ሀበሻ MEDIA🔅
874 subscribers
131 photos
18 videos
2 files
15 links
Join my channel
Download Telegram
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 22 ሺህ 101 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1386 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 32,722 ደርሷል። በሌላ በኩል 414 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ስሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 12 ሺህ 938 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
32 የኦነግ ሸኔ አባላት እጃቸውን ለመንግሥት ሰጡ
****************

የጥፋት ተልእኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ እጃቸውን ለመንግሥት መስጠታቸው ተገለጸ።

ኦሮሞን ነጻ እናውጣ በሚል ሽፋን ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን የመግደል፣ የሕዳሴውን ግድብን የማደናቀፍና ሌሎች የመሠረተ ልማት ተቋማትን የማጥቃት ተልእኮ ተቀብለው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

እጃቸውን ከሰጡ የኦነግ ሸኔ አባላት መካከል አቶ ገልማ ቡሌ በትግል ስም 'ዲና ራሳ' የተባሉት የጥፋት ተልእኮውን ለማሳካት ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

የጥፋት መንገድን በመከተል የክልሉን ሕዝብ ነጻ ማውጣት እንደማይቻል በመገንዘብ፣ ችግርም ካለም በውይይት እና በድርድር በመፍታት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እጃቸውን እንደሰጡም ገልጸዋል፡፡

ሌላው አበበ ጂሎ በትግል ስም 'አብዲ ሰባ' የተባለው ደግሞ "ኦሮሞ ተበድሏል" በሚል ተታልሎ እና ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ለጥፋት ተልእኮ ኦነግ ሸኔን እንደተቀላቀለ ተናግሯል፡፡
"የኦነግ ሸኔ ዓላማ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ መዝረፍና በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረስ በመሆኑ በዚህ ተግባር መቀጠል ስላልፈለኩ እጄን ለመንግስት ሰጥቻለሁ" ብሏል፡፡

ሌላው አጋ አረቦ በትግል ስም 'ቄራንሶ ሰባ' የኦነግ ሸኔ የትግል ስልት እና ዓላማ ከኦሮሞ ባህላዊ ስርዓት ያፈነገጠና የክልሉን ህዝብ የማይመጥን በመሆኑ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሻለሁ ብሏል፡፡

የሰው ሕይወት እያጠፉና የመሰረተ ልማትን እያወደሙ ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ ማለት እራስን ማታለል ስለሆነ ከዚህ በኋላ ዳግም እንደማይሳሳትና እንደማይቀበለውም ገልጿል።

የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ቃሉዎች ኦነግ ሸኔ ሰላማዊ የትግል አማራጭ እንዲከተል ጥያቄ አቅርበው እንደነበርም አስታውሷል፡፡

የምዕራብ ጉጂ ዞን አሰተዳደሪ አቶ ተፈሪ ወንድይፍራው በኦሮሞ ህዝብ ስም ጫካ መሽጎ የሰው ሕይወት የሚያጠፋ፣ ንብረት የሚዘርፍና የመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት የሚያደርስን ኃይል አንታገስም ብለዋል፡፡

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በኦነግ ሸኔ ተመልምለው በህዝብ ላይ ጥፋት ሲፈጽሙ የነበሩ ወገኖች ዓላማው ሲገባቸው ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስ መጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከኦነግ ሸኔ የጥፋት አጀንዳ ተቀብለው የሚሰማሩ የጥፋት ኃይሎችን የዞኑ ህዝብ በየቀኑ እያጋለጠና አሳልፎ እየሰጠ እንደሚገኝም ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ 336 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፣ 370 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
***************
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 21 ሺህ 326 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 336 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ 58 ደርሷል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 370 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 308 ሆኗል።
ባለፉት 24 ሰዓታት የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 600 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት 20 ሺህ 148 ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በሕክምና ላይ ሲገኙ 255 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 672 ሺህ 637 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ 829 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ 17 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል፡፡

#Ethiopia : በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 23 ሺህ 35 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 829 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 37 ሺህ 665 መድረሱንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ 638 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገባቸው፤ 515 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል
****************

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 20 ሺህ 153 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 638 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 40 ሺህ 671 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 515 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14 ሺህ 995 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት የምርመራ ጊዜ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 678 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 24 ሺህ 996 ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ሕክምና ላይ ሲገኙ 291 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 757 ሺህ 57 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ከመጠን በላይ ውፍረት በኮቪድ-19 የሚመጣ ሞትን 48 በመቶ ይጨምራል-ጥናት
***************************************

ከመጠን በላይ ውፍረት በኮቪድ-19 የሚመጣ ሞትን ወደ 50 በመቶ ገደማ እንደሚጨምር እና ለበሽታው የሚሰጡ ክትባቶች ብዙም ውጤታማ እንዳይሆኑ ያደርጋል ሲል አዲስ የወጣ ዓለም አቀፍ ጥናት አመለከተ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ባለሞያዎች ያደረጉት ይኸው ጥናት ከመጠን በላይ ክብደት ላላቸው ሰዎች ያለው አደጋ ቀደም ሲል ሲታሰብ ከነበረው በላይ ነው ብለዋል።

ጥናቱ በዓለም ባንክ በኩል የተካሄደው ሲሆን መንግሥታት ከመጠን በላይ ውፍረትን መከላከል ላይ እንዲሠሩ ለማድረግ ግፊት እንዲበረታባቸው ያደርጋል ብሏል።

አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ከመጠን በላይ ውፍረት ያለባቸው ሰዎች ቀዳሚ መገኛዎች መሆናቸውም ተመልክቷል።

በአሜሪካ መንግሥት አሐዛዊ መረጃ መሠረት ከ40 በመቶ በላይ አሜሪካውያን ከመጠን በላይ ውፍረት እንዳለባቸው ያሳያል።

እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ከ27 በመቶ በላይ ጎልማሶች የችግሩ ተጠቂ ናቸው ተብሏል።

አሜሪካ ቻፕል ሂል በሚገኘው የኖርዝ ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ የተሠራው ይኸው ጥናት ከመጠን ባላይ ውፍረት ያለባቸው ሰዎች በብዙ መንገድ የኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ተጋላጭነት እንዳላቸው አሳይቷል።

በጥናቱ መሠረት ከመጠን ባላይ ውፍረት ያላቸው ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የመግባት ዕድላቸው 113 በመቶ፣ ጽኑ ሕክምና ክፍል ውስጥ የመግባት 74 በመቶ እንዲሁም በቫይረሱ ለሞት የመዳረግ ዕድላቸው ደግሞ 48 በመቶ መሆኑን አሳይቷል።

ጥናቱን የመሩት በኖርዝ ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ግሊንግስ ዓለም አቀፍ የኅብረተሰብ ጤና ት/ቤት የሥነ ምግብ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ባሪ ፖፕኪን፣ በግኝቱ መደንገጣቸውን ለጋርዲያን ተናግዋል።

ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው ሰዎች በኮቪድ-19 የመሞታቸው እድል ማንም ከሚያስበው በላይ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን መጥቀሳቸውን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል።

“ይህ ለእኔ ትልቅ ተፅዕኖ ነው” ያሉት ፖፕኪን “የጥናት ግኝቱ አደጋው 50 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ያሳየ ነው። ይህም በጣም አስጨናቂ አሐዛዊ መረጃ ነው። ከጠበቅኩትም በላይ ነው” ብለዋል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ16 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,724 የላብራቶሪ ምርመራ 1,533 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 515 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 45,221 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 725 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,311 ደርሷል።
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,766 የላብራቶሪ ምርመራ 1,733 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 586 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 48,140 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 758 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 17,415 ደርሷል።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ 514 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገባቸው፤ 701 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል
*******
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 19 ሺህ 194 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 514 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 49 ሺህ 654 ደርሷል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 701 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 18 ሺህ 116 ሆኗል።
ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 770 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት 30 ሺህ 766 ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ሕክምና ላይ ሲገኙ 329 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 869 ሺህ 430 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,499 የላብራቶሪ ምርመራ 1,468 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 266 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 51,122 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 793 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,382 ደርሷል።
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,449 የላብራቶሪ ምርመራ 976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 482 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 59,648 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 933 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 21,789 ደርሷል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