"የእነ እገሌ ስብከት"
ትውልዱ ይዘጋጅ ቀይ ባህር ይመለስ፣
ልክ እንደ ውሃችን ደማችሁም ይፍሰስ።
እኛም እንላለን....!
ለባህር በራችን ካልቀረ ክተቱ፣
የደሃ ልጅ ደሙ ከሚፈስ በከንቱ፣
በፊት ይሰለፉ ባለስልጣናቱ።
ገጣሚ ጊዜአለው
ትውልዱ ይዘጋጅ ቀይ ባህር ይመለስ፣
ልክ እንደ ውሃችን ደማችሁም ይፍሰስ።
እኛም እንላለን....!
ለባህር በራችን ካልቀረ ክተቱ፣
የደሃ ልጅ ደሙ ከሚፈስ በከንቱ፣
በፊት ይሰለፉ ባለስልጣናቱ።
ገጣሚ ጊዜአለው
👎2
#ጠርጥር፦
1. መጀመሪያ ደግነት የሚያበዛ
👉 አድሮ አደገኛ ነው!
2. ድንገት በአፉ የሚደልልህ
👉 የሚወስድብህ ነገር አለው!
3. ከመሬት ተነስቶ የሚያነግስህ
👉 ከመሬት ተነስቶ የሚጥልህ ነው!
4. ጓዳህ ድረስ የሚያውቅህ
👉 በጓዳ ምስጢርህ የሚነግድ ነው።
5. ላገኘው ሁሉ የሚያወድስህ
👉 ላገኘው ሁሉ የሚያማህ ነው!
ጠርጥር ሳትመነጠር።
1. መጀመሪያ ደግነት የሚያበዛ
👉 አድሮ አደገኛ ነው!
2. ድንገት በአፉ የሚደልልህ
👉 የሚወስድብህ ነገር አለው!
3. ከመሬት ተነስቶ የሚያነግስህ
👉 ከመሬት ተነስቶ የሚጥልህ ነው!
4. ጓዳህ ድረስ የሚያውቅህ
👉 በጓዳ ምስጢርህ የሚነግድ ነው።
5. ላገኘው ሁሉ የሚያወድስህ
👉 ላገኘው ሁሉ የሚያማህ ነው!
ጠርጥር ሳትመነጠር።
❤3
የአሁኑ ህይወታችን ልክ እንደተቆራረጠ ኢንተርኔት ነው። አለ ለማለት ይከብዳል፣ የለም ለማለትም ይከብዳል።ሁላችንም አንድን ነገር ለማድረግ እንነሳለን፣ ግን ደግሞ አቅም የለንም። እንስቃለን፣ ግን ደግሞ ሳቃችን ውስጣችን አይደርስም። እናዝናለን፣ ግን እንባ የለንም። ይህ የመደንዘዝ ሁኔታ ትልቁ ስቃይ ነው።
ስሜት ሲጠፋ ነው ሰውነታችንን የምናጣው። በዙሪያችን ያለው ዓለም እየተናወጠ ቢሆንም፣ እኛ ግን በሐዘን ባህር ውስጥ መስጠም ሰልችቶን በላዩ ላይ እንደ ግዑዝ ነገር እየተንሳፈፍን ነው። ማንነታችን አለ ይባላል እንጂ፣ እውነተኛው ማንነታችን ከሐዘን ማዕበል ስር ተቀብሮ ቀርቷል።
ጀምስ ክሌር
ስሜት ሲጠፋ ነው ሰውነታችንን የምናጣው። በዙሪያችን ያለው ዓለም እየተናወጠ ቢሆንም፣ እኛ ግን በሐዘን ባህር ውስጥ መስጠም ሰልችቶን በላዩ ላይ እንደ ግዑዝ ነገር እየተንሳፈፍን ነው። ማንነታችን አለ ይባላል እንጂ፣ እውነተኛው ማንነታችን ከሐዘን ማዕበል ስር ተቀብሮ ቀርቷል።
ጀምስ ክሌር
❤3
"መኖር የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው!"
በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው! ረሀብ የለም። በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው ብርድ የለም። ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም ምቾት፣ መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሀ ውስጥ መንሳፈፍ ነው። ግን ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድክበት ቅፅበት ይለወጣል።
መተንፈስ ግድ ይላል! ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን ለመኖር፤ አለበለዚያ መኖር የለም! መታፈን፣ በረሀብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሀታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ። በእናታችን ማህፀን ውስጥ የምናውቀው መኖርን ብቻ ነው። መወለድን ግን አለመኖርን አመላካች ነው!
.......
አለመኖር
በዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ

#ተገትረህ_አትቅር
ትናንት፦
ከገንዘብ ፍቅር ይበልጣል ያሉህ
ዛሬ፦
ገንዘብ ስሌለህ ይንቁሃል!
