፍቅር በራችሁን አንኳኩቶ ያውቃል? በጭራሽ! ምክንያቱም ገና ፍቅር መስጠት አልቻላችሁም። ማስታወስ ያለባችሁ የሰጠነው ሁሉ ወደ እኛው ተመልሶ እንደሚመጣ ነው። ይህም ከህይወት ህጎች አንዱ ነው።መላው ዓለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም። ጥላቻ እንሰጣለን፣ ጥላቻም ወደኛው ተመልሶ ይመጣል። ሌሎችን እንሳደባለን ከዛም ስድብ ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። እሾህ ስንሰጥ እሾህ ወደኛው ተመልሶ ይመጣል፡፡ የምንሰጠው ሁሉ በተለያዩ መንገዶች ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። ፍቅርን ካካፈልንም እንደዚሁ በተለያዪ መንገዶች ተመልሶ ወደኛው ይመጣል። ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ፍቅር ወደ እኛ ተመልሶ ካልመጣ ፍቅር እንዳልሰጠን ማወቅ አለብን፡፡ፍቅር የምትሰጠው እንጂ የምትቀበለው አይደለም።

Join us👇👇👇👇 share
@HTperspective
@HTperspective
HT useful perspectives pinned «ወደ ኋላ ቀርታችሁ አልዘገያችሁም ወደ ፊትም ሄዳችሁ አልፈጠናችሁም የኒውዮርክ የሰዓት አቆጣጠር ከካሊፎርኒያ በ3 ሰዓት ይቀድማል፡፡ ይህ ማለት ግን ካሊፎርኒያ ቀርፋፋ ናት ማለት ግን አይደለም። አንዳንዶቹ በ22 አመታቸው ትምህርታቸውን ጨርሰው ይመረቃሉ ግን ትክክለኛውን ስራ እስከሚያገኙ ድረስ 5 አመት ሊጠብቁ ይችላሉ.. አንዳንዱ በ25 አመቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ግን በ50 አመቱ ሊሞት ይችላል። አንዳንዱ…»
መጨነቅ አቁሙና መሰራት ጀምሩ!

ከቁጥጥራችሁ ውጪ በሆኑና ፈጽሞ ለመለወጥ በማትችሏቸው ነገሮች ላይ ከማተኮርና ስለእነሱ ከመጨነቅ ይልቅ በቁጥጥራችሁ ስር ባለውና ለመለወጥ በምትችሉት ነገር ላይ በማተኮር ብትሰሩ ውጤቱ እጅግ የላቀ ነው፡፡

ፈጽሞ የማትችሉትን ለፈጣሪ አሳልፋችሁ በመስጠት መለወጥ የምትችሉት ላይ በማተኮር ስትሰሩ፣ ውስጣችሁ አረፍ ይላል፣ በአቅማችሁ የሰራችሁት ስራ ውጤት ሌላ አዲስ የእድል ደጅ ይከፍትላችኋል፣ የመተማመን መጠናችው ይጨምራል . . . !


Join us 👇👇👇
@HTperspective
ህልምህ!

ከምናደንቃቸውን ሰዎች ስኬት ጀርባ ያለውን የስህተት ብዛት ብናይ....ለካ እኔ ደጋግሜ መሳሳት ስለምፈራ ነው ብዙ ነገር ጀምሬ የማቆመው፤ እንጂ እንደዚህ መሳሳትማ መቼ ያቅተኛል እንላለን ።

ህልምህ ጋር ለመድረስ ስህተትና ሽንፈትን ጓደኛህ ማድረግ አለብህ! ወዳጄ እየተሳሳትክ ካልሆነ ምንም አዲስ ነገር እየጨመርክ አይደለም።


@HTperspective

Join us
ስብዕና
"ከህመሞች ሁሉ ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን #ከስብዕና_መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሠው የገጽ ሽፋን ነው። ስብዕና ግን የሠው እውነተኛ መልክ ነው። በየዕለቱ አብረን የምንኖረው ሰው ቢኖር፣ እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ሰብዕናችን ነው። በዓይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ሰብዕናችን ነው። የሰብዕና ስንኩልነት፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ፣ አገር ይንዳሉ፣ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከም ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ህመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው።

