G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#2014_EntranceExam

ጉዳዩ፡- የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ይመለከታል

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት አስመልክቶ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጣቸው ማብራሪያ ተሰጥቷል

📌አዲስ በተጠናው የትምህርትና ሥልጠና ፍንተ-ካርታ መሠረት ቀደም ሲል የሁለተኛ ደረጃ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የነበረው በአዲሱ የትምህርት እርከን መሰረት 👉 ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል። በዚህ መሠረት ቀደም ሲል 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና 12ኛ ክፍል ማብቂያ ላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ወደፊት የሚሰጠው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና መሸፈን ያለበት የትምሀርት ያዘት 👉ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለው ምን እንዳለበት፥


📌የኢኮኖሚክስ ትምህርትን በተመለከተ በ2013 የትምህርት ዘመን የ11ኛና የ12ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ወጥ በሆነ መልኩ እየተሰጠ እንዳልነበር ያሳያል፡፡ በመሆኑም በተሰበሰው መረጃ መሠረት የትምህረቱ አሰጣጥ ወጥነት ሳይኖረው ፈተናውን መስጠት በፈተናው አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሰለሚያሳድር የኢኮኖሚክስ ትምህረት ፈተና #ባይሰጥ የተሻለ መሆኑን ቀደም ሲል በተሰጠው ምክረ ሃሳብ መሠረት እንዲቀጥል ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ተማሪዎች ከወዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች አውቀው እንዲዘጋጁ ይገለፅላቸው ዘንድ እናሳስባለን። #MoE

📌 Join and Share👇👇👇

JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
👍1
#MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ አመት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል

📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, 🎖📖🎖
━━━━━━
📚 JOIN :@GTutorialclass
         JOIN :@GTutorialclass

𝐹𝑜𝑟 𝑎𝑛𝑦 𝑐𝑜𝑚𝑚𝑒𝑛𝑡 𝑎𝑛𝑑 𝑞𝑢𝑒𝑠𝑡𝑖𝑜𝑛 ⤵️𝗽𝗿𝗲𝘀𝘀 𝗵𝗲𝗿𝗲 🔛
#MoE

ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈቱ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።



የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቻናል👇👇
 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  🎖📖🎖
━━━━━━━━━━━━
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
#MoE

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።
አልሰራም ካለዎት በዚህ ያናግሩናል 👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻
@FromGTutorial

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#MoE

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም  ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ፦
1.  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2.  አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3.  አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4.  ሲቪል ሰርቪርስ ዩኒቨርሲቲ
5.  ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
6.  ጅማ ዩኒቨርሲቲ
7.  ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ናቸው።

ተማሪዎች የሞሉትን ምርጫ በ student.ethernet.edu.et በኩል ማረጋገጥ የሚችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1