ገድለ ቅዱሳን
6.53K subscribers
17.7K photos
354 videos
53 files
790 links
@Gedelat
ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡
በአድራሻችን @Mnfesawi_bot
Download Telegram
6
🕊                        💖                       🕊
                    
†   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †
💛 💛

❝ በመብረቆች ብልጭታ [ ታጅቦ ] ንጉሥ በሚመጣበት ጊዜ ፣ የዕለታት ሁሉ አውራ [ አለቃ ] የሆነችው ሰንበት ለዘለዓለም ትሰጠናለች ፤ ያኔ ጨረቃ የለም ፣ ፀሐይም ቢሆን ክረምትና በጋም ቢሆን አይኖርም።  ❞ [ ቅዱስ ያሬድ ]

🕊                        💖                       🕊

❝ እስከዚኽች ሰዓት ለአደረሰን ለክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል፡፡ የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ለጌትነትህ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው ? ❞ [ ቅዱስ ያሬድ ]


                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y
🕊                        💖                       🕊
2
2
🕊                        💖                       🕊

            [   ሆሣዕና በአርያም !   ]

💛                        🕊                    💛

❝ ነቢይ " እነሆ ባዕለ ጠጋ የሆነ ንጉሥሽ ወደ አንቺ መጥቷልና እጆችሽን በመጽፋት በደስታ አመስግኚው።" ያለሽን ስሚ፡፡ ወደ አንቺ በትሕትና እንጂ በክብር አይመጣምና፡፡ እንደ ነገሥታት ባለ ክብር የሚገለጥልሽ አይደለም:: በከበረ ሠረገላ ወይም በፈረሶች ተጭኖ ወደ አንቺ እንደማይመጣ አታምኝምን? ነገር ግን ጌታሽ ሲሆን በአህያ ውርንጭላ ላይ ተጭኖ ይመጣል እንጂ፡፡ ሠረገላ ከእስራኤል ፈረስም ከኤፍሬም አይጠፋምና፡፡ በትሕትናውም መኳንንቱን ያዋርዳቸዋል ፤ ነገራት መምጣቱንም ተረጎመላት።

እርሷ ግን በምስጋና የሚዘምሩትን የሕፃናትን ድምፅ ሰምታ ደነገጠች፡፡ ነቢዩ ዳዊት ከሕፃናትና ከሚጠቡት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ ያለውን አላስተዋለችምና፡፡ እነሆ እኔ የነቢያትን መንገድ እከተላለሁ። የቃላቸውን ምሥጢርም እተረጕማለሁ፡፡ ምድርን ሁሉን በየ ወገኑ ታስገኝ ዘንድ ያዘዛት የሁሉ ጌታ እንደ ሆነም እናገራለሁ። በኃይሉም እንስሳትን ሁሉ ፈጠረ።

እርሱ ግን ከልዑል መንበሩ ሳይጎድል በአህያ ውርንጭላ ተቀመጠ፡፡ ወደ ፈረሰች ከተማ በገባ ጊዜ በትሕትናው ፊትም ልብሳቸውን አነጠፉ፡፡ እርሷ ግን አልተቀበለችውም፡፡ ከፍ ከፍም አላደረገችውም፡፡ ለክብሩም አልተገዛችም፡፡ በኃይሉም እንስሳትን ሁሉ ፈጠረ፡፡

ሕፃናቱ ግን ሰማያዊ ክብሩን ዐወቁ፡፡ ሆሳዕና በአርያም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነውም አሉ። ይኸውም በአህያ ውርንጭላ የተጫነው የዓለም ሁሉ መድኃኒት ነው፡፡ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጥ እሱ በትሕትና ወደ ምድር ወረደ፡፡ በምድር በዘንባባ ዝንጣፊ ይመሰገናል፡፡ በሰማይ በመንፈሳውያን መላእክት ክንፍ ይጋረዳል።

