ጎህ ሲቀድ-Goh Siked
15 subscribers
90 photos
23 links
Download Telegram
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ነጥቦች

የተሰበረውን በመጠገን፣ ልዩነቶቸን በማጠበብ፣ የተጣመመውን በማቃናት እና ስህተቶችን በማረም ሀገርን በማይናወጥ መሰረት ልናፀና ይገባል፣ ቆም ብለን የመጣንበትን መንገድ ገምገመን ያተረፍንበትን በማጠናከር የከሰርንበትን ደግሞ ማስተካከል ይኖርብናል፣ ያደጉ የምንላቸው ሀገራት ዛሬ ላይ የደረሱት ልዩነት ሳይኖራቸው ቀርቶ ሳይሆን ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት በመቻላቸው ነው፣ ትላንት ለነገ ትምህርት እንጂ እንቅፋት ሊሆን አይገባም፣ የትናንት ታሪክ የአብሮነት መገንቢያ እንጂ የልዩነት መሆን የለበትም።
ባንኩ ያወጣቸውን አዳዲስ ክፍት የስራ መደቦች ለመመልከት ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የሊንክድኢን ገጹን ይመልከቱ፡፡
https://www.linkedin.com/company/awash-bank-s-c/

Gita hojii haaraa baankiin Awaash baase geessitu armaan gadii cuqaasuun fuula Liinkidiinii baankichaa irraa daawwadhaa.
https://www.linkedin.com/company/awash-bank-s-c/
Live stream started
ይህ ቡካዮ ሳካ ነው 'ጥቁሩ ጋሪንቻ' ከመድፉ መንደር አብዛኛው ተመልካች ሙሉ ስሙን በዉል ለይቶ አያውቀውም። ቡካዮ አዮይንካ ተሚዳዮ ሳካ ይባላል። እንደ አውሮፓውያኑ የግዜ ቀመር መስከረም 5 2001 ዓ.ም ከናይጄሪያውያን ስደተኛ ቤተሰቡ በታላቋ ብሪታኒያ 'ኤሊንግ' ውስጥ ተወለደ። 1:78 ሳ.ሜ የሚረዝመው ሳካ ከደቡባዊ ናይጄሪያ 'ያሩባ' ከሚባል ጎሳ የሚመዘዘው የዘር ሀረጉ እንደ ብሄረሰቡ ትርጓሜ ሳካ ማለት ደስታን የሚጨምር ወይም ተጨማሪ ደስታ እንደማለት ነው። ይህ የጥቁር ፈርጥ ከቤተሰቡ አልፎ ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ የደስታ ምንጭ ሊሆን በምትሀተኛው ግራ እግሩ የአለምን ኳስ ተመልካች ሊያስደምም መንገድ ከመጀመሩ በፊት ፊደል መቁጠር ነበረበት። በዚህም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እዛው በተወለደበት እንግሊዝ 'ኤድዋርድ ቤታም ቸርች ኦፍ ኢንግላንድ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን 'በግሪን ፎርድ' ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል።

በትምህርቱም የቀለም ቀበኛ እንደ ሀገራችን አባባል ' ጎጫ' የሚባል ተማሪም እንደሆነ ይነገርለታል። እሱ ግን የተፈጠረው ለእግር ኳስ ነበር ያለ ኳስ ውሎ ማደር አይችልም ለእግር ኳስ የተፈጠረ ኮከብ። ምንም እንኳን በቀለም ትምህርቱ የበረታ ተማሪ ቢሆንም  ኳስ አሸነፈችው እጁን ሰጠላት። ይህንን የተረዱት ቤተሰቦቹ ልክ እድሜው 5 ሲሞላ የዋትፎርድ ወጣቶች አካዳሚን እንዲቀላቀል አደረጉት። ብዙም አልቆየ ዕድሜው 7 ሲሞላ ዛሬ ላይ መሰረት ወደ ጣለበት የአርሰናል ወጣቶች  አካዳሚ ወደ ሆነው ' ሀሌ ኢንድን' ተቀላቀለ። በአካዳሚውም ከዕድሜው በላይ በመብሰል ሁሉንም የአርሰናል ቤተሰቦች ማስደመሙን ተያያዘው ። በጣም የሚያስገርመው ሳካ በአርሰናል ወደ ዋናው ቡድን ለማደግ ግዜ አልፈጀበትም። ለሁሉም የእድሜ እርከኖች ለአርሰናል መጫወት የቻለው ሳካ እንደ አውሮፓውያኑ የግዜ ቀመር በኖቬምበር 29,2018 በኢሮፓ ሊግ አርሰናል ከፖልታቫ ጋር ባደረገው ጨዋታ ለመጀመሪያ ግዜ በሲኒየር ደረጃ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ መጫወት ቻለ በወቅቱም የ 17 አመት ታዳጊ ነበር። በዚህም አልተወሰነም ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ለሁሉም እድሜ እርከኖች ተጫውቶ አሳልፏል። በዚህም:-