ትናንት፦
ጠንክረህ ተማር ያሉህ
ዛሬ፦
መማርህ የት አደረሰህ ይሉሃል!
ትናንት፦
በጉብዝናህ ያደነቁህ!
ዛሬ፦
ጎበዝ ሰርቶ የሚለወጥ ነው ይሉሃል!
ዛሬህን ምሰል! ባለፈ ሀሳብ ተገትረህ አትቅር!
@Goldanmind
ትናንት፦
ከገንዘብ ፍቅር ይበልጣል ያሉህ
ዛሬ፦
ገንዘብ ስሌለህ ይንቁሃል!
ትናንት፦
ጠንክረህ ተማር ያሉህ
ዛሬ፦
መማርህ የት አደረሰህ ይሉሃል!
ትናንት፦
በጉብዝናህ ያደነቁህ!
ዛሬ፦
ጎበዝ ሰርቶ የሚለወጥ ነው ይሉሃል!
ዛሬህን ምሰል! ባለፈ ሀሳብ ተገትረህ አትቅር!
@Goldanmind
👍1
ሀብታም ነኝ ብለህ የምታስበው በባንክ ሂሳብህ ባለው የገንዘብ መጠን ከሆነ ተሳስተሀል። ትክክለኛው ጥያቄ፡- "ዛሬ ስራ መስራት ብታቆም፣ ያጠራቀምከው ገንዘብ ወይም ንብረት ለስንት ጊዜ በህይወት ያቆይሀል?" የሚለው ነው።
"ሀብታም ሰው ማለት ስራ ባይሰራም እንኳ ንብረቱ የኑሮ ወጪውን የሚሸፍንለት ሰው ነው። ድሃ ማለት ግን ስራው ሲቆም ህይወቱ የሚቆምበት ሰው ነው።
📕ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ
📚 @Goldanmind
"ሀብታም ሰው ማለት ስራ ባይሰራም እንኳ ንብረቱ የኑሮ ወጪውን የሚሸፍንለት ሰው ነው። ድሃ ማለት ግን ስራው ሲቆም ህይወቱ የሚቆምበት ሰው ነው።
📕ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ
📚 @Goldanmind
👍2
የሰው ልጅ በህይወት ለመኖር የሚያስፈልገው ምግብ፣ ውሃና መጠለያ ናቸው። ስንፈጠር የነበረው እውነታ ይህ ነው፤ እነዚህን መሰረታዊ ነገሮችም በነፃ ያገኝ ነበር። በዃላ ሰለጠንኩ ዘመንኩ ብሎ በቡድን በመንጋ ማሰብ ሲጀምር በንጉስና ፖለቲከኞች መተዳደር ጀመረ ..... ከዛ ምግብ፣ ውሃና መጠለያ ከፖለቲከኞቹ እየለመነ መኖር ቀጠለ።
❤1👍1🔥1
የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት
በህይወት መኖር በራሱ ትልቅ ፍርሃት ነው። ትልቁ ፍርሃት ሞት አይደለም፤ በሕይወት የመኖርን አደጋ (risk) መጋፈጥ እንጂ፡፡ የሰው ልጅ ትልቁ ፍርሀት እራሱን የመሆን ፍርሃት ነው።
ከልጅነታችን ጀምረን የተማርነው የሌሎች ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት መኖርን ነው። ተቀባይነት ማጣትን እና በሌሎች አይን በቂ ሆኖ አለመታየትን አምርረን ስለምንጠላ፣ በሌሎች ሰዎች አመለካከት ታስረን መኖር እጣ ፈንታችን ሆኗል፡፡

👍2❤1
"ማህበረሰቡ የተወለድክበትን የመጀመሪያውንና እውነተኛውን ማንነትህን ይወስድብሃል፤ በእሱ ምትክ ደግሞ ሌላ ሰው ሠራሽ ማንነት ይሰጥሃል።
ስም ይሰጥሃል፣ ሃይማኖት ይሰጥሃል፣ የማህበራዊ ደረጃ ይሰጥሃል... ከዚያም ያንተ እውነተኛ ማንነት በነዚህ ተደብቆ ይረሳል። አንተም በሰዎች ፊት የምትለብሰውን ጭንብል እውነተኛው ማንነቴ ነው ብለህ ማመን ትጀምራለህ።
በእውነተኛው ማንነትህና በለበስከው ጭንብል መካከል ትልቅ ክፍተት ይፈጠራል። የጭንቀትህ፣ የብቸኝነትህና የውስጥ መታወክህ ምስጢር ይሄው ነው!
የለበስከውን ጭንብል አውልቀህ ስትጥልና ወደ ገዛ እውነተኛ ተፈጥሮህ ስትመለስ ብቻ ነው ፍጹም ሰላምና ደስታ የሚሰማህ።"

ደፋርና የተግባር ሰው መሆን!
