1.1K subscribers
351 photos
17 videos
12 files
123 links
ትክክለኛውንና እውነተኛውን ወንጌል የምስራች ለአለም ሁሉ የሚያበራውን #ኢየሱስ ብቻ ሚሰበክበት
contact us @tsegamulat
Download Telegram
የማወራችሁ ስለ ኃይል ነው! ኃይል ያስፈልገናል!

ኃይል ስል፡ የማወራው፡ መሬት ላይ ጥሎ እንደ ትል ስለሚያንፈራፍረው ኃይል አይደለም፤ የማወራው መርሴዲስ ቤንዝ (Mercedes benz) ለመንዳት አዋጅ እንድናውጅ ስለሚያደርገን ኃይል አይደለም፤ የማወራው፡ ያልተፈወሰውን ተፈወሰ ስለሚያስብለው የውሸት ኃይል አይደለም። የማወራው፡ የክርስትናን ሕይወት በሚገባ እንድትኖሩ ስለሚያስችለው ኃይል፤ እውነተኛ በሆነ ፍቅር ስለሚያራምድ ኃይል፤ ስለ ጸሎት ኃይል፤ ወንጌል-መስካሪ ስለሚያደርግ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ነው የሚያስፈልገን።

መጋቢ ፖል ዎሸር
(Paul Washer)

("Empowered by the holy spirit" ከሚለው ስብከት የተቀነጨበ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥇A gold from The Golden Mouth🥇

ቅዱስ ዩሀንስ አፈወርቅ ቤተክርስቲያንን  በሆስፒታል ይመስላታል። ቤተክርስቲያን ለሀጢያተኞች ፍርድን የምታከፋፍል ፍርድ ቤት ሳትሆን በምትሰጣቸው በምስጢራት (በጥምቀት ና በጌታ እራት) ና በቃሉ ለሐጢያተኞች ህክምና የምታደርግ የእግዚአብሔር ተቋም ናት። በአጭሩ ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችም። አንዳንድ ሰዎች ሲደክሙ ከቤተክርስቲያን ይጠፋሉ ምክንያቱም በእነርሱ አዕምሮ ውስጥ ቤ/ያን ፍርድ ቤት ነች። የተወደዳችሁ በአዕምሯችን ማስረፅ ና ማተም ያለብን ቤተክርስቲያን መታከሚያ ቦታችን እንደሆነች ነው፡

''ከቤተክርስቲያን ውጪ ወደኾነው ሆስፒታል ብትሔዱ አንድ የቀዶ ጥገና ልዩ ባለ ሙያ (Specialist) አስቀድሞ የታካሚውን ቁስል ሳያይ የቁስል ፋሻን ማድረግ አይችልም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ አንደኛ በአንድ ጊዜ ብዙ ሕሙማን ይታያሉ፡፡ ኹለተኛ ሕክምናው የሚሰጠው በምሥጢር ነው፡፡ የእያንዳንዱን ኃጢአተኛ ኃጢአትን በአደባባይ አንናገርም፡፡ ከዚያ ይልቅ መጀመሪያ ኹሉንም አንድ ላይ እናስተምራለን፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ሕሊናውን እንዲያደምጥ እናደርጋለን፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ካስተማርነው ትምህርት እንደ በሽታው ዓይነት የሚስማማውን መድኃኒት እያነሣ ይወስዳል፡፡''

👉 የታመሙ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መሄድ ብቸኛ መፍትሄያቸው እንደሆነ ሁሉ በሐጢያት በሽታ ና በሰውነት ድካም ለምትሰቃይ ነፍሳችን እውነተኛ ማረፊያ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናት። እግዚአብሔር ለቁስላችን ፈውስ እንድትሆን አድርጎ በእርሷ እንድንፀና አቅም ሊሆነን መጠጊያ አድርጎ ሰጥቶናል። ለእያንዳንዱ የፀጋ ስጦታን የሰጠ ጌታ አንዱ በአንዱ እንዲፅናና እንዲተጋገዝ በእምነቱም እንዲበረታታ በምህረቱ ህብረትን መስርቶልናል። ተወዳጆች ስትደክሙ ወደ ሆስፒታላችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ተጠጉ🙏

