Ŋever Ĝivĕ űp
42 subscribers
172 photos
137 videos
18 links
Never give up.everyone has bad days .
Pick yourself up& keep going.

👉 quotes & facts

👉 funny videos 😀😁 & tiktok video

👉 poem

👉 best🌆 wallpapers 🌌
Download Telegram
#ለምዶበት_ነው_እንጂ

ለምዶበት ነው እንጂ ጥርሴ የሚስቀው
የልቤን መከፋት እኔ ነኝ የማውቀው
የራሴን በሽታ ላስታም ብዬ ራሴ
ለሰው ሳላወጋው ሸሽጌ በጥርሴ

በሳቄ መለያ ስቃይ እያጫወትኩ
የውስጤን ጫጫታ ራሴው እያዳመጥኩ
አለሁኝ እስካሁን ለይምሰል እየሳቅኩ:

የደበነው ውስጤ በበደል ያረረው
ጠባሳ የሞላው ውስጤ የማይሽረው
ያለኔ ማን አውቆት የልቤን ስብራት
የምለውን እንጂ የምላሴን ማውራት
ፈገግታዬ እንጂ ስሜቴ ማ ገብቶት
መደሰቴን እንጂ ማንባቴን ማን አይቶት

በይምሰል ፈገግታ ውስጤን እየደበቅኩ
አለሁኝ እስካሁን ለይምሰል እየሳቅኩ
በመሰለች ምድር ለምሳሌ እየኖርኩ
ስቄ ላልስቅበት ጥርሴንም እያስዋብኩ

ህህ ልበልና ፈገግታዬን ላሳይ
ደብቄው ነው እንጂ በዝቷል የኔ ስቃይ
ለምዶበት ነው እንጂ ጥርሴ አመል ሆኖበት
ፈገግ የሚያስብለኝ ስቄ ላልስቅበት።
....#Selam
#Join and #Share
@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn