Getcha Tech's📱💻
136 subscribers
26 photos
3 files
20 links
Download Telegram
🖱ሲም ካርድን ይተካል የተባለው ኢ ሲም ምንድን ነው…?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❖እንደ ኦ.ኢ.ኤም፣ አፕል እና ጎግል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች ደግሞ በአዳዲስ ምርቶቻቸው ላይ ኢ ሲም ማካተት መጀመራቸው ተሰምቷል።

❖“ኢ ሲም ምንድን ነው”..? ካላችሁ ኢ ሲም ልክ እንደ መደበኛው ሲም ካርድ በስማርት ስልካችን ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለን ነው።

❖ነገር ግን ኢ ሲም በጠቅታ በስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ የሚገጠም እንጂ እንደ ከዚህ በፊቱ አይነት ማስገቢያ የሚፈልግ እንዳልሆነ ተነግሯል።

❖ኢ ሲምን አጠቃቀምም አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ሲም ካርድ ጋር ሲነጻጸር ቀላል እንደሆነም ነው የተነገረው።

❖እንዲሁም ኢ ሲም አንድ ጊዜ የስማርት ስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ ከተገጠመ በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ እንደሚሆንም ነው የተጠቆመው።

❖ከዚህ በተጨማሪም ኢ ሲም የስማርት ስልክ አምራቾች በጣም ጠፍጣፋ ስልክ ለማምረት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነም ነው የተገለፀው።

❖በአሁኑ ወቅትም አንድ አንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በስልኮቻቸው ላይ ከመደበኛው ሲም ካርድ በተጨማሪ ኢ ሲምን እንደ አማራጭ እያቀረቡ እንደሆነም ተነግሯል።

❏አሁን በገበያ ላይ የዋሉ እና ኢ ሲምን የሚቀበሉ ስማርት ስልኮችም ጎግል ፒክስል 2፣ ጎግል ፒክስል 2 XL፣ ጎግል ፒክስል 3፣ ጎግል ፒክስል 3 XL፣ ጎግል ፒክስል 3a፣ ጎግል ፒክስል 3a XL፣ አይፎን XS፣ አይፎን XS Max፣ አይፎን XR፣ አይፓድ ፕሮ እና ኳልኮም ስናፕድራጎን 850 ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ዊንዶውስ 10 ኮምፒውተሮች ይገኙበታል።
Credit_Nurhusen Yesuf
#Share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
ሞባይል ስንገዛ ኦርጅናልና ፌክ መሆኑን እንዴት ማወቅ እንደምንችል እነሆ

✔️ከሌሎች በይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም📱 በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡

🔆ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣ የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡

⚠️ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን እነዚህን 👇 መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ...

የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 👇

💢#ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡

1⃣. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም‼️

2⃣. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል‼️

3⃣. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል‼️

4⃣. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል‼️

5⃣. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን ይመለከታሉ‼️

የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም *

1⃣. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል 😡

2⃣. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች 🎮 እና አፕሊኬሽኖችን ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡ 😡😡

3⃣. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም😡😡😡

የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም

1⃣. ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ...

2⃣. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ #Settings የሚለዉን ይጫኑ...

3⃣. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

4⃣. እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም #ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም *

💢ወደ ስልክ📱 መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ✔️ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን 😭 ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

1⃣. *#0*# 👉 አጠቃላይ መገምገሚያ

2⃣. *#1234# or *#9999# 👉 ስልኩ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ

3⃣. *#12580*369# 👉 ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ

4⃣. *#06# 👉 የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር ማወቂያ

5⃣. *#9998*246# 👉 የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ

ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም *

💢ከላይ 👆 በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1⃣. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት💻 ላይ ይጫኑት...

2⃣. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት

3⃣. ሶፍትዌሩ ስልኩን 📱ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤ ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

❖ ውድ የ Getcha_techs ቤተሰቦች ድጋፋችሁን ቻናላችንን ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን።
Credit Nurhusen yesuf
#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ናችሁ? 👆👆👆
አሁን ደግሞ ይዤላችሁ የመጣሁት እኛን ትምህርት ቤታችንን፣ ወረዳችንን፣ ዞናችንን፣ ክልላችንን፣ እንዲሁም ሀገራችንን ሊጠቅም የሚችል ምርጥ የፈጠራ ስራ ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ። ስራውም ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ የግልም ሆነ ለመንግስት ትምህርትቤቶች የሚጠቅም ከዚህ በፊት የነበረን የወረቀት የተማሪዎችን የመረጃ አያያዝ ወደ ኮምፒውተራይዝድ Online system(Students Information Management System) ይዤላችሁ ምርጥቻለሁ። ስለሆነም ከጥቅሙ ስነሳ
የትምህርት ቤቶች የመረጃ አያያዝ በጣም ዘመናዊ የሚያደርግ።
የሀብት፣ የጉልበት እንዲሁም የጊዜን ብክነት ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ የሚቀንስ።
ለመምህራን፣ ለተማሪዎች፣ የመረጃ አያያዝ ባለሙያዎች ስራንና መረጃ አያያዝን ቀላልና ቀልጣፋ የሚያደርግ።
ሌላም ሌላም ዘርፈ ብዙ ስራዎችንና ጫናወችን የሚቀንስ።
◄◄◄ የሚሰራቸው ስራዎች▻▻▻
የመረጃ ሲስተሙ ለብዙ አመታት መረጃን መያዝ የሚችል ነው። የአንድ አመትን ውጤት ብቻ ይዞ የሚያቆም አይደለም።
ሲስተሙ እያንዳንዱ የሚመለከተው ተጠቃሚ(Users) ለምሳሌ መምህራን ር/መምህራን የመረጃ ባለሙያዎች በአንድ ላይ እንደማንኛውም ለምሳሌ እንደ ፌስቡክ username and password በማስገባት መጠቀም ይችላሉ።
ሲስተሙ ብዙ ተጠቃሚዎችን ማስጠቀም ይችላል
መምህርንን ተማሪዎችን በአንድ ላይ መዝግቦ ይይዛል።
የመረጃ ስርአቱ በትምህርት ቤቱ ህጋዊ ባለሙያ በአንድ ቦታ ቁጭ ብሎ መቆጣጠር የሚያስችል።
የሚመለከተው አካል ለምሳሌ የትምህርት ቤት ር/ መምህሩ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያለውን የተማሪዎችን ውጤት ያለበትን ሁኔታ ማየትና መከታተል የሚያስችል።
ለምሳሌ ምን ያክል ተማሪ የማለፊያ ውጤት፣ ወደሚቀጥለው ክፍል መዘዋወር ያልቻሉት ምን ያክል ናቸው እንዲሁም ሌሎች ተግባራቶችን ማየትና መሰራት ያለበትን ስራ እንዲያይ ይረዳዋል።
መምህራን ወቅታዊ ውጤት በማስገባት ብቻ ሲስተሙ ለምሳሌ transfer sheet, Roster, student result sheet, ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን automatically ሲስተሙ የሚሰራቸው ስራዎች ለምሳሌ የውጤት ድምር፣ አማካይ ውጤት፣ ደረጃን እንዲሁም ሌሎችን መስራት ይችላል።
ለተማሪዎች በ1 ደቂቃ ውስጥ ለምሳሌ የተማሪውን transcript, result sheet በወረቀት ከተፈለገ print በማድረግ አገልግሎት ማግኜት ይቻላል።
የተማሪዎች ማንኛውንም ውጤት አስተማሪው የራሱን ተማሪዎችን ውጤት መሙላት የሚያስችል።
ተማሪዎች የራሳቸውን ውጤት ቀን በቀን ምን ያክል እንደሰሩ መከታተል የሚያስችል።
ተማሪዎች ውጤታቸውን በማየት ማስተካከል ያለባቸው የትምህርት አይነት ጠንክረው በማንበብ እንዲሁም በአለበት እንዲቀጥሉ ማድረግ የሚያስችል።
Credit_Muhammed Computer Technology(MCT)
#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ናችሁ? 👆👆👆
ቢያውቋቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ወሳኝ ድረገፆች
********
ኢንተርኔት እንደዓለም ዳርቻ እጅግ ጥልቅ በሆነበት በአሁን ሰዓት ሁሉንም የድረገፅ አይነት
አውቆ መጠቀም ምናልባትም በዓለማችን በሚገኙ እያንዳንዱ ቦታዎች ተዘዋውሮ
እንደመጎብኘት እጅግ ሊከብድ ይችላል፡፡ ታዲያ እነዚህ ጥበብን፣ እውቀትን፣ ልምድን እና
በጠቅላላውም ህይወትን ለመቀየር የሚያስችሉትን፤ ወሳኝ ድረገፆች አውቆ ለመጠቀም
የሌሎች ጠቋሚነት እጅግ ወሳኝ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ በመሆኑም ለዛሬ ከዚህ በፊት
የማያውቋቸው ነገር ግን ከዚህ በኋላ ቢያውቋቸው እጅግ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ድረ
ገፆችን ከተለያዩ ምንጮች አሰባስበናል፡፡
ያወቁትን ሌሎች እንዲያውቁት ብታደርጉ የበለጠ ያተርፋሉ!!!
1. ከሌላው ዓለም ህዝብ ጋር ጥበብን፣ አውቀትን እና ልምድን ለማጋራትና ለማንሸራሸር
MentalFloss.com
Lifehacker.com
https://www.quora.com/
https://medium.com/
Lumosity.com
2. አዲስ ነገር መማር ሲፈልጉ
• Make code (Microsoft MakeCode) {Must visit!}
• Guitar ( https://www.justinguitar.com/ ) {you can thank}
• Duolingo (Learn a language for free)
• Tutorials Point (Tutorials)
• Experiments with Google
3. ለግራፊክስ ዲዛይነሮች ከphotoshop ውጭ ሌላ አማራጭ ሲፈልጉ
• Free Pik ( https://www.freepik.com/ )
• Flaticon ( https://www.flaticon.com/ )
• Adobe colour picker (Adobe Color CC)
• Pexels ( https://www.pexels.com/ )
• Video Pexels (Free stock videos - Pexels Videos)
• Canva (Amazingly Simple Graphic Design Software
4. ከEmail ውጭ ሌላ አማራጭ ይኖር ይሆን ካሉ
www.bluebottle.com
http://mail.yahoo.com
http://gmail.google.com
www.hotmail.com
www.walla.com
5. የጤናዬ ጉዳይ ያሳስበኛል ካሉ
www.nelh.nhs.uk
www.hpa.org.uk
www.food.gov.uk
www.bmj.com
www.avert.org
6. ሲደብሮትና እና ራሶን ለማንቃት ሲፈልጉ
• Ted ( https://www.ted.com/
www.7billionworld.com
www.beesbeesbees.com
www.sanger.dk