© Mere-Protestantism
ኹሉም የእምነት ማሕበረሰብ "የኔ" የሚላቸው የእምነትና ሥነ ምግባር እሴቶች አሉት። አንኳርና አብይ ብሎ ሚያቀርባቸው የማንነቱና ንጽረቱ ማሳያዎችም አያጣም። በጊዜ ፈተና መንቀዝ እንዳይመጣ፤ ልማድና ትውፊቶቹም ተጠብቀው እንዲዘልቁ ፤ ትውልዳዊ ቅብብሎሹም እንዳይከስም ብዙ ሙከራ ይደረጋል። በዚህ ረገድ አንዳንድ የእምነት ማሕበራት ሲሳካላቸው አንዳንዶች ደግሞ ይነቅዛሉ።

ማንነትን አስጠብቆ መኖር ከልቀናቸው መኻል ፊተኞቹ እኛ ሳንሆን አንቀርም። ምሳሌ ላንሳ። ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት አንድን ወንጌላዊ አማኝ አስቁማቹ በቅርቡ በአውደ ምሕረታችሁ "የጸጋ አብዮት ፍንዳታ" በሚል መሪ ቃል ኬክ ቆረሳና በኬክ መራጨት ሊደረግ እንደሚችል ታስባለህ ወይ ብትሉት ሰማይና ምድር ካልተጣበቁ በቀር ይኽ ድርጊት በኛ አውደ ምሕረት ፈጽሞ አይከወንም ይላችሁ ነበር። ልበ ሙሉ ኾኖ፣ ፍርጥምም ብሎ የክስተቱን ርቁነት ያስረዳችሁ ነበር። ለታሪክ ባኖርነውና በሰነድነው ውድቀታችን ግን ኬኩም ተቆርሶ ስንራጨው ተገኘን።

ከአስር ዓመት በፊት "የዝማሬ ድግስ" ባልነው ክስተት መኻል ውሃ መራጨትና ሰንደቅ አላማ አንጥልጥሎ ማወዛወዝ ሊመጣ እንደሚችል የጠረጠረ ማን ነበር? ከጥቂት ዓመታት በፊት ጦርነት ቀድሰንና ባርከን ማዝመት እንደምንችል የገመተ ማን ነበር? በዚህ አማኝ ሕዝብ ፊት አይደረጉም ካልናቸው ነገሮች መኻል ያልተደረገ ምን አለ? አሁን በርግጥ በኛ መኻል መደረግ ማይችል ነገር እንደሌለ ብቻ ነው ማምነው! አብደትን ሚያስቀና ነገር ኹሉ በኛ መኻል ያለ ብዙ ተግዳሮት መከወን ይችላል።

ባለፎው የገና በአልን ምክንያት በማድረግ በኛ ስም ሚጠራ አንድ ወፈፌ ለጌታችን ልደት መታሰቢያ በጉባኤ መኻል ኬክ ቆረሰ። Happy birthday Jesus እያለ ሲለፋደድም ታየ። ትስጉትን ሚያክል ነገረ መለኮታዊ ጭብጥ ኬክ ቆረሳ ኾኖ ተልከሰከሰ። አሁን ያየሁት አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ደግሞ እንደ እምነት ማሕበረሰብ የገባንበትን አዘቅት ቁልጭ አድርጎ ሚያሳይ ኾኖ አግኝቼዋለው።

መደበኛ ጉባኤ መኻል የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምስል ነው። ዘማሪው መድረክ ላይ ኾኖ ያዜማል። ጉባኤውም አብሮት። በዚህ መኻል ዝማሬውና አምልኮው እየተደረገ ሳለ ኬክና አበባ የተሸከሙ እንስቶች ወደ ጉባኤው ይገባሉ። የባለ ራዕዩ ልደት መኾኑ ነው። ዝማሬን አስቁመን ልደት ማክበር ምንችል ሰዎች ልንሆን እንደምችል ጠርጥረን ቢኾን ኖሮ አወዳደቃችን ባልከፋ ነበር። አምልኮን አቋርጠን እኛ ወደ ምንመለክበት ጭንገፋ የደረስንበት ፍጥነት ይዘገንናል!!! እንደ እምነት ማሕበረሰብ መልሰን መልካችንንና እሴታችንን መቃኘት ይኖርብናል።

©ኢብሳ ቡርቃ
Audio
ልመንህ?

  ብዙ አብረን መጥተናል አሁን ተስፋ እንዳልቆርጥ
  ድምፅህ አልተለወጠም ከጉያህ እንዳልሮጥ
  ባይህ ባይህ ሁኔታ እንጂ አንተ አልተለወጥክም
  እንዳልከስህ ሰበብ አጣሁ ጥፋት የለብህም
  ባይህ ባይህ ህይወት እንጂ አንተ አልከፋህብኝም
  እንዳላማህ እቅም አጣው ጎኔን አልለቀክም


  ወይ ውስጤ ቆርጦ አልቆረጠ ወይ ተስፋ አላደረኩብህ
  አንተስ ምን ትለኛለህ ኢየሱስ ልጠይቅህ
  ልመንህ አይደለ? መረቤን ልጣለው?
  ከዚያ ከሚመጣው እጥፍ እጠግባለሁ?
  እንጀራዬን በውሀው ላይ አምኜ ልጣለው?
  ተመልሼ ስመጣ ወይ አገኘዋለሁ?


  የአንተ አላማ ውብ ነው ይህንን አዉቃለሁ
  እቅድህ ሰፊ ነው በደንብ አውቃለሁ
  ግን እንዴት ትስማ ይህቺ ነፍሴ ዝምብላ ትሰጋለች
  ምትወድቅ ይመስላታል ለፍርሃት ትረታለች

  ወይ ውስጤ....

  ይኸው ፀሎቴ በፊትህ
  ውስጤን አልደብቅ አልሸሽግህ
  የዘገየህ ቢመስል በእኔ ጊዜ ቀመር
  መኖርህን ልቤ ፍፁም አይጠረጥር
  ከነጎድጓድ በላይ ጮክ ብሎ ያወራል
  እኔ ፀጥ ካልኩኝ ዝምታህ ይሰማል

  ይኸው ፀሎቴ በፊትህ
  ውስጤ አይሸሸግ አልደብቅህ
  የዘገየህ ቢመስል በእኔ ጊዜ ቀመር
  መኖርህን ልቤ ፍፁም አይጠረጥር
  ከነጎድጓድ በላይ ጮክ ብሎ ያወራል
  እኔ ፀጥ ካልኩኝ ዝምታህ ይሰማል


ዝም እላለው በፊትህ ፀጥ
  ጊዜው ደርሶ መልስ እስክትሰጥ
  አላወራም እላለሁ ዝም ፣
  ዞር ብዬ አላማህም

  አዎን አምንሃለሁ መረቤን እጥላለሁ
  ከዚያ ከሚመጣው እጥፍ እጠግባለሁ
  እንጀራዬን በውሃው ላይ አምኜ እጥላለሁ
  ተመልሼ ስመጣ አዎ አገኘዋለሁ

© ዘማሪት ኢየሩሳሌም ወርቁ
ልዩት ሆኖ መኖር:-

* ለቅጽበታዊ ደስታ እና ርካታ በሚኖር ዓለም ውስጥ ለዘላለማዊ ግብ መኖር
* ከሁሉም አንደኛ ለመሆን በሚፈልግ ዓለም ውስጥ ሌሎችን ለማገልገል መኖር
* በቃኝ በማይል ዓለም ውስጥ ያለኝ ይበቃኛል ብሎ መኖር
* በእርኩሰት በሚኖር ዓለም ውስጥ በቅድስና መኖር
* ሁሉንም አንጻራዊ አድርጎ በሚቆጥር ዓለም ውስጥ በእርግጠኛነት መኖር

የሚቻለው በክርስቶስ ማንነትን ስናገኝ ብቻ ነው። We as a community of faith are to live the Gospel by being distinctive, so that the world can see the transformative power of God.
@ዛዲግ ብርሃኑ
በቤተክርስቲያን....
    ጭብጨባው በረታ
     ከበሮው ተመታ
    መድረኩ ተናጠ
     ቤቱ ተናወጠ
የምዕመናን ልብ ፥ በደስታ ቀለጠ

