Getcha Tech's📱💻
136 subscribers
26 photos
3 files
20 links
Download Telegram
የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡

❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡

🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡

“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K

“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።

“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡

🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ

”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) ያደረጋል፡፡

“Y” - Extremely low Power

“U” – Ultra low Power

ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U

🦋#Share🦋
👩‍💻 @getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs 👩‍💻
https://t.me/Getcha_Tech
🔷🔴📲Samsung A10s

🔰 used orginal ®

📶 Dual Sim

⏳👉👉 2GB Ram

📼Storage :- 32 GB

☢ 4000 mAh Battery
👨‍💻SD ፣ HD ፣ 4K እና 8K ምንድን ናቸው❓
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔆የቴክኖሎጅ ርቀት እና ምጥቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በተለይ ከእይታ (ምስል) ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ደግሞ ለማመን የሚከብዱ ተአምራት እየሆኑ መጥተዋል ።
የምስል ጥራት በፒክስል የሚለካ ሲሆን በ3 ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላል።

እነሱም፦
➀ SD [standard_definition]-መደበኛ ጥራት
➁ HD [High definition] - ከፍተኛ ጥራት
➂ UHD [Ultra high definition ]- ከመጠን ያለፈ ጥራት ናቸው።

ፒክስል ስንል አንድን ምስል ለመስራት የሚያስችል ትንሿ ነጥብ(ስኩዌር ◾)ማለታችን ነው።
✅የፒክስሎች ስብስብ ሪዞሉሽን ሊሰኝ ይችላል።

ለምሳሌ ፦ ከአንድ ምስል ላይ አንድ ስኩየር (ልክ ኬሚስትሪ ላይ atom እንደምንለው) ወስደን ብንመለከት የወርድ ነጥቦች ስብስብ ብዛት × የቁመት ነጥቦች ስብስብ ብዛት ፒክስል ይባላል ማለት ነው ።

🔴720 × 480 pi ሲባል
720=የወርድ(w)ነጥቦች ብዛት እና
480= ቁመት(h) ነጥቦች ብዛት በአንድ ሊከፈል በማይችል ስኩዌር ውስጥ ማለታችን ነው ። ፒክስል በበዛ ቁጥር ጥራት ይጨምራል። በሌላ በኩል የምስሉ MB ም ይጨምራል ።⬆️

📌በየዘመናቱ የመጡ የምስል ጥራት እድገትን ብንመለከት ከመጀመሪያው እስከ አሁን ድረስ የሚከተሉትን ይመስላል።

✅SD= 720 × 480
◾PAL= 768 × 576
◾NTSC= 720 × 534 (የድሮ ሪሲቨሮች)
✅HD= 2K
◾HD = 1280 × 720
◾Full HD =1920 x 1080
✅UHD=
◾4K= 3840 × 2160 (16:9 YouTube size)
◾5K= 5120 × 2700
◾6K = 6144 × 3160
◾8K = 7680 × 4320 አሁን የደረስንበት የመጨረሻው ቴክኖሎጅ።

📌ሀገራችን ላይ በስፋት በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው ሰው ቤት የሚገኘው Full HD እና 4K ሪሲቨር ሲሆን አልፎ አልፎ 8Kም ይኖራል። ነገር ግን እዚ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ቢኖር ባለ 8K ቻናልን ለመመልከት ሪሲቨራችን እንዲሁም ቲቪያችን የግዴታ 8K ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ የቻናሉ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ ለመለየት እንቸገራለን ። ያ ማለት HD ቻናሎችን በAV ኬብል እንደመመልከት ይሆናል ማለት ነው።

📌በዚህ ጊዜ 8K እንኳን ቀርቶ 4K ቲቪ ራሱ የሚገዛ ሰው ኪሳራ ላይ እንደወደቀ ይሰማኛል፤ ምክንያቱም በ4K Quality Broadcast የሚያደርጉ የቲቪ ቻናሎች የሉንም🥺🥺🥺

@getcha_techs
VidMate_com.nemo.vidmate_346_3.46_.apk
8.1 MB
👆👆አፑን ለማውረድ
ከዩትዩብ ላይ ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለማውረድ, የዩትዩብ ቪዲዮ በጥራት ለመመልከት የፈለግነውን ፋይሎች በቀላሉ ለማስተላለፍ የሚጠቅመን አሪፍ አፕ ነው፡፡
@getcha_techs
ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን?


