G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የጥንቃቄ መልዕክት

ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ ምግቦች!!!!
-----------------------------------------------
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአካሄደው የገበያ ዳሰሳ ጥናት የቁጥጥር መስፈርቱን ያላሟሉ የተለያዩ የምግብ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳስባል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣንና ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በአደረገው የገበያ ጥናት በተለያዩ አካባቢዎች ተመርተው በገበያ ውስጥ አስገዳጅ የደረጃ ምልክት ሳይኖራቸዉ ወይም ሳይለጥፉ እንዲሁም አስገዳጅ የገላጭ ፅሁፍ ስታናድርድ CES 73 ሳያሞሉ ወደ ገበያ መውጣታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

መስፈርቱን ያላሟሉት የምግብ ምርቶች የገበታ ጨው፣ የለውዝ (የኦቾሎ) ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ አቼቶ፣ ከረሜላ እና ማር ሲሆኑ በምርቶቹ ላይ የተገኘው ጉድለት ደግሞ የማምረት የብቃት ማረጋገጫ (ሲኦሲ) የሌላቸው፣ የአምራች ድርጅት ስምና አድራሻ እንዲሁም አስገዳጅ የደረጃ ምልክት የሌላቸው፣ ምርቱ የተመረተበትና የሚያበቃበት በተለይም መለያ ቁጥር የሌለውና የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያለመገለፅ ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት የምግብ ምርቶች ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለሰልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡

#የገበታ #ጨው
1.  ሴፍ                           16. ዜድ
2.  ማሚ                          17. ማሂ
3.  ሶም                           18. ኤልሳ
4.  ኒያ                            19. አርኪ
5.  ኤ ኤም                         20. ሜናታ
6.  አሜን                          21. ፎር ኤፍ
7.  ኑና                            22. ዋን
8.  ዘመን                          23. አዮዲን
9.  ስኬት                          24. ዳግም
10.  ቴንሲያ                         25. ቶም
11.  እሙ                           26. ጆይ
12.  ጠሊል                          27. ሳሊህ
13.  መስቱራ                        28. ዛክ
14.  ጊዜ                            29. ትዝታ
15.  ኩል                            30. ዊን

#የለውዝ (ኦቾሎኒ) ቅቤ
1.  መና                            8. ዓለም
2.  ፋና                             9. ፀዬ (Tseyie)            
3.  ሰናይት                         10. አዱሊስ
4.  MAZA( ኤም ኤ ዜድ ኤ)           11. ጊፍት
5.  ሉሲ                            12. ስዊት
6.  ኤ ኤፍ                         13. ሐበሻ
7.  አያልነህ                         14. ሀናን

#የምግብ ዘይት
1.  ፍትህ                           7.ዝናሽ
2.  የኛ                             8. ፍፁም
3.  Tina Oil                        9. ሙሐ
4.  ፋሚሊ                          10. ተስኒም
5.  እድገት                          11. ፀሐይ
6.  ረዲ                             12. እፎይታ

#አቼቶ
1.  Hade Aceto

#ከረሜላ
1.  Hawi Fruits candy
2.  Best Jar
3.  MAMIE
4.  Mamie Lollipop
5.  Best Pop Lollipop
   
#ማር
1.  ፀደይ ማር
2.  ኬሪ የጫካ ማር

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
🙏2😢1
በኢትዮጵያ ስንት ስዓት ይታያል
ዛሬ ምሽት ጳጉሜ 2፣ 2017 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ጨምሮ በአብዛኛው የአፍሪካ፣ እስያ እና አውስትራሊያ በሚገኙ ሀገራት ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ወይም "የደም ጨረቃ" ይታያል። ይህ ክስተት ጨረቃ ቀይ ቀለም የምትይዝበት አስደናቂ ወቅት ሲሆን፣ እስከ 82 ደቂቃዎች ሊቆይ ይችላል።

የጊዜ ሰሌዳ (በኢትዮጵያ ሰዓት)

