G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#ይሄ ቻናል እንደ ድሮ active እንዳልሆነ አውቃለሁ..

ውዴ የቻናሌ ቤተሰቦች በመጀመርያ ከልቤ ይቅርታ መጠየቅ ፈልጋለሁ....

#active ያልሆነበት ምክንያት እኔ እንደ ድሮ social media ላይ ብዙ ሰአት አልቆይም plus በዝህ ትምህርት አለ ከትምህርት ውጪ ሌላም ........

ይሄ ቻናል ከ 5 በላይ admin ቢኖረውም ግን #adminochu በትምህርት ምክንያት መሰለኝ active አይደሉም😔...

So አዲስ admin ልንመርጥ ስለሆነ admin መሆን የምትፈልጉ ልጆች ተዘጋጁ.....
እንደ ድሮ ዝም ብለን admin አናደርግም ...admin ምናደርገው ከኛ ጋ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ plus አብረውን የምዘልቅ...

#Criteria admin ለመሆን..

👉ከዝህ በፊት telgram ላይ admin ሆኖ የምያውቅ

👉ሰውን ለመርዳት ፍቃደኛ የሆነ

👉የተለየ idea ያለው ( እዝህ ቻናል ላይ ይሄን ብንሰራ ....)


❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
ሌላው ደሞ
በቅርቡ tiktok ልንጀምር ስልሆነ የተለየ idea ያላችሁ ልጆች inbox🤙
❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
engineering_mechanics_-_dynamics_12th_edition_rc_hibbeler.pdf
22.5 MB
📚 Engineering Mechanics.

📚 Hibbler 12th edition.

📚 For 2nd year Engineering Students.

📚 የግቢ መምህራኖች ከ Mariam ጎን ለ ጎን ይህን መፅሀፍ ለ ማስተማሪያነት ፈተና ለማውጣት እና Assignment ለመስጠት ይጠቀሙበታል።

📌 Join and Share 👇👇👇

@Aconcise
@Aconcise
Engineering_Mechanics__Dynamics.pdf
39.7 MB
📚 Engineering Mechanics.

📚 Hibbler 14th edition.

📚 For 2nd year Engineering Students.

📚 የግቢ መምህራኖች ከ Mariam ጎን ለ ጎን ይህን መፅሀፍ ለ ማስተማሪያነት ፈተና ለማውጣት እና Assignment ለመስጠት ይጠቀሙበታል።

📌 Join and Share 👇👇👇

@Aconcise
@Aconcise
📚#inbox የተላከልን ስለ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ❗️

"እስኪ
ስለ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዮኒቨርሲቲ
ትንሽ ነገር ልንገራችሁ

1.በቅርቡ ነው university የሆነው
እኔ
ፍሬሽ ተማሪ ነኝ

Natnael እባላለሁ
CGPA 3.96 አለኝ
ግን
ምን ያረጋል
ሚመረጥ ደህና የሆነ ፊልድ የለም

ገና ወደ ግቢ ሳንገባና
ከገባን በኋላ
የተባልነው ይለያያል

አሁን
ዲፓርትመንት
ይለያያል


በቃ ያሉት ዲፓርትመንቶች

10 ናቸው
be Natural ማለት ነው

Computer Science
Ena Architecture

Keza 4 teaching
Sport science
Environmental science
Urban land management
Urban land transport bicha
new

ግን ገና ግቢ
ሳንገባ

Health Science field አሉ ተብለን ነበር

menelik II Hospital lay

ግን አሁን online ላይ

እነዚህ ብቻ ናቸው

Cs Ena Arch
Be Coc
ተመርጠዋል

እኔ እነሱን ስለማልፈልግ
አልተወዳደርኩም


አሁን ግን ሚጠብቀኝ ነገር ፈጣሪ ይወቅ

እና

እስኪ በየ ቻናሉ

ተናገሩ
ግቢውን እስኪ

እናጠያይቀው


በናንተ ቻናል
አስተላልፉት

እስኪ


በግቢው ድክመት ምክንያት

እኛ

ማንፈልገውን ዲፓርትመንት መማር አለብን እንዴ"

📌 Join and Share 👇👇👇

@GTutorialclass
A+ Tutorial Class❗️

📚 በሺዎች የሚቆጠሩ የአምና የመጀመሪያ አመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተደምመውበታል። ከ 4 - 3.7 ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበውም ወደ ሚፈልጉት ዲፓርትመንት ተቀላቅለውበታል። ታዲያ ይህ Tutorial Class አዳዲስ ባህርያቶችን ና ዘውጎችን በማካተት ለ ዘንድሮ አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እነሆ የምስራች መልዕክት አለው።

የዘንድሮ Freshman ተማሪ ናችሁ

ከእናንተ መሃል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማይፈልግ ማነው?