1. cmdን በአንሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)

2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ:netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው

3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password
⚠️ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን

4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን። ከዛም OK በለን እንወጣለን

5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን

6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።
@getcha_techs
#አንብቧት😊

📌መቼም ቢያንስ ስልክ📲 የሌለው ሰው የለም😁 ያ ማለት ሁላችንም ወደድንም ጠላንም #ቴክኖሎጂ ሳይነካን አያልፍም።‼️ ሲኖር ለመጠቀም ሲበላሽ ለማስተካከል የተጠየቃችሁትን መክፈል ወይም #በራሳችሁ መስራት የግድ ነው።

📌ደጋግመን እንደምንናገረው የኛ ቻናል እና ግሩፕ ዋና አላማ ቢያንስ ቀላሎቹን ችግሮች በራሳችሁ እንድትፈቱ፣ የማታውቁትን እንድታዉቁ ነው።🙏🙏🙏

📌እዚ ምንማማረው 1ሰው ለሺዎች ነው #በተጨማሪ ግሩፑን @getcha_techs_group ብትቀላቀሉ ሺዎች ለሺዎች ትማማራላችሁ፤ ትረዳዳላችሁ👏 ስለዚህ ጊዜ ሳታጠፉ ተቀላቀሉ።😊🙏🙏🙏
💢ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ

✅This Application Stopped Working‼️
✅Crashing‼️
✅Won’t open‼️
✅Won’t respond‼️
✅Isn’t working properly‼️እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ

1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

⚠️ስልካችሁን📲 #Restart አድርጉት።

⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

⚠️Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2⃣.Update Google Play Services

⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ Setting ውስጥ ገብታችሁ #Forced_Stop አድርጉት።

⚠️System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።

4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።

⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️

📌መረጃዎችን ለወዳጅዎ 🗣👥 ያጋሩ።
❓ጥያቄ ካለዎት @getcha_techs_group 🤖🤖ላይ ይላኩልን።

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 🖥 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

@getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs
Yacine TV telegram.apk
8.1 MB
yacin tv

👉WORK WITH A LOW CONNECTION
👉WORKS FOR LOW STORAGE DEVICES
👉WITH OUT ANY CODES

ይህ App Yacine tv app ይባላል በጣም ጥሩ ነው ትወዱታላችሁ ዳውሎንድ አድርጋችሁ የተለያዩ ሊጎች ጨዋታወችን በጥራት መመልከት ትችላላችሁ።
@getcha_techs
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለባችሁ 10 ወሳኝ ነገሮች
✍1ኛ :- ያለንበትን ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልከውን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላክዋን ከፍተን location የምለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::
✍ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የምለውን እንነካለን ከዛ passcode የምለወን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::
✍ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንደይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የምለዉን እንነካለን ከዛ
ከዛ when using mobile data -OF-አድርጉት ::
✍4ኛ :- የለክነዉን message ከደረሰ ቦኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የለነክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የምለውን Also delete receive የምለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
✍5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት
✍6ኛ :- በተላይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፈ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከምሰጠን የመልክ ምርጫ የፍለግነዉን እንመርጣለን ::
✍7ኛ :- ቴሌግራም የሉ ፅፎች አልነበብ እየሎት ተቸግረዋል ማለት ፍደሎችሁ አንሰዉ ለዓይን አልተይ ከለ ፍደሎቹሁን ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
አዎ በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፍለግነዉን ያህል ትልቅ ማድርግየ ይቻላል ::
✍8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የምለውን ነክተን create new channel የምለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፍለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::
✍9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራፍ ጉሩፒ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ የለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የምለውን እንነካለን ከዛ create new groupጠ የምለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፍለግነዉን የጉሩፒ ስም እናስገባለን ::
✍10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የምለውን በመንካት የፍለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።
@getcha_techs
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-

1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡

2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡

3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡

4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡

5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

@getcha_techs
በPATTERN ወይም የተዘጉ ስልኮች ካለ ምንም ኢንተርኔት እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መመለስ እንደምንችል ከዚህ በፊት ሰፋ ባለPassword ፕሮግራም መልቀቃችን ይታወሳል ለማታቁት ዛሬም እናቀርባለን።