እነሆ
ደማቁ ዝማሬ ፥ በአዳራሹ ናኘ
በሆታ በእልልታ ፥ ኢየሱስ ተሸኘ

(ገጣሚ ዳዊት ፀጋዬ
💥 ለጥሪው መብቃት፡

ክርስትና የሆነውን ለመሆን (to become what we are) የምንጓዘው ጉዞ ነው።
* የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል፤ የእግዚአብሔር ልጆች ሊሆኑ የሚገባቸውን ግን ገና እየሆንን ነው።
* ቅዱሳን ሆነናል፤ ቅዱሳን ሊሆኑ የሚገባቸውን ግን ገና እየሆንን ነው።
* ተጠርተናል፤ የተጠሩ ሊሆኑ የሚገባቸውን ግን ገና እየሆንን ነው።
* ድነናል፤ የዳኑ ሊሆኑ የሚገባቸውን ግን ገና እየሆንን ነው።

👉 ክርስትና ያልሆነውን ለመሆን የሚደረግ ጥረት አይደለም። ወይም የሆነውን ወደ አለመሆን መመለስም አይደለም። ክርስትና ጉዞ ነው!! ጉዞው ወዴት ነው? ከተባለ የሆነውን ወደ መሆን የሚደረግ ጉዞ ነው!!!

ዛሬ ከጳውሎስ ጋር እንዲህ እንፀልይ እስቲ፡
“..አምላካችን ለጥሪው የበቃችሁ አድርጎ እንዲቈጥራችሁ፣ ....እንጸልያለን።”
  — 2ኛ ተሰሎንቄ 1፥11

* አምላካችን እንዲጠራችሁ እንፀልያለን አይልም። መጥራት የእግዚአብሔር ነው። ስለ ፀለይን አልተጠራንምና። ፀሎቱ የሚደረገው ለጥሪው ብቁ ያደርገን ዘንድ  ነው። ማለትም ለተጠራንበት ጥሪ የሚመጥን ህይወት ይኖረን ዘንድ የሚፀለይ ፀሎት ነው።

* አባት ሆይ የተጠራሁበት ጥሪ እጅግ ታላቅ ነው። በእኔ አቅም ና ጉልበት ለዚህ ጥሪ የሚመጥን ህይወት ይዤ መመላለስ አልችልም። ነገርግን ራሴን ለአንተ ሰጣለሁ። አንተ በፀጋህ ለጥሪህ ብቁ አድርገኝ።

©Mere-Protestantism
💥 ሚዛናዊ ትጋት

በሐዋርያትም ትምህርትበኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።” — ሐዋርያት 2፥42

ሶስቱን ነገሮች ተመለከታችሁ? የቀደመችው ቤተክርስቲያን የነበራት ብርታት በሶስት ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነው፡
👉 በሐዋሪያቱ ትምህርት
👉 በህብረት (እንጀራ መቁረስ= የጌታ እራት)  [ምስጢራት]
👉 በፀሎት

* የቀደመችው ቤተክርስቲያን ብርቱ የነበረችው እነዚህን ነገሮች በመያዟ ብቻ ሳይሆን በትጋት በመያዟ ነው። 'ይተጉ ነበር' የሚለው ቃል እጅግ አስደናቂ ነው!! የክርስቶስን መልክ በሙላት መያዝ የምኞት ሳይሆን የትጋት ውጤት ነው። በአሁኑ ዘመን ከብዙ ክርስቲያኖች ህይወት ትጋት ጠፍቷል። ብቅ ጥልቅ ባዩ ብዙ ነው። ትጋት አላቸው የሚባሉትም ቢሆኑ ሚዛናዊ ትጋት የላቸውም። ማለትም ወይ በትምህርቱ ብቻ 'ሲተጉ' ይገኛሉ ወይ ደግሞ በፀሎቱ ብቻ!! ነገርግን ክርስትና ''አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠንጥሎ'' በሚለው አይሆንም!! በሶስቱም ዘርፎች ላይ በሚዛናዊነት መትጋት አለብን። አንዱ ሌላውን አይተካም፤ አንዱም ያለሌላው አይሆንም!! ሰዎች አንዱን ሲጥሉ በጊዜ ሂደት ሌሎቹንም መጣላቸው አይቀርም።

