Channel created
#ታድለሽ

አዛኝ ልብ ሰቶሻል የሚራራ ለሰው፣
ከእናቶች ልብ ነው ላንቺ የተቀነሰው፣
-ታድለሽ የኔ አለም-
በዚ ሰአት እኮ የዋህ ልቦች የሉም፣
ቆንጆዎች በሙሉ መልካሞች አይደሉም፣
ከምን ተመርጥሽ ነው ግን የተለየሽው፣
የዋህ ልብ ቁንጅናን የተከናነብሽው፣
-ታድለሽ የኔ አለም-
ፈገግ በይ ሳቂልኝ እኔ ልድመቅ ባንቺ፣
ጥርስሽ ያበረያል ከንፈርሽን ስትከፍቺ፣
ሁሌም ተናገሪ ዝም ብዬ ልስማ፣
አንደበትሽ ማር ነው ለጆሮ ሚስማማ፣
-ታድለሽ የኔ አለም-
ሁሉም ተሰቶሻል ምስኪን ነሽ አፍቃሪ፣
ውብ ፀሀይ የመሰልሽ ሁሌ አብረሽኝ ኑሪ፣
በአሁን ሰአት እኮ የዋህ ልቦች የሉም፣
ቆንጆዎች በሙሉ መልካሞች አይደሉም።
ገጣሚ
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
#ከዚህ_ቡሀላ_ግጥም_በቃኝ😭
የተፈጠረውን ላስረዳችሁ ከላይ የለቀቁላችሁ ቪዲዮ የተሰራው ከኔ የተረቀ ግጥም ነው የተወሰኑ ቃላቶች ብቻ ነው የተቀየሩት የተሰረቀውን ግጥሜን ስላላጠፋውት ከላይ ማረጋገጥ ትችላላችሁ እኔ ግጥሙን የፃፍኩት 2023 በፈረንጆቹ ነበር ቪዲዮውን እኔ ያየየሁት አሁን ቢሆንም የሰሩት ግን በ2024 በፈረንጆቹ ነው ብቻ ከዚህ ነገር የተገነዘብኩት ዛሬ ላይ አንድ ቪዲዮ ከሰሩ ነገ ደሞ ሰርቀው መፅሐፍ ቢያሳትሙት ምን ዋስትና አለኝ?
ምናልባት ቪዲዮ ላይ ለኔ እውቅና ቢሰጡ ችግር አልነበረውም ግን የሰውን ስራ እንደራስ አድርጎ መጠቀም በጣም ይደብራል ሁላችሁም ግን እስከዛሬ እያበረታታችሁኝ አይዞህ እያላችሁ ሞራል ስለሆናችሁኝ አመሰግናለሁ ምናልባት እግዚአብሔር ከፈቀደኮ ራሴ በመፅሐፍ አሳትማቸው ይሆናል ከዚህ ቡሀላ አዲስ ግጥሞችን ብፅፍም እዚህ ቻናል ላይ አለቅም ከዚህ በፊት የፃፍኳቸውንም አጥፍቻቸዋለሁ ከተቻለኝ ሁኔታዎችንን አመቻችቼ በቲክቶክ እለቃለሁ ምክንያቱም ብሰረቅ እንኳን የቪዲዮ ማስረጃ ይኖረኛል ይሄ በመፈጠሩ ባዝንም እንደ ማንቂያ ደውል እወስደዋለሁ በዚህ ጉዳይ ልታዋሩኝ ከፈለጋችሁ
👇👇👇
@kaseshart ሀሳባችሁን ፃፉልኝ
ብዙ ጊዜ ቢቆይብኝም ስዬ ጨርሼዋለሁ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጌታ እንዳንለው እንደ ባርያ ሮረ፣
ባርያ እንዳንለው በመስቀል ዙፋን ነው እርሱ የከበረ፣
ነቢይ እንዳይባል አምላክ ሆኖ ሠራ፣
አምላክም ላይሰኝ ቁጭ ብሎ በላ ከሐጢአተኛ ጋራ፣
ዝቅ ብሎ ሲገለጥበምድር እንደ ተራ፣
በጨለማችን ላይ ብርሐን ሆኖ በራ።
✍️ በ አቤል አለማየሁ
ቀን11/11/2017
።።።።።።።ድካም።።።።።።።
የ ድካም ብርታቱ በ አምላክ መረታቱ፣
ይባል ነበረ በዘመነ ጥንቱ፣
ዛሬ ግን ድካሜን ቀይሬው፣
አምላክን ከወንበሩ ሽሬው፣
በራሴ ደከምኩ እኔው።

✍️ አቤል አለማየሁ
ቀን 26/11/2017
@getemk2g
@getemk2g
@getemk2g
Please join
፠፠፠፠፠ ሕሊና ፠፠፠፠
ልቤ ወደ ግብጽ ሂድ ይለኛል፡
በረሃ በረሃዉን ያሰኘኛል፡
ይበራል ሕሊና ሁሌ ግብጽን ፡
ሊፈልግ አምላክን፡
እሻለው ስዱድ ብላቴና ፡
በጀርባዋ ሕይወት አለና፡
ይህች ብላቴና ማናት የበቀለች ቁጥቋጦ፡
ለምለም ግብጽ የሆነው በረሃው ተውጦ፡
በጸደይ ወር እንዴት ነው የወረድኩ ከግብጽ በረሃ፡
ጥማት ባየለበት ምግብ በጠፋበት የሚጠታ ዉሃ ፡
እንዴት ወረድኩኝ ግብጽ እንዴት ናፈቀችኝ አዛኝት እናቴ ፡
ግብጽ ወርዳለች ሲሉ ጨርቄን ማቄን ሳልል የወጣው ከቤቴ፡
እንዴት አገበረኝ ፍቅሯ የእመብርሃን ፡
ለበረሃው ጉዞ መግብን የረሳሁኝ የዘነጋው ዉሃን፡
አረ እንዴት ሆነልኝ እመቤቴን መውደድ፡
አረ እንዴት ሆነልኝ ከ እርሷ ጋር መሰደድ፡
የታለ የጠማኝ በረሃ ላይ ሳለው፡
የታለ ያስፈራኝ የበረሃ ግርማው፡
የታል የተራቆትኩ ልብሴ አልቆሸሸም፡
ሰውነቴ አልጃጀ እድሜዬም አልሸሸም፡
ይገርማል በህሊና ሳሉ መታደስ መታደስ፡
እንዴት ያጸድቅ ይሆን ከእርሷ ጋር መገስገስ፡
እንዴት ድነን ይሆን እሷን ስላሰብናት፡
ልባችን በረካ ተሰደን አብረናት፡
ሕልማችን ተሳክቶ አንዴ እሷን ብናይ፡
ገነትን አንሻም እሷ እንደው ሰማይ፡
እያለ ሕሊና ሰማይ ግብጽ እያለ ሲያባክነኝ ኖረ፡
ግና
ሰማየ ሰማያት መውጣት ከብዶት ኖሯል ከአይራት እርቦአቸው ከዛ በታች ቀረ።

በኃይለ ሚካኤል
getemk2g
እውነትም ለሰዎች ያ ሞት ነው ያነሰን፣
እኛ እየሸሸነው አምላክ አለው ሲለን
።።።።።።።።።።።።።።።

።።።።።።።።።።።።።።።

በአምላክ ፊት መቆም ፣
ችግርን መጠቆም፣
ትልቅ መፍቴሄ አለው
በአምላክ መታመን፣
በፊቱ መማጸን፣
ያሰጣል ጉልበትን፣
እርሱን ብቻ ማመን በእርሱ ላይ መደገፍ፣
ከሞት ነው የሚያተርፍ፣
ስለዚህ ወዳጄ
ሲከፋህ ጩህበት አልቅሰህ ተጣራ፣
ካንተ ይወገዳል የነፍስህ መከራ።

✍️ በ ኃይለ ሚካኤል
ቀን/7/09/2018

@getemk2g
@getemk2g
@getemk2g
Date: 24 Oct 2023
Subject: አየሁሽ

አንቺን መናፈቄን በየለት ውሎዬ ስነግርሽ ኖሬአለው፣
ፍቅሬን ብትገፊም እመካብሻለሁ አስብልሻለው፣
ደግሞ ያየሁሽለት ሲነሳ ህመሜ፣
ሳልጠግብሽ ሳልረካ ሲጠፋ ሰላሜ፣
እታመማለሁኝ እንዳዲስ አፍቃሪ፣
ከሌላ እንዳልደርስ አድርገሺኝ ፈሪ፣
ያላንቺ አማራሪ፣
ሰው ሲያይ የቀድሞ የተለየውን ሰው፣
የጥላቻ እሳት ውስጡ ሚለኮሰው፣
የኔ አጀብ ጉድ ነው ሳይሽ ነው ምሳሳው፣
ደሞ ዛሬ አየሁሽ ልትናፍቂኝ ነው፣
እንደ ሙሾ አድራሽ ደረቴን ስደቃ ሳነባ ላድር ነው፣
አወይ መውደድ ደጉ አወይ ማፍቀር ደጉ፣
ስለይሽ ናፍቆታት በውስጤ አደጉ፣
ሆዴ ደሞ አየሁሽኝ ፣
ከአይኔ ሳትርቂ ደጋግመሽ ናፈቅሺኝ፣
እኔ ያንቺ ጎጆ ኮሳሳው ደሳሳው ፣
ራቅ ስትዪ ነው መኖርሽን ምረሳው፣
እኔ ያንቺ አንቀልባ ታዝለሺኝ ካልያዝሺኝ፣
የወደኩ ለታ ሁሉ ነው ሚረሳኝ፣
አዎን ውዴ ፍቅሬ አልይሽ አልራቅሽ፣
ያየሁሽ የራኩሽ ለታ ነው የማጣሽ፣
አረ አጀብ ጉድ ነው ስትርቂ ሚያስከፋኝ ፣
ስትቀርቢ ሚያስነባኝ፣
አቤት ጉድ መፋቀር፣
አጀብ ነው መዋደድ፣
ቀድሞስ ምን አስኬደኝ በተረሳ መንገድ፣
ባልታወሰ ፍቅር በሄደ መቃብር፣
እየመጣሽ ጎብኚኝ እዛው ነው የምኖር፣
ኑሮዬ በዛነው መቃብር ሞት ጠሪ፣
አጠብቅሻለው አንቺ እንዳትቀሪ፣
አዎ እንዳትቀሪ እጠብቅሻለው፣
ባንቺ ያገኘሁት የሰራሁት ቤቴን ላሳይሽ እሻለው፣
እጠብቅሻለሁ።

✍️ፈ በ አቤል

@getemk2g
@getemk2g
@getemk2g
ማርያም ዝምታ ነች

ማርያም አልቅሰው ሲነግሯት፣
መናገሩን ስትችል ዝም ነው ሚቀናት፣
ማርያም
እንኳን በሰው ጭንቀት በራሷ ልቡና የእሳት ሰይፍ ሲያልፍ፣
ምነው ማለት ስትችል የእርሷ ንግግር ከዝምታም አያልፍ፣
       ማርያም እንዲህ ናት
አልቀሰው ሲነግሯት አብራ ታለቅሳለች፣
ለሳቅ ለደስታ ግን ዝምን ትመርጣለች፣
       ማርያም እንዲህ ናት
እርቃኑን አቁመው ልጇን ሲገርፉባት፣
ከብዙ ሺ ቃላት አንድ እንባ ያላት   ማርያም እንዲህ ናት
ማርያም ነፍስ ናት አትመረምርም ፣
ስትሰራብን እንጂ ሥጋ አካል ገዝፋ ስትኖር አትታይም፣
ይህች ናት ማርያም ነገሯ አርምሞ፣
ሰው የሚድንባት ዝም ባለ ቃል ታክሞ፣
ማርያምስ ምንጭ ናት  የሰላም
በዝምታዋ ቃል ሰው ከመዳን አይድንም።

✍️ፈ በአቤል አለማየሁ

@getemk2g
@getemk2g
@geremk2g
      እናቷ ጸበል ግባ አሉኝ
ልጃቸውን ወስደው ካበቁ በኋላ ልቤ እንዲቆስል፣
ጸበል ተጠምቄ ልክ እንደ ጂኒ እሪ ብላ ጮሀ ትወጣ ይመስል ።

@getemk2g
@getemk2g
@getemk2g
በአንደበት ቃሌ መሀል ዝም ያለ ጩኸት መልቶ፣
በእቅፌ እንባ ስፍር የሚናገር ቃል አውጥቶ፣
ከእቅፉ እንድገባ መሀል እጁን እንዳገኘው፣
ነፍሴን ከእጁ ስር ሰጥቶ መጣል ለተመኘው፣
አያይ ይሆን መጎስቆሌን ፣
አያይ ይሆን እንባ ቃሌን፣
በሕይወቴ እንዳነግሰው እንድሰጠው ሙሉ አካሌን፣
በፈለኩት በዳበሳ በወደኩኝ ከእግሩ ስር፣
ለእግሮቹ አፈር ትቢያ መዳበሻ በሆነልኝ የኔ ጸጉር፣
በደረስኩኝ ቀራንዮ፣
ፍቅሩ ገብቶኝ ባልኩኝ ወዮ፣
በተገኘው ካረፈበት፣
ሽቱ ይዤ ላፈስበት፣
ከዚህ ሁሉ ልቡና ጋር ወደቤቱ ብገሰግስ ፣
እላለሁኝ ስለሐጢአቴ ተንበርክኬ አንዴ ባለቅስ፣
ሙቅ እቅፉን በቀመስኩት፣
ችንካሮቹን ግርፋቱን ከዮሐንስ ጋር ባየሁት፣
በተጠጋሁ ከደረቱ፣
በዝሙቴ ብሰለጥን ባደረገኝ ጎበዝ ብርቱ፣
አያይ ይሆን መጨነቄን፣
ስለ ሀጢያት ስጥል ጨርቄን፣
አያይ ይሆን ዘበት ህልሜን፣
በመቅደሱ የፈለኩት ያን መቆሜን፣
አይሰማ ይሆን ዝም ብዬ ሳነባበት፣
አይሰጠኝም ያን ምኞቴን የኔን መሻት፣
ሊቀ ካህን የታመነው የኛ አባት፣
አስወጥቶ አይሰዳቸው ከልባቸው ለፈለጉት።


ቀን 8/9/2018
           በ ኃይለ ሚካኤል
አቤል