#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
📍Ethio Telecom

ወደዚች ዓለም የተቀላቀላችሁባትን #የልደት ቀናችሁን አብረናችሁ ለማክበር ልዩ የልደት የሞባይል ጥቅል በስጦታ ስናበረክት ደስ እያለን ነው።
ምን ይሄ ብቻ በልደት ቀናችሁ በሚደርሳችሁ መልእክት መሰረት ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ተጨማሪ 20% ቅናሽ የተደረገበት የልደት ጥቅልም አቅርበናል፡፡

የልደት ቀን መረጃችሁ ድንገት ትክክል ባይሆን ወደ አገልግሎት ማዕከሎቻችን ጎራ ብላችሁ ማስተካከል ይቻላል።

                    #share
👩‍💻 @getch_techs 👨‍💻 @getcha_techs 👩‍💻
ጥሪ ሲቀበሉ/ሲደውሉ ቀድሞ በሚደርስ መልዕክት ሃሳብዎን ለመግለፅ የጥሪ መለያ (call signature) አገልግሎታችንን ምርጫዎ ያድርጉ!
ለዕለታዊ *623*1*1# ወይም ለሳምንታዊ *623*1*2# በመደወል ይመዝገቡ።
ስልክ ሲደወልልዎ ጥሪውን ከማንሳትዎ በፊት ለደዋዩ የሚፈልጉትን መልዕክት ለማስተላለፍ፤ ማስተላለፍ የሚፈልጉትን የመልዕክት ይዘት ወደ 623 በፅሁፍ መልዕክት ይላኩ።
ወደ ሌሎች ሲደውሉ ጥሪው ሳይነሳ ለሚደውሉላቸው ደንበኞች መልዕክት ለማስተላለፍ፤ BC ን አስቀድመው የሚተላለፈውን የመልዕክት ይዘት ወደ 623 በፅሁፍ መልዕክት ይላኩ።
#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻@getcha_techs
ውድ ደንበኞቻችን
ዘመናዊውን የኢ-ሲም አገልግሎት መስጠት መጀመራችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!
በቀላሉ ከስልክ ቀፎዎ ጋር በማናበብ ብቻ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለውን ይህን አዲስ ቴክኖሎጂ ቸርችል ጎዳና በሚገኘው የፕሪሚየም አገልግሎት ማዕከላችን ያገኙታል፡፡
በቅርቡ በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን አገልግሎቱን መስጠት እንጀምራለን!
ለተጨማሪ መረጃ እና በኢ-ሲም አገልግሎት የሚሰጡ የሞባይል ስልኮችን ዝርዝር ለመመልከት፡ bit.ly/3LlPDmD
#share
👨‍💻@getcha_techs👨‍💻getcha_techs
ቴሌግራም እምቢ ላላችሁ  vpn ወይ ይህንን proxy ያለ vpn በነፃ ተጠቀሙ