እነዚህን ሶስት ነገሮች ነጣጥሎ በአንዱ ላይ ብቻ ትኩረት ለማድረግ መሞከር ግን የስሁት ቲዎሎጂ ሁሉ እናት ይመስለኛል። ለምሳሌ፡ አንዳንድ ፔንቴኮስታሎችን አስተውላችሁ ከሆነ ፀሎት ላይ በጣም በማተኮር ሌሎቹን ገለል ያደረጋሉ። ይህ ደግሞ ብዙ ጊዜ የስህተት ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ ልምምዶች እንዲነግሱባቸው ምክንያት ሲሆን ተመልክተናል። እንደ ካቶሊክ ያሉት ደግሞ ምስጢራት ላይ ያተኩሩ ና ሌሎቹን ትኩረት ይነፍጋሉ። አንዳንድ ኢቫንጀሊካልስ ደግሞ ቃሉ ላይ አተኩረው ሌሎቹን ያገላሉ።

👉 ነገርግን ቃሉም፣ ፀሎቱም እንዲሁም ምስጢራቱም በሚዛናዊ ትጋት ቢያዙ ትክክለኛ ክርስትያናዊ እድገት ይሰጡናል። ሚዛናዊ ትጋት ሚዛናዊ እድገት ያመጣልና። አንዱን መጣል ግን ሁሉንም ያስጥላል። ለዘመናችን በሶስቱም ትጉ የሆነች ቤተክርስቲያንን ጌታ ያብዛልን!!

* በግል ህይወታችሁ ደግሞ ሚዛናዊ እድገት ይኖራችሁ ዘንድ ለሁሉም ሰዐት መድቡ!! ለፀሎት፣ ለመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት እንዲሁም ለቤተክርስቲያን ህብረት የማይነካ ጊዜ ይኑራችሁ።

©Mere-Protestantism
ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ሞተ?
          


“እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥”
  (1ኛ ቆሮንቶስ 15፥3)


“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።”
       (2ኛ ቆሮ 5፥15)


“ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።”
            (ገላትያ 1፥4)


"እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።"
               (ኤፌሶን 2፥14-16)


“በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤”
     (ኤፌሶን 5፥25-26)


“በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤”
                 (ቆላስይስ 2፥14)


“የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።”
      (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥10)


“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ”
       (1ኛ ጴጥሮስ 2፥24)


“መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።”
               (ቲቶ 2፥14)


“በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።”
     (ዕብራውያን 10፥10)
💥 የተዋረደው ንጉስ
ሰብዐ ሰገል ለአይሁድ ንጉስ ለመስገድ ያላቸውን ሁሉ ሰብስበው ወደ ቤተ-መንግስት ገሰገሱ። መቼስ ንጉስ ከተባለ ቤተ-መንግስት እንጂ ከወዴት ሊገኝ ይችላል?? መጨረሻው ሲጠራ ግን ንጉሱ በቤተመንግስት ሳይሆን በበረት ተኝቷል። አሄ ምን ይባላል??

ንጉሱ በበረት
ንጉሱ በስደት
ንጉሱ በናዝሬት
ንጉሱ በመከራ
ንጉሱ በክስ
ንጉሱ በድካም
ንጉሱ በስድብ
ንጉሱ በመከዳት
ንጉሱ በመገረፍ
ንጉሱ በመናቅ
ንጉሱ በመተፋት
ንጉሱ በመገፋት
ንጉሱ በቁስል
ንጉሱ በመድቀቅ
ንጉሱ በብቸኝነት
ንጉሱ በመስቀል!!!

እንደ ንጉስ ያልኖረ ብቸኛ ንጉስ! በማንነቱ ንጉስ ነው፤ በኑሮው ግን በባርያ ያልደረሰው ደርሶበታል! ኑሮውን ያዩ፣ ስቃዩን ያዩ ''የአይሁድ ንጉስ'' ብለው ዘበቱበት። ''ራስህን አድን'' እያሉ ተሳለቁበት!! እርሱ ግን ...

##ለኔ ነው ጌታ ሆይ!!!

© Mere-Protestantism
ሄኖክ ኃይሌ፣ “ሰባኪ” ከኾነ ከመጽሐፍ ለምን አይጠቅስም?