ኣስፈላጊ ነገሮች:-
1 aroma file manager በሌላ ስልክ ማውረድ ኣለብን
2 ሚሞሪ ካርድ(ያወረድነውን app
የምንናስቀምጥበት)
3 የተዘጋው ስልክ
~
Step1:- aroma file manager ካወረዳቹ ወደ ሚሞሪ ካርዱ ጫኑት እና ካርዱ ወደ ተዘጋው ስልክ ኣስገቡት
Step2:- ከዛ ስልኩ power off እናረገው እና የ recovery stock ወይም ስልካችን ካጠፋነው ቡሃላ የ power እና የ ድምፅ መጨመርያ ኣንድ ላይ ተጭነን እንቆያለን( እንደ የ ስልኩ ኣይነት ሊለያይ ይችላል)
Step3:- ወደ recovery mode ከገባን ቡኋላ የ ድምፅ መጫኞቹ ወደ ላይ እና ታች የ power መጫኛው ደሞ እንደ ok ሁነው ያገለግላሉ
Step4:- recovery mode ላይ install zip from sd card የሚለውን ላይ ok/power button እንጫን እና aroma file manager ያስቀመጥንበት folder ገብተን install እንለዋለን
Step5:- ከዛ aroma file manager ከከፈታቹ ቡኋላ ወደ nevigate የሚለውን ትወርዱ እና automount all devices on start የሚለውን ተጭናቹ ከዛ ዝጉት።
Step 6:- step4 ላይ እንዳደረጋችሁት step6 ላይም ድገሙት
Step7:- aroma file manager እንደገና ሲከፈት ወደ data folder ከዛ system folder ትገቡ አና 'gesture.key' or 'password.key' የሚል ታገኛላቹ
Step8:- ከዛ ያገኛችሁት gesture.key or password.key ኣጥፉት ከዛ ስልካቹ reboot ኣድርጉት
Step9:- ስልኩ ሲከፈት የማትረሱትን pattern ወይም password በማስገባት መክፈት ትችላላቹ።

@getcha_techs
ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ እንዴት ማስተካከል ይቻላል?
በተለያዩ አጋጣሚዎች ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፣ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ከመደናገጥ ይልቅ ቀላል የሆኑ አካሄዶችን በመከተል ስልክዎ. እንዳይበላሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ከሁሉም በፊት ስልክዎን በፍጥነት ከዉሀ ዉስጥ ማዉጣት ይኖርቦታል፡፡ ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ በቆየ ቁጥር ዉሀ ወደ ስልክዎ ዋና ክፍሎች ዉስጥ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
ሊከተሉዎቸዉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እንመልከት፡
በፍጹም ሊያደርጉዎቸዉ የማይገቡ ነገሮች
• ስልክዎን እንዳያበሩት
ስልክዎ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች አይንኩ
•ስልክዎን አያወዛዉዙት ወይም ስልክዎ ከሌሎች ነገሮች ጋር አያጋጩት
•የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች አይንቀሉ፡፡
ስልክዎ የዉሀ ብልሽት አመላካች(Liquid Damage Indicator(LDI)) ተገጥሞለታል፣
የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች የሚከፍቱት ከሆነ ይህ የዉሀ ብልሽት አመላካች አክቲቭ(Active) ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ከስልኩ አምራች
ድርጅት የሚሰጠዉን Warranty ያሳጣዎታል፡፡
በትንፋሽዎ ዉሀዉን ለማድረቅ አይሞክሩ፣
ምክንያቱም ስልክዎ ላይ በሚተነፍሱበት ጊዜ ዉሀ ወደ ዉስጠኛዉ የስልክዎ ክፍል ዉስጥ ሊገባ ስለሚችል ነዉ፡፡
ስልክዎን በማንኛዉም አይነት. የሙቀት መሳሪያ ለማድረቅ አይሞክሩ፡፡

ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ ከብልሽት የሚከላከሉባቸዉ አካሄዶች
1) ስልክዎን ከዉሀ ዉስጥ ሲያወጡት እየበራ ከሆነ ያጥፋት እና ቀጥ አድርገዉ ይያዙት፡፡
2) የስልክዎን ከቨር በመክፈት ባትሪ፣ሲም ካርድ እና ሚሞሪ ካርዱን ያዉጡ፡፡
3) ደረቅ ጨርቅ ወይም ማድረቂያ በመጠቀም ስልክዎን ያድርቁ፡፡
ዉሀ ወደ ሌላ የስልክ ክፍሎች እንዳይተላለፍ ይጠንቀቁ፡፡
4) በጐድጓዳ ሰሀን ላይ ያልተቀቀለ ሩዝ ይጨምሩ እና ስልክዎን ሩዝ ዉስጥ ይክተቱት፡፡ ሩዝ ዉሀን የመምጠጥ አቅሙ በጣም ከፍተኛ
ስለሆነ አብዛኛዉን ጊዜ ስማርት ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለማድረቅ ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡
5) ስልክዎ በሩዝ ዉስጥ ለአንድ ወይም ሁለት ቀን እንዲቆይ ያድርጉ፡፡ በእነዚህ ቀናቶች ዉስጥ ስልክዎን ለማብራት እንዳይሞክሩ፡፡
6) ከጥቂት ቀናቶች በሗላ ስልክዎን ከሩዝ ዉስጥ ያዉጡ እና ባትሪዉን አስገብተዉ ያብሩት፡፡
ስልክዎ አሁንም ካልበራ ባትሪዉን ቻርጅ ያድርጉት፣
ቻርጅ ተደርጎም የማይበራ ከሆነ ባትሪዉ ብልሽት አጋጥሞታል ማለት ነዉ፡፡
ባትሪ ይቀይሩለት ወይም ወደ ስልክ ሰሪዎች ይዉሰዱት፡፡

@getcha_techs
✴️ የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ድረገፆች ( website )
1 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ www.aau.edu.et
2 መቀሌ ዩኒቨርስቲ www.mu.edu.et
3 አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ www.astu.edu.et
4 አክሱም ዩኒቨርስቲ www.axu.edu.et
5 አምቦ ዩኒቨርስቲ www.ambou.edu.et
6 አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ www.amu.edu.et
7 ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ www.bdu.edu.et
8 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ www.dbu.edu.et
9 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ www.dmu.edu.et
10 ዲላ ዩኒቨርሰቲ www.du.edu.et
11 ጎንደር ዩኒቨርስቲ www.gu.edu.et
12 ጂማ ዩኒቨርስቲ www.ju.edu.et
13 ሃረማያ ዩኒቨርስቲ www.haramaya.edu.et
14 ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ www.hu.edu.et
15 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ www.wsu.edu.et
16 ወለጋ ዩኒቨርስቲ www.wu.edu.et
17 ድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ www.ddu.edu.et
18 ወሎ ዩኒቨርስቲ www.wou.edu.et
19 ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ www.jgu.edu.et
20 መዲ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ www.mwu.edu.et
21 ሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
22 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ www.su.edu.et
23 ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ www.kuc.edu.et
24 አአ ሾል. & ቴክ ዩኒቨርሲቲ www.aastu.edu.et
25 አዲግራት ዩኒቨርሲቲ www.adu.edu.et
26 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ www.asu.edu.et
27 ቡሌ ሁራ ዩኒቨርስቲ www.bhu.edu.et
28 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ www.dbtu.edu.et
29 መቱ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
30 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ www.wcu.edu.et
31 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ www.wku.edu.et
32 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ www.wdu.edu.et
33 አርሲ ዩኒቨርሲቲ www.aru.edu.et
34 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ www.gmu.edu.et
35 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ www.obu.edu.et
☆Getcha Tech☆
@getcha_techs
✳️ የሞባይል ባትሪያችንን የሚጎዱ ነገሮች

▫️ሙቀት


➠ ሙቀት አንደኛው የስልካችን ባትሪ ጠላት ነው።በተለይ ስልክን ሞቃጣማ ቦታ ላይ charge ማድረግ።ስልካችንን አብዝተን ስንጠቀም ባትሪያችንን ሙቀት ከሚጎዳው ይልቅ ይጎድለዋል።ስልክን በቀዝቃዛ ቦታ ቻርጅ ማረግ ቻርጅ ሲያረግ ፍጥነቱን ይቀንሳል።

▫️ቻርጀር(charger)

➠ ሌላኛው ደግሞ የምንጠቀመው ቻርጀር ነው።በአሁን ጊዜ ገበያ ላይ ብዙ አይነት ፈጣን ቻርጀር(fast charger)አሉ።
ስልክ ስንገዛ ከስልኩ ጋር ቻረጀር የሚሰጠን, ያ ቻርጀር የሚመጣውን የኤሌትሪክ ሀይል ለስልካችን መጥኖ ወደ ስልካችን ይልከዋል።ነገር ግን ከገበያ የሚገዛው ለስልካችን አብዝቶ ወይም አሳንሶ ነው ሚሰጠው።

▫️የስልክ ቻርጅ አደራረግ ባህል

➠ ስልካችን ቻርጅ እያረገ መጠቀም
ስልካችን ቻርጅ እያረገ ስንጠቀም, ወደ ባትሪው መሄድ ያለበት የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ ባትሪዉ መሄዱን ትቶ ወደ screen እና ሌሎች ክፍል በመሄድ ሙቀት እንዲፈጠር ያደርጋል።

➠ ስልካችን እስኪዘጋ ጠብቆ ቻርጅ ማረግ
በባለሙያዎች የሚመከረው ስልካችን ከ 30% እስከ 80% እንዲሆን ነው።

▫️overcharging

➠ ስልካችንን over ቻርጅ ስናደርግ የስልካችን ሙቀት ይጨምራል።

@getcha_techs
☆ ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።

♡ ኮምፒውተራችንን ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል አድርገን እንዴት መቆለፍ እንችላለን።

1 ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት this pc ወይም my computer ላይ Right Click እናደርጋለን።
2 ከዛም ከሚመጡልን ምርጫዎች ውስጥ Manage የሚለውን እንመርጣለን።
3 ቀጥሎም Device Manager
4 ከዛም በቀኝ በኩል ካሉት ምርጫዎች Universal Serial Bus Controllers ከሚለው ስር ያለውን drop down arow ወይም የዝርዝር ቀስቱን እንነካለን።
5 ከዛም extensible host controller ላይ ራይት ክሊክ እናደርጋለን ።
6 ከተዘረዘሩት ዉስጥ Disable ክሊክ እናደርጋልን አለቀ!!
♡ ወደነበረበት ለመመለስ Enable Device የሚለውን ይጫኑ!

☆ አሁን ላፕቶፓችን ወይም ዴስክ ቶፕ ኮንፒተራችን ፍላሽ፣ሃርድዲስክ እንዳያነብ ብሎክ ሁኖል ማለት ነው።
@getcha_techs
በስልካችን ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ሰዓት ብዙ ብር እየወሰደ ካስቸገሮት የሚከተለውን መፍትሄ ያንብቡ። ያነበቡትንም ለሌሎች ያጋሩ።
.
ላይክ እና ሼር ማድረግ አይርሱ!
.
መጀመሪያ ስልኮን በመክፈት Setting  Connection ( Wireless and networks) ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ ስንገባ ኢንተርኔት በጣም የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን በደረጃ ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ ይክፈቷቸው። Foreground (ከፍተው የተጠቀሙት) እና Background (ሳይታዩ አፕሊኬሽኑ በራሱ የተጠቀመው) ምን ያህል Mega Bytes እንደሆነ ይነግረናል፤ ከታች ደግሞ Limit background process የሚል አማራጭ አለ። ከእሱም ፊት ያለውን [ √ ] በማድረግ ካለ እኛ ፈቃድ አፑ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል እንችላለን። ወደ ኋላ እየተመለስን ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ አፖች እየከፈትን መዝጋት (Limit) ማድረግ የሚወስድብንን ብር መቀነስ እንችላለን። በተጨማሪም ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን መዝጋት ይኖርብናል።
አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ Setting  Accounts and Sync ገብተን Background data የሚለውን አለመምረጥ ።
በተጨማሪም Setting  Privacy የሚለውን በመክፈት Back up my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ።
ለHuawei ስልኮች Data usage
ለመግባት፣ Setting  wireless & Networks  more..  Data Usage ->
Restrict background data የሚለውን [ √ ] በማድረግ መምረጥ
Setting -> personal ከሚለው ስር Location access የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት።
ይሄም ስልካችን ያለንበትን ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ያደርጋል።
Setting -> Developer option (About phone ከሚለው ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ ታች ስንወርድ Background Process limit የሚለውን እንክፈት። ይሄ ሁሌም ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን ይመርጠዋል። እዚህ ላይ No background process የሚለውን እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard limit ስለሚቀየር እየገባን መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10 አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል።
Developer option የሚለውን Setting ውስጥ ካጡት
የሚከተለውን ያድርጉ። Setting  About phone የሚለው ውስጥ እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንካው። ከዚያ ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone ከሚለው ከፍ ብሎ Developer option ያገኙታል።
የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ (update) መዝጋት።
ለዚህም Setting  About phone (device)  Software update ገብተን Auto update የሚለው
የተመረጠ ከሆነ [√] እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ።
GPS መዝጋት.
ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት የማይጠይቁ አፖችን (ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣ ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት ያስቀራል።
Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን ኢንተርኔት አለመግባት።
Opera Mini የምንጠቀም ከሆነ Opera Setting ውስጥ Image quality የሚለውን Low quality ማድረግ። ይሄም ኦፔራ ፈጣን እንዲሆን እና ብዙ ገንዘብ እንዳይቆጥርብን ይጠቅመናል።


👉 መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
☆ Contact
☆ Group and Channel share አድርጉልን ከምስጋና ጋር።
@getcha_techs 💻 @getcha_techs
💻ኮምፒውተር ለመግዛት ሲያስቡ ወይም የገዙትን የኮምፒውተር ምን አይነት Specification እንዳለው ለማወቅ ከፈለጉ!

✅በቅድሚያ "My Computer" ወይም "This Computer" የሚመውን icon desktop ይፈልጉ ወይም "Start" ይጫኑ. "My Computer" ወይም "This Computer" ከሚለው ላይ Right-click ያድርጉ. ከሚመጡ አማርጮች ውስጥ "Properties" የሚል መጨረሻ ላይ ያገኛሉ ከዛም ይጫኑ .
አዲስ ፔጅ ይመጣላችኋል...

✅ በመጀመሪያ ደረጃ
የተጫነበትን Windows Edition ምን እንደሆነ ያሳየናል ለምሳሌ Windows 10 Pro

✅ Windows(Opreating System) በመቼ Edition እንደሆነ ያሳየናል።
ለምሳሌ ©2015

✅ RAM(Random Access Memory) ስንት እንዳለው ለምሳሌ ከምስሉ እንደምታዩት 4GB RAM ነው

✅System Type ባለ 64 Bit Opreating System እንደተጫነበትና ኮምፕዩተሩ ባለ X64-Based Processor መሆኑን ያመላክታል።

✅ System Processor መረጃ ይነግራችኋል።
Processor:

Intel(R) Core(TM) i3-5005U CPU @ 2.00GHz 2.00 GHz

🔶 ይህ ማለት ኮምፒውተሩ Core i3 መሆኑን ያመላክታል።
🔶 5005U 5th generation መሆኑን ያመላክታል።
🔶 CPU @2.00GHz የኮምፒውተሩ ፍጥነት ያመላክታል።
~
የ
Computer System Information ምንድን ነው?
~~

1ኛ አማራጭ
Open Start. 1.
Search for msinfo32 and click the top result to open the System Information app.

2. Select the System Summary category from the left navigation pane.
ሰርች ቦክስ ላይ በመግባት System Information የሚለውን ይፈልጉ
2ኛ አማራጭ Windows+R, ስንጫን RUN ይመጣልናል  “msinfo32” ብለው ይጻፉ ከዛም Okን ይንኩ።
System Information የሚል ይመጣላችኋል።
ከእነዚህም ውስጥ

✅ OS Name ይህ የሚያሳየን ከኮምፒውተሩ ላይ የተጫነውን Opreating System ምን እንደሆነ ያሳየናል ለምሳሌ Microsoft Windows 7 Home premium

✅ Version የሚለው የኮምፒውተሩ ላይ ዩየተጫነው Opreating System Versionና Service Pack ስንት እንደሆነ ያሳየናል።

✅ OS Manufacturer ይህ የሚያሳየን Opreating System አምራች ድርጅቱ ማን እንደሆነ ያሳየናል።

✅ System Name ይህ የኮምፒውተሩን System Name ያሳየናል። ይህም ስም የሚገኘው ኮምፒውተሩ እንዳዲስ ሲከፈት ወይም ፎርማት ሲደረግ የሚሰጠው ስም ነው።

✅ System Manufacturer የኮምፒውተሩን አምራች ድርጅት ማን እንደሆነ ያሳየናል። ለምሳሌ Dell, Toshiba, HP

✅ System Model ይህ የሚያሳየው የኮምፒውተሩን ሞዴል ምን እንደሆነ ያሳየናል።

✅ System Type ይህ የሚያሳየን ምን አይነት ከሁለት አንዱን ሲሆን 1ኛው X86-based PCና  2ኛው X64-based PC ናቸው ይህ ማለት X86 ከሆነ 32 Bit Opreating system Support የሚያደርግ ሲሆን X64 ማለት ደግሞ 64 Bit Opreating System Support ያደርጋል ማለት ነው።

✅ Processor የኮምፒውተሩን ፕሮሰሲንግ ፍጥነት በኽርትዝ ስንት እንደሆነና ኮር ስንት እንደሆነ የፕሮሰሰሩ አይነትን ያሳየናል።

✅ BIOS version/Date ይህ የሚያሳየን የአምራቹን ድርጅት ስም፣ የVersion ቁጥርና በመቼ ግዜ እንደተመረተ እ.ኤ.አ ያሳየናል።

✅ SMBIOS version ይህ የሚያሳየን System Management BIOS Version  በቁጥር ያሳየናል።

✅ Windows Directory ይህ የሚያሳየን Windows የተጫነበትን Path ያሳየናል።

✅ System Directory ይህ የኮምፒውተሩን ሲስተም32 System32 የተጫነበትን Path ያሳየናል።

✅ Boot Device የኮምፒውተሩን Boot Device ቦታን ያመላክታል።

✅ User name ይህ የተጠቃሚው Userን ያሳየናል።

✅ Time Zone ይህ ከኮምፒውተሩ ላይ የተሞላውን Time Zome ያሳየናል።

✅ Randome Access Memory(RAM) ከኮምፒውተሩ ላይ ያለው RAM ምን ያክል Size እንደሆነ ያስየናል።

✅ physical available memory ኮምፒውተሩ loading Opreating system ሜሞሪ የያዘውን ሳይጨምር ቀሪው ሜሞሪን ያመላክታል። ምን ግዜም ይቀንሳል ግን መጠኑ ይለያያል እንጅ።

✅ Total Virtual memory ምናባዊ ሜሞሪ ሲባል ኮምፒተርን physical memory እጥረቶችን ለማካካስ የሚያስችል ነው።

📌"The main difference between physical and virtual memory is that the physical memory refers to the actual RAM of the system that stores the currently executing programs, but the virtual memory is a memory management technique that allows the users to execute programs larger than the actual physical memory."

📌እስኪ የእርሶን ኮምፒውተር💻 በዚህ መሰረት ስለኮምፒውተርዎ መረጃ ይወቁ!😊

                  
#Share
👩‍💻@getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs
ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብንና ልናስተውል የሚገቡ ነገሮች

1= ስልካችንን ቻርጀር በ አግባብ መጠቀም
የ ቻርጀሩን Cable ገመድ መጠቅለል የለብንም

2= ስልካችን ቻርጀር ላይ እያለ በ እርጥብ እጅ መንካት የለብንም

3= ስልካችንን ስንገዛ በሚሰጠን ቻርጀር ብቻ ቻርጆ ማድረግ

ለምሳሌ➡ ስልካችሁ (Samsung)ቢሆን በ Huawei] ቻርጀር-ቻርጅ አለማድረግ በራሱ
ቻርጀር ብቻ ቻርጅ ማድረግ ዝምብላቹ ባገኛችሁት ቻርጀር ቻርጅ የምታደርጉ ከሆነ (ባትሪዉ አቅሙን ያጣል)