   -ከ2016 - 2817 ለ16 አመት በታች 6ጨዋታ አደረገ   - ከ2017- 2018 ለ17 አመት በታች 9 ጨዋታ አደረገ   -2018 ለ18 አመት በታች 5 ጨዋታ አደረገ
-ከ2018- 2019 ለ19 አመት በታች 10 ጨዋታ አደረገ

-ከ2020 ለ21 አመት በታች 1 ጨዋታ አድርጎ በዛው አመት ለመጀመሪያ ግዜ ለዋናው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጠርቶ መጫወት ቻለ። የሳካ የእግር ኳስ ሂወት በውጣ ውረዶች የተሞላ ነው። በጥቁርነቱ ከሚደርስበት መገለል ባለፈ ለስደተኞች ምቹ እንዳልሆነች በሚነገርባት እንግሊዝ  ምድር በቅሎ በምርጥነቱ አለም በአንድ ድምፅ የሚመሰክርለት ኮከብ ለመሆን በቅቷል። ታታሪ እና ዝምተኛ ነው ሳቅ እና ፈገግታ ከፊቱ ማይጠፋ እውነተኛ ፕሮፌሽናል እንደስሙ ደስታን ፈንጣቂ ከቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ይልቅ እሱ ተሽሎ የተመረጠ ኮከብ አዎ 'እውነት እልሀለው የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ባንበላ እድሜ ልካችንን እንቅር ሳካ ከሚሸጥብን' ይህ የአርሰናል ደጋፊዎች ምርጫ ነው ጥቁሩ ጋሪንቻ ከመድፉ መንደር አሁን ላይ አለም ላይ ካሉት ምርጥ የግራ መስመር የክንፍ አጥቂዎች ተርታ ይመደባል እሱ የአርሰናል ልብ ምት ነው። የ23 አመቱ የመድፉ ጦር ግራ አዝማች።እስካሁን በእግርኳስ ሂወቱ በሲኒየር ደረጃ ለክለቡ አርሰናል 196 ጨዋታዎችን አድርጎ 44 ጎል ከመረብ ሲያሳ ለሀገሩ በ30 ጨዋታ 11 ጎል አስቆጥሯል።
አዋሽ ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን መፍረሳቸው ተሠምቷል
በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡
በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።
በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎች ገልጸዋል።
ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት
2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።
"የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል" ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱን ገልጿል።
የአካባቢው ነዋሪዎች የትናንቱ መንቀጥቀጥ ተወሰኑ ቤቶችን እንዳፈረሰ፣ መሬትን እንደሰነጠቀ እና በተለይ እንስሳት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገቡ ገልጸዋል::
የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ትናንት እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች መናገራቸውን አሐዱ ዘግቧል።
በ40 ዓመቷ በጨጓራ ካንሰር ከመሞቷ በፊት በዓለም ታዋቂው ዲዛይነር እና ደራሲ “ክሪስዳ ሮድሪጌዝ” እንዲህ ስትል ፅፋለች።

1. ጋራዥ ውስጥ የአለማችን ውድ መኪና ነበረኝ፣ አሁን ግን በዊልቸር መንቀሳቀስ አለብኝ።

2. ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸው ልብሶች፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች ይሸጣል፣ አሁን ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል።

3. በባንክ ውስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ።  አሁን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም።

4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለሁ።

5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል.  አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመንቀሳቀስ ጊዜዬን አሳልፋለሁ

6, በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገርግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸው።

7, ፀጉሬን ለመስራት ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ ፣ አሁን ግን - በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም።

8, በግል ጄት ላይ፣ የትኛውም ቦታ መብረር እችላለሁ፣ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዎች ያስፈልጉኛል።

9, ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም, አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ክኒን እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨው ውሃ ጠብታዎች ናቸው::

10, ይህ ቤት፣ ይህ መኪና፣ ይህ አውሮፕላን፣ ይህ የቤት ዕቃ፣ ይህ ባንክ፣ ብዙ ዝናና ዝና፣ አንዳቸውም አይመጥኑኝምነበር። አሁን ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም ሊደርሱልኝ እና ሊጠቅሙኝ አልቻሉም፡፡ 

“የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ማን ናቸው?
...
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ 1 ሺህ 300 በሚጠጉ ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ከአውሮፓ ውጭ ያሉ የቫቲካን መንበር የበላይ ጠባቂ ናቸው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትሁት፣ ወደፊት የሚመለከቱ፣ የሞት ቅጣት እና የሴቶች ሚና የመሳሰሉ ማኅበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምትከተለውን ቀኖና ለማቅለል ጥረት ያደረጉ እንደሆነም ይነገርላቸዋል።
በዛሬው ዕለት 88 ዓመታቸው ቫቲካን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ያረፉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እ.አ.አ ታኅሣሥ 17 ቀን 1936 ፍሎረስ ቡኖስ አይረስ፣ አርጀንቲና ውስጥ ነበር የተወለዱት።
የሕይወት ጉዞአቸው ምን ይመስል ነበር
• እ.አ.አ በ1958 በ21 ዓመታቸው ወደ ኢየሱሳውያን ማኅበር (ጀስዊቶች) ተቀላቀሉ፤
• በ1969 የካቶሊክ ቄስ ሆነው ተሾሙ፣
• አርጀንቲና በሚገኘው የኢየሱሳውያን ኮሌጆች ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ሥነ ጽሑፍ አስተምረዋል፤
• ከ1973 እስከ 1979 በአርጀንቲና የሚገኘው የኢየሱሳውያን ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሆነው ሠርዋል፤
• በአርጀንቲና ወታደራዊ አምባገነናዊ አገዛዝ ወቅት ጠንካራ መንፈሳዊ አቋም በመውሰድ አገዛዙን በመቃወም ይታወቃሉ፤
• በ1992 የቦነስ አይረስ ረዳት ጳጳስ ሆነው ተሾሙ፤
• በ1998 ካርዲናል ኳራሲኖ ሕልፈት በኋላ የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ፤
• በቀለል ያለ አኗኗራቸው የሚታወቁት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፣ ቀለል ባለ አለባበስ፣ ለትራንስፖርት የሕዝብ መጓጓዣዎችን እንዲሁም ለመኖሪያ አነስተኛ የሆኑ አፓርታማዎችን ይጠቀሙ ነበር፤
• በ2001 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዳግማዊ ጆን ፖል ወደ ካርዲናልነት ከፍ አደረጉአቸው፤
• በማኅበራዊ ፍትሕ ረገድ ለድሆች እና ችግረኞች ጥብቅና በመቆም መልካም ስምን አትርፈዋል፤
• መጋቢት 13 ቀን 2013 266ኛውን የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል፤
• የአየር ንብረት እንቅስቃሴን እና በሃይማኖቶች መካከል ንግግር እንዲኖር በማበረታታት ይታወቃሉ፤
• በቫቲካን እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዲካሄድ ያበረታታሉ፤
• በአየር ንብረት እና አከባቢ፣ በወንድማማችነት እና በማህበራዊ ወዳጅነት እንዲሁም በቤተሰብ ፍቅር ላይ ያተኮሩ ሦስት መጽሐፍትን አሳትመዋል፤
• ስፓኒሽ፣ በጣሊያንኛ እና ላቲን ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ይናገራሉ፤
• ለእግር ኳስ፣ ለታንጎ እና ለሥነ ጽሑፍ ጥልቅ ፍቅር አላቸው፤ EBC
🦠 የቶንሲል ሕመም | Tonsillitis

ቶንሲል ህመም ለኩላሊት መድከም፣ ለልብ ህመም፣ እና ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል ያውቃሉን?

በታዳጊ አገራት እድሜያቸው ከ 5 እስከ 15 ባሉ ልጆች ላይ የሚከሰተው የልብ በሽታ (ሪውማቲክ ዲዚዝ) በአግባቡ ካልታከመ የቶንሲል ኢንፌክሽን እንደሚከሰት በቅጡ ያውቃሉን?

የቶንሲል መርፌ ቀርቷል የሚባሉ ብዥታዎችን ለማጥራት ይረዳን ዘንዳ ካነበብኩትና ከልምዴ ጀባ አልኳችሁ።

አባት የ 3 አመት ልጅ አምጥተው ለልጁ ትኩሳት ምክንያቱ የቶንሲል ኢንፌክሽን ነው ስንላቸው አዎ በረዶ መጥባት ይወዳል ልጁ አሉኝ።

የቀዘቀዘ ምግብን ወይም መጠጥን አብዝቶ መጠቀም አሊያም በሃይለኛ የፀሐይ ሙቀት በመመታት የቶንሲል ኢንፌክሽን ተብሎ በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ የሚታሰበው የቶንሲል ህመም መነሻ ምክንያቱ ከእነዚህ በእጅጉ የተለየና፤ ተገቢውን ህክምና በወቅቱ ካላገኘም እስከሞት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት የሚያስከትል አደገኛ የጤና ችግር መሆኑን በቅጡ ያውቃሉን?

✳️ መንስኤው ምንድነው?

ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች በፀሐይ ላይ መመገብ፣ እንደ አይስክሬም ያሉ የቀዘቀዙ ምግቦችን በተለይ ለህፃናት መስጠትና በከባድ ፀሐይ መመታት፤ ከቶንሲል ህመም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለውና በሽታው በባክቴሪያና በቫይረስ ሳቢያ የሚከሰት የጤና ችግር ነው።

በጉሮሮአችን ውስጥ የሚገኙት የቶንሲል እጢዎች በጀርሞች ተጠቅተው ሲቆጡና ሲያብጡ የሚከሰተው ህመም ቶልሲላይተስ ተብሎ ይጠራል።

እነዚህ ቶንሲሎቻችን እንዲቆጡና እንዲያብጡ በማድረግ ህመም እንዲሰማን የሚያደርጉት ባክሬቴሪያና ቫይረሶች ናቸው።

የቶንሲል ህመም (ቶንሲላይተስ) በአብዛኛዎቻችን ዘንድ እጅግ የተለመደና በየጊዜው የሚያጋጥም የህመም አይነት ነው።

አንድ ልጅ በየዓመቱ በአማካይ እስከ ስምንት ጊዜ ያህል በቶንሲል ህመም ሊጠቃ ወይንም ቶንሲላይትስ ሊይዘው ይችላል።

የቶንሲል ህመም መንስኤ የሆነው ቫይረስ ወይንም በባክቴሪያ በተለያየ መንገድ በዋነኛነት በትንፋሽ ወደ ሰውነታችን ገብቶ ቶንሲሎቻችንን ከበከለ በኋላ ባሉት ሁለትኛ ሶስት ቀናት በህመምተኛው ላይ የበሽታው ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡


✳️ የቶንሲል ህመም ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

የቶንሲል ህመም በብዛት የሚያጠቃዉ ህፃናትን ሲሆን የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡

🧅 የቶንሲል መቅላትና እብጠት
🧅 የቶንሲል መከርከር
🧅 ምግብ በሚዉጡበት ወቅት ህመም መኖር ወይም ለመዋጥ መቸገር
🧅 ትኩሳት
🧅 በአንገት ላይ ያበጡና ህመም ያላቸው ዕጢዎች መከሰት
🧅 የድምፅ መቀየር
🧅 መጥፎ የአፍ ሽታ
🧅 የሆድ ህመም (በተለይ በእድሜያቸዉ ትናንሽ ህፃናት ላይ)
🧅 የአንገት ህመም/መጠንከር
🧅 የራስ ምታት ናቸው።

በጣም ጨቅላ በሆኑ ህፃናትና የህመማቸዉን ሁኔታ መግለፅ በማይችሉ ህፃናት ላይ:-

ሲውጡ ህመም ስላላቸዉ የምራቅ/ለሃጭ መዝረከርክ
ምግብ መመገብ እምቢ ማለትና
ያልተለመደ ድካም የህመሙ ምልክቶች ናቸዉ፡፡

✳️ ልጅዎ ቶንሲል ኢንፌክሸን እንደያዘው እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

ህመምተኛው አፉን እንዲከፍት በማድረግ ጉሮሮው በሚታይበት ጊዜ ከምላሱ ኋላ በግራና ቀኝ የጉሮሮ ግድግዳዎች ላይ እብጠትና ቅላት ይታያል።

እነዚህ የጉሮሮ ግራና ቀኝ ግድግዳ ላይ የሚገኙ የቶንሲል እጢዎች እብጠታቸው አንዳንዴ ከፍተኛ ይሆንና ጉሮሮን ሙሉ በሙሉ ሊዘጉ ይችላሉ።

ባክቴሪያ ወለዱ ቶንሲላይተስ ከመደበኛው የቶንሲል ህመሞች ምልክቶች በተጨማሪ፤ ከሚኖረው የበሽታው ምልክት መካከል በጉሮሮ ግድግዳዎች ላይ በሚኖረው እብጠት ላይ ነጫጭ አይብ መሰል ነጠብጣቦች (ሽፍታዎች) ሊታዩበት ይችላሉ።

የቶንሲል ህመም በትንፋሽ አማካይነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍና ህፃናትን በይበልጥ የሚያጠቃ የበሽታ ዓይነት ነው።

✳️ የቶንሲል ህመም (ቶንጀሲላይትስ) በሸታውን በወቅቱ ወይም በዘጠኝ ቀናት ውስጥ አለመታከም አደጋው ምንድነው?

ስትሬፕቶኮከስ ፓዪጂንስ በተባለው ባክቴሪያ ሳቢያ በሚመጣው የቶንሲል ህመም የተያዘ ሰው በአግባቡና በወቅቱ ህክምናውን ካላገኘ ከኩላሊት መድከም (ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆም) እስከ ልብ ህመም ብሎም እስከሞት ሊያደርሱ የሚችሉ መዘዞችን ያስከትላል።

በባክቴሪያ ወለዱ የቶንሲል ህመም የተያዘ ሰው ተገቢውን ህክምና ካላገኘ ቶንሲሎቹ ዙሪያቸውን ያብጡና መግል ይቋጥራሉ።

የህመምተኛው አንገትም ይበልጥ መግል ወደተቋጠረበት አቅጣጫ ያዘማል።

ይህም የማጅራት አለመታዘዝንና መንጋጋን እንደልብ መክፈት አለመቻልን ከማስከተሉም በላይ፤ ታማሚው ህክምና ካላገኘ ባክቴሪያው በደም ውስጥ በመሰራጨት የኩላሊትና የልብን መደበኛ ስራ በማስተጓጎል ታማሚውን ለሞት ሊዳርገው ይችላል።

ባክቴሪያ አመጣሹ ቶንሲላይተስ ሰበብ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች መካከል አጣዳፊ የኩላሊት መድከም፣ የልብ ህመም፣ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) የቆዳና የጉሮሮ ኢንፌክሽኖች፣ ጥቂቶቹ ናቸው።

ስትሬፕቶከክስ ፓዮዲኒስ በተባለው የባክቴሪያ አይነት ሳቢያ የሚከሰተውን እና እጅግ አደገኛ የሆኑ ችግሮችን የሚያስከትለውን የቶንሲል አይነት ቫይረስ አመጣሽ ከሆነውና በቀላሉ ከሚድነው የቶንሲል አይነት መለየቱ አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም ሁሉም ዓይነት የቶንሲል ህመሞች በአግባቡና በወቅቱ ህክምና ማግኘት አለባቸው፤ የሚባለውም ለዚሁ ነው

✳️ የሕክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?

🍋 በ24 ሰዓታት ውስጥ ለውጥ የሌለው የቶንሲል ህመም ካጋጠምዎ
🍋 ምግብ ሲውጡ ህመም ካለዎት እና
🍋 የድካም ወይም የመዝለፍልፍ ስሜቶች ከፍ ያለ ከሆኑ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

✳️ ለቶንሲል ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች

🍓 ለጋ እድሜ፡- የቶንሲል ህመም ትናንሽ ህፃናትንና ለጋ እድሜ ላይ ያሉ ልጆችን በብዛት ያጠቃል።

🍓 በተደጋጋሚ ኢንፌክሽኑን ለሚያመጡ ጀርሞች መጋለጥ፡- በትምህርት ቤት የሚዉሉ ህፃናት ከአቻዎቻቸው ጋር ያላቸዉ የቀረበ ግንኙነት/ንክኪ ለቫይረሶችና ባክቴሪያዎች በቀላሉ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል።

✳️ የቶንሲል ህክምና ምንድናቸው?

1️⃣ የቤት ውስጥ ህክምናዎች
የቶንሲል ህመሙ በቫይረስም ይሁን በባክቴሪያ ምክንያት ቢከሰትም የቤት ዉስጥ ህክምናዎችን መከወን ምቾት እንዲሰማዎና ቶንሲሉ ቶሎ እንዲድን ያደርገዋል።

የቶንሲል ህመሙ የተከሰተዉ በቫይረስ መሆኑ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያዎ ምንም ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒት ስለማያዝልዎ ህመሙ እንዲድን የቤት ዉስጥ ህክምና ማከናወን የህክምናዉ ዋናዉ አካል ነው። የቶንሲል ህመም በ10 ቀናት ዉስጥ ሊሻሻል ይችላል።

👉👉 ሊደረጉ የሚችሉ የቤት ዉስጥ ህክምናዎች:-

🍑 በቂ እረፍት ማግኘት:- ብዙ ያለማዉራትና በቂ እንቅልፍ ማግኘት።

🍑 ፈሳሽ በበቂ መጠን መዉሰድ።

🍑 ምቾትን ሊሰጡ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ:- ትኩስ ፈሳሾች እንደ ሾርባ፣ ካፊን የሌለዉ ሻይ፣ የሞቀ ዉሃ በማር እንዲሁም ቀዝቃዛ የሆኑ እንደ በረዶ ያሉ ነገሮች የጉሮሮ መከርከርን ሊያክሙ ይችላሉ።

🍑 ጨዉ ባለው ውኃ አፍን መጉመጥመጥ።

🍑 ወደ ውስጥ የሚገባዉን አየር እርጥበታማ/ሂሙድፋይ እንዲሆን ማድረግ:- ወይ የቀዝቃዛ አየር ሂሙድፋየር መጠቀም አለዚያ ደግሞ እንፋሎት መታጠን ደረቅ አየር ጉሮሮ ላይ የሚያመጣዉን መከንከን እንዲቀንስ ያደርጋል።

🍑 ሊቆጠቁጡ የሚችሉ ነገሮችን ማስወገድ፦ ጉሮሮን ሊከረክሩ ከሚችሉ እንደ የሲጋራ ጭስና የቤት ማጽጃ ኬሚካሎች እራስን መጠበቅ።

🍑 ህመምና ትኩሳት ካለ ማስታገሻ መዉሰድ፦ እንደ ፓራሲታሞላና አይቡ ፕሮፌን ያሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡፡

2️⃣ መድሃኒቶች

የቶንሲል ህመም የተከሰተው በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ከሆነ የግድ ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶችን (አንቲባዮቲክሶችን) መውሰድ ያስፈልጋል።

ከአስር ቀናት ሹርፕ አለርጅ ለሌላቸው አንድ ጊዜ የሚሰጠው መርፌ ይመከራል።

በህክምና ባለሙያዎ የታዘዘልዎትን መድሃኒት በአግባቡ ወስዶ መጨረስ የሚያስፈልግ ሲሆን፤ በአግባቡ ካልተወሰደ ግን ባክቴሪያው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰራጭ፤ ህፃናት ላይ ደግሞ የልብ ህመም እንዲከሰት መንስኤ መሆንና ቀጣይነት ያለው የቶንሲል ህመም (ክሮኒክ ቶንሲላይትስ) እንዲከሰት ያደርጋል።

✳️ የቶንሲል ህመምን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ቶንሲልን ሊያመጡ የሚችሉ ጀርሞች (ባክቴሪያና ቫይረስ) ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ ናቸው።

ስለሆነም የቶንሲል ህመምን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ዉስጥ ዋነኛዉ የግል ንፅህናን መጠበቅ ነው።

👉👉 እራስዎም ሆኑ ልጆችዎ:-

🍅 ምግብ ከመመገባችሁ በፊትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጃችሁን በደንብ መታጠብ
🍅 የመጠጫና መመገቢያ እቃዎችን በጋራ ያለመጠቀም ይመከራል፡፡
ልጆች የቶንሲል ህመም ካላቸዉ ኢንፌክሽኑን ወደሌሎች እንዳያዛምቱ
🍅 ልጅዎ ታሞ ከሆነ ለተወሰነ ቀናት እቤት እንዲቆይ ማድረግ
🍅 ልጅዎ መቼ ትምህርት ቤት መሄድ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር
🍅 ልጅዎ በሚስልበትና በሚያስነጥስበት ወቅት አፍና አፍንጫዉን በሶፍት ወይም በክርኑ የዉስጠኛዉ ክፍል እንዲሸፍን ማስተማርና
🍅 ልጅዎ ካሳለዉ ወይም ካስነጠሰዉ በኃላ እጁን/እጇን እንዲታጠቡ ማስተማር ናቸው።


ምንጮች
ማህበራዊ ሚዲያ
አርሰናል በስፖርቲንግ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ፍላጎቶች ምክንያት ቪክቶር ግዮኬሬስን ለማስፈረም የነበረውን እምቅ ፍላጎት ሊተወው እንደሆነ ተዘግቧል።