* 12:21 PM: ሙሉዋ ጨረቃ በምስራቅ አድማስ መውጣት ትጀምራለች።

* 12:28 PM: ግርዶሹ መታየት ይጀምራል።

* 1:27 PM: ከፊል ግርዶሹ ይጀምራል።

* 2:30 PM: ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ተጀምሮ ጨረቃ ደም የምትመስልበት ሰዓት ይሆናል።

* 3:11 PM: ጨረቃ በጥላው ማእከል የምትሆንበት እና ቀይ መምሰሏ የሚጨምርበት ሰዓት ይሆናል።

* 3:52 PM: ሙሉ ግርዶሹ ያበቃል።

ይህን አስደናቂ ክስተት በባዶ ዓይን ማየት ምንም አይነት የጤና ችግር ስለማያስከትል ያለ ምንም ስጋት ልትመለከቱት ትችላላችሁ።

አካባቢያችሁ ደመናማ ካልሆነ በደንብ ይታያል። ይህንን ታሪካዊ ክስተት እንዳያመልጣችሁ!

Via_መጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደስ
===================
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
4
ኢንተርኔት በነፃ‼️
የታላቁ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ነገ የምረቃ ስነስርዓቱን በቀጥታ ስርጭት በነፃ ይከታተሉ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ብስራት አሰምቷል።
#አዩዘሀበሻ
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
3👍1
🌻      እንኳን አደረሳችሁ    🌻

                    2018
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌻2018🌻መልካም🌻አዲስ አመት🌻

            🌻🌻🌻
     መልካም🌻አዲስዓ መት
  መልካም🌻     አ🌻🌻
መልካም 🌻        ዓ🌻🌻
ለወዳጄ 🌻          ዓ🌻🌻
🌻🌻🌻🌻        አ🌻🌻
                         ዓ🌻🌻
                       አ🌻🌻
                     አ🌻🌻
                   ዓ🌻🌻
                 አ🌻🌻
            ዓ🌻🌻
        አ🌻🌻
      ዓ🌻🌻
   አ🌻🌻
🌻🌻ት               🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

            🌻   🌻   🌻
      🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻
  አ🌻🌻ስ          ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ            ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ            ዓ🌻🌻
  አ🌻🌻ስ          ዓ🌻🌻
       🌻🌻🌻🌻🌻
             🌻  🌻  🌻

                    
                🌻🌻አዲስ
           🌻🌻🌻አመት
        🌻🌻🌻ልካም
   🌻🌻አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
            አዲስ🌻ዓመት
  🌻መልካም  🌻 አዲስዓመት
  🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
   አዲስዓመት🌻ለወዳጄ🌻🌻
  🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

            🌻   🌻   🌻
      🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻
  አ🌻🌻ስ          ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ             ዓ🌻🌻
  አ🌻🌻ስ            ዓ🌻🌻
     አ🌻🌻ስ      ዓ🌻🌻
      አ🌻🌻ስ  ዓ🌻🌻
    አ🌻🌻ስ       ዓ🌻🌻
  አ🌻🌻ስ           ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ            ዓ🌻🌻
🌻🌻ስ              ዓ🌻🌻
  አ🌻🌻ስ          ዓ🌻🌻
       🌻🌻🌻🌻🌻
             🌻  🌻  🌻

              

🇪🇹ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት 🙏 🕊🌻🌻
🌻🌻🌻  ያሰብነው የሚሳካበት          🌻🌻
🌻🌻🌻                                         🌻🌻
🌻የካሳ🌻የሰላም🌻የጤና🌻የበረከት🌻🌻
🌻🌹🌾ዓመት 💐🌷ይሁንልን።🌻🕊🌻🌻
3🙏1
አሳዛኝ ዜና‼️
በከሰል ጭስ የ3ሰዎች ህይወት አለፈ‼️
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7ጣፎ ኮዲሚኒየም እድሜቸው 75 አመት አዛውንት ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አመት ዋዜማ ምሽት በከሰል ጭስ ታፍነው ህይወታቸው አልፏል። በተመሳሳይ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ህዳሴ ትምህርት ቤት ጀርባ በአዲስ አመት መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 6 ሰአት ባለትዳሮች በከሰል ጭስ ታፍነው ሞተው መገኘታቸውን ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል።

ባለትዳሮቹ እሱ የ35 አመት ወጣት የትዳር አጋሩም ደግሞ የ27 አመት ወጣት መሆናን ፖሊስ የገለፀ ሲሆን በከሰል ጭሱ ሁለቱም ሞተው መገኘታቸውን ተነግሯል።
ከሰል ስንጠቀም በቤት ውስጥ በቂ አየር እንዲኖር ማድረግ እና ስራ ከጨረሱ በኋላ ማጥፋት እንዳለብን ይመከራል።
#አዩዘሀበሻ
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ 📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
😢2👍1
የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️
" ሲያልቅልን ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ትክክለኛ ቀን እናሳውቃችኋለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት‼️
በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች " የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ነው ይፋ የሚደረገው ? ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጳጉሜን 4/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋል ብለው ነበር ሳይደረግ አለፈ ውጤት ይፋ የሚደረገው መቼ ነው ? " ለሚለው ጥያቄ:-👇 "ውጤት ሲያልቅ እንገልፃለን በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ይለቀቃል፤ ትክክለኛው ቀን ሲወሰንም በይፋ ሚዲያ ጠርተን እናሳውቃለን " ብለዋል።

" የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ተማሪዎችን እያወናበዱ ነው " ያሉት አመራሩ ተማሪዎች ውጤቱ ይፋ የሚደረግበትን ቀን ከተቋሙ እስኪሰሙ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች (በፌስቡክ ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ) " ስለ ውጤት ከምንጮቻችን መረጃ አገኘን በዚህ ቀን ይወጣል " እያሉ የሚሰራጩት መረጃዎችም ሀሰተኛ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

" እኛ በሚያልቅ ጊዜ እናንተን ጨምሮ ሚድያዎችን ጠርተን እናሳውቃለን " ያሉም ሲሆን " ' በዚህ ቀን ይወጣል ተብሎ ነበር ' የሚለው ሳይሆን ጥርት ብሎ ሲያልቅልን በፍጥነት እናሳውቃለን " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
=================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍4
ውጤት ለማየት‼️
የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆኗል‼️
የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡ ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡
አድራሻዎቹ፡
1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot
3. አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡ 6284 ማየት ይችላሉ።
==============
💎⬇️⬇️👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
የኢፌድሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተከለከሉ እና የእርምት እርምጃ የሚያስከትሉ ተግባራትን ዘርዝሮ አሳወቀ‼️
👉ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ ሲያስተምር የተገኘ አዲስ ተቋም፤
** ፈቃድ ባልተገኘበት ካምፓስ ወይም ቅርንጫፍ ትምህርት ሲሰጥ የተገኘ ተቋም፤
**ባልተፈቀደ የትምህርት-መስክ እና መረሀ-ግብር ትምህርት እየሰጠ የተገኘ ተቋም፤
** ፍቃድ ሳያድስ ስያስተምር የተገኘ ተቋም፤
** ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ የህንጻ ለውጥ ያደረገ ተቋም፤
** የአጫጭር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት ፈቃድ ሳይሰጣቸው የሚሰሩ ተቋማት ወይም የሙያ ማህበራት፤
** በባለሥልጣኑ ከተሰጠው የደረጃ ስያሜ ውጪ ሌላ የደረጃ ስያሜ ሲጠቀም የተገኘ ተቋም፣
** አሳሳች ማስታወቂያ ያሰራጨ ተቋም፤
** የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም፤
** በባለሥልጣኑ ተገምግሞ ያገኘውን ስርዓተ ትምህርት ሳይከተል ትምህርት የሰጠ ተቋም፤
** የመምህራንን ቁጥር እና ደረጃ አጓድሎና ቀይሮ የተገኘ ተቋም፤
** በባለስልጣኑ ከተፈቀደው ቁጥር በላይ መዝግቦ ሲያስተምር የተገኘ ተቋም፤
** የተማሪ መረጃ አያያዝ፣ አጠባበቅና አላላክ፤
ባለሥልጣኑ የተሰጠውን የፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት ደብዳቤ በግልጽ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በሚታይ ሁኔታ ያለጠፈ ወይም ያላሳወቀ ተቋም እና
** ግብአቶችን አጓድሎ ወይም ከተቋም ወደ ሌላ ተቋም ወይም ካምፓስ አዛውሮ የተገኘ ተቋም፤ሐሰተኛ ሰነዶች እና ትክክለኛ ያልሆኑ ማስረጃዎች ትክክለኛ አድርጎ ማቅረብ ተጠያቂ ያደርጋል።

👉ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ከደብረማርቆስ‼️
እስከ 8ኛ ክፍል መኪና ከማይደርስበት ገጠር ቀበሌ ከወረዳ ከተማ 4 ሰዓት የእግር መንገድ በላንባ እያጠና የተማረና ከ 9ኛ ክፍል ጀምሮ በክልል አቀፍ ደረጃ ተወዳድሮ በደብረማርቆስ ሀዲስ አለማየሁ አዳሪ ት/ቤት እየተማረ 11ኛ ክፍልን ክልሉ በገጠመዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት በ3 ወር ብቻ ተምረዉ ከፍተኛ ዉጤት ያመጣዉ ተማሪ ናትናኤል አብዩ።
ደብረማርቆስ ሐዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት ካስፈተናቸው 25 ተማሪዎች መካከል 24ቱ ከ 529 በላይ እና 3ተማሪዎች 573 ከ600 በማምጣት አስመዝግበዋል።

==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
Updateየተደረመሰው መድረክ‼️
የአባይ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በአዲሳ አበባ በባለፈው እሁድ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ተሰርቶ የነበረ መድረክ ላይ ልምምድ ሲሰሩ የነበሩ በርካታ ወጣቶች በዋዜማው ቅዳሜ ምሽት የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው የእንጨት መድረክ በምስል ይህን ይመስላል።
ጥቁር አንበሳ ብቻ ከ80 በላይ ተጎጂዎችን ተቀብሎ ማከሙን፣ ከፍ ያለ ጉዳት ያጋጠማቸው ደግሞ ሪፈር እየተባሉ መሆኑ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ የካቲት 12 ሆስፒታል በርካታ ተጎጂዎችን እያከመ ይገኛል። አብዛኞቹ ተጎጂዎች ወጣቶች ናቸው፣ቁጥራቸው ባይታወቅም የሞቱ ሰዎችም አሉ።
ለተጎጂዎች መልካሙን ሁሉ እንመኛለን።

==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
አሳሳቢ ነው‼️
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ቁጥር በየዓመቱ እየቀነሰ ነው ተባለ‼️
ምንም እንኳ የብሔራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች ቁጥር መሻሻል ቢያሳይም፣ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይገኛል።

በ2017 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ብዛት 581,905 ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 48,929 (8.4 በመቶ) የሚሆኑት ብቻ የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ አሃዝ ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው። ለምሳሌ በ2014 ዓ.ም. 896,520 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የተፈታኞች ቁጥር ማሽቆልቆል በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብቻ የተገደበ አይደለም።

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ተራዳኦ ድርጅት (UNICEF) ሪፖርት መሰረት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ህጻናት በግጭት፣ መፈናቀል እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል። ሪፖርቱ፤ ከ6,000 በላይ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ከ10,000 በላይ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብሏል።

በተጨማሪም፤ በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑበት ክልል፤ #አማራ ክልል ሲሆን ብዛታቸውም 4.4 ሚሊዮን መሆኑን ገልጿል። በ #ኦሮሚያ ክልል 3.2 ሚሊዮን እና በ #ትግራይ ክልል1.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውንም ሪፖርቱ ማስታወቁ ይታወቃል።
#አዲስ ስታንዳርድ
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋት ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ መቀመጧን ጥናት አመለከተ‼️
ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በብሉምስበሪ አሳታሚ ላይ የታተመ የጥናት መጽሐፍ አመላከተ።


“የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ” በሚል ርእስ በፊሊሽያ አንቶኒዮ እና ቶኒ ሮበርትስ የተጠናውና መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ባደረገው ብሉምስበሪ አሳታሚ ድርጅት ላይ በመጸሐፍ መልክ ታትሞ የወጣው ጥናት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 በአህጉረ አፍሪካ በሀገራት የተፈጸመውን የኢንተርኔት መዘጋት ገምግሟል።


በዚህም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 ባሉት በለፉት ዘጠኝ ዓመታት 193 የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ አህጉር መመዝገቡን ገልጿል።
በተጠቀሱት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋት ድግግሞሽ መጠኖች ሀገራትን በደረጃ ያስቀመጠው ጥናቱ ኢትዮጵያን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ሰላሳ ጊዜ ኢንትርኔት የዘጋች በሚል ከ55ቱ የአፍሪካ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ አስቀምጧታል።
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
ፆታ ሊያስፈትሹ‼️
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የባለቤታቸውን ጾታ ሴትነት ለማረጋገጥ ሊያስፈትሹ ወስነዋል ተባለ!!

የትዳር አጋራቸው ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በተደጋጋሚ ጾታቸውን የቀየሩ ወንድ እንጂ ሲወለዱ ሴት አልነበሩም የሚለውን ወቀሳ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ሊያስፈትሿቸው ነው።

ከፍተሻው በኋላም ፕሬዝዳንት ማክሮን ሚስታቸውን በፎቶ እና በሳይንሳዊ ማስረጃ ሴት መሆኗን ለአለም ያሳያሉ ተብሏል።

ቀዳማዊት እመቤት ብሪጂት በወርሃ ግንቦት በቬትናም ጉብኝታቸው ወቅት የባለቤታቸውን ፊት ጥፊ በሚመስል መልኩ ሲገፈትሩ መታየታቸውን ተክትሎ በጾታቸው ጉዳይ እውነቱ እንዲታወቅ ግፊት እየተደረገባቸው ይገኛል።
#ቢቢሲ
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🤣2
የመመዝገቢያ መስፈርቶች‼️
በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ መርሐ-ግብር ተመዝጋቢዎች የሚከተሉትን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
👉የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት አለባቸው፤
👉ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች በከፍተኛ ትምህርት በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ለመመዝገብ በሠለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይንም በቀድሞ 10+3 ወይንም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ እኚህ መረጃዎች በምዝገባው ዕለት ተሟልተው ሳይቀርቡ መስፈርቱን ያላሟላ ተመዝጋቢ መቀበል የተከለከለ ነው፡፡

👉ለ2ኛ ዲግሪ ተመዝጋቢዎች በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡

👉ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያ መስፈርት የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡
👉ከተጠቀሱ መመሪያዎች ውጪ ገብተው ለሚማሩ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ ይሆናል።
==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1
72ቢሊዮን ዶላር ለወደብ‼️
ኢትዮጵያ ላለፉት 36 አመታት ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ 72 ቢሊዮን ዶላር ከፍላለች። ይህ በአሁኑ የዶላር ምንዛሪ ተመን ወደ ብር ሲቀየር 10 ትሪሊዮን ብር ነው።
የጅቡቲ ህዝብ ብዛት 1.1 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆን 10 ትሪሊዮን ብር ለጅቡቲ የህዝብ ብዛት ሲካፈል ኢትዮጵያ ለእያንዳንዱ የጅቡቲ ዜጋ 9.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ከፍላለች ማለት ነው። እስካሁን ለጅቡቲ ወደብ ኪራይ የተከፈለው ብር 12 የህዳሴ ግድቦችን ይገነባ ነበር።

==================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
2
ጴጥሮስ ማስረሻ የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ጴጥሮስ ማስረሻ አሸንፏል።

የውድድሩ አሸናፊ ጴጥሮስ ማስረሻ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆኗል።
2