ሰብዕና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሠው ሰብዕና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነት ጊዜ በትክክል የሚቀርፀው ካለገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። ዕድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶት አገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሰራቱ... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነ ክፉ እውቀቱ ነውና።"
#ከ'ሌላ ሰው መጽሐፍ የተወሰደ
በዶ/ር ምህረት ደበበ
በቅንነት ሼር ያድርጉልን👇
@HTperspective
Have a great dream
For any comment ena cross @nyat12
Qoutes
Funny videos😂
Memes
Music🎼🎼
Different graffiti and drawings🎨
Poem
Tricks
Fam pic
Cute pics
https://t.me/Yenetsedeye
መሆን ራስን

••• ራስን መሆን ሲባል ከፀባይ ጀምሮ አለማስመሰል፣ የሌለን ነገር አለኝ ማለትን ጨምሮ እቅድን፣ የወደፊትን ሃሳብዎን፣ እምነት ላይም ሆነ ነገሮች ላይ ያለን አመለካከትን በተመለከተ የሚያምኑበትንና የሆነውን ከመናገር ይጀምራል።

••• ከዚህ በተቃራኒው ሆነው ጊዜያዊ ለሆነ ነገር ሰው ማግኘትን ባይለምዱት ይላሉ ባለሙያዎቹ።

••• ዘወትር በየትኛውም ቦታ ራስዎን ሆነው መቅረብን ልማድዎ ያድርጉ።

Join us share👇👇
@HTperspective
💎 የዱባና የቲማቲም ተክሎች በሳምንት እና ቀናት ውስጥ ያድጋሉ፤ ለረጅም ቀናትና ሳምንታት ፍሬያማ ሆነው ብዙ ያመርታሉ የበረዶው ጊዜ ሲያልፍ ግን ፍሬያቸው ረግፎ ይሞታሉ።

በተቃራኒው ዛፎች ለማደግ ብዙ ወራትን አመታትን ይወስዳሉ፤ ካደጉ በኋላ ግን የበረዶውንና ከባዱን ጊዜ በኩራት ያልፉታል። አየህ በፍጥነት ወደላይ ሽቅብ ከወጣህ በፍጥነት ቁልቁል ትወርዳለህ!

ዛፎቹን እንዲቆዩ ያደረጋቸው በአመታት መሬት ለመሬት የዘረጉት ስር ነው፤ አንተም ለገንዘብና ስኬት ሳትጓጓ ራስህ ላይ በደምብ ስራ! አለበለዚያ ስኬት የመሰለህ ነገር ጊዜያዊ ስለሆነ እንደ ንፋስ ሽው ብሎ ያመልጥሀል።💎

👇👇👇👇
@HTperspective
@HTperspective
🎯 በቀን ውስጥ ማድረግ ያሉብህን ሁሉ የምታደርገው በአንድ ጊዜ አዲስ ተዓምር ለምፍጠር አይደለም፤ ግን እንደ ጨለማ ቀስ እያለ የሚገፈፈውን የስኬት ብርሀንu ለመግለጥ ነው።

ስለዚህ ጠዋት መነሳት ካለብህ ትነሳለህ! ማንበብ ካለብህ ታነባለህ! ስራ መግባት ካለብህ መግባት ብቻ ሳይሆን ወጥረህ ትሰራለህ! መማር ካለብህ ከልብህ ትማራለህ! ወዳጄ አሁን የለፋኸው አሁኑኑ ሳይሆን እንደ ባንክ ወለድ ተጠራቅሞ ሲከፈልህ እንኳን በሙሉ አቅሜ ለፋው ትላለህ።
ረጅሙ ሳቅ

አንዳንዴ ነገሮች ሲደበላለቁብህ ሰማይ የተደፋብህ ያህል ሊሰማህ ይችላል፤ ወዳጄ ካልደፈረሱ የማይጠሩ ነገሮች አሉ።

ማን እንደሆንክ የምታሳየው በምቾት ላይ ሆነህ አይደለም ግን በፈተና ውስጥ ሆነህ ነው፤ አትርሳ ረጅሙን ሳቅ የሚስቀው በመጨረሻ የሚስቅ ሰው ነው!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@HTperspective👈👈join
@HTperspective👈👈
አስተውል ይሄ እውነታ ነው ‼️

•| ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም !ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ ።

•| ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ ።

•| ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ ።

•| አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም !ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ ።

•| ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም ! በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ ።

•| ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም !ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ ።

•| ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ ።

•| ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ ::


👇👇👇👇👇👇
@HTperspective
HT useful perspectives
Always challenge ur self
Belive in ur self
Dont waste ur time
Dont fear of change
Do it now before its late
Work hard
Failure is lnevitable

@HosiAb

@yatiyee
https://t.me/HTperspective
🌼🌼🌼 Happy New Year 🌼🌼🌼

🎉እንኳን ለ ➋0➊➍ ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል #እንቁጣጣሽ በሰላም አደረሳችሁ።

🎉በዓሉ የሰላም፤የፍቅር፤ የጤና እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን !!