📌በመጀመሪያ ዓመት ዩኒቨርስቲ ቆይታው ጥሩ ውጤት [CGPA] አስመስግቦ የሚፈልገውን Department መግባት የሚፈልግ?

የምትፈልጉትን የትምህርት ዘርፍ መግባት ቀላል እንዳይመስላችሁካሉት ተማሪዎች ጋር ከባድ ውደድር ስላለ ውጤት በደንብ መስራት ይጠበቅባችኃል።

📌በግቢ የሚያጋጥማችሁን ፈተና ሁሉ በብቃት መወጣት የሚፈልግ ማነው?

ወደ ግቢ ከገባችሁበት ቀን ጀምሮ እስከምትወጡበት ጊዜ ድረስ የተለያዩ ብዙ ፈተና ያጋጥሟቸዋል። የአየሩ፣ የምግብ፣አለመስማማት፣ ዶርም ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች፣ የዉጤታችሁ መውረድ [ከሁሉ የበለጠው ፈተና ይሄ ነው፥ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት ሲያመጡ ተስፋ ለመቁረጥና ለተለያዩ ሱሶች ይዳረጋሉ።]
በባህር ውስጥ አሳ🦈 ብቻ ሳይሆን እባብም🐍 እንዳለ አትርሱ፥ በግቢም መልካም ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ብዙ የሚያሰናክሉና የሚያዘናጉ ነገሮች አሉ።

📌የጥናት መንገዶችን ማወቅ የሚፈልግ?

ሲጠና ዝምብሎ አይጠናም። ጥናት ምቹ ጊዜ፥ ቦታና ምቹ የማጥኛ ማቴሪያል ያስፈልጓል። በምን ጊዜ ነው ማጥናት ያለብኝ? ቀን ወይስ ሌሊት? በየትኛው ሰዓት ባነብ ይጠቅመኛል? እና ደግሞ Library ወይስ Dorm ላንብብ? የሁለቱ ጥቅሙና ጉዳቱ ምንድነው? ምን አይነት ማቴሪያሎችን፣ ሞጁሎችን ልጠቀም? አሪፍ Reference መፅሃፍቶች 📚 የትኞቹ ናቸው የሚለውን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋችኋል።

📌በውስጣችሁ ያለውን Passion [የውስጥ ፍላጎት] ማወቅ እንዲሁም ወደ ስራ መለወጥ የሚፈልግ?

በዚህ ዘመን ያለው የትምህርት ስርዓት በዘረጋላችሁ መንገድ ብቻ መሄድ የለባችሁም። ነገር ግን በውስጣችሁ ያለውን Passion ወደ Profession በመቀየር በግቢ ሳላችሁ በገንዘብም💵 ሆነ በLife Skill ተፅዕኖ መፍጠር ይኖርባችኋል። ስራ ለመያዝና ገንዘብ ለማግኘት እስክትመረቁ👨‍🎓 ድረስ መጠበቅ የለባችሁም። አሁን ላይ እንዴት ነው Skill'አችሁን አዳብራችሁ ለራሳችሁ ስራ መፍጠር የምትችሉት? ሁሌ Class እየተመላለሰ የሚማር፣ የቤት ስራ፣ አሳይመንት፣ፈተና የሚሰራ ተማሪ ብቻ አትሁኑ። ይህ የተለመደ ህይወት ነው። እራሳችሁን ፈልጋችሁ ማግኘት አለባችሁ።

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች አሰላስሏቸው። በግቢ ቆይታችሁ በዋናነት የሚያስፈልጓችሁ ናቸው።

በተጨማሪ እኚህንና የተለያዩ ፈተናዎችን ለመቆጣጠር [Handle ለማድረግ]፣ የተለያየ ምክር ሲያስፈልጋችሁ፣ በትምህርታችሁና በህይወታችሁ ስኬታማ ለመሆን ከፈጣሪ በተጨማሪ ከጎናችሁ ሆኖ የሚያበረታታችሁ ሊኖር ያስፈልጋል።

እናም እንዲህ አይነቱን አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በዚህ ዘመን እምብዛም ናቸው። አሁን ካሉትም ውስጥ በጣም ተፅዕኖ ፈጣሪና ተወዳጅ የሆነውን እናስተዋውቃችሁ

👉A+ Tutorial Class.