ሄኖክ ሃይሌ፣ ለጳጳሱ አባ ገብርኤል በመለሰው መልስ ውስጥ እንዲህ የሚል ንግግር አለው፣
“ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና … ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም። ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን።”

ነገሩን ግልጽ ለማድረግ፣ ሙሴ “ቤዛ” የተባለበትን ዐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማየቱ እጅግ መልካም ነው። በታላቁ መጽሐፍ ውስጥ በእስጢፋኖስ አንደበት፣

“ … ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።” (ሐ.ሥ. 7፥35)

ተብሎ ተጠቅሶአል። ስለ ሙሴ ጥቂት እንናገር፣ ሙሴ በግብፃዊቷ ልዕልት ቤት ያደገ ዕብራዊ ሰው ነበር (ዘጸአት 2፥1-10)። ለእኛ ባልተገለጠና የመጀመሪያው ዘገባ በማይገልጠው መንገድ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከባርነት ነፃ ለማውጣት እግዚአብሔር እንደ ላከው ያውቅ ነበር (ሐ.ሥ. 7፥25)። በመጀመሪያ ሙከራው ሙሴ ዕብራዊውን እየደበደበ ያለውን ግብፃዊ ሰው ገደለ። በማግስቱ፣ እስራኤላውያን ረድኤቱንና ሥልጣኑን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ግድያውን እንደሚያውቁ ተገነዘበ። ፈርዖን ሳይገድለው ሙሴ ወደ ምድያም ምድር ሸሸ (ዘጸ. 2፥11–15)።

በምድያም፣ ሙሴ የካህን ሴት ልጅ አግብቶ የአማቱን በጎች ይጠብቅ ጀመር። እሱ ከደረሰ ከአርባ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር በቁጥቋጥ ተገለጠለት (ዘጸ. 3፥4)፤ እስጢፋኖስ ለሙሴ የተገለጠው መልአክ እንደ ኾነ ተናገረ፣ በብሉይ ኪዳን ደግሞ “የእግዚአብሔርን መልአክ” ተብሎ በብዙ ስፍራ የተጠቀሰው፣ በኋለኛው ዘመን ሥጋ የለበሰውን ክርስቶስን እንደሚያመለክት እሙን ነው። እስጢፋኖስ ያንን እዚህ ላይ ቢያብራራ ጠቃሚ ይሆናል፤ ግን አላደረገም።

ሙሴ ወደ ምድያም ከመሸሽ በፊት፣ አንድ እስራኤላዊ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ያደረገህ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። (ዘጸ. 2፥14) “አለቃ” የሚለው ቃል፣ የንጉሥ ፈርዖን ባለሥልጣንን ወይም ተወካይን ያመለክታል። “ፈራጅ - ዳኛ” ደግሞ፣ ሕጋዊ ውሳኔ ለመስጠት ሥልጣን ያለው ሰው መኾኑን። እስጢፋኖስ፣ ሙሴ እውነተኛ ገዥና የአምላክ ወኪል እንደ ነበረ ገልጾአል። ከዚህም በላይ አምላክ እስራኤላውያንን አዳኝ እንዲኾን መረጠው። ተከራካሪዎቹ እስራኤላውያን፣ ሙሴን የፈርዖን ፍርድ ቤት ተወካይ አድርጎ የሰጠውን አቋም በመሳለቅና በመቃወም አልተቀበሉትም፤ ሙሴ እነርሱን ለማዳን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከ አላስተዋሉምና።