#መልካም_በዓል
🌼🌼

@HosiAb
@yatiyee
" የገንዘብ ትልቁ ኀይሉ የኪስን ድህነት ማጥፋቱ ሳይሆን የአእምሮን ራቁትነት ማጋለጡ ላይ ነው ። "

ገንዘብ ኖሮክ አሰተዳደሩን ወይም አጠቃቀሙን ካላወቅክ የገንዘብ ሀያልነት አንተ ላይ ሲሰራ ይታያል እንድትገዛበት (እንድትገበያይበት) የተፈጠረው ነገር አንተን ሲገዛ ይገኛል ያኔ ገንዘብክ የአምሮክን እርቃንነት ልትሸፍነው በማትችለው መልኩ ይገለጣል ይህ ደግሞ አጠቃቀምን አለማወቅ ነው ክፋቱ ያንተ ታውሮ የሌሎችንም ማሳወሩ ።

ገንዘብ ኖሮክ ደግሞ አጠቃቀሙን ስታውቀው ግን ገንዘብ መጠቀሚያ እንጂ የአምሮ ወይም የአሰተሳሰብ ልዕልናክን አሊያም ዝቅጠትን የሚያጋልጥ ሳይሆን አንተን የሚያገለግል ስለሚሆን አንተን ጠቅሞ ሌላውን ይጠቅማል።

ስለዚህ ገንዘብ በራሡ ነፃ (neutral) ነገር ነው። የማንም የአእምሮ ራቆትነት ብሎም የአስተሳሰብ ልዕልናን አያሣይም ሠውየው ስለ ገንዘብ እና አጠቃቀሙ ያለው እስተሳሰብ እንጂ ገንዘብ ከመጠቀሚያነት ያለፈ ሀይል ያለው ነገር ሆኖ አይደለም።"

ዶ/ር ምህረት ደበበ \ የተቆለፈበት ቁልፍ

Join us👇👇

@HTperspective
@HTperspective
It's okey to not be okey
Its just not okey stay that way
The one thing i know about emotion is that they change
1hour from right now u will not feel the same way and i wanna encourage you that you might be in your darkest moment you might be going through hell and high water but i konw this.It is always too soon to quit you have a reason to live . Your best days are in front of you get up your future is brighter than your past Get up .your latter is greater than your former Get up because the best is still yet to come



Join us👇👇👇
@HTperspective
#አንድ_ቀን_ከእንቅልፍህ_ስትነቃ!

#የዘ_አልኬሚስት መጽሐፍ ጸሀፊ 'ፓውሎ ኮኤልሆ'' እንዲህ አለ፦

አንድ ቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው!!

የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።

ሕልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ "አይሳካልኝም" የሚል ፍርሃት።

ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው፤ በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ!

አንድ ነገር አስታውስ፦

#ልብህ_ያለበት_ቦታ_ሀብትህም_ተቀምጧል!

Join us 👇👇👇
@HTperspective
@HTperspective
ትላንት ማን ሞተ? ዛሬም የሆነ ሰው ይሞታል::ግን ይህ አለም እውን ነውን ወይስ ህልም? ብዙ ሰው አለምን እውነታ አድርጎ ይወስደዋል::አንድ ቀን ግን የሞት አልጋው ላይ ሲተኛ ሁሉም ነገር ህልም እንደሆነ ይገባዋል::ሞት እየመጣ ነው::በአለም ያንቀላፋን እንንቃ::ከስሜት ህዋሳችን ጠለቅ ባለው የአምላክ መንግስት እንኑር::ያኔ በአለም ሞተን በመንፈስ እንነቃለን::ሞተን ሞት እንደሌለ እንረዳለን::

Join : @HTperspective
Join : @HTperspective
Join : @HTperspective
Join : @HTperspective