አምና ለብዙ ተማሪዎች መከታ የሆነና ብዙዎችን በ ዩኒቨርሲቲ Academic🧑‍🏫👨‍🏫 ትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የረዳቸው ድንቅ የTutorial Class ነው። የግቢ መምህሬኖች እንኳን ለማስረዳት የሚቸገሩባቸው የትምህርት ክፍሎች ይህ tutorial class ብትንትን አድርጎ በማስተማር ብዙዎችን ለቁም ነገር አብቅቷል። ምን ይሔ ብቻ ቀጥታ ፈተና የሚወጡ ትምህርቶችን በማስተማር ና በመጠቆም ብዙዎችን እጃቸውን በአፋቸው እንዲጭኑ አድርጓል።

ምዝገባ በቅርብ ቀን ይጠብቁን❗️

Registration Coming Soon!

ጥያቄም ካላችሁ በዚህ
@Ucan_ScoreBot አድርሷቸው።

@GTutorialclass

መልካም የግቢ ቆይታ
👍1
እኛ የተማርነው:-

* እኛ የተማርነው ጦርነት ምን እንደሆነ ነው።

* እኛ የተማርነው ወድቆ መነሳትን እና ጠላትን ድል ማድረግን ነው።

* እኛ የተማርነው እናንተን ከባርነት አላቀን በደማችን ነፃ ማውጣትን ነው።

* እኛ የተማርነው ህግ ማስከበርና ሞራል ያለው ትውልድን ማስቀጠልን ነው።

* እኛ የተማርነው አገር ተወራ ጣር ውስጥ በገባች ጊዜ የአባቶቻችን ልጆች ሆነን አገር ማትረፍን ነው!

* እኛ የተማርነው አገርና ህዝብን ለማስቀጠል መሳሪያ መፍታትና መግጠምን ነው።

* እኛ የተማርነው ሞቶ ማኖርን ነው።

* እኛ የተማርነው የስናይፕር፣ የድሽቃ፣ የክላሽ፣ የብሬንና የሌሎችን መሳሪያ አተኳኮስን ነው።

* እኛ የተማርነው የመድፍ ጩኸት፣ የጥይት፣ የድሽቃና ብሬን ድምፅ መለየትና ምን ያህል ርቀት ተጉዘው ጠላትን ይመታሉ የሚለውን ነው።

*እኛ የተማርነው ቆረጣ፣ መቆረጥን፣ መማረክንና ፅናትን ነው።

* እኛ የተማርነው የህዝቡን ሞትን በሞታችን ቀይረን ማኖርን ነው።

* እኛ የተማርነው እንደ መሃል አገር ተማሪዎች ቁጭ ብለን ሳይሆን:- አስከሬን ስንቀብር፣ ቁስለኛ ስናነሳ፣ ሬሽን ተሸክመን ዳገት ቁልቁለት ስንወጣና ስንወርድ፣ ለወታደር ደጀን ሆነን ይቺን ቀን ማምጣትን ነው።

* እኛ የተማርነው ብዙ የሰቀቀን ቀናትን ማለፍን ነው። ስለዚህ እኛ የተማርነውና ተፈትነን ያለፍነው በቶን እሳት ነው። እንደ ሌሎች አገራችን ልጆች ታዳጊዎች እድለኞች ሆነን ተረጋግተን አልተማርንም። ይህንን ከግምት ውስጥ የማያስገባ መንግስት ይኖር ይሆን?

ይህን የምለው የአማራ ተማሪዎችን ሰቀቀን ወደ እኔ ሳመጣውና የእነሱን ትንፋሽ ስተነፍስ ነው። እናም መንግስት የታዳጊዎችን ህይወት እንዳያበላሽ እንደገና ነገሮችን መመልከት አለበት። አመሰግናለሁ

© ሔቨን ዮሐንስ

📌 Join and Share 👇👇👇



@GTutorialclass
Chapter Four.ppt
3.8 MB
📚 Chemistry Best PPt

📚 For Freshman 2nd semester.
Share
@GTutorialclass
ታህሳስ 12/2014****

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ አቅም ማነስ ላለባቸው ተማሪዎች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።

ድጋፎቹ እየተደረጉ ያሉት ከበርካታ ቅን ኢትዮያዊያን በሚደረግ ድጋፍ ሲሆን ከአሁን በፊት በዩኒቨርሲቲያችን ማህበራዊ ሚድያ አድራሻዎች የበጎ ፈቃደኞች ስም ዝርዝር መለጠፋችን ይታወሳል።