በጣም የሚያስፈሩህ ነገሮች ከብዙ ነገር ያስቀሩሀል፤ እንደ ንፋስ ሽው ብሎ ለሚያልፈው ዘመንህ እስከመቼ በፍርሀት ትኖራለህ? ምንም ነገር እስክትጀምረው ድረስ ነው ልብህ የሚያመነታው።
መሳሳት የማይፈልግ ሰው ጥጉን ይዞ ይቀመጥ፤ ስኬትና ደስታ ያለው ግን ከፍርሀትህ ጀርባ ነው። ቆራጥ መሆን ምርጫ ነው እንጂ ዕድል አይደለም! ያመንክበትን ለማድረግ፣ የምትፈልገውን ሰው ለመሆን ደፋርና የተግባር ሰው መሆን አለብህ!

#ለድህነት_አፍቃሪዎች_በሙሉ
ገንዘብ ደስታን እገዛም ብላችሁ አትሸወዱ
ገንዘብ 5ቱን ይገዛል
1. እንደፈለጉ የመኖር ነጻነትን
ጠዋት በዝናብ፣ ከሰአት በጸሐይ
መደብደብ የሚቀርልህን ገንዘብ ካለህ ነው።
2. ከፈጣሪ በታች ዋስህ ነው
ብትታሰር ያስፈታሃል፣ ብትታመም ያሳክምሃል።
3. የእድል በርህን ይከፍትልሃል
አመድ ለአመድ አትንከራተትም። ቀጥ ብለህ
ሸራተንና ሂልተን ትገባለህ።
4. የአእምሮ ሰላም ይሰጥሃል
ኪራይ ደረሰ ብለህ እንቅልፍ አታጣም።
ታክሲ ተወደደ ብለህ አታለቃቅስም።
5. ለወገንህ ደራሽ ያደርግሃል
ማገዝ ያለብህን ታግዛለህ እንጂ ከንፈርህን መጥጠህ
ብቻ አታልፈውም።
ገንዘብ ደስታን እገዛም ብላችሁ አትሸወዱ
ገንዘብ 5ቱን ይገዛል
1. እንደፈለጉ የመኖር ነጻነትን
ጠዋት በዝናብ፣ ከሰአት በጸሐይ
መደብደብ የሚቀርልህን ገንዘብ ካለህ ነው።
2. ከፈጣሪ በታች ዋስህ ነው
ብትታሰር ያስፈታሃል፣ ብትታመም ያሳክምሃል።
3. የእድል በርህን ይከፍትልሃል
አመድ ለአመድ አትንከራተትም። ቀጥ ብለህ
ሸራተንና ሂልተን ትገባለህ።
4. የአእምሮ ሰላም ይሰጥሃል
ኪራይ ደረሰ ብለህ እንቅልፍ አታጣም።
ታክሲ ተወደደ ብለህ አታለቃቅስም።
5. ለወገንህ ደራሽ ያደርግሃል
ማገዝ ያለብህን ታግዛለህ እንጂ ከንፈርህን መጥጠህ
ብቻ አታልፈውም።
👍3👏1
በእኛ ሀገር ጠቢብ መሆን አብሪ ትል መሆን ማለት ነው፡፡ አብሪ ትል ከሌሎች ትሎች የሚለየው ገላው እንደፍም ማብራቱ ነው፡፡ ታድያ ብላቴኖች በጨለማ ሲያበራ ሲያዩት በገዛ ብርሃኑ ተመርተው ይመጡና አንስተው ይጨፈልቁታል፡፡ ለጠላቶቹ መንገድ ከማሳየት አልፎ የገዛ ብርሃኑ ለምንም አይጠቅመውም፡፡ ”
© በዕውቀቱ ሥዩም (ጉባኤው )
© በዕውቀቱ ሥዩም (ጉባኤው )
👍4
«እግዚአብሔር ነኝ ካላልክ በስተቀር ይኽን እርስበርስ የሚጠፋፋ ዛራም (ዘረኛ) ትውልድ አስተምሬ አድናለሁ አትልም። ለዚህ ትውልድ ብዬ እነሱ የሚፈልጉትን አይነት ፊልም አልሰራም። ምሁርነትና ዘረኝነት አብሮ አይሄድም። እሳት የላሰ፣ ምርጥ ትውልድ ይወለዳል፤ ይመጣል። እነሱ ሲመጡ እንዳይሳሳቱ መንገዱን (map) ማሳየት አለብህ፤ እምነትህን በጽሑፍ ይኹን በፊልም ቀርጸህ ለእነሱ ማስተላለፍ አለብህ። ለእነሱ ነው ፊልም የምሠራው።»
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ
👍3