በርግጥ ሙሴ ለእስራኤል ዘሥጋ ታዳጊና ቤዛ ኾኖ ተልኮ ነበር፤ ዋና ዓላመውም፤ ከፈርዖን ቤት፤ ከባርነት ቀንበር ነጻ ለማውጣት ነውና። ሙሴ ራሱ ግን ፍጹም ቤዛና አዳኝ እንዳልኾነና ከርሱ የሚበልጥ ሌላ እንዳለ ሲናገር እንዲህ አለ፤ “ይህ ሰው[ሙሴ] ለእስራኤል ልጆች፦ እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት ያላቸው ሙሴ ነው።” (ሐ.ሥ. 7፥37) አስተውሉ፤ እስጢፋኖስ ይህን እየተናገረ ያለው፣ አሻግሮ ስለ ኢየሱስ እንጂ ስለ ሙሴ እንዳልነበረ በመደምደሚያው እንዲህ አለ፣ “… በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን[ክርስቶስን] አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም።” (ሐ.ሥ. 7፥52-53) ይላል።
ሙሴ ምንም ለእስራኤል ዘሥጋ “ቤዛ” ቢባልም፣ በጥላለነት ያገለገለው እስራኤል ዘነፍስን በቤዝወቱ ነጻ ላወጣው ለኢየሱስ ነው። በሌላ ንግግር ሙሴ ያገለገለው፣ የኢየሱስን አገልግሎት በጥላነት ነው። አካሉ ሲመጣ ደግሞ ጥላው በራሱ ጊዜ ስፍራውን ለአካሉ ይለቅቃል፤ ኢየሱስ ባለበት ሙሴ ደግሞ ዘወትር ባሪያና አገልጋይ ብቻ ነው።
“ዲያቆን” ሄኖክ ግን፣ የትክክለኛውን ዲያቆን እስጢፋኖስን ንግግር እንኳ አንብ ሳያስረዳ፣ ማርያምን ከክርስቶስ በላይ እንደሚመለከታት፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” በሚለው ንግግሩ ይታወቃል። ለዚህ ንግግሩም ከዓመታት በፊት በጡመራ መድረኬ መልስ ሰጥቼበታለሁ። ከዚህ በዘለለ፣ በሰሞኑ በአባ ገብርኤል “ማርያም ለኀጢአታችን ቤዛ አይደለችም” በሚለው ትምህርት ዙሪያ፣ ብዙ ስድብና ዘለፋ ካቀረበ በኋላ በመቋጫው ከላይ የጠቀስሁትን ተናግሮአል።
“ዲያቆን” ሄኖክ፣ ያስተማሩት ክህደት ነው ሲል፣ ምኑ ክህደት እንደ ኾነ አይናገርም፤ የኢየሱስ ቤዛ መባልንና በትክክል መኾንን አንድም ቦታ ሳይናገር[ይህ ለአንድ ሰባኪ የሞት ያህል መራራ ነው!]፣ የሙሴን “ቤዛ” መባል ግን ዋቢ ይጠቅሳል፤ ሙሴ “ቤዛ” ቢባል፣ መሲሑን ተክቶ ለእስራኤል ደሙን አፈሰሰን? ከኀጢአት ባርነት ሕዝቡን ነጻ አወጣን? ሕዝብን ከሰው አገዛዝ ባርነት ነጻ አውጥቶ መምራቱ “ቤዛ” ቢያስብለው፣ እንደ ኢየሱስ “ቤዛችን ሙሴ ሆይ፤ ምትክ ኾነህ ሞተኽልናልና” ተብሎ ሊጠራ ነውን?

ጳጳስን “ሰንበት ተማሪ” ብሎ መሳደብ፣ አይከብድ ይኾናል፤ እንዲህ ያለ ከሰንበት ተማሪ ያነሰ ዕውቀት ይዞ “በስመ ደጋፊ ብዛትና በዕብጠት” መናገር ግን “እባብ እያስተፉ ዘንዶ የመዋጥ ያህል” ይቀፍፋል። በርግጥ እነ ዘበነ ለማና ምሕረተ አብ አሰፋ በኢየሱስና በመጽሐፍ ቅዱስ “ሲሸቅጡ”፣ ምንም ሊባሉ አይችሉም፤ ማርያምን እስካልነኩ ድረስ የሚናገራቸው አይኖርም!

የኢየሱስ ቤዝወትና አስታራቂነት ሲነገር ግን፣ ሄኖክና ባልንጀሮቹ ይንጨረጨራሉ፤ እርር ኩምትር ይላሉ፤ ምክንያቱን በትክክል ባልረዳም፣ ከጤናማ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የሚወጣ ባህርይ እንዳልኾነ የተገለጠ ነው። ስለ ኢየሱስ አትጻፉ፤ ማርያምንም አምልኩ፣ ግን እንዴት ስለ ኢየሱስ ሲነገር እንዲህ ይከፋችኋል?! ጌታ ይገስጻችሁ!

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6:24) አሜን።

© ዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