Getcha Tech's📱💻
136 subscribers
26 photos
3 files
20 links
Download Telegram
ስልካችን ቢበላሽ እንዴት አድርገን ስልክ
ቁጥሮቻችንን እናገኛለን ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ይዘን ቀርበናል እባኮትን ይህንን የማያውቁ እህት ወንድሞቻችን እንዲያውቁ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup መያዝ አለብን እንዴት Backup እንያዝ?
Step By Step
1:-contact ዉስጥ መግባት
2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን
3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ
እሱን መጫን\
4:-ከዛ Export to Storage ወይም export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ እሱን
መጫን በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ
FileManager መክፈት
5:-Phone Storage ወይም Memory Storage መክፈት
6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ
7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ Coppy ማረግ ይቻላል
8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad
በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል
2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት
በሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ አንደምንችል

1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየኋችሁ Memory Card ላይ Coppy ማድረግ አለብን
2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት
3:-ከዛ setting button ዉስጥ መግባት
4:-import/ export ዉስጥ መግባት
5:-Import from Storage ማድረግ
3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንደምንችል፡፡ እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን በጂሜይል / Gmail / ላይ ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር አገናኝተን የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ አድራሻችንን እዛ ላይ ማኖር ያስችለናል።
በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን እንዳይጠፉብን ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን ድንገት ቢጠፉብን እንኳ ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን ውስጥ
1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት አድራሻ /
2:-Contacts/ የሚለውን መጫን
3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ / Restore contacts/የሚለውን በመጫን የስልክ አድራሻችንን ጂሜይል ላይ ማኖር እንችላለን።


▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ ጓደኞቻችሁ
❖ Contact
❖ Group and Channel share
አድርጉልን!!

📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
@getcha_techs
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
#Laptop ስንገዛ #corei3፣ #corei5 #corei7፣#corei9 ሲባል ምን ማለት ናቸው?

#ሼር_ይደረግ

እነዚህ ነገሮች ስለ ላፕቶፑ ምን ይነግሩናል?

ኮምፒውተር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች መካከል #CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ #አእምሮ ማለት ነው።

ይህ #CPU ወይም #processor የተለያዩ ክንዋኔዎችን(Tasks) ተራ በተራ ማከናወን የሚያስችል የኮምፒውተሩ ዋና ክፍል ነው።

በሌላ አነጋገር #CPU ወይም #processor ላፕቶፓችን በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን በከፍተኛ ፍጥነት እንዲሰራ የሚያስችለው የላፕቶፑ ዋና ክፍል ነው።

ታስታውሱ እንደሆነ የመጀመሪያዎቹ ኮምፒውተሮች በአንድ ግዜ አንድ ሰራ ብቻ ነበር መስራት የሚችሉት።ለምሳሌ #Word ከፍታችሁ እየሰራችሁ ከሆነ ጎን ለጎን excel ወይም ሌላ ሶፍትዌር ከፍታችሁ መስራት አትችሉም ነበር።

እዚህ ጋር #Core የሚለው ቃል ይመጣል ።#Core ማት #አንድ ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።#CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ ትልቅ አእምሮ ብትሉት፤ #Core ማለት ትልቁ አእምሮ ውስጥ ያለ #አንድ_ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።

እንደምታውቁት የዘንድሮ ዘመናዊ #ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎች በከፍተኛ ፍጥነት ማከናወን ይችላሉ ።ለምሳሌ #Word ላይ እየሰራን ጎንለጎን #Excel ላይም ልንሰራ እንችላለን፤እንዲሁም ዩቲዩብ ከፍተን ልናይ እንችላለን።....ባጭሩ ብዙ ስራዎችን በአንድ ግዜ ማከናወን ይችላሉ ።

ታድያ #አንድ_core ሜለት #አንድ_አእምሮ ነው ካልን እና #አንድ_አእምሮ ደሞ በአንድ ግዜ አንድ ስራ ብቻ ከሆነ የሚያከናውነው፤የዘመኑ ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንዴት ቻሉ?

አሁን #corei3፣ #corei5 #corei7፣#corei9 የተባሉት ነገሮች ይመጣሉ።

🍭 Corei3 ማለት 3 #processors ወይም 3 አእምሮች ማለት ነው።

🍭 Corei5 ማለት 5 #processors ወይም 5 አእምሮች ማለት ነው።

🍭Corei7 ማለት 7 #processors ወይም 7 አእምሮች ማለት ነው።

🍭 Corei9 ማለት 9 #processors ወይም 9 አእምሮች ማለት ነው።

የ #core ቁጥር እያደገ ሲመጣ ላፕቶፑ በአንድ ግዜ የሚያከናውናቸው ሰራዎች ከፍ እያሉ ይሄዳል ማለት ነው።
Telegram👉@getcha_techs👈
🔊 ዛሬ የምነግራቹ ያገለገለ ስልክ ከ ሰው ላይ ስትገዙ ማድረግ ያለባችሁን ጥንቃቄ እና ማረጋገጥ ያለባችሁን ነገሮች ናቸው....

❗️ከስር የዘረዘርኳቸው ነገሮች በ እናንተ ፍላጎት ልትተዋቸውም ትችላላቹ

➜ በመጀመሪያ ከስልኩ Screen ጀምሩ ና የፊት screen ኑ አለመሰበሩን ጉዳት አለመድረሱን አጣሩ

➜ በመቀጠል የፊት ካሜራው ላይ ጉዳት አለመድረሱን አጣሩ / ጥራቱን ሳይሆን ከተሰበረ ምናምን

➜ አሁን ወደ ጎን ሂዱና የጎን volume እና power buttons መታዘዝ አለመታዘዛቸውን አረጋግጡ

➜በመቀጠል ወደ ኀላ ዙሩና ከኀላ ያሉትን እንደፊቱ አጣሩ

➜ቀጣይ ስልኩ የ sim card በትክክል መቀበሉን, Sd card, Earphone እና በተጨማሪም USB የሚቀበል መሆኑን አጣሩ/ ይሄ ሊቀርም ይችላል ግን ቢሰራ በጣም ጥሩ ነው በቀላሉ በ Connector usb flash በስልካቹ መጠቀም ትችላላቹ። ስልኩን የ ኀላ ክዳን የሚከፈት ከሆነም የ ባትሪ power ስንት እንደሆነ ማየት ትችላላቹ።የማይከፈት ከሆነ ወይም ካልተፃፈ ቡሀላ መፍትሄውን ነግራቹአለው።

➜ ቀጣም ወደ ውስጥ እንግባ የ lock screen check አድርጉ ወደ ውስጥ ገብታችሁም Call, sms,WiFi አጣሩ
➜ አሁን የስልኩን camera, ቅድም ያስገባቹትን sd card ማንበቡን አረጋግጡ

➜ አሁን ከዚህ ቡሀላ ያለውን ሙሉ ነገር ለማጣራት አንድ አኘ ብቻ ስልኩ ላይ መጫን ይበቃል።Device info ይባላል በጣም ገራሚ አኘ ነው ከሌሎች አፓች በተለየ መልኩ ሁሉንም የስልኩን መረጃ ማረጋገጥ ያስችላችኀል።ቅድም ያልኳችሁንም Battery States በዚህ አኘ ማየት ትችላላቹ።

➜ ምናልባት ሰውየው አኘ በ xender ስትላላኩ እንዳይደብረው በቀላሉ አፑን መጀመሪያ memory card ላይ copy አርጋቹ አስቀምጡ በመቀጠልም Memory check ለማረግ ስታስገቡ install አርጋቹ ማየት ነው።አፑ ሁሉንም ነገር ያሳያል

✳️ አሁን አንድ የማቀር ነገር አለ የምትገዙት ስልክ Original ወይስ copy መሆኑን ማረጋገጥ።ይሄም በፍላጎታችሁ ላይ ይወሰናል 👇👇👇

🤜 መጀመሪያ ስልኩ ላይ *#06# አስገቡ እና የ ስልኩን imei no አግኙ/ያዙ

🤜 http://www.imei.info ወደ ዚህ Website ሂዱ እና የ ስልኩን Imei no አስገቡ

🤜 ከዛ search አርጎ ያመጣው የዛን ስል information ከሆነ original ነው👍 ማለት ለው የ ሌላ ስልክ info ካመጣ ደሞ FAKE 😭

🔊 አሁን ሙሉ መረጃውን አውቃችኀል ስልኩን መግዛትም መተውም ትችላላቹ.....