በዛሬው እለትም (ታህሳስ 12/2014) በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፤ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ሀብት በማፈላለግ ከኩደጃ ትሬዲንግ ባገኙት የሴቶች ንጽህና መጠበቅያ ቁሳቁስ በሰሜኑ የሀገራችን ቤተሰብ ለተፈናቀለባቸዉ ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ድጋፍ ተደርጓል። ፡

በድጋፉ ወቅት የተገኙት የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፍ የሆኑት አቶ ዮሀንስ ጳዉሎስ ድጋፉ ቀጣይነት የሚኖረው እንደሆነ በመግለጽ በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል የደረሰዉን ችግር በተባበረ ክንዳችን እንወጣለን ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

//በዩኒቨርሲቲያችን ስም የሰብአዊነት ሀላፊነታችሁን እየተወጣችሁ ላላችሁ ወገኖቻችን፤ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የክብር መዝገብ ውስጥ ተፅፋችኋል//

*እውቀት ለለውጥ*

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @ethiouniversity1bot

   ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
🔰@Freshstudents 🔰
♥️@Freshstudents ♥️
🔰@Freshstudents 🔰
#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ሆነው ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ተደርጎላቸው በወቅታዊ ችግር ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ያልሄዱ ተማሪዎች መጋቢት 29 እና 30 /2014 ዓ/ም በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በአካል ተገኝተው ምዝገባ እንዲያደርጉ እና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ውሳኔ ተላልፋል።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አላስተናግድም ብሏል።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
👉 @ethiouniversity1bot

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
🔰@GTutorialclass🔰
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና ሂደት የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አስታወቀ
የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሉ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ የተማሪዎች ውጤት ያሳሰበው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

በአሁን ሰዓትም ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮቸና ባለሙያዎች፣ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፣ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና መምህራን የተውጣጣ ቡድን ወደ ፈተናወች ኤጀንሲ መላኩ ታውቋል፡፡

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
👉 @ethiouniversity1bot
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
🔰@GTutorialclass 🔰
የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡
በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህም ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡


📚 JOIN :@GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
#Update

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 25 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ካሉት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 43ቱ ብቻ ተማሪዎች የሚቀበሉ መሆኑ የዩኒቨርስቲዎችን የቅበላ አቅም ዝቅ ማድረጉ ተነስቷል።

በተጨማሪም ዘንድሮ የተፈታኝ ተማሪዎች ብዛት የጨመረ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ ከፍ እንዲል እንዳደረገው ተገልጿል፡፡

በሁለት ዙር የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን 287 ሺህ 223 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወሳል።



📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጠ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከ " 12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት እና ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ " ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍል ከ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ጋር ተያይዞ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የ12ኛ ክፍል ፈተና በ2 ዙር እንዲሰጥ መደረጉንና በመጀመሪያው ዙር የስነ-ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ከፈተናው ቀን ቀድሞ በመውጣቱና የውጤት ግሽበት በመምጣቱ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከወሠዱት 544ሺ 682 ተማሪዎች ውስጥ 44 ከመቶዎቹ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።

በሁለተኛው ዙር ከተፈተኑት 53ሺ 997 ተማሪዎች ውስጥ 28 ከመቶዎቹ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር 554 ሺ 682 ተፈታኞች ውስጥ ደግሞ 25 ከመቶዎቹ ይመደባሉ ብለዋል።

የ10 ክፍል የማትሪክ ፈተና በመቅረቱ ምክንያት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በዘንድሮው አመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ወስደዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አራት ዩኒቨርሲቲዎቻችን መቀበል በማይችሉበት ሁኔታ ከአምናው የተሻለ ቁጥር ያለው ተማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን አብራርተዋል።

በትግራይ ያሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውና ዘንድሮም ይመደቡ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉ 48ሺ ተማሪ የቅበላ አቅም አጥተናል ብለዋል።

ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በ43 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 152 ሺ 14 ተማሪዎች እንዲመደቡ መደረጉና ይህም ከአምናው የቅበላ አቅም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።

ፀጥታ ችግር ያጋጠማቸው አከባቢዎች በተመለከተ የተለየ መቁረጫ ነጥብv ለመወሰን የሚያስገድድ የውጤት ትንተና ስላልተገኘ በበመደበኛው የመቁረጫ ነጥብ ተስተናግደዋል ብለዋል።

በባለፈው አመት በ47 ዩኒቨርሲቲዎች 147 ሺህ ተማሪዎች ምደባ የተደረገ ሲሆን ዘንድሮ በ43 ዩኒቨርሲቲዎች 152ሺ 014 ተማሪዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

====================
∞ ነኝ።😊👍
======================

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !

📚 JOIN: @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass