ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአርባ ምንጭ ማዕከል የሚገነቡ የክልል ተቋማት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ጎበኙ
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባ ምንጭ ማዕከል የሚገነቡ የክልል ተቋማት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ በስፍራው ተገኝተው ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ በምልከታቸው ወቅት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም የግንባታው ሂደት ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው በክልሉ በየማዕከላቱ የተጀመሩ የተቋማት የህንፃ ግንባታዎች በላቀ ውጤታማነት የህዝቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለተጀመሩ ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ ስኬት ሚናቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተቋማት የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶቹ የክልሉን የአስፈጻሚ ተቋማት ተቋማዊ አቅም በማጠናከር በተሻለ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለክልላዊ የልማትና የብልጽግና ራዕይ ስኬት አበርክቷቸው ከፍ ያለ መሆኑንም ጠቅሰው፤ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱቹ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልፀዋል፡፡https://www.facebook.com/share/p/1DTyr92Qfs/

በየአካባቢያቸው የሚገኙ አማራጮችን በመጠቀም በማህበር የተደራጁ ወጣቶች፣ ራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተገለፀ
አርባምንጭ፦ ጥር 3 / 2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ ኮሙኒኬሽን)
የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በዛሬው እለት በብርብር ከተማ አስተዳደር የሚገኘውን "ሳቱሳ የፍየል እርባታ ማህበርን" ጎብኝተዋል።
ማህበሩ በቤተሰብ የተደራጀ የቢዝነስ ሞዴል ማህበር ሲሆን
ከ250 በላይ ምርጥ ዝርያ ያላቸውን ፍየሎች በማርባት ላይ ይገኛል።
ማህበሩ ከመንግስት ድጋፍ ውጪ ራሳቸውን በመቻል ለሌሎች የስራ ዕድል መፍጠር የቻሉበት ሂደት አበረታች ነውም ተብሏል ።
ልዑካን ቡድኑ በምልከታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ ይህ የፍየል እርባታ ዘርፍ ያልተለመደና ትልቅ ልምድ የሚወሰድበት ነው። በተለይም ወጣቶች የጋራ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን በማስተባበር የጀመሯቸው መሰል ኢንተርፕራይዞች፣ የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ተመራጭ መንገድ መሆኑም ጠቁመዋል።https://www.facebook.com/share/p/1CckAoXiMU/

በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን በላይ ቡና ተመርቷል
አርባምንጭ ጥር 03/2018 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚኒኬሽን )
በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ15 ነጥብ 8 በላይ ቶን ቡና መመረቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።
በተያዘው ዓመት 2 ሚሊየን 462 ሺህ 718 ሔክታር በቡና ልማት መሸፈኑን በባለሥልጣኑ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፈቃዱ ደፈረስ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥ አሁን ላይ ምርት የሚሰጥ የቡና መሬት ሽፋን በአርሶ አደር 1 ሚሊየን 537ሺህ 626 እንዲሁም በባለሃብት 143 ሺህ 140 ሔክታር መሆኑንም አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ዘንድሮ የለማው መሬት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 ነጥብ 7 በመቶ እንዲሁም ካለፉት ሥድስት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የ211 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን አረጋግጠዋል።
በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን በላይ ቡና መመረቱን ጠቅሰው፤ ከዚህ ውስጥ 14 ነጥብ 37 ሚሊየን ቶን በአርሶ አደር ቀሪው በባለሃብት መመረቱን ገልጸዋል።
ይህም ካለፉት ሥድስት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከሦስት እጥፍ በላይ ብልጫ ማሳየቱን ነው ያስታወቁት።
ምርታማነትን በተመለከተም በባለሃብት 9 ነጥብ 9 እንዲሁም በአርሶ አደር ማሳ 9 ነጥብ 4 ኩንታል በሔክታር መሆኑን ጠቅሰዋል።https://www.facebook.com/share/p/14R9EQbREXF/

በጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የተመራ ሉዑክ 'ጮዬ ማስቃላ' በዓል ለማክበር በደራማሎ ወረዳ ይገኛል
አርባ ምንጭ:- ጥር 03 /2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)
በጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የተመራ ሉዑክ 'ጮዬ ማስቃላ' በዓልን ለማክበር ደረማሎ ወረዳ ገብቷል።
ሉዑካን ቡድኑ 'ጮዬ ማስቃላ' በዓልን ለማክበር ዳራማሎ ወረዳ ሲደርሱ በወረዳው አመራሮች፣ ሀገር ሽማግሌዎች እና አከባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
https://www.facebook.com/share/p/1HjwzMDpa3/

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው በዶራሌ ወደብ ያደረጉት ጉብኝት በምስል
https://www.facebook.com/share/p/17hiDHYCyX/