@getcha_techs
🎉አሻምቴሌ

📌አሻምቴሌ በቋሚነት የድምጽ ጥሪ፣ የዳታ/የኢንተርኔት፣ አጭር የፅሁፍ መልዕክት እንዲሁም የቴሌብር አገልግሎቶችን ስትጠቀሙ #ነጥቦችን መሰብሰብ ያስችላችኋል፡፡

📍በሰበሰባችኋቸውም ነጥቦች የስልክ ቀፎ📲፣ ታብሌት📱፣ ላፕቶፕ💻 እና ጥቅሎችን💰 መግዛት እንዲሁም ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችዎን መፈፀም ትችላላችሁ፡፡

🦋#Share🦋
👩‍💻 @getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs 👩‍💻
✳️ ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ የምናየው ኢንተርኔት ስንጠቀም ዳታ ለመቆጠብ ከስር ያሉትን ዘዴዎች መጠቀም እንችላለን
Step ይከተሉ።

1. Setting ይጫኑ
2. Data Usage ይጫኑ
3. Option ወይም ... ከላይ እነዚህን ሶስት ነጥብ ይጫኑ
4. Restricted Background Data ሚለውን ይጫኑ።

ወይንም

1. Setting ይጫኑ
2. Network and Internet ይጫኑ
3. Data Saver ይጫኑ
4. Data Saverን On ያርጉት


😌 የ ሶሻል ሚዲያ አፖች ላይ ዳታን ለመቆጠብ እነዚህን መንገዶች ተጠቀሙ።

▫️Telegram ላይ ዳታን ለመቆጠብ

1.Telegram ይክፈቱ
2. setting ይጫኑ
3. Data and Storage ይጫኑ
4. When Using.Mobile Data ይጫኑ
5. ራይት(✅) የተደረጉትን በሙሉ ያጥፉት

▫️Facebook Lite ላይ ዳታን ለመቆጠብ

1. Facebook Lite ይክፈቱ
2. Setting ይጫኑ
3. Data Usage ይጫኑ
4 Data Saverን On ያርጉት

▫️WhatsApp ላይ ዳታን ለመቆጠብ

1. Whatsappን ይክፈቱ
2. Option ወይም --- ከላይ እነዚህን ሶስት ነጠብጣብ ይጫኑ
3. Settingን ይጫኑ
4. Data and Storage Usage ን ይጫኑ
5. Whan using Mobile Data ን ይጫኑ
6. ራይት(✅) የተደረጉትን በሙሉ ያጥፉት

▫️TikTok ላይ ዳታን ለመቆጠብ

1. TikTokን ይክፈቱ
2. Option ወይም --- ከላይ እነዚህን ሶስት ነጠብጣብ ይጫኑ
3. Cache & Cellular Dataን ይጫኑ
4. Data Saver ይጫኑ
4 Data Saverን On ያርጉት።

ወይንም

▫️10 ተመራጭ ዳታ #ቆጣቢ አፕሊኬሽኖች መርጦ በመጫን እና #ፕሮሰስ እንዲያርጉ የማይፈለጉትን አፕሊኬሽኖች #መዝጋት
መፍትሔ ማግኘት ይቻላል።

1. Datally
2. My Data Manager
3. Data Usage Monitor
4. DataEye
5. GlassWire
6. Net-Guard
7. Data Monitor
8. InternetGuard
9. Data Saver
10. Data Manager
🦋#Share🦋
👩‍💻 @getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs 👩‍💻
የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡

❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡

🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡

“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር የሚደረግ CPU ናቸው፡፡
ለምሳሌ Core i7-6700k እና Core i7-5820k ባሉ የሞዴል ቁጥር መጨረሻ ላይ unlocked(ያልተቆለፈ) ስለሆሀን Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) የተሠሩ ናቸው ፡፡ ይህ ማለት Unloc Processors ከፋብሪካ ዋና ፍጥነቶች በበለጠ ፍጥነት ከመጠን በላይ ሊጫኑ ይችላሉ ፡፡ የተቆለፉ ማቀነባበሪያዎች (Processors) ከመጠን በላይ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር) አይችሉም።
ስለዚህ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K

“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።

“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡

🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ

”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) ያደረጋል፡፡

“Y” - Extremely low Power

“U” – Ultra low Power

ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡

ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U

🦋#Share🦋
👩‍💻 @getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs 👩‍💻
https://t.me/Getcha_Tech
🔷🔴📲Samsung A10s

🔰 used orginal ®

📶 Dual Sim

⏳👉👉 2GB Ram

📼Storage :- 32 GB

☢ 4000 mAh Battery
👨‍💻SD ፣ HD ፣ 4K እና 8K ምንድን ናቸው❓
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔆የቴክኖሎጅ ርቀት እና ምጥቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን በተለይ ከእይታ (ምስል) ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ደግሞ ለማመን የሚከብዱ ተአምራት እየሆኑ መጥተዋል ።
የምስል ጥራት በፒክስል የሚለካ ሲሆን በ3 ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላል።

እነሱም፦
➀ SD [standard_definition]-መደበኛ ጥራት
➁ HD [High definition] - ከፍተኛ ጥራት
➂ UHD [Ultra high definition ]- ከመጠን ያለፈ ጥራት ናቸው።

ፒክስል ስንል አንድን ምስል ለመስራት የሚያስችል ትንሿ ነጥብ(ስኩዌር ◾)ማለታችን ነው።
✅የፒክስሎች ስብስብ ሪዞሉሽን ሊሰኝ ይችላል።

ለምሳሌ ፦ ከአንድ ምስል ላይ አንድ ስኩየር (ልክ ኬሚስትሪ ላይ atom እንደምንለው) ወስደን ብንመለከት የወርድ ነጥቦች ስብስብ ብዛት × የቁመት ነጥቦች ስብስብ ብዛት ፒክስል ይባላል ማለት ነው ።

🔴720 × 480 pi ሲባል
720=የወርድ(w)ነጥቦች ብዛት እና
480= ቁመት(h) ነጥቦች ብዛት በአንድ ሊከፈል በማይችል ስኩዌር ውስጥ ማለታችን ነው ። ፒክስል በበዛ ቁጥር ጥራት ይጨምራል። በሌላ በኩል የምስሉ MB ም ይጨምራል ።⬆️

📌በየዘመናቱ የመጡ የምስል ጥራት እድገትን ብንመለከት ከመጀመሪያው እስከ አሁን ድረስ የሚከተሉትን ይመስላል።

✅SD= 720 × 480
◾PAL= 768 × 576
◾NTSC= 720 × 534 (የድሮ ሪሲቨሮች)
✅HD= 2K
◾HD = 1280 × 720
◾Full HD =1920 x 1080
✅UHD=
◾4K= 3840 × 2160 (16:9 YouTube size)
◾5K= 5120 × 2700
◾6K = 6144 × 3160
◾8K = 7680 × 4320 አሁን የደረስንበት የመጨረሻው ቴክኖሎጅ።

📌ሀገራችን ላይ በስፋት በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው ሰው ቤት የሚገኘው Full HD እና 4K ሪሲቨር ሲሆን አልፎ አልፎ 8Kም ይኖራል። ነገር ግን እዚ ላይ ልንገነዘበው የሚገባን ነገር ቢኖር ባለ 8K ቻናልን ለመመልከት ሪሲቨራችን እንዲሁም ቲቪያችን የግዴታ 8K ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ የቻናሉ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ ለመለየት እንቸገራለን ። ያ ማለት HD ቻናሎችን በAV ኬብል እንደመመልከት ይሆናል ማለት ነው።

📌በዚህ ጊዜ 8K እንኳን ቀርቶ 4K ቲቪ ራሱ የሚገዛ ሰው ኪሳራ ላይ እንደወደቀ ይሰማኛል፤ ምክንያቱም በ4K Quality Broadcast የሚያደርጉ የቲቪ ቻናሎች የሉንም🥺🥺🥺

@getcha_techs
VidMate_com.nemo.vidmate_346_3.46_.apk
8.1 MB
👆👆አፑን ለማውረድ
ከዩትዩብ ላይ ቪዲዮዎችን በፍጥነት ለማውረድ, የዩትዩብ ቪዲዮ በጥራት ለመመልከት የፈለግነውን ፋይሎች በቀላሉ ለማስተላለፍ የሚጠቅመን አሪፍ አፕ ነው፡፡
@getcha_techs
ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን?


1. cmdን በአንሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)

2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ:netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው

3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password
⚠️ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን

4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን። ከዛም OK በለን እንወጣለን

5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን

6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።
@getcha_techs
#አንብቧት😊

📌መቼም ቢያንስ ስልክ📲 የሌለው ሰው የለም😁 ያ ማለት ሁላችንም ወደድንም ጠላንም #ቴክኖሎጂ ሳይነካን አያልፍም።‼️ ሲኖር ለመጠቀም ሲበላሽ ለማስተካከል የተጠየቃችሁትን መክፈል ወይም #በራሳችሁ መስራት የግድ ነው።

📌ደጋግመን እንደምንናገረው የኛ ቻናል እና ግሩፕ ዋና አላማ ቢያንስ ቀላሎቹን ችግሮች በራሳችሁ እንድትፈቱ፣ የማታውቁትን እንድታዉቁ ነው።🙏🙏🙏

📌እዚ ምንማማረው 1ሰው ለሺዎች ነው #በተጨማሪ ግሩፑን @getcha_techs_group ብትቀላቀሉ ሺዎች ለሺዎች ትማማራላችሁ፤ ትረዳዳላችሁ👏 ስለዚህ ጊዜ ሳታጠፉ ተቀላቀሉ።😊🙏🙏🙏
💢ስልካችሁ📲 ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ

✅This Application Stopped Working‼️
✅Crashing‼️
✅Won’t open‼️
✅Won’t respond‼️
✅Isn’t working properly‼️እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ

1⃣.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

⚠️ስልካችሁን📲 #Restart አድርጉት።

⚠️Setting➡️ Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን📲 Operating System #Update አድርጉ።

⚠️Playstore ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2⃣.Update Google Play Services

⚠️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3⃣. አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ Setting ውስጥ ገብታችሁ #Forced_Stop አድርጉት።

⚠️System App ካልሆነ #Uninstall❌ ያድርጉት።

4⃣. Clear App and Cache ይሞክሩ።

⚠️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5⃣. እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች📲 ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

⚠️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም‼️

📌መረጃዎችን ለወዳጅዎ 🗣👥 ያጋሩ።
❓ጥያቄ ካለዎት @getcha_techs_group 🤖🤖ላይ ይላኩልን።

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 🖥 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

@getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs
Yacine TV telegram.apk
8.1 MB
yacin tv

👉WORK WITH A LOW CONNECTION
👉WORKS FOR LOW STORAGE DEVICES
👉WITH OUT ANY CODES

ይህ App Yacine tv app ይባላል በጣም ጥሩ ነው ትወዱታላችሁ ዳውሎንድ አድርጋችሁ የተለያዩ ሊጎች ጨዋታወችን በጥራት መመልከት ትችላላችሁ።
@getcha_techs
ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለባችሁ 10 ወሳኝ ነገሮች
✍1ኛ :- ያለንበትን ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልከውን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላክዋን ከፍተን location የምለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::
✍ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል እንዴት መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የምለውን እንነካለን ከዛ passcode የምለወን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::
✍ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንደይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የምለዉን እንነካለን ከዛ
ከዛ when using mobile data -OF-አድርጉት ::
✍4ኛ :- የለክነዉን message ከደረሰ ቦኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የለነክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የምለውን Also delete receive የምለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::
✍5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት
✍6ኛ :- በተላይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፈ ላይ የለወን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከምሰጠን የመልክ ምርጫ የፍለግነዉን እንመርጣለን ::
✍7ኛ :- ቴሌግራም የሉ ፅፎች አልነበብ እየሎት ተቸግረዋል ማለት ፍደሎችሁ አንሰዉ ለዓይን አልተይ ከለ ፍደሎቹሁን ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
አዎ በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፍለግነዉን ያህል ትልቅ ማድርግየ ይቻላል ::
✍8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የምለውን ነክተን create new channel የምለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፍለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::
✍9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራፍ ጉሩፒ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ የለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የምለውን እንነካለን ከዛ create new groupጠ የምለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፍለግነዉን የጉሩፒ ስም እናስገባለን ::
✍10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የምለውን በመንካት የፍለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።
@getcha_techs
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-

1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡

2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡

3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡

4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡

5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

@getcha_techs
በPATTERN ወይም የተዘጉ ስልኮች ካለ ምንም ኢንተርኔት እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መመለስ እንደምንችል ከዚህ በፊት ሰፋ ባለPassword ፕሮግራም መልቀቃችን ይታወሳል ለማታቁት ዛሬም እናቀርባለን።

ኣስፈላጊ ነገሮች:-
1 aroma file manager በሌላ ስልክ ማውረድ ኣለብን
2 ሚሞሪ ካርድ(ያወረድነውን app
የምንናስቀምጥበት)
3 የተዘጋው ስልክ
~
Step1:- aroma file manager ካወረዳቹ ወደ ሚሞሪ ካርዱ ጫኑት እና ካርዱ ወደ ተዘጋው ስልክ ኣስገቡት
Step2:- ከዛ ስልኩ power off እናረገው እና የ recovery stock ወይም ስልካችን ካጠፋነው ቡሃላ የ power እና የ ድምፅ መጨመርያ ኣንድ ላይ ተጭነን እንቆያለን( እንደ የ ስልኩ ኣይነት ሊለያይ ይችላል)
Step3:- ወደ recovery mode ከገባን ቡኋላ የ ድምፅ መጫኞቹ ወደ ላይ እና ታች የ power መጫኛው ደሞ እንደ ok ሁነው ያገለግላሉ
Step4:- recovery mode ላይ install zip from sd card የሚለውን ላይ ok/power button እንጫን እና aroma file manager ያስቀመጥንበት folder ገብተን install እንለዋለን
Step5:- ከዛ aroma file manager ከከፈታቹ ቡኋላ ወደ nevigate የሚለውን ትወርዱ እና automount all devices on start የሚለውን ተጭናቹ ከዛ ዝጉት።
Step 6:- step4 ላይ እንዳደረጋችሁት step6 ላይም ድገሙት
Step7:- aroma file manager እንደገና ሲከፈት ወደ data folder ከዛ system folder ትገቡ አና 'gesture.key' or 'password.key' የሚል ታገኛላቹ
Step8:- ከዛ ያገኛችሁት gesture.key or password.key ኣጥፉት ከዛ ስልካቹ reboot ኣድርጉት
Step9:- ስልኩ ሲከፈት የማትረሱትን pattern ወይም password በማስገባት መክፈት ትችላላቹ።

@getcha_techs
ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ እንዴት ማስተካከል ይቻላል?
በተለያዩ አጋጣሚዎች ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፣ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ከመደናገጥ ይልቅ ቀላል የሆኑ አካሄዶችን በመከተል ስልክዎ. እንዳይበላሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ከሁሉም በፊት ስልክዎን በፍጥነት ከዉሀ ዉስጥ ማዉጣት ይኖርቦታል፡፡ ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ በቆየ ቁጥር ዉሀ ወደ ስልክዎ ዋና ክፍሎች ዉስጥ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
ሊከተሉዎቸዉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እንመልከት፡
በፍጹም ሊያደርጉዎቸዉ የማይገቡ ነገሮች
• ስልክዎን እንዳያበሩት
ስልክዎ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች አይንኩ
•ስልክዎን አያወዛዉዙት ወይም ስልክዎ ከሌሎች ነገሮች ጋር አያጋጩት
•የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች አይንቀሉ፡፡
ስልክዎ የዉሀ ብልሽት አመላካች(Liquid Damage Indicator(LDI)) ተገጥሞለታል፣
የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች የሚከፍቱት ከሆነ ይህ የዉሀ ብልሽት አመላካች አክቲቭ(Active) ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ከስልኩ አምራች
ድርጅት የሚሰጠዉን Warranty ያሳጣዎታል፡፡
በትንፋሽዎ ዉሀዉን ለማድረቅ አይሞክሩ፣
ምክንያቱም ስልክዎ ላይ በሚተነፍሱበት ጊዜ ዉሀ ወደ ዉስጠኛዉ የስልክዎ ክፍል ዉስጥ ሊገባ ስለሚችል ነዉ፡፡
ስልክዎን በማንኛዉም አይነት. የሙቀት መሳሪያ ለማድረቅ አይሞክሩ፡፡

ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ ከብልሽት የሚከላከሉባቸዉ አካሄዶች
1) ስልክዎን ከዉሀ ዉስጥ ሲያወጡት እየበራ ከሆነ ያጥፋት እና ቀጥ አድርገዉ ይያዙት፡፡
2) የስልክዎን ከቨር በመክፈት ባትሪ፣ሲም ካርድ እና ሚሞሪ ካርዱን ያዉጡ፡፡
3) ደረቅ ጨርቅ ወይም ማድረቂያ በመጠቀም ስልክዎን ያድርቁ፡፡
ዉሀ ወደ ሌላ የስልክ ክፍሎች እንዳይተላለፍ ይጠንቀቁ፡፡
4) በጐድጓዳ ሰሀን ላይ ያልተቀቀለ ሩዝ ይጨምሩ እና ስልክዎን ሩዝ ዉስጥ ይክተቱት፡፡ ሩዝ ዉሀን የመምጠጥ አቅሙ በጣም ከፍተኛ
ስለሆነ አብዛኛዉን ጊዜ ስማርት ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለማድረቅ ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡
5) ስልክዎ በሩዝ ዉስጥ ለአንድ ወይም ሁለት ቀን እንዲቆይ ያድርጉ፡፡ በእነዚህ ቀናቶች ዉስጥ ስልክዎን ለማብራት እንዳይሞክሩ፡፡
6) ከጥቂት ቀናቶች በሗላ ስልክዎን ከሩዝ ዉስጥ ያዉጡ እና ባትሪዉን አስገብተዉ ያብሩት፡፡
ስልክዎ አሁንም ካልበራ ባትሪዉን ቻርጅ ያድርጉት፣
ቻርጅ ተደርጎም የማይበራ ከሆነ ባትሪዉ ብልሽት አጋጥሞታል ማለት ነዉ፡፡
ባትሪ ይቀይሩለት ወይም ወደ ስልክ ሰሪዎች ይዉሰዱት፡፡

@getcha_techs
✴️ የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ድረገፆች ( website )
1 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ www.aau.edu.et
2 መቀሌ ዩኒቨርስቲ www.mu.edu.et
3 አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ www.astu.edu.et
4 አክሱም ዩኒቨርስቲ www.axu.edu.et
5 አምቦ ዩኒቨርስቲ www.ambou.edu.et
6 አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ www.amu.edu.et
7 ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ www.bdu.edu.et
8 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ www.dbu.edu.et
9 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ www.dmu.edu.et
10 ዲላ ዩኒቨርሰቲ www.du.edu.et
11 ጎንደር ዩኒቨርስቲ www.gu.edu.et
12 ጂማ ዩኒቨርስቲ www.ju.edu.et
13 ሃረማያ ዩኒቨርስቲ www.haramaya.edu.et
14 ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ www.hu.edu.et
15 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ www.wsu.edu.et
16 ወለጋ ዩኒቨርስቲ www.wu.edu.et
17 ድሬ ዳዋ ዩኒቨርስቲ www.ddu.edu.et
18 ወሎ ዩኒቨርስቲ www.wou.edu.et
19 ጅጅጋ ዩኒቨርስቲ www.jgu.edu.et
20 መዲ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ www.mwu.edu.et
21 ሚዛን ቲፒ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
22 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ www.su.edu.et
23 ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ www.kuc.edu.et
24 አአ ሾል. & ቴክ ዩኒቨርሲቲ www.aastu.edu.et
25 አዲግራት ዩኒቨርሲቲ www.adu.edu.et
26 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ www.asu.edu.et
27 ቡሌ ሁራ ዩኒቨርስቲ www.bhu.edu.et
28 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ www.dbtu.edu.et
29 መቱ ዩኒቨርሲቲ www.mtu.edu.et
30 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ www.wcu.edu.et
31 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ www.wku.edu.et
32 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ www.wdu.edu.et
33 አርሲ ዩኒቨርሲቲ www.aru.edu.et
34 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ www.gmu.edu.et
35 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ www.obu.edu.et
☆Getcha Tech☆
@getcha_techs
✳️ የሞባይል ባትሪያችንን የሚጎዱ ነገሮች

▫️ሙቀት


➠ ሙቀት አንደኛው የስልካችን ባትሪ ጠላት ነው።በተለይ ስልክን ሞቃጣማ ቦታ ላይ charge ማድረግ።ስልካችንን አብዝተን ስንጠቀም ባትሪያችንን ሙቀት ከሚጎዳው ይልቅ ይጎድለዋል።ስልክን በቀዝቃዛ ቦታ ቻርጅ ማረግ ቻርጅ ሲያረግ ፍጥነቱን ይቀንሳል።

▫️ቻርጀር(charger)

➠ ሌላኛው ደግሞ የምንጠቀመው ቻርጀር ነው።በአሁን ጊዜ ገበያ ላይ ብዙ አይነት ፈጣን ቻርጀር(fast charger)አሉ።
ስልክ ስንገዛ ከስልኩ ጋር ቻረጀር የሚሰጠን, ያ ቻርጀር የሚመጣውን የኤሌትሪክ ሀይል ለስልካችን መጥኖ ወደ ስልካችን ይልከዋል።ነገር ግን ከገበያ የሚገዛው ለስልካችን አብዝቶ ወይም አሳንሶ ነው ሚሰጠው።

▫️የስልክ ቻርጅ አደራረግ ባህል

➠ ስልካችን ቻርጅ እያረገ መጠቀም
ስልካችን ቻርጅ እያረገ ስንጠቀም, ወደ ባትሪው መሄድ ያለበት የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ ባትሪዉ መሄዱን ትቶ ወደ screen እና ሌሎች ክፍል በመሄድ ሙቀት እንዲፈጠር ያደርጋል።

➠ ስልካችን እስኪዘጋ ጠብቆ ቻርጅ ማረግ
በባለሙያዎች የሚመከረው ስልካችን ከ 30% እስከ 80% እንዲሆን ነው።

▫️overcharging

➠ ስልካችንን over ቻርጅ ስናደርግ የስልካችን ሙቀት ይጨምራል።

@getcha_techs
☆ ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።

♡ ኮምፒውተራችንን ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል አድርገን እንዴት መቆለፍ እንችላለን።

1 ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት this pc ወይም my computer ላይ Right Click እናደርጋለን።
2 ከዛም ከሚመጡልን ምርጫዎች ውስጥ Manage የሚለውን እንመርጣለን።
3 ቀጥሎም Device Manager
4 ከዛም በቀኝ በኩል ካሉት ምርጫዎች Universal Serial Bus Controllers ከሚለው ስር ያለውን drop down arow ወይም የዝርዝር ቀስቱን እንነካለን።
5 ከዛም extensible host controller ላይ ራይት ክሊክ እናደርጋለን ።
6 ከተዘረዘሩት ዉስጥ Disable ክሊክ እናደርጋልን አለቀ!!
♡ ወደነበረበት ለመመለስ Enable Device የሚለውን ይጫኑ!

☆ አሁን ላፕቶፓችን ወይም ዴስክ ቶፕ ኮንፒተራችን ፍላሽ፣ሃርድዲስክ እንዳያነብ ብሎክ ሁኖል ማለት ነው።
@getcha_techs