https://t.me/proxy?server=russia-dd.proxy.digitalresistance.dog&port=443&secret=ddd41d8cd98f00b204e9800998ecf8427e

@getcha_techs
✳️ የባትሪ እድሜ (Battery life)

◽️ በዚህ ዘመን በርካቶች የዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ይታመናል። ዘመናዊ ስልኮች ከስሪታቸው አንጻር ባትሪያቸው ቶሎ የሚያልቅና አጭር ጊዜን የሚያስጠቅሙ ናቸው። ከዚህ አንጻርም ተጠቃሚዎች ባትሪውን ቶሎ ቶሎ ሃይል ለመሙላት (ቻርጅ ለማድረግ) ሲሞክሩ ይስተዋላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ምናልባትም የባትሪን እድሜ ሊያሳጥር እና ሙሉ በሙሉ ሊያበላሸውም ይችላል።

◽️ ስልክን ከመጠቀም ባለፈ ግን የባትሪ እድሜን ማራዘምና በአግባቡ ቻርጅ በማድረግ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። እርስዎ ከእነዚህ ተጠቃሚዎች አንዱ ከሆኑ ስልክዎን ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖራሉና እነዚህን የባለሙያ ሃሳቦች እናካፍልዎ፡

ቻርጅ እያደረጉ ስልክን በጭራሽ አለመጠቀም፦

◽️ አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ባይጠቀሙ ይመረጣል። ምናልባት የግድ ከሆነ ደግሞ ስልኩ ከተሰራበት ኩባንያ አብሮ የተዘጋጀን ቻርጀር እየተጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎች።

ጥራት ያላቸውን ባለማራዘሚያ ቻርጀሮች መጠቀም፦

◽️ ባለማራዘሚያና በአብዛኛው በነጭ መደብ የተሰሩ እውነተኛ ቻርጀሮችን መጠቀም የባትሪን እድሜ ለማራዘም ይረዳልና ይጠቀሙበት።

ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ከማድረግ መቆጠብ፦

◽️ ወደ መኝታ ሲያመሩ ስልክዎን ቻርጀር ላይ ሰክቶ መተው አደጋ አለው። ይህም ባትሪው ከመጠን በላይ ቻርጅ በማድረግ ማዳከም ይጀምራል፥ በአብዛኛው ስልክን በ40 እና በ80 ፐርሰንት መካከል ቻርጅ ማድረግ መልካም መሆኑንም ይመክራሉ። ምክንያታቸው ደግሞ 40 ፐርሰንት ከደረሰ ቻርጅ ማድረጉ ግዴታ ሲሆን 80 ከሆነ በኋላ ነቅለው ቢገለገሉበት ችግር የለውም የሚል ነው።

ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት፦

◽️ ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደሚፈልገው ሁሉ ስልክን ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት። ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳል።

ባትሪው እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ አለማድረግ፦

◽️ ሌላውና በብዙ ሰዎች የተለመደው ጉዳይ ደግሞ የስልክ ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ለባትሪ እድሜ የመጀመሪያውና ዋናው ጠር ነውና ባትሪው 40 ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ቻርጅ ማድረጉን ይመክራሉ። ይህ ባይሆን እና በጣም ከወረደ በኋላ ቻርጅ ለማድረግ መሞከሩ ግን ባትሪን በመግደል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላልና ይህን ልማድ ያስወግዱም ይላሉ።

◽️ ከዚህ ባለፈም ቻርጀሩን ከቀጥተኛው ሶኬት ላይ አለመሰካት እና ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው ቻርጀሮች አለመጠቀም መልካም ነው። እርስዎም ከላይ የተጠቀሱትን የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የስልክዎን ባትሪ እድሜ ያራዝሙ።


▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
     ❖ Contact
     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር
#share
     
        
@getch_techs
Channel name was changed to «Get Tech's Gallery📱💻»
Channel name was changed to «Getcha Tech's📱💻»
የ3ጂ/ 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ፍጆታን ለመቆጣጠር ወይንም ለመቀነስ 12 ጠቃሚ ምክሮች! በተለይ ቁጥር 3. በጣም ጠቃሚ ነው..

የኢንተርኔት አጠቃቀምን መመጠን
የተለያዩ መተግበሪያዎች/
Applications/ ሙሉ በሙሉ ስራላይ በሚሆኑበት ጊዜ የተለያየ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ..
ለምሳሌ:-
ቪዲዮ የሚያጫውቱ እንደ ዩቲዩብ/youtube/ እና ፌስ ቡክ/facebook/ ያሉ መተግበሪያዎች ከሌሎች መተግበሪያዎች ይልቅ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
በመሆኑም ስልክዎ ላይ ጭነው የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የሚጠቀሙትን የኢንተርኔት መጠን ለመቆጣጠር የሚከተለውን ቅደም ተከተል መተግበር ይችላሉ፡
ከተቻለ ሁልጊዜም ለወይፋይ ቅድሚያ ይስጡ ካልሆነ ግን የሚከተሉትን መላዎች ይጠቀሙ
1.ሴቲንግ /Setting/ ውስጥ Data usageን ይመርጣሉ > mobile data ውስጥ > data usage cycle የሚለው ላይ > ቀስቶቹን በማንቀሳቀስ ምን ያህል መጠን ያለው ኢንተርኔት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚፈልጉ መመጠን ይችላሉ፡፡
2. በራስ መር ማዘመንን /Update/ ማጥፋት ስልክዎ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች ወይም መተግበሪያዎች እንዲዘምኑ /Update/ ካልፈቀዱ በስተቀር በራሳቸው ጊዜ ያለርስዎ ፈቃድ እንዳይዘምኑ በማድረግ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡
3. ቪዲዮ ሙዚቃ እና ጌም በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ መመልከት/መጫወት ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎችን በቀጥታ ሲመለከቱ ወይም ሲያወርዱ በተለይ ደግሞ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ቪዲዮዎች እናሙዚቃዎች ከሆኑ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡በአንዳንድ አጋጣሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ እና ሙዚቃን መምረጥ በጥራት ዝቅተኛ ከሆነ ተመሳሳይ ይዘትካለው ቪዲዮ እና ሙዚቃ በሁለት እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡ለምሳሌ:-በሞባይልዎ ከዩቲዩብ (youtube)ቪዲዮ እና ሙዚቃን እየተመለከቱ ከሆነ ጥራቱን ዝቅ በማድረግየኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡ ይህንንለማድረግ
3.1. ስልክዎ ላይ የዩቲዩብ/youtube/ መተግበሪያን ይክፈቱ
3.2.ሜኑ የሚለው ውስጥ ጄነራል/General/ን ይምረጡ
3.3.High Quality on Mobile የሚለውን ያልተመረጠ
/Un-tick/ በማድረግ የቪዲዮውን ጥራት ዝቅ ማድረግ ይችላሉ
ያስተውሉ
* ከፍተኛ ጥራት ያለው ሙዚቃ(ምስል የሌለው) በ(256kbps) የጥራት መጠን ሲጠቀሙ በሰዓት እስከ 100 ሜጋባይት የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ቪዲዮ በHD ጥራት ሲመለከቱ በሰዓት እስከ 1ጂቢ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
ጌሞችን ከኢንተርኔት በቀጥታ እየተጠቀሙ ከሆነ በሰዓት ከ10 እስከ 80 ሜ.ባ ድረስ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
4. መተግበሪያዎች ማሳወቂያ/
Notification/ እንዳይልኩ ማድረግ እና ከጀርባ በኩል/Background/ ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ ማገድ
★አንዳንድ መተግበሪያዎች እየተጠቀሙባቸው ባይሆንም በውስጥ በኩል እርስዎ ሳያውቁ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ
ለምሳሌ:- የተሻለ የመተግበሪያው/Application/ ስሪት ሲኖር ራሳቸውን ያዘምናሉ። ስለዚህ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ስለመተግበሪያው የተለያዩ ማሳወቂያዎች/
notifications/ እንዲደርስዎ ይፈልጉ እንደሆነ ሲጠየቁ መከልከል እንዲሁም አካባቢዎን ፈልጎ እንዲያገኝ ፈቃድ ሲጠየቁ ባለመፍቀድ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡
የጫኗቸውን መተግበሪያዎች ማዘመን /አፕዴት ማድረግም ሆነ መጠቀም ሲፈልጉ ብቻ ራስዎ ገብተው እንዲፈቅዱ አድርገው መጫን ይችላሉ
#share

👩‍💻@getcha_techs 🧑‍💻 @getcha_techs
ውድ የGetcha Tech's ተከታታዮች በዚህ ፔጅ ማንኛውም ቴክኖሎጅ ነክ ጉዳዮችን በማንሳት እንማማራለን እናንተም ያልገባችሁን ወይም ደግሞ ማወቅ ስለምትፈልጉት ጉዳይ ርእስ በማንሳት በኮሜንት ቦታው ልታጋሩን ትችላላችሁ፡፡ በተቻለ ፍጥነት ጥያቂያችሁን ለመመለስ ዝግጁ ነን፡፡
በተጨማሪም እናንተ ያወቃችሁትን ለጓደኞቻችሁ ለማጋራት ሊንኩን share በማድረግ መጋበዝ ትችላላችሁ፡፡
#share

🧑‍💻 @getcha_techs🧑‍💻@getcha_techs
https://t.me/Getcha_Techs
🔷🔴📲Samsung _A10s

🔰 used Orignal®

📶 Dual Sim

👉👉 2GB Ram

📼Storage :- 32GB

4000 mAh Battery
🔮የቴሌ የበአል ጥቅሎች🤩

                  #Share
👩‍💻 @getcha_techs 👨‍💻 @getcha_techs 👩‍💻
ምርጥ 11 የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች

1) getintopc
https://getintopc.com
የተለያዩ ክራክ የተደረጉና ምርጥ ነጻ ሶፍትዌሮችን በማቅረብ የሚታወቅ ምርጥ ዌብሳይት ነው። በመሆኑም በዚህ ዌብሳይት የፈለጉትን ሶፍትዌሮችን በመፈለግ ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ በብዙ ሰዎች ዘንድ ተፈላጊ ነው።

2) Download
https://download.cnet.com

የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡

3) FileHippo
https://filehippo.com

ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅመናል፡፡

4) ZDNet
https://downloads.zdnet.com

ይህ ሳይትም እንደሌሎቹ ብዙ የ ሶፍትዌር አማራጮችን የያዘ እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳይት ነዉ፡፡

5) Softpedia
https://www.softpedia.com

Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

6) Tucows
https://www.tucows.com/downloads

ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡

7) FreewareFiles
https://www.freewarefiles.com

ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

8) MajorGeeks
http://m.majorgeeks.com

ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ዩሰር ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

9) FileCluster
https://www.bytesin.com

FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

10) Soft32
https://www.soft32.com

በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡

11) File Horse
https://www.filehorse.com

እንደ ሌሎቹ ሳይቶች በቁጥር ብዙ ሶፍትዌሮችን ያካተተ ባይሆንም በጣም ታወቂ እና ጥራት ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የምናወርዳቸዉ ፋይሎችም ቫይረስ እንደሌለዉ የሚያረጋግጥ ሲስተም አካቷል፡፡

#share
🧑‍💻@getcha_techs🧑‍💻@getcha_techs🧑‍💻
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለእየሱስ ክርቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
በዓሉ የሰላም የጤና የመተሳሰብ በዓል ያድርግልን!! 🙏🙏🙏
ውድ የቻናሌ ተከታታዮች በመጀመሪያ ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች
በሙሉ እንኳን ለታላቁ የሁዳዴ  ጾም በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፤ እግዚአብሔር አምላካችን ዘወረደ ብሎ
በሠላም እንዳስጀመረን በሠላም አስፈጽሞ ለብርሃነ  ትንሳኤው ያድርሰን ያድርሳችሁ! 🙏
በመቀጠል የተለያየ ብራንድ ኦርጅናል የአንድሮይድ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት ለምትፈልጉ በሙሉ በውስጥ መስመር @GetchaHD በማናገር መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
#share
🧑‍💻@getcha_techs🧑‍💻@getcha_techs🧑‍💻
https://t.me/Getcha_Techs
🔷🔴📲Samsung _A32

🔰 used Orignal®

📶 Dual Sim

👉👉 6GB Ram

📼Storage :- 128GB

5000 mAh Battery