4= ስልካችን ውስጥ ውሃ ከገባ ወዲያው ባትሪውን መንቀል
ባትሪው የማይነቀል ከሆነ ወደ ባለሞያ መውሰድ

5= በጣም ሙቀት ያለበት ቦታ ስልካችንን አለማስቀመጥ ባትሪው ሊፈነዳ ይችላል

6= ስልካችንን በቀን ውሰጥ ቶሎ ቶሎ
በተደጋጋሚ መሰካት ባትሪውን እድሜ ያሳጥራል አንዴ ካደረግን በቂ ነው

7= ስልካችን ስንጠቀም የሚግል ከሆነ ለተወሰነ ደቂቃዎች Power Off ማድረግ እና ከተወሰነ
ደቂቃ መጠቀም

8= ብዙ ግዜ photo ስንነሳ flash light እንጠቀማለን ለ ፎቶ ጥራት ብለን ነገር ግን ከ
ስልካችን የሚወጣ light ብርሃን ለ ዐይናችን በጣም መጥፎ ነው የማየት አቅማችንን ያደክማል

9= ስልካችንን ሙሉ በ ሙሉ ጨለማ በ ሆነ ክፍል ውስጥ አለመጠቀም የስልኩ ጨረር የዐይንናችንን ይጎዳል ስለዚህ ብራይትነስ የሚቀንሱ አፖችን መጠቀም

10= headset (ኤርፎን) ስንጠቀም ድምፅ እስከ መጨረሻው አለመጨመር ለምን ቢባል

ከፍተኛ ሆነ ድምፅ ለጆሮ መጥፎ ስለሆነና ኤርፎኑም ስለሚበላሽ

11= ሙዚቃ ና የፊልም በ ( ኤርፎን) አይተን ከጨረስን ቦሀላ ኤርፎኑን ከመንቀላችን በፊት ድምፅን መቀነስ ያለበለዚያ ሊበላሽ ይችላል
#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
✅ ስልካችን ቢበላሽ እንዴት አድርገን ስልክ ቁጥሮቻችንን እናገኛለን?

✅ እባኮትን ይህንን የማያውቁ እህት ወንድሞቻችን እንዲያውቁ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup መያዝ አለብን

~1ኛ~~~
እንዴት Buckup እንያዝ?
🔶 Step By Step
1:-contact ዉስጥ መግባት
2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን
3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ
እሱን መጫን\
4:-ከዛ Export to Storage ወይም export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ እሱን
መጫን በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ
FileManager መክፈት
5:-Phone Storage ወይም Memory Storage መክፈት
6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ
7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ Coppy ማረግ ይቻላል
8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad
በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል
~2ኛ~~
2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት
በሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ አንደምንችል
1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየሁችሁ Memory Card ላይ Coppy ማድረግ አለብን
2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት
3:-ከዛ setting botton ዉስጥ መግባት
4:-inport/ export ዉስጥ መግባት
5:-Import from Storage ማድረግ
3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንደምንችል፡፡ እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን በጂሜይል / Gmail / ላይ ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር አገናኝተን የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ አድራሻችንን እዛ ላይ ማኖር ያስችለናል።
በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን እንዳይጠፉብን ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን ድንገት ቢጠፉብን እንኳ ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን ውስጥ
~3ኛ
1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት አድራሻ /
2:-Contacts/ የሚለውን መጫን
3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ / Restore contacts/የሚለውን በመጫን የስልክ አግራሻችንን ጂሜይል ላይ ለማኖር እንችላለን

#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች(Laptop Buying Guide)

በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር አስቀምጠንላችዋል፡፡

1.የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Chrome OS
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ቀላል፤ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፡፡በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆን ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻልም ይነገርለታል፡፡
ክሮም(Chrome OS) ባለቤትነቱ የጎግል ሆኖ ቀላል እና ጥብቅ የደህንነት(security) ያለው ስርዓተ ክውና (OS)ነው፡፡

2.የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደ የስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡ ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡

3.ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡

4.ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡

5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡

6.የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080 የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም ይታወቃል፡፡

7.የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡

8. ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን፡፡
• ከመለዋወጫ አንፃር በሃገራችን Toshibaን የሚያክል ላፕቶፕ የለም፡፡ከተበላሸ እና እክል ካጋጠመው በተመጣጣኝ ዋጋ መለዋወጫ ማግኘት ይቻላል፡፡ Acer ላፕቶፕም የተሻለ መለዋወጫ አለው፡፡
• ከጥራት አኳያ ደግሞ APPLEን የሚደርስ የለም፡፡ HP እና Dell ም የተሻሉ ብራንዶች ሆነው መለዋወጫ ግን እንደልብ ማግኘት አይቻልም፡፡

#Share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs