በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን በላይ ቡና ተመርቷል
አርባምንጭ ጥር 03/2018 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚኒኬሽን )
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ15 ነጥብ 8 በላይ ቶን ቡና መመረቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።
በተያዘው ዓመት 2 ሚሊየን 462 ሺህ 718 ሔክታር በቡና ልማት መሸፈኑን በባለሥልጣኑ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፈቃዱ ደፈረስ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥ አሁን ላይ ምርት የሚሰጥ የቡና መሬት ሽፋን በአርሶ አደር 1 ሚሊየን 537ሺህ 626 እንዲሁም በባለሃብት 143 ሺህ 140 ሔክታር መሆኑንም አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ዘንድሮ የለማው መሬት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 ነጥብ 7 በመቶ እንዲሁም ካለፉት ሥድስት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የ211 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አረጋግጠዋል።
በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን በላይ ቡና መመረቱን ጠቅሰው፤ ከዚህ ውስጥ 14 ነጥብ 37 ሚሊየን ቶን በአርሶ አደር ቀሪው በባለሃብት መመረቱን ገልጸዋል።
ይህም ካለፉት ሥድስት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከሦስት እጥፍ በላይ ብልጫ ማሳየቱን ነው ያስታወቁት።
ምርታማነትን በተመለከተም በባለሃብት 9 ነጥብ 9 እንዲሁም በአርሶ አደር ማሳ 9 ነጥብ 4 ኩንታል በሔክታር መሆኑን ጠቅሰዋል።https://www.facebook.com/share/p/14R9EQbREXF/

በጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የተመራ ሉዑክ 'ጮዬ ማስቃላ' በዓል ለማክበር በደራማሎ ወረዳ ይገኛል
አርባ ምንጭ:- ጥር 03 /2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)
በጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የተመራ ሉዑክ 'ጮዬ ማስቃላ' በዓልን ለማክበር ደረማሎ ወረዳ ገብቷል።
ሉዑካን ቡድኑ 'ጮዬ ማስቃላ' በዓልን ለማክበር ዳራማሎ ወረዳ ሲደርሱ በወረዳው አመራሮች፣ ሀገር ሽማግሌዎች እና አከባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
https://www.facebook.com/share/p/1HjwzMDpa3/

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው በዶራሌ ወደብ ያደረጉት ጉብኝት በምስል
https://www.facebook.com/share/p/17hiDHYCyX/