ከግርማው የተነሣ ልዑላን የሚንቀጠቀጡለት ይህ ነው፡፡ በአርያም የሚመሰገን እርሱ በሕፃናት አንደበት በጽዮን ገበያዎች ተመሰገነ፡፡ በእሳት መንበሮች የሚቀመጥ በቅዱሳን መላእክትም የሚመሰገን እርሱ እንደ ችግረኛ ያዳናትን ጠላችው ናቀችውም᎓᎓ የሥራዋ ክፋትና ጕስቁልናዋም ተገለጠ፡፡ አብን አስቆጣችው ወልድንም አልወደደችውም፡፡ ልቧ ኃጢአትን ጠገበ፡፡ ከነቢያት ስብከትም ራቀች፡፡ ሕፃናቱንም የምስጋናን ቃል እንዳይናገሩ ዝም ታሰኛቸው ዘንድ ወደደች:: አመፃን እየወደደች እንዴት እውነትን መጠበቅ ይቻላታል? ሕፃናቱ በዘንባባ ዝንጣፊ ሲያመሰግኑ በሰማች ጊዜ በቅናት ነደደች። ተከዘችም፡፡ ❞ [ ቅዱስ ኤፍሬም ]

🩵  ሆሣዕና በአርያም 🩵   ]

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
1
3
🕊                        💖                       🕊

[      🕊  መድኃኔ  ዓለም    🕊     ]

† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

🕊                       💖                   🕊

❝ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይወውዑ አድባር ወአውግር ወኵሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ ፤ ❞

ትርጉም ፦ [ ሰማይ ደስ ይለዋል ፣ ምድር ፍስሐን ታደርጋለች የምድር መሠረቶችም መለከትን ይነፋሉ ፣ ተራሮችና ኮረብቶችም ይነዋወጣሉ ፣ ሁሉም የበረሃ ዛፎችም [ ይነዋወጣሉ ] በሰማያትም ዛሬ እጅግ ትልቅ ደስታ ይደረጋል፣ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን [ በከርስቶስ ደም በተገኘ ማዕዶት የተገኘ ደስታን ] ታደርጋለች። ] [ ድጓ ዘፋሲካ ]

🕊                       💖                   🕊

❝ ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርአዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳዕ ዘተኃጕለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ ፤ ❞

ትርጉም ፦ [ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን በጻድቃን ላይ የሚያበራ ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ነው ፣ የጠፋው ይረዳ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደ እኛ መጣ [ ሰው ሆነ ] ] [ ድጓ ዘአስተምህሮ ]

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
2
2
🕊                        💖                       🕊

[   † ሰሙነ ሕማማት  †   ]

                      †                        

‹ ሰሙን › – " ሰመነ ስምንት [ ሳምንት ] አደረገ " ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከዕለተ ሆሣዕና ሠርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ‹ ሕማም [ ሕማማት ] › – ‹ ሐመ ታመመ › ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ይህም የሰውን ዘር ዂሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኵነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት ፣ የሚያለቅሱበት ፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት ፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት ፤ ኀጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡

════════†════════

በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልዕት አይበሉም ፤ ይልቁን በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን ፣ ሕማሙን ፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት ፣ ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡ መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም " እግዚአብሔር ይፍታህ " አይሉም፡፡ ሥርዓተ ፍትሐት አይፈጸምም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመኾኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምፅ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መኾናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
2
05
mareta
3
🕊                        💖                       🕊

  [   🕊  ሕ ማ ማ ት   🕊  ]  
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕማማት + ለምን + እንዴት  ]

════════════════
                           †††             

[  የሕማማት ሳምንት ሥርዓቶች ! ]

- የሕማማት ትርጉምና ምሥጢር
- ጸሎትና የጸሎት መጻሕፍት
- የጾም ሰዓትና ሥግደት
- ሌሎችም ሥርዓቶች

    💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ]

════════════════
                           †††
               ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟
🕊                        💖                       🕊
                        👇
Audio
2