G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
አሳይመንት እንዴት እንስራ?
© በቀለሜ ተዘጋጅቶ በConcise English ተሻሽሎ የቀረበ
#sample #assignment #guide

🔆 ክፍል 1 - Case Study Type


🔰 በአብዛኛው ጊዜ ንባብና ሽምደዳ በሚጠይቁ እንደ Anthropology እና Civics አይነት ኮርሶች የሚሰጥ የአሳይመንት አይነት ነው።

🔰 የዚህ የአሳይመንት አይነት ዋና አላማ አንድን ርዕስ በጥልቀት በተለያዩ ንዑስ አርዕስት ከፋፍለን ከፍተኛ ገለፃ እንድንሰጥ ነው።

🔰 እንደዚህ አይነት አሳይመንት ሲሰጠን የምናካትታቸው የአሳይመንት ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው።

- Cover page (ሁሌም መቅረት የለበትም)
- Table of Contents
- Introduction
- Body
- Conclusion
- Reference

አንዳንድ ጊዜም Acronym, List of tables, List of diagrams, List of graphs እና ሌሎች ተጨማሪ ክፍሎችን ልትጨምሩ ትችላላችሁ። አሳይመንቱ ሲሰጣችሁ መምህራችሁ አብሮ መመሪያ ስለሚሰጥ ልታካትቷቸውም ላታካትቷቸውም ይችላል።

🔰 ለዚህ የአሳይመንት አይነት ያጋራናችሁን Sample ብትጠቀሙ አሪፍ ነው። አሳይመንቱን እዚህ ጋር ማግኘት ትችላላችሁ።

1⃣ Cover Page

🔰 Cover page ስትሰሩ ያጋራናችሁን Sample assignment ተጠቀሙ።

2⃣ Table of Contents

🔰 ይሄ በአማርኛ "ማውጫ" የምንለው ክፍል ሲሆን እያንዳንዱ ርዕስ እና ንዑስ ርዕስ የትኛው ገፅ ቁጥር ላይ እንደሚገኝ ያሳያል።

3⃣ Introduction

🔰 ይሄ "መግቢያ" ማለት ሲሆን ስለምትሰሩበት የአሳይመንት ርዕስ ጥቅል መረጃን የምታቀርቡበት ክፍል ነው። ለምሳሌ ርዕሱ Manufacturing Industry in Ethiopia ቢሆን መግቢያው ላይ Manufacturing Industry በኢትዮጵያ ምን ይመስል እንደነበር፣ አሁን ስላለበት ሁኔታ፣ ስለ Manufacturing Industry ማህበረሰቡ ያለው ሀሳብና አስተያየት፣ እና መሰል ገለፃዎችን ማድረጊያ ክፍል ነው።

4⃣ Body

🔰 Body ዋናው ክፍል ሲሆን እያንዳንዱን ርዕስ እና ንዑስ ርዕስ በደንብ እያብራራን ገለፃ የምንሰጥበት ክፍል ነው።

5⃣ Conclusion

🔰 Conclusion የማጠቃለያው ክፍል ሲሆን ከ7-10 ገፅ የፈጀውን የአሳይመንቱን Body በአንድ ገፅ አሳጥሮ እና እንደ አስፈላጊነቱ የራስን ሀሳብ እንደ መደምደሚያ የማቅረቢያ ክፍል ነው።

6⃣ Reference

🔰 ይሄኛው ክፍል ደግሞ የአሳይመንት የመጨረሻው ክፍል ሲሆን በተሰጠን ርዕስ ዙሪያ ያገኘናቸው መረጃዎች ከየት እንደሆኑ የምንፅፍበት ክፍል ነው።

🔰 መረጃ ያገኘንባቸውን ድረ-ገፆች (Websites) እንዲሁም የመፅሃፍትን ስም በአግባቡ መፃፍ አለብን።

⚠️ ከዚያ በተረፈ ከዚህ በፊት ያጋራናችሁን የአሳይመንት አሰራር ጥበቦች ተጠቀሙ። ይህንን ፅሁፍ ስትነኩ ወደዚያ ይመራችኋል።

⚠️ በቀጣይ ስለ Calculation የአሳይመንት አይነት በሰፊው እናብራራላችኋለን፣ በቅርቡ ይጠብቁን!

━━━━━━━━━━━━
📚 JOIN :
@GTutorialclass
JOIN :
@GTutorialclass
━━━━━━━━━━━━