G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ሰላም እንዴት ናችሁ🙌

ዛሬ እንደተለመደው Psychology
Course እንቀጥላለን! በተቻለኝ መጠን ግልፅ ለማድረግ ጥሬያለሁ😇

የሚገርማችሁ ያዘጋጀዉላችሁ ኮርስ ግማሹ Clear ሆኖብኝ😭 በችኮላና በንዴት ነበር እንደገና ያዘጋጀውት፣ ነገር ግን አንድም ያስቀረሁት የለም😊
ግልፅ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አለኝ። ኖቱ እንዳይበዛባችሁ ስላሰብኩ ግማሹን ጠዋት የቀረውን ከሰዓት እንለቃለን።

በርቱ! አንብቡ!

©A+ tutorial class
📚PERCEPTION

በዚህ Sub-Chapter Major
Charecteristics of Perception የሆኑትን👇 እናያለን

📌Selectivity of Perception
📌Form Perception
📌Depth Perception
📌Perceptual Constancies
📌Perceptual illusion

እነዚህን ዘርዘርን መንዝረን አንድ በአንድ እናያቸዋለን፣ ነገር ግን ውስብስብ ስለሚመስል አንዱን ስትይዙ ሌላው እንዳያመልጣቹ😇

1⃣Selectivity of Perception (Attention!)

Note that at any given time, our sense organ is bombarded by many stimuli.
🖇እንደምታውቁት ሁልጊዜ የስሜት ህዋሳቶቻችን ከተለያዩ ብዙ ክስተቶች ጋር ይገናኛሉ፣ ነገር ገን እኛ attention ሰጥተን Response የምንሰጠው ለጥቂቱ ብቻ ነው።

ይሄ አንዱ ላይ Focus አድርገን ሌላውን stimuli ደግሞ ignore የማድረጉ ነገር(Selective Perception), #Attention ይባላል።

What does this selectivity of perception imply?🤔

🌹Selectivity of Perception imply የሚያደርገው, የልምምዳችን ሁኔታ ከየትኛውም ነገር በላይ ሁለት ነገር ላይ ነው የተመሰረተው።
📌Focus
📌Margin

🖇Events or Stimuli that you percieve clearly are the #focus of our experience.

🖇Events or stimuli that you percieve dimly or Vaguely are #Margin of our experience.
ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ላስረዳችሁ ለምሳሌ በDSTv ቤት ሆናችሁ የሰዎች ጫጫታ ብርድ ባለበት ስፍራ ሆናችሁ የኳስ⚽️ ጨዋታ እያያቹ አይናቹ የሚከታተለው ኳሱን የያዘው ሰውዬ ላይ ነው፥ ይሄ Focus ይባላል። ነገር ግን Still የሰዎቹ ጨጫታ፣ብርዱ ምናምን አለ፣ ነገር ገን እናንተ ለእነዚህ ነገሮች ሙሉ ትኩረት አልሰጣቹም፤ ማለትም በቃ Dimly/Vaguely ነው ትኩረት ያረጋቹት እንዲህ ሲሆን #Margin ይባላል።

ልብ በሉ👆ጫዋታው ካለቀ በኃላ ግን ቅድም ትኩረት ያልሰጣቿቸው ነገሮች አሁን ትኩረት ማድረግ ትጀምራላችሁ።(ምንድነው ብርዱ ምንድነው ጫጫታው ትላለህ😺)

So, አያቹአ ቅድም Focusአቹ የነበረው(ኳሱ) አሁን ሲያልቅ ብዙም ትኩረት ስላልሰጣቹት Marginአቹ እየሆነ መጣ። ደግሞም ቅድም #Marginአቹ የነበሩት አሁን Focusአቹ ሆነዋል። 🤚ይሄ ምንድነው ሚያሳየው Attention Constantly shifting እንደሆነ🤷‍♂

What factors do you think determine your attention?
ሰው ለምንድነው በአንድ ነገር ትኩረቱ የሚሳበው?🤨🤨

🌹Paying attention is in general a function of two factors: factors external to the perceiver and factors internal to the perceiver.

External Factors የሚባሉት
📌Size and Intensity
📌Repitition
📌Novelty(Newness)
📌Movement
🔸Size and intensity👉 Bigger and Brighter የሆኑት ነገሮች ከsmaller እና ደብዛዛ ከሆኑት ነገሮች ይልቅ ትኩረት ሳቢ ናቸው። ለዚያኮ ነው፣ Bolded የሆኑ Letters እንዲሁም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ትኩረታችንን የሚያገኘው።

🔸Repitition👉repeatedly or frequently የሚደረገው ድርጊት አንዳንዴ ትኩረታችንን ይስባል። ለዚያ ነው መፈክሮች(Slogans)፤ Advertisements የሚደጋገሙት።
❗️ነገር ግን አንዳንዴ ነገሩ ምንም ያክል ትልቅ ቢሆን ነጭ ቢሆን ቢደጋገም ትኩረት ላንሰጥ እንችላለን😒 ምናልባት ይሄ የሚሆነው ነገሩን Adapt ስላደረግነው ይሆናል፣ This is Called Sensory Adaptation[Habituation]. ባለፈው አይተናታል እቺን😎

🔸Novelty(Newness)👉ይሄ ማለት አንድ ነገር በEnvironmentኡ ውስጥ ካሉት ነገሮች ጋር Contrast ሲያደርግ ትኩረታችንን ያገኛል። ለዚያ ነው ቤት ውስጥ ካሉት ሰዎች ይልቅ ህፃን(First born) attentionአችንን የሚያገኘው😘

🔸Movement👉እንደምታውቁት Moving objects ከNon-moving/stagnant objects በላይ ቶሎ ትኩረት ይስባሉ። ለዚያ ነው ቢራቢሮ🦋 ወዲህ ወዲያ ስትል የምንመሰጥባት😁

Internal Factors የሚባሉት
📌Set or Expectency
📌Motive or needs

🔸Set refers to the idea that you may be "ready" and "primed for" certain kinds of sensory input.
ህፃን ልጅ ያላት እናት👩‍🦱 ሁሌ የምትጠባበቀው "ልጄ አለቀሰ ወይስ አላለቀሰም" የሚለው ከሆነ..የሚያለቅስ የህፃን ድምፅ በሰማች ቁጥር ልጄ ነው ወይ ትላለች😍😍 Because እየተጠባበቀችው ስለሆነ እንግዲህ ይሄ ነው "Set" ሚባለው።

🔸Motive(Needs):- ሰው ትኩረት የሚያደርገው ውስጥ ባለው ፍላጎትMotive ላይ ተመስርቶ ነው። ለምሳሌ የራበው ሰው Focus የሚያረገው Food ላይ ነው፣ አሁን እናንተ የመማር ፍላጎት በውስጣቹ ስላለ ነው፣ ለዚህ tutorial ትኩረት የሰጣቹት።

2⃣Form Perception

🌷The meaningful shapes or patterns or ideas that are made perhaps out of meaningless and discrete or pieces and bites of sensations refer to form perception.

🖇ይሄ meaningless ከሆኑ ነገሮች ማለትም ከምናያቸው፣ ከምንሰማቸው..ነገሮች ትርጉም ያለው ነገር መመስረት ነው Form perception የሚባለው።
ለዚህ ደግሞ Objectኡን[figure] ከSurroundingኡ[Ground] መለየት ያስፈልገናል።

Figure-Ground Perception
በግድግዳ ላይ የተሳለ ስዕል ብንወስድ፦ ስዕሉን እንደ figure ግድግዳውን ደግሞ እንደ ground ነው የምንወስደው ሌላ ደግሞ በመሬት ላይ የፃፈ ፁፍ እዚጋ ደግሞ መሬቱ እንደ Ground ሲሆን ፁፉ ደግሞ እንደ figure ነው🤷‍♂

የሆነው ሆኖ How Can we separate the figure from the general Ground and Form Perception?
ለዚህ 2 ዘዴዎች አሉ😊
📌Contours
📌Organization

Contours in Form Perception

🔰Contours are formed whenever a marked difference occurs in the brightness or color of the background. Figureን ከground ለይታችሁ የምታውቁት Contourኡን ስታውቁ ነው!
ለምሳሌ በጥቁር እስክሪብቶ🖊 Blackboard ላይ ብትፅፉ፣ ጥቁሩን ፁፉ ከblackboardኡ የለያችሁ ጊዜ Contourኡን ታገኛላችሁ። ከዚያ በኃላ ፁፉ Figure, blackboardኡ ደግሞ ground እንደሆነ ማወቅ አይከብዳችሁም👍
ሌላ ምሳሌ፣ ጥቁር ሰው ጥቁር ልብስ ለብሶ አስቡት🙈🙉 ሰውዬውን ከልብሱ የለያችሁ ጊዜ Contourኡን ታገኛ
1. 4 📚Set Theory

🔖እዚህ ስር ሶስት ነገሮች በዋናነት ታጠናላችሁ፦
📌Concept of set
📌Description of set
📌Operation of sets
1⃣Concept of set ማለት ያው የSet definition እንደማለት ነው። by the way "set"ን ከአምስትኛ ክፍል ጀምረን ነዋ የተማርነው🤨። ስለዚህ የሚከብድ ነገር የለሁም። Handout page 26 ላይ ታገኛላችሁ!

2⃣Description of Sets
ይሄ ማለት ደግሞ Set Describe የሚደረግበት (የሚገለጽበት) መንገድ ነው።
There are four different ways for this!
1. Verbal method
2. Roster Method
3. Partial listing method
4. Set builder method
📔ግልፅ በሆነ መንገድ ሞጁሉ ላይ
ተብራርቷል፣ ደግሞ ከPage 28-31 ያሉትን 11 የExercise አትለፏቸው! ሞክሯቸው!

3⃣Set Operation and Venn Diagrams
📔Set Operation is just the process of forming new set, it may be taking:
common elements
[intersection የሚባለው],
Non-Common elements
[Relative Complement የሚባለው]
Putting all together
[Union የሚባለው]

እና በእነዚህ ሶስት መንገዶች ተጠቅመን አዲስ Set ስንፈጥር ነው Set operation የሚባለው።

Theorem 1.1 and 1.2 ላይ ያሉትን Properties እዩዋቸው።

Elementary ትምህርት የሆነው Venn diagram እዚህ ላይም አለ😁...የሚገርማችሁ Math ላይ በጣም ቀላል የሆኑ ትምህርቶችን ሳይ እናደዳለሁ😁

ከPage 36-38 ላይ ያሉትን 13 ጥያቄዎች ምክሯቸው!

በሚቀጥለው Chapter 2
The real and Complex number system እናያለን😊

ጥያቄ ካላችሁ @Ucan_scorebot ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ🙏

©A+ tutorial class
😊 ሰላም ቤተሰቦቻችን እንዴት ናችሁ ግቢ ለመግባት ዝግጅት እንዴት ነው አይዟችሁ በርቱ።

😊 ዛሬ የ logic and Critical thinking ትምህርት ይኖረናል። ከጥቂት ሰአታት በሗላ ኖት ይለቀቃል። ዛሬ የምንማረው ትምህርት ሁሉም ግቢዎች ላይ ፈተና ይወጣበታል። ስለዚህ በአግባቡ ተረዱት።

😊 እሁድ ወይም ሰኞ የ logic ትምህርት chapter 1 & 2 ከ 30% ፈተና ይኖራችሗል። 93% ቱ ከ chapter 2 እና 7% ቱ chapter 1 ነው።

😊 እንደተለመደው ከ 1 እስከ 5 የወጡ የካርድ ሽልማት አለው። ፈተናውን የሚደፍን ተማሪ ደግሞ ለየት ያለ ሽልማት ተዘጋጅቶለታል። አንብቡ ተዘጋጁ😎

ሎጂክን በተመለከተ ጥያቄ ወይም አስተያየት ካላችሁ👇

@Inquiry_receving_bot
📚 Chapter Two.

📖 Basic Concepts of Logic.

📕 Evaluating Arguments.

📗 Validity and Soundness

📚 Types of Deductive Argument.

😎 በባለፈው ትምህርታችን deductive argument ምን እንደሆነ አይተናል።

🤓 ዛሬ ደግሞ የ deductive argument አይነቶችን እናያለን።

🌹 There are two types of deductive argument.

📍1) Valid deductive argument or valid argument.

📍2) Invalid deductive argument or invalid argument.

😁 እስቲ ሁለቱንም ለየቅል እንመልከት።

📍Valid Argument

🌀 Valid Argument - is a type of deductive argument such that the premises are assumed true, it is impossible for the conclusion to be false.

🌀 Valid Argument - the conclusion follows with strict necessity from the premises.

😊 እስቲ ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት እንሞክር።

😎 ማስረጃዎቹ(Premises) እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የማይችል ከሆነ ወይም በሌላ አባባል conclusion ኑ 100% እውነት ከሆነ argument ቱ valid argument ይባላል።

🥺 ታዲያ እዚጋ ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው ማለት፡

👉 ማስረጃዎቹ በነባራዊው አለም እውነትም ውሸትም ሊሆኑ ይችላሉ። እሱን እኛ አያገባንም። በነባራዊው አለም እውነትም ይሁኑ ውሸትም ይሁኑ ፡ እኛ ግን በ አምሮኣችን እውነት ናቸው ብለን እናስባለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ሆኑ🤗

👉 ታዲያ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የማይችል ከሆነ valid deductive argument ይባላል። ምሳሌዎችን እንመልከት፡

🔷Example 1

All football players are Americans.
Tedy Afro is a football player.
Thus, Tedy afro is an American.

🥺 ተመልከቱ ይህን ምሳሌ።

All football players are Americans እና Tedy Afro is a football player የሚሉት premises ናቸው።

🤔 በነባራዊው አለም ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው እንዴ አይደለም።

🤔 በነባራዊው አለም ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ናቸው እንዴ አይደሉም።

😁 አያችሁ አይደል ሁለቱም ማስረጃዎች በነባራዊው አለም ውሸት ናቸው። እኛ ግን አያገባንም🙅‍♀🙅‍♂። እውነት ናቸው ብለን ነው assume የምናደርገው። ስለዚህ እውነት ናቸው🤗

👉 ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ከሆኑ
👉 ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ከሆነ
👉 ስለዚህ ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው።

😊 ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው የሚለው conclusion ፈፅሞ ውሸት መሆን አይችልም። ምክንያቱም ቴዲ አፍሮ በሁሉም ኳስ ተጫዋቾች ውስጥ ነው ያለው። ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች ደግሞ አሜሪካዊ ናቸው። ስለዚህ ቴዲ አሜሪካዊ ነው።

😋 So, the argument is valid deductive argument.

አሁን ደግሞ invalid argument ን እንመልከት።

📍Invalid argument

Invalid argument - is a type of deductive argument such that the premises are assumed true, it is possible for the conclusion to be false though it is claimed to.

📍Invalid argument - the conclusion does not follow with a strict necessity from the premises.

😎 እስቲ እናብራራው።

ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የሚችል ከሆነ argument ቱ Invalid deductive argument ይባላል።

🥺 ታዲያ እዚጋ ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው ማለት፡

👉 ማስረጃዎቹ በነባራዊው አለም እውነትም ይሁኑ ውሸትም ይሁኑ ፡ እኛ በአምሮኣችን እውነት ነው ብለን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው🤗

👉 ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የሚችል ከሆነ invalid argument ይባላል። ምሳሌ እንመልከት😎

🔷Example 2

All football players are Americans.
Tedy Afro is an American.
Therefore, Tedy Afro is football player.

🥺 ተመልከቱ ይህን ምሳሌ፡

All football players are Americans እና Tedy Afro is an American የሚሉት premises ናቸው።

😟 ከላይ የቀረቡት ሁለቱም premises በነባራዊው አለም ውሸት ናቸው። እኛ አያገባንም ፡ እውነት ናቸው ብለን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው🤗። ከዛ ፡ ተመልከቱ😊

👉ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ናቸው።
👉 ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው።
👉ስለዚህ ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው።

ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው የሚለው conclusion ውሸት መሆን ይችላል። እንዴት

እዚጋ በደምብ ተከታተሉኝ ውዶቼ

ለምሳሌ በአለም ላይ 1000 ሺህ ኳስ ተጫዋቾች ቢኖሩ እና በአለም ላይ 5000 አሜሪካውያን ቢኖሩ። እንዲሁም ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው።

ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች ማለትም 1000 ሺዎቹም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ከሆኑ ፡ ይህ ማለት ከ 5000 አሜሪካውያኖች 1000 የሚሆኑት ኳስ ተጫዋች ናቸው። 4000 የሚሆኑት አሜሪካውያን ኳስ ተጫዋቾ አይደሉም ማለት ነው። ስለዚህ ቴዲ አፍሮ ከ 4000 አሜሪካውያኖች መካከል ሊሆን ይችላል። ማለትም ኳስ ተጫዋች ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው የሚለው ውሸት መሆን ይችላል።

ከዚህ ምን እንረዳለን

ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካውያን ናቸው ማለት ሁሉም አሜሪካውያን ኳስ ተጫዋቾች ናቸው ማለት አይደለም።

ገባችሁ ኣ በጣም simple ነው😂

ተወዳጆች ሆይ ከ Example 1 Example 2 ምን ተረዳችሁ? የሆነ formula ማግኘት ትችላላችሁ። እስቲ ሞክሩት። አስፈላጊ ከሆነ ቡሗላ ላይ እነግራችሗለሁ።

ስለዚህ deductive argumentvalid እና invalid ብሎ መፈረጅ ወይም መክፈል validity ተብሎ ይጠራል።

ስለዚህ ከምሳሌዎቹ መረዳት እንደቻልነው Validity(valid or invalid) ማለት premises እና conclusion በ ነባራዊው አለም እውነት መሆናቸውን ወይም ውሸት መሆናቸውን የሚገመግም ሳይሆን premises እና conclusion ያላቸውን የምክንያታዊነት ዝምድና ፡ መደጋገፍ የሚገመግም ነው። ስለዚህ

Validity is not determined by the actual truth and falsity of the premises and the conclusion.

👆 ያዙት True/false ላይ ብዙ ጊዜ ይወጣል።

ማንበቡ እንዳይሰለቻችሁ ቀጣዩን ኖት ከሰአት እለቅሏችሗለሁ።

©A+ tutorial class.
1
📚 ግቢ ላይ የት የት ቦታዎች ማንበብ እንችላለን

በ Concise English(@Aconcise) ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ።

📍በ ሁሉም የግቢ ተማሪዎች ሊባል በሚቻመልኩ በግንባር ቀደምነት ተመራጭ የሆኑ የመቸከያ ቦታዎች መካከል፡

📖 1ኛ) ላይብረሪ
📖 2ኛ) ስፔስ
📖 3ኛ) ዶርም

📚 ላይብረሪ

👩‍🏫👨‍🏫 12 አመታትን በትምህርት ላሳለፈ ተማሪ ስለ ላይብረሪ መናገር ልጅ ለ እናቷ ምጥ እንደ ማስተማር ነው😁። ነገር ግን ግቢ ላይ ስላለው የ ላይብረሪ የአሰራር ስርአት አንዳንድ ነገር ማወቁ አይከፋም😊

📖 ላይብረሪ አያሌ በሆኑ የግቢ ተማሪዎች ተወዳጅ የሆነ የመቸከያ ፡ የመሰገጫ ፡ የመፍለጫ ቦታ ነው።

👨‍🏫 ታዲያ ላይብረሪ ሔደን ለመገልገል ልንተገብራቸው የሚገቡ ደንቦች ና መመሪያዎች አሉ። በ ሁሉም ግቢ ተፈፃሚነት ያላቸውን ደንቦች ና መመሪያዎች ጠቅለል ባለ መልኩ እንመልከት።

📍 የ ግቢ መታወቂያ ካር ወይም ID Card መያዝ ግዴታ እና ግዴታችሁ ነው ላይብረሪ ስትሔዱ። 😎 ሰሞኑን ግቢ ልትገቡም አይደል ፡ እንደገባችሁ ከ 2 እና ከ 3 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ ግቢ መታወቂያ ካርድ ይሰጣችሗል። ስለዚህ መታወቂያ ካርድ መያዝ ግዴታ ነው ላይብረሪ ስትሔዱ።

📍 ጠሽ ጠሽ የሚል ሸበጥ ጫማ መልበስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ቋ ቋ ቋ የሚል Hill ጫማ መልበስ የተከለከ ነው👠። እንዲሁም ውስጥ ላይ ማስቲካ ማነክ አይቻልም።

📍 Ear phone በፍፁም የተከለከለ ነው☹️። አደራችሁን የምላችሁ ነገር Ear phone አድርጋችሁ ወደ ላይብረሪ እንዳትሔዱ ፡ ላይብረሪ ውስጥም እያነበባችሁ ear phone በፍፁም እንዳትጠቀሙ። ቅጣቱ አይጣል ነው😩። ገጠመኝ ስላለኝ በዚህ ጉዳይ።

📍 አሁን ዘመኑ የ ኮሮና ም አይደል Mask መልበስ ግዴታችሁ ነው።

👆 እንግዲህ ከሞላ ጎደል መሰረታዊ የሚባሉት መመሪያዎች ናቸው።

👨‍🎨👩‍🎨 ታዲያ የ ላይብረሪው መግቢያው በር ላይ የ ላይብረሪ ዘበኞቾ፡ ተቆጣጣሪዎች አሉ። ልክ ከ ላይብረሪው መግቢያ በር ስትደርሱ Id card አውጥታችሁ ለ ተቆጣጣሪዎቹ ማሳየት ይኖርባችሗል። መመሪያዎቹን ካላሟላችሁ ይመልሷችሗል። ምንም ርህራሔ የለም😟

😎 ደንብና መመሪያውን ካማላችሁ ግን Sanitizer 🤲 አድርገውላችሁ በክብር ወደ ውስጥ እንድትገቡ ይፈቅዱላችሗል።

🔐 Ok አሁን ተቆጣጣሪዎችን አልፈን ወደ ላይብረሪው ውስጠኛው ክፍል እና ግብዳ ግብዳ መፅሀፍ በ ስርአት ወደ ተደረደሩበት ቦታ እያመራን ነው። እስቲ ተከተሉኝ፡

📚 እሺ እንግዲህ ላይብረሪው ውስጥ ከገባን በሗላ የምንፈልገውን መፅሀፍ እንዴት ነው ማግኘት የምንችለው🤔

🤗 በሁለት አይነት መንገድ ማግኘት እንችላለን።

🎈1ኛው) Open book ነው።
🎈2ኛው) በ ላይብረሪስቶች አማካኝነት።

📚Open book

Open book የሚባለው ምን መሰላችሁ😊

📖 የ እያንዳንዱ ኮርስ ወይም subject መፅሀፍቶች ስርአት ባለው መልኩ ተደርድረው ፡ ከመድረደሪያው ላይ የኮርሶቹ ወይም የ ሰብጀክቶቹ ስም በ ማርከር ተፅፎ ተለጥፏል።

📖 ስለዚህ እናንተ ከተደሩት መፅሀፍ መካከል የምትፈልጉትን መፅሀፍ መርጣችሁ ታወጣላችሁ። ከዛስ🤔

ከዛ ያወጣችሁትን መፅሀፍ ይዛችሁ ቀጥታ ወደ ላይብረሪስቶች ወይም አስነባቢዎች ትሔዳላችሁ። ከዛ ID card ኣችሁን ለ ላይብረሪስቶች ትሰጣላችሁ። ID card ከሰጣችሁ በሗላስ🤔

ከዛ መፅሀፋችሁን ይዛችሁ ብትፈልጉ ground ላይ ሁናችሁ ብትፈልጉ ፎቅ ላይ ሁናችሁ ፡ ብትፈልጉ tension box ውስጥ ሁናችሁ ብትፈልጉ ከ tension box ውጭ ሁናችሁ ፡ አሪፍ እና ምቹ ወንበሮች አሉ ከዛ ቁጭ ብላችሁ መሰገጥ መቸከል ነው። ከዛ አንብባችሁ ከጨረሳችሁ በሗላ መፅሀፋን ካነሳችሁበት ቦታ ትሔዱና በስርአት መልሳችሁ ታስቀምጣላችሁ። ከዛ ከላይብረሪስቶች ሒዳችሁ ID card ኣችሁን ትቀቡሉ እና ትወጣላችሁ ማለት ነው። ከዛ ፈተናውን ድፍን😋። መድፈን ይቻላል ውዶቼ።

📚ላይብረሪስቶች

ሁለተኛው መፅሀፍ የምናገኝበት ዘዴ በ አስነባቢዎች ወይም በ ላይብረሪስቶች አማካኝነት ነው።

እንዴት መሰላችሁ ውዶቼ🤔

📖 ላይብረሪ እንደገባን ቀጥታ ወደ አስነባቢዎቹ እንሔድና የምትፈልጉትን የመፅሀፍ ስም ትገሩታላችሁ/ትነግሯታላችሁ፡ ከዛ እኑሱም መፅሀፉን አምጥተው ይሰጧችሗል። መፅሁፉን ስትቀበሉ ID card ኣችሁን ለአስነባቢዎቹ ትሰጣላችሁ። ከዛ መፅሀፋችሁን ይዛችሁ አሪፍ እና ምቹ ወንበሮች አሉ ከዛ ቁጭ ብላችሁ መቸከል ነው። አንብባችሁ እንደጨረሳችሁ ፡ መፅሀፋን ለላይብረሪስቶች አስረክባችሁ ID card ኣችሁን ተቀብላችሁ ትወጣላችሁ ማለት ነው።

📚 እንግዲህ አንዳንድ ላይብረሪዎች ላይ የምትፈልጉትን መፅሀፍ የምታገኙት በ open book አማካኝነት ነው። አንዳንድ ላይብረሪዎች ላይ ደግሞ የምትፈልጉትን መፅሀፍ የምታገኙት በላይብረሪስቶች አማካኝነት ነው። ስለዚህ እንደ ላይብረሪው የአሰራር ስርአት መገልገል ትችላላችሁ።

📚 ታዲያ ላይብረሪ ውስጥ ስናበብ ፡ ሰላማዊ ሌሎች ተማሪዎችን ሊረብሽ በማይችል መልኩ መሆን አለበት። ከ ተቁነጠነጣችሁ ፡ ማን አለብኝ ብላችሁ ዘራፍ የምትሉ ከሆነ ተቆጣጣሪዎች ስላሉ ጓ ይሉባችሗል።

📚 ግቢ ላይ ላይብረሪዎች 24 ሰአት ሊባል በሚቻል መልኩ ክፍት ናቸው። ከ ጧቱ 12:00 ሰአት እስከ ጧቱ 2:00 ሰአት ብቻ ነው የማይሰሩት። ስለዚህ በፈለጋችሁበት ሰአት ሒዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

📚 እዚጋ ግን ለ ሴቶች እህቶቻችን የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ፡ ሌሊት ላይ ላይብረሪ ሔደሽ ማንበብ የምትፈልጊ ከሆነ በፍፁም ብቻሽን እንዳትሔጂ። 3 ወይ 4 ሁናችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ነው መሔድ ያለባችሁ። መደፈር የሚባል ነገር አለ😓። ገጠመኞችን ስለማውቅ ነው። አንዱን ገጠመኝ በትንሹ ልንገራችሁ።

👩‍🏫 ልጅቷ ሰቃይ ተማሪ ናት ። Cumulative 3.96 ነው ያላት። እና ልጅቷ ቀን ቀን ማንበብ አትወድም። ከ ሌሊቱ 5 ሰአት በሗላ ነው የማንበብ ልምድ ያላት። እና እንደተለመደው ሀገር ሰላም ነው ብላ ሌሊት 5 ሰአት አካባቢ ላይብረሪ ሔደች። ከዛ እሷም ማንበቧን ተያያዘችው።

ከሌሊቱ 10 ሰአት አካባቢ ግን
ያልጠበቀችው ዱብ ዕዳ ሰይፍ በነፍሷ ሊያልፍ ሆነ።

📚 በርካታ ተማሪዎች ላይብረሪውን ጥለው ወጥተዋል። ላይብረሪስቶች ወይም አስነባቢዎቹ የሰውነት ባህሪ አሸንፏቸው ለ እንቅልፍ እጃቸውን ሰጥተዋል። አስነባቢዎቹ ደማሚት ቢፈነዳ እንኳን መስማት በማይችሉበት ሁኔታ ለ ሞት በተቃረበ በሚመስል እንቅልፍ ተጠምደዋል።

📚 ወዲህ ደግሞ፡ ስሜቱ ያሸነፈው ፡ በፍትዎት ልቡ የታወረ የዚቺን ሰቃይ ተማሪ ተስፋ ና ልፋት ገደል ለመክተት ፡ ወደዚች ሰቃይ ተማሪ ያመራል።

😁 ልባችሁን አንጠለጠልኩት መሰል። ብቻ ልጅቷ በ ተአምር ከ መደፈር አደጋ ተረፈች🙏። አሁን ልጅቷ GC ናት የማዕረግም ተመራቂ ናት👩‍🎓

📚 ተወዳጆች ሴቶች ሆይ እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ፡ ምሽት ላይ ላይብረሪ ስትሔዱ ብቻችሁን አትሒዱ ፡ በቃ በጨለማ ራሳችሁን በሚያጋልጥ መልኩ አትንቀሳቀሱ ምክንያቱም ብዙ አይነት ባህሪ ያለው ሰው ግቢ የሚገባው።

😊 ለዛሬ ይብቃን። በቀጣይ ደግሞ ስለ space እና dorm ሹክ እንባባላለን።

📌 Join and share 👇👇

@Aconcise
@Aconcise
#inbox_የተላከልን

በጣም አሪፍ ጥያቄ ነው። በጣም አሪፍ ነው የማመሰግነው። 🤔ግን እናንተ ይህ ጥያቄ በአምሮኣችሁ አልተመላለሰም?

Hello teacher I have one question 🙋 previously you defined deductive argument as "DA is an argument in which the premises are claimed to support the conclusion in such a way that it is impossible for the ቀpremises to be true and the conclusion false " እና ዛሬ ደግሞ invalid deductive argument define ስታረግ "invalid argument is a type of deductive argument in which if the premises are assumed true it is possible for the conclusion to be false"🙄🙄 thoug`h`` i`t is claimed (እዚጋ underline ከሆነው መሰለኝ ምስጢሩ ) ጥያቄየ ምንድን ነው invalid deductive argument ወስጥ ከተካተተ እንዴት ነው ሁለቱ ሀሳቦች ሚስማሙት አይቃረኑም ??
#እና_ደግሞ if premises are assumed to be true it is possible for the conclusion to be false (invalid ) በዚ definition መሠረት invalid deductive argument ከ inductive argument በምን ነው ምለየው አባክህን መምህር እዚጋ በደንብ ያስረዱኝ 😁 10Q ስላነበብከው
Observational ነው Learning ነው፣ ማለት የኔ ሞዴል ነው ከምንለው ሰው የምንማረው የLearning አይነት ነው።

🖱Because of its reliance on observation of others, a social phenomenon; the perspective taken by Bandura is often referred to as a social cognitive approach to learning.

Bandura identifies three forms of reinforcement that can encourage observational learning.

Direct Reinforcement
Vicarious Reinforcement
Self Reinforcement

Bandura mentions four conditions that are necessary before an individual can successfully model the behavior of someone else.

1. Attention: the person must first pay attention to the model. መጀመርያ ያ ሞዴል ለሚሆነን ሰው ትኩረት መስጠት አለብን።

2. Retention: the observer must be able to remember the behavior that has been observed. ከዚያ ያ ሞዴላችን ላይ ያየነውን/ያስተዋልነውን ባህሪ ማስታወስ መቻል አለብን።

3. Motor reproduction: is the ability to replicate the behavior that the model has just demonstrated. ከዚያ ደግሞ በሞዴላችን ላይ ያየነውን ባህሪ ደግመን ደጋግመን መለማመድ መቻል አለብን።

4. Motivation: This means that learners must #want to demonstrate what they have learned. ይሄ ደግሞ የውስጥ ተነሳሽነት ሊኖረን እንደሚገባ የሚገልፅ ነው።

Educational Implications of Social Learning Theory

🌱Students often learn a great deal simply by observing other people.
🌱Teachers should expose students to a variety of other models.
🌱Modeling provides an alternative to shaping for teaching new behaviors.
እና የመሳሰሉት ናቸው፣ ያው ግልፅ ስለሆኑ ነው በአማርኛ ያልተረጎምኩት😊

Cognitive Learning Theory

It is about understanding how the human mind works while learning.
ስለዚህ ይሄ ካለፉት ሁለቱ (Classical and Operant) ለየት የሚያረገው በአይምሮ አጠቃቀም🧠 ላይ ትኩረት ማድረጉ ነው።

Cognitive learning may take two forms:

🔖Latent learning
🔖Insight learning (gestalt learning or perceptual learning

1. Latent Learning
እንደምታውቁት "Latent" ማለት በራሱ "ድብቅ" ማለት ነው።
ስለዚህ Latent Learning ማለት የምናውቀው ነገር ሆኖ ነገር ግን ምቹ ሁኔታ አግኝቶ እስኪገለጥ ድረስ የተደበቀ ማለት ነው።
ለምሳሌ አንተ ቤተሰቦችህ ወጥ ሲሰሩ እያየህ ከሆነ ያደከው፣ ወደፊት ላጤ👨‍💼 ስትሆን ሳትወድ በግድህ ወጥ ትሰራለህ😁 ይህ ማለት ቀድሞ ባንተ ውስጥ ተደብቆ የነበረው ወጥ የመስራት እውቀት አሁን ተገለጠ፥ ስለዚህ Latent learning ለዚህ ለዚህ ይጠቅማል።

latent learning is learning that occurs but is not evident in behavior until later, when conditions for its appearance are favorable

2. Insight Learning

It is a cognitive process where by we reorganize our perception of a problem.
It doesn't depend on conditioning of particular behaviors for its occurrence.

ይህ ማለት ደግሞ ሞካክረን ያቃተን ነገር ግን በድንገት በአንድ ጊዜ መፍትሄውን ስናገኝ ነው።
ለምሳሌ ቀን ላይ አጥንተህ አጥንተህ🥵 ያልገባህ ነገር ለሊት ተነስተህ ስታጠናው በአንዴው ከገባህ፦ "aha😃 እንዲህ ነው እንዴ ምናምን ብለህ...ይህ Insight learning ይባላል።

Human beings who solve a problem insightfully usually experience a good feeling called an 'aha' experience.

የዛሬውን በዚህ አበቃን!
ሰላም ሁኑ! ደግሞም አንብቡ!

All Rights Reserved!
©A+ Tutorial Class
1
curs after some average number of responses but the number varies from reinforcement to reinforcement.
ይሄ ደግሞ እንደየResponsኡ የሚያበረታታው ነገር (reinforcer) የተለያየ ሲሆን ነው። ለምሳሌ ልብሱን👕 ባመረቱ ቁጥረ ዛሬ 2dollar ከሰጧቸው ሌላ ቀን ደግሞ የሚጨምር ወይም የሚቀንስ ወጋ መክፈል፣ አንደዚህ ሲሆን አሁን አሪፍ ነው።

3⃣Fixed- Interval Schedule- occurs only if a fixed amount of time has passed since the previous reinforcer.
ለምሳሌ የመንግስት ሰራተኞች ለሚሰሩት ስራ ደሞዝ (reinforcer) የሚከፈላቸው በየወሩ በቀን 25 ከሆነ ይሄ Fixed interval ነው።

4⃣Variable- Interval Schedule- occurs only if a variable amount of time has passed since the previous reinforcer.
ይሄም ደግሞ ለምሳሌ ደሞዝ ዛሬ ተከፍሏቸው ከዚያ የዛሬ ሶስት ሳምንት ከተከፈላቸው፣ ከዚያ ደግሞ በሁለት ሳምንት ምናምን እያለ በተለያለ ሰዓት ከተከፈላቸው ነው።

❗️የአራቱን ልዩነት አያቹ አ
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የreinforcer ልዩነት ላይ ነው የተመሠረቱት
የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ደግሞ የሰዓት ልዩነተ ላይ ነው

🔖Punishment
Is a stimulus that weakens the response or makes it less likely to occur again.
ቅጣት አንድ መጥፎ ነገር ደግመን እንዳናደርግ የሚያደርገን ነገር ነው።

Like reinforcers, punishers can also be primary or secondary.

➨Primary punishers: such as pain, extreme heat, cold and the like are inherently punishing.

➨Secondary punishers: such as Criticism, demerits, bad grades,...

Both primary and secondary punishers can be positive or negative.

Positive punishment ማለትም አንድ ሰው መጥፎ ባህሪ ካለው ያንን ባህሪውን እንዲያቆም መልሰን መጥፎና ያልተገባ ነገር ስናደርግበት ነው።

➨Negative punishment
ማለትም ያ ሰው ያንን መጥፎ ባህሪውን እንዲተው የሚወደውን ነገር ስንቀማው ነው።

The pros and cons of Punishment

ያው የReinforcement እና
Punishment ልዩነት ገብቷቿላ።
በአጭሩ Reinforcement የሚፈለግን ባህሪ ለማምጣት ሲሆን Punishment ማለት ደግሞ የማይፈለግን ባህሪ ለማጥፋት ነው።

Advantage And DisAdvantage of Punishment

📝Immediacy: When punishment follows immediately after the behavior to be punished.
ልክ የማይፈለገው ባህሪ እንደተከሰተ መቅጣት ማለት ነው፣ ለምሳሌ አባት ልጁ እንደሰረቀ ካወቀ ቶሎ ሲቀጣው ማለት ነው።

📝Consistency: When punishment is inconsistent the behavior being punished is intermittently reinforced and therefore becomes resistant to extinction.
ይሄ ደግሞ ቅጣቱ ቀጣይነት ያለው ካልሆነ እንደ ሽልማት ሊቆጠር ይችላል። ማለትም ሌባ ሰርቆ ካልጠቀጣ ወይም አንዴ ተቀጥቶ ሌላ ጊዜ ሚተው ከሆነ እንደ ጥሩ ቆጥሮት ሌብነቱን ሊቀጥል ይችላል። ስለዚህ Punishment ቀጣይነት ያለው (consistent) መሆን አለበት።

📝Intensity: In general terms severe punishments are more effective than mild ones.
አንዳንድ ጊዜ ቀለል ካሉ ቅጣቶች ይልቅ ከበድ የሚሉ የተሻሉ ናቸው፣ እንደየ ሁኔታው።

ጥቂት የPunishment disadvantage ደግሞ እንይ እስኪ👇👇👇

📍Most behavior is hard to punish immediately.
📍People often administer punishment inappropriately or mindlessly.
📍The effectiveness of punishment is often temporary, depending heavily on the presence of the punishing person or circumstances
📍The recipient of punishment often responds with anxiety, fear..

Shaping

🌷Shaping is an operant conditioning procedure in which successive approximations of a desired response are reinforced.
Shaping ማለት ደግሞ ያን የሚፈለገውን ባህሪ ለማምጣት በዚያ ሰው ላይ ለውጥ እየታየ በመጣ ቁጥር እያበረታቱ መምጣት ነው። ሌባው ሌብነቱ እየተወ በመጣ ቁጥር በርታ፣ ጎበዝ እያልን reinforce የምናደርግበት Process ነው Shaping የሚባለው።

🌱The responses that you reinforce on the way to the final one are called successive approximations.

Application of the theory of operant conditioning

1. Conditioning study behavior
እዚህ ስር አሁን ለምሳሌ፣ ቅድም ያየናቸው የreinforcement schedules Apply ሊደረግ ይችላል ማለትም ለምሳሌ አስተማሪው Variable-interval እየተጠቀመ ፈተና ቢፈትን፣ ተማሪዎቹ በጥናታቸው ሁሌ ዝግጁ ይሆናሉ።

2. Conditioning group behavior
እዚህጋ ደግሞ ለምሳሌ ተማሪ አስተማሪውን ቢሰድብ ለአስተማሪው ጥሩ ስሜት አይሰጠውም! ግን ክላስ ውስጥ ሲሳተፍ ምናምን አስተማሪው ደስ ይሏል። (ማለትም Reinforced ይሆናል) ስለዚህ Operant conditioning ለዚህ ለዚህ ጠቃሚ ነው።

3. Managing Problem Behavior
Operant conditioning is a behavior therapy technique that shape students behavior. To do this, teachers should admit positive contingencies like praise, encouragement etc. for learning.

እና Operant Conditioning እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ነገሮች👇 ላይም Apply ሊደረግ ይችላል [ማለትም ለብዙ ነገር ጥቅም ይኖረዋል]

4. Conditioning and Cognitive Processes
5. Shaping Complex Behavior
6. Conditioning and classroom behavior

Social Learning Theory (observational learning) theory

🖱According to Bandura, a major part of human learning consists of observational learning, which is learning by watching the behavior of another person, or the model.

ይሄ Theory ከስሙ እንደምትረዱት፣ አብዛኛው ሰው ለመማር የሚጠቀምበት የመማር አይነት
Operant Conditioning Theory

The term "operant" emphasizes this point:
The organism operates on its environment to produce a desirable result.
ወይም በአጭሩ "Operant" ማለት "Response" /ምላሽ ነው ማለት እንችላለን።

🌷Operant conditioning is learning in which a voluntary response is strengthened or weakened, depending on its favorable or unfavorable consequences.
መጀመሪያ ላይ እንዳየነው Classical conditioning Involuntary ነበር Operant ግን Voluntary ነው፣ ማለትም አስበንበት የምንሸጠው ምላሽ ነው። ለምሳሌ አንድ ተማሪ ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚያሸልም ካወቀ በደንብ ሊያጠና ይችላል። አያችሁ አ ለመሸለም🏆 ለሚለው Consequence በደንብ ማጥናት የሚለውን ምላሽ ነው የሰጠው። ከዚያ በደንብ እያጠና በመጣ ቁጥር Behaviourኡ እየተለወጠ ሊመጣ ይችላል። ይህ አይነቱ የLearning type Operant Conditioning ይባላል።

The behaviour is followed by a consequence, and the nature of the consequence modifies the organisms tendency to repeat the behaviour in the future.

Classical ላይ እንደምሳሌ Pavlov Experiment ማየታችን ይታወሳል፣ እዚህጋ ደግሞ የSkinner Analysis [B.F Skinner was American Psychologist] እናያለን።

Skinner ምን አለ መሰላች የሰውን ባህሪ ለማወቅ የዚያን ሰው ውጫዊ የባህሪው ምንጭ እንጂ የውስጡን የባህሪ ውጤት ማወቅ የለብንም! ቆይ በኃላ በምሳሌ ነግራቿለው!
"To explain behavior, he said, we should look outside the individual, not inside."

In Skinner‘s analysis, a response (operant) can lead to three types of consequences:

📍 a neutral consequence
📍 a reinforcement
📍 a punishment.

🔖A neutral Consequence is the consequence that does not alter the response. ውጤቱ ለምላሻችን ምንም አይነት አስታዋፆ ከሌለው።
ለምሳሌ የሆነ ነገር ሰርተህ ሰርተህ ምንም አይነተ encourage ወይም discourage የሚያደርግ ውጤት ሳታይ ስትቀር።😶

🔖 A reinforcement is the consequence that strengthens the response or makes it more likely to recur. ለምሳሌ አንድ ተማሪ በደንብ አጥንቶ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ከተሸለመ፣ እና ሽልማቱ ከጣመው🥰#ደጋግሞ_ያጠናል

There are two basic types of reinforcers or reinforcing stimuli.

➨Primary reinforcers: is in general, have the ability to strengthen a behavior without prior learning. Eg. Food, water, light, comfortable air, etc እነዚህ ነገሮች አንድን ሰው ሊያበረታቱ ይችላሉ።

➨Secondary reinforcers: These reinforce behavior because of their prior association with primary reinforcing stimuli. Eg. Money, praise, applause, good grades, awards, and gold stars are common secondary reinforcers.
እዚህጋ ቅድም ያየነውን የተማሪውንና የሽልማቱን ምሳሌ መውሰድ እንችላለን።

Both primary and secondary reinforcers can be positive or negative.

➨Positive reinforcement is the process whereby presentation of a stimulus makes behavior more likely to occur again. ለምሳሌ አንድ ሰው መልካም ነገር ሰርቶ ከተመሰገነ፣ ያ ምስጋና ያን መልካም ነገር ደጋግሞ እንዲሰራ ሲያደርገው positive reinforcement እንላለን።

➨Negative reinforcement is the process whereby termination of an aversive (የሚያስጠላ) stimulus makes behavior more likely to occur.
ለምሳሌ አንድ ሰው አጥኑ ብሎ
ከጨቀጨቃችሁ፣ ከዚያ ልክ እሺ
ስትሉ ጭቅጭቁ የሚቆም ከሆነ
ጥናታችሁን በደንብ ታጠናላችሁ።
አያቹ አ ጭቅጭቁ አሁን Negative reinforcer ነው😇
ማለትም ጭቅጭቁ በደንብ እንድታጠኑ ያደርጋችኋል።
የሚገርማችሁ እኔ ግን ተቃራኒ ነኝ አጥና ብለው ሲጨቀጭቁኝ ጭራሽ ይብስብኛል🚶‍♂🚶‍♂😁😁

Negative Reinforcementም ለሁለት ይከፈላል። የሚከፋፈል ነገር በዛ አ🤧

➤Escape Conditioning: Behaviour is reinforced by the elimination of expected event from happening
➤Avoidance Conditioning: Behaviour is reinforced by preventing an expected event from happening.

👆ሁለቱም የሚመሳሰሉ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ትንሽ ልዩነት አላቸው። አጥኑ ተብላችሁ ከተጨቀጨቃች፣ ጭቅጭቁን አስወግዳችሁ በደንብ ምታጠኑበት ሁለት መንገድ አለ፣ የመጀመሪያው እሺ🙏 ማለት ነው [Escape]..ሁለተኛው አትጨቅጭቁኝ😡 ማለት ነው [Avoidance]

Schedules of reinforcement

🔖When a response is first acquired, learning is usually most rapid if the response is reinforced each time it occurs. This procedure is called continuous reinforcement.
ለምሳሌ፦ ጎበዙ ተማሪ ሁሌ ከፍተኛ ውጤት ባመጣ ቁጥር ሲሸለም በደንብ እያጠና ይመጣል። ግን ከተደጋገመና ሽልማቱን ከለመደው😐 የልጁ በደንብ የማጥናት ልማድ እየቀነሰ ይመጣል።

🔖 If it is rewarded on an intermittent (partial) schedule of reinforcement, which involves reinforcing only some responses, not all of them. This is called intermittent reinforcement.
ይሄ ደግሞ ተማሪዉ ሁሌ ከፍተኛ ውጤት ባመጣ ቁጥር አለመሸለም፣ አልፎ አልፎ ማድረግ።

There are four types of intermittent schedules.

1⃣Fixed-ratio schedules- Occurs after a fixed number of responses. It produces high rate of responding.
ይሄ ደግሞ ለምሳሌ የልብስ ፋብሪካ ውስጥ ሰራተኞቹ አንድ ልብስ👕 ባመረቱ ቁጥር (response) 2Dollar (reinforcer) ሲከፈላቸው፣ ነገር ግን በጣም ብዙ ካመረቱ ብዙ ብር ስለሚያገኙ😋 ስራቸው ሊቀንስ ይችላል።

2⃣Variable-Ratio Schedule- Oc
Channel name was changed to «ልዩ ነው ይመቻል 👌👌»
Channel name was changed to «G---Tutorial ልዩ ነው ይመቻል 👌👌»
Channel name was changed to «G---Tutorial ይመቻል 👌👌»
📚CHAPTER 4

📖MEMORY AND FORGETTING

ባለፈው ትምህርታችን ስለ Learning መማራችን ይታወሳል፣ አሁን ደግሞ ከእሱጋ ተያያዥነት ያለውን Memory🧠 and Forgetting🤦🏼‍♂ እናያለን።

በዚህ ቻፕተር ስር የምናየው👇

📖Memory
📍Meaning and Processes of Memory
📍Stages/Structure of Memory
📍Factors Affecting Memory

📖Forgetting
📍Meaning and Concepts of Forgetting
📍Theories of Forgetting

በዚህ ምዕራፍ ስር እንግዲህ የማስታወስ ችግር ያለባችሁ ምናምን ትፈወሳላችሁ😎😁
በደንብ አንብባችሁ ተግባራዊ ብታደርጉት በጣም ይጠቅሟቸዋል።

📔Meaning and Processes of Memory

📌Memory is the retention of information/what is learned earlier over time. It is the way in which we record the past for later use in the present.

Memory ማለት እንደምታውቁት "ትውስታ" እንደማለት ነው። ትውስታ ማለትስ ምን ማለት ነው?😁 ከላይ ያለውን ደግማችሁ አንብቡት!

አሁን ቀጥለን ስለ Memory Processኦች እና ስለ Memory Structure እናያለን።

The processes of Memory

📌Are the mental activities we perform to put information into memory, to keep it there, and to make use of it later.
አብዛኛውን ጊዜ ሳይኮሎጂስቶች የMemoryን Nature ከComputer🖥ጋር አያይዘው ያዩታል። ሶስቱ የMemory ሂደቶች፤ አንድ ነገር ለማስታወስ ነገሩ በሚከተሉት ሂደት ውስጥ ያልፋል።

1⃣Encoding: In encoding we transform a sensory input into a form or a memory code that can be further processed.
ይሄ ከውጪ የመጣው Information ቀጥታ ወደ አይምሮ ሄዶ Useable በሆነ form የሚቀመጥበት ነው።

2⃣Storage: Is a location in memory system in which material is saved. Storage is the persistence of information in memory.
ይሄ ደግሞ encode የተደረገው Information የሚቆይበት የአይምሮ ክፍል ነው።

3⃣Retrieval: This is the point at which the material in memory storage is located, brought into awareness and used.
ይሄ Stored የሆነውን information አስታውሰን፣ የምንጠቀምበት የመጨረሻው ሂደት ነው።

ስለዚህ በቀላሉ Memoryን እንዲህ👇 ማብራራት እንችላለን።

"Memory is the process by which information is encoded (phase1), stored (phase 2) and later retrieved (phase 3)."

Structure of Memory

📌Memory structure is the nature of memory storage itself- how information
🔖Is represented in memory
🔖How long it lasts
🔖How it is organized
ያው እኛ በተለምዶ memoryን ወይም ማስታወስን ቀለል አድርገን እናዩዋለን እንጂ Memory structure ትንሽ ከበድ ይላል፣ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩ ሶስት ነገሮችን ያጠቃልላል።

Like computer, we also store vast amounts of information in our memory storehouse.
ከstorehouseኡ አውጥተን ነው እንግዲህ mental screen ላይ display የምናደርገው። ማለትም ነገሩን በ ህሊናችን እናውቀዋለን።
በእንደዚህ👆 አይነት መልኩ ብዙ የmemory structure ሞዴሎች ተመስርቷል።

One of the most important and influential of these is the one developed by Richard Atkinson and Richard Shiffrin (1968). According to Atkinson and Shiffrin, memory has three structures.

1) Sensory Memory
👉It is the entry way to memory. It is the first information storage area.
እዚህጋ አንድ ያያቹት (Iconic memory) ነገር storage ውስጥ የሚቆየው ቢበዛ ለአንድ በሰከንድ🕧 ነው።
የሰማችሁት ነገር (Echonic memory) ደግሞ ቢበዛ ለሁለት ሰከንድ storageኡ ውስጥ ይቆያል።

ስለዚህ በSensory memory ውስጥ save ያደረግነው ነገር ብዙ አይቆይም ነገር ግን attention👀 ከሰጠነው ትንሽ ይቆያል [ማለትም ወደ 2ተኛው👇 memory/storage ይተላለፋል]

2) Short-term Memory: is part of our memory that holds the contents of our attention.
🔸STM is important in a variety of tasks such as thinking, reading, speaking, and problem solving.
አያችሁ የዚህ Memory ጥቅሙ ከመጀመሪያው የተሻለ ነው። ለምሳሌ ስታስቡ፣ ስታነቡ፣ ስታወሩ ምናምን informationኡ Save የሚሆነው በዚህ Memory ውስጥ ነው።
🔸ይሄ memory ሌሎች የተለያዩ ስሞች አሉት።
📌Working memory
📌 Immediate memory
📌 Active memory
📌 Primary memory

STM is distinguished by four characteristics

📍It is active- information remains in STM only so long as the person is consciously processing, examining, or manipulating it. ይሄ Active ነው ማለትም እንደ sensory memory ለአንድ ወይም ሁለት ሰከንድ ብቻ አይደለም የሚቆየው።

📍Rapid accessibility - Information in STM is readily available for use. በውስጣችሁ ያለውን information ቶሎ አውጥታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ፤ ይሄ ከlong term memory የተሻለ ያደርገዋል።

📍Preserves the temporal sequence of information- mean that STM keeps the information fresh until it goes to further analysis and stored in LTM in meaningful way. ይሄኛው ባህሪ ደግሞ Store ያደረግነው information Fresh ሆኖ ይቀመጣል ይላል።

📍Limited capacity
Short-term memory is a limited - capacity store that can maintain unrehearsed information up to 30 seconds.
አያቹአ ይሄ memory በጣም ያልተለማመድነው ወይም ብዙ ትኩረት ያልሰጠነው ነገር እስከ 30ሰከንድ በዚህ (STM) ውስጥ ሊቆይ ይችላል።

Capacity:
“The magic number” (George Miller)
Humans have the ability to retain 7 + -2 items of information (in adults).
ይሄ George Miller የተባለው ሰውዬ አንድ ወጣት ሰው በውስጡ ከ5 እስከ 9 የሚጠጉ ነገሮችን የመያዝ አቅም አለው ይላል።

People can group information in ways to expand their short-term memory capacity called “Chunking.”

“Chunking” allows for easier encoding.
እስኪ የሚከተለውን ምሳሌ እንመልከት
285566297488
ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ቁጥር ሲሰጠን ለመያዝ እንዲቀለን በchunking ከፋፍለን ነው ምንይዘው ማለትም👇
285 566 297 488

ልክ እንደዚህ ማለት ነው😎

3. Long Term Memory

It is a memory system used for the relatively permanent storage of meaningful information.
እስኪ እስካሁን ከአይምሮአችሁ ያልጠፋውን ወደፊትም probably ሊጠፋ የማይችል ብላችሁ የምታስቡት ነገር አስቡ፣ አአአዎ👍 እሱ አሁን Stored የሆነው በLTM ውስጥ ነው።

LTM stores information for indefinite periods. It may last for days, months, years, or even a lifetime.

The LTM is assumed to be composed of different sub systems.

Declarative/ explicit memory: the conscious recollection of information such as specific facts or events that can be verbally communicated.
It is further subdivided into semantic and episodic memories.

Semantic memory: factual knowledge like the meaning of words, concepts and our ability to do math.

Non-declarative/ implicit memory: One of the most important kinds of implicit memory is procedural memory.
It is the "how to" knowledge of procedures or skills.
ይሄን ከመጀመሪያው ለየት ሚያረገው፣ የመጀመሪያው (declarative) ለምሳሌ ስለ ፀጉር አቆራረጥ የተለያዩ መረጃ ስታገኝ እሱ declarative ስር ነው ሚመደበው፥ ነገር ግን "ፀጉሬን እንዴት ልቆረጥ" ካልን ከዚህኛው (implicit) memory ጋር ነው የሚያያዘው።

Serial Position Effect

📌Occurs when you are introduced to a lot of people at a party and find you can recall the names of the first few people you met and the last, but almost no one in between.

📌That is, recall will be best for items at the beginning of the list (the primacy effect) and at the end of the list (the recency effect).
ይሄኛው ከላይ እንዳነበባችሁት፣ ለምሳሌ👇
John
Merry
Kran
Malin
Dan
ይሄኛው ዝርዝር ስታዩ አብዛኛውን ጊዜ ምታስታውሱት የመጀመሪያውንና የመጨረሻውን ስም ነው፣ ይሄ ነው serial position effect ሚባለው።

Factors Affecting Memory

📍Ability to retain
📍Good health
📍Age of the learner
📍Maturity
📍Sleep or rest, and so on.

Forgetting
ይህን በሚቀጥለው ጊዜ እናያለን።
የግቢ ትምህርት እንዳይደራረብባችሁ መፅሐፋችሁን በደንብ ከስር ከስር አንብቡ!

ሰላም ሁኑልን🙏፣ እንወዳቿለን።

All Rights Reserved!
©A+ Tutorial Class
🙌 ተወዳጆች ሆይ እንዴት ናችሁ በአያሌው‼️

ግቢ እንዴት ነው ትምሮስ

😘From the bottom of our heart ከ መልካም የሆነ ሁሉ ስኬት እንዲያጅባችሁ ምኞታችን ነው‼️

👩‍🏫👨‍🏫 በ ነገሮች አለመመቻቸት ምክንያት ለ ተወሰኑ ሳምንታት የቲቶርያል ትምህርቱ መቋረጡ የሚታወቅ ነው።

🙋‍♂🙋‍♀ እናንተም በውስጥ መስመር ትምህርቱ እንዲቀጥል ጥያቄዎችን ስታቀርቡ ነበር። ብር እንጨምር እና ትምህርቱ ይቀጥል ያላችሁም አላችሁ። ብር መጨመሩ ን ሳይሆን የምንፈልገው የምንለቅላችሁ ኖት እንዲገባችሁ ፡ ለፈተና ም እንዲያግዛችሁ ፡ A+ እንዲታመጡ እና internalize እንድታደርጉት ነው።

🙏 ምንም እንኳ እናንተን ማስተማር ባይገባንም አቅማችን በፈቀደ ፡ ሁሉ ለመርዳት ዝግጁ ነን።

👩‍💼👨‍💼 ከሰሞኑ የቲቶርያል ትምህርቱን ካቆምንበት እንደምንጀምር ስናበስራችሁ ፡ አራት ይዞ አምስት በማያጠፋ ታላቅ ሀሴት ነው።

ከሰሞኑ ይጠብቁን‼️

ተወዳጆች ሆይ ምን አልባት የመጀመሪያዎቹን quizzes or tests በምትፈልጉት መልኩ ላትሰሩ ትችላላችሁ። በዚህ ብዙም frustration አይሰማችሁ።

🤷‍♂ ከእናንተ የሚጠበቀው ብልጥ መሆን ብቻ ነው። የመምህሮቹን የፈተና አወጣጥ ስነ ልቦና መረዳት ብቻ ነው🤷‍♀

🤔 እስቲ የተሰጣችሁት course outline ላይ objectives ተመልከቷቸው❗️በየ unit ቶቹ ያሉትን subtopic ተመልከቷቸው❗️ that is it😉

A+ can be merely caught ‼️

©A+ tutorial class.
👉 እንስሳቶች cell wall አላቸው። ይህ ማለት ግን cell wall ያላቸው በሙሉ እንስሳት ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህ ውሻ cell wall አለው ማለት የግድ እንስሳት ነው ማለት አይደለም፡ ምክንያቱም cell wall ያላቸው በሙሉ እንስሳት ናቸው ማለት ስላላደለ። ስለዚህ invalid
ነው።

👆 ስለዚህ አንድ deductive argument በነባራዊው አለም false premises እና true conclusion ኑሮት invalid argument መሆን ይችላል።

📚 False premises and false conclusion.

ማስረጃዎቹ(premises) በነባራዊው አለም ውሸት ሁነው እንዲሁም conclusion ኑ በነባራዊው አለም ውሸት ሁኖ argument ቱ valid ሊሆን ይችላል ወይም invalid ሊሆን ይችላል። ምሳሌ

🌀 Example 1

All human beings are immortal.
Plants are human beings.
Therefore, plants are immortal.

👆Valid ነው።

🌀Example 2

All human beings are immortal.
Cats are immortal.
Therefore, cats are human beings.

👆 Invalid ነው።


📚Soundness

There are two types of deductive arguments.

📍1) Sound deductive argument or sound argument.

📍2) Unsound deductive argument or unsound argument.

ስለዚህ deductive argument ን sound እና unsound ብሎ መክፈል ወይም መፈረጅ soundness ይባላል።

😎 እስቲ ሁለቱንም እንመልከታቸው።

📚 Sound argument - is a type of deductive argument that is valid and has all factually true premises.

Sound argument ማለት argument ቱ valid የሆነ እና ማስረጃዎቹ(premises) በነባራዊው አለም እውነት የሆኑ። ስለዚህ😎

አንድ deductive argument sound ለመባል ሁለት ነገሮችን በተመሳሳይ ጊዜ ማሟላት አለበት።

🎈1ኛ) valid መሆን አለበት
🎈2ኛ) ማስረጃዎቹ(premises) በነባራዊው አለም እውነት መሆን አለበት። ስለዚህ😎

📚 Sound argument = valid argument + true premises.

ምሳሌዎችን እንመልከት፡

🌀Example 1

All planets revolve around the sun.
Earth is a planet.
Therefore, Earth revolves around the sun.

👆 Sound ነው። እንዴት

ምክንያቱም argument ቱ valid ነው እንዲሁም ማስረጃዎቹ(premises) በነባራዊው አለም እውነት ናቸው።

እንዴት valid እንደሆነ ማስረዳት አይጠበቅብኝም ምክንያቱም validity ን ተረድታችሁታል ይመስለኛል።

📚 Unsound argument - is a type of deductive argument that is invalid.

📚 Unsound argument - is a type of deductive argument that is valid but the premises are factually false.

Unsound argument ማለት invalid argument ነው። እንዲሁም

Unsound argument ማለት valid argument ሁኖ ነገር ግን ማስረጃዎቹ(premises) በነባራዊው አለም ውሸት የሆኑ።

🌀 Example 1

All Ethiopians are Egyptians.
Biniyam is an Ethiopian.
Therefore, Biniyam is an Egyptian.

👆 Argument valid ነው ። ነገር ግን All Ethiopians are Egyptians የሚለው premises በነባራዊው አለም ውሸት ነው። ስለዚህ argument ቱ unsound ነው።

🌀Example 2

All human beings are mortal.
Cats are mortal.
Therefore, cats are human beings.

👆 Argument ቱ invalid ነው። ስለዚህ unsound ነው ማለት ነው።

እሺ የዛሬው ክላስ በዚህ አበቃ👐። ለማጠቃለል ያህል፡

📚 Validity is determined by the inferential link between the premises and the conclusion.

📚 Soundness is determined by both the inferential link and the factual link between the premises and the conclusion.

👇👇ከታች ፎቶ ለቅቄላችሗለሁ።

©A+ tutorial class.
😊 አሁን ደግሞ validity በ actual truth or falsity of the premises and the conclusion እንደማይወሰን እንመልከት።

📚 True premises and true conclusion.

🌷 በ ነባራዊው አለም እውነት የሆኑ premises እና በ ነባራዊው አለም እውነት የሆነ conclusion የያዘ deductive argument valid ሊሆን ይችላል ወይም invalid ሊሆን ይችላል። እስቲ ምሳሌዎችን እንመልከት ፡

🌀Example 1

All human beings are mortal. Pr.minister Abiy Ahmed is a human being. It follows that pr.minister Abiy Ahmed is mortal.

ተመልከቱ ይህን ምሳሌ🥺

All human beings are mortal እና Pr.Minister Abiy Ahmed is a human being የሚሉት ማስረጃዎች ወይም premises ናቸው። ሁለቱም ማስረጃዎች በ ነባራዊው አለም እውነት ናቸው።

Pr.Minister Abiy Ahmed is Mortal የሚለው conclusion በነባራዊው አለም እውነት ነው።

😊 ስለዚህ Argument ቱ በነባራዊው አለም true premises እና true conclusion ነው ያለው።

😎 Argument ቱ valid ነው ወይስ invalid ነው

😋 Valid ነው። እንዴት

👉ሁሉም የሰው ልጆች ሟች ከሆኑ።
👉ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰው ከሆነ።
👉ስለዚህ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሟች ነው።

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሟች ነው የሚለው conclusion ውሸት መሆን አይችልም። ምክንያቱም አብይ አህመድ በ ሁሉም የ ሰው ልጆች ውስጥ ነው የሚካተተው። ሁሉም የሰው ልጆች ደግሞ ሟች ናቸው።

👆ስለዚህ አንድ Deductive argument በነባራዊው አለም true premises እና true conclusion ኑሮት valid መሆን ይችላል።

🙌 እሺ አሁን ደግሞ deductive argument በ ነባራዊው አለም true premises እና true conclusion ኑሮት invalid መሆን እንደሚችል እንመልከት።

🌀Example 2

All beers are beverages. ዳሽን ቢራ is a beverage. Therefore, ዳሽን ቢራ is a beer.

All beers are beverages እና ዳሽን ቢራ is a beverage የሚሉት premises በነባራዊው አለም እውነት ናቸው።

ዳሽን ቢራ is a beer የሚለው conclusion በነባራዊ አለም እውነት ነው።

😊 ስለዚህ argument ቱ በነባራዊው አለም true premises እና true conclusion ነው ያለው።

😟 Argument ቱ valid ነው ወይስ invalid ነው

😎 invalid ነው። እንዴት

እዚጋ የሚያምታታ ይመስላል። ቡሗላ ላይ ፎርሙላውን እነግራችሗለሁ። ለአሁኑ እስቲ እንዲሁ እናብራራው። ተመልከቱ

👉 ሁሉም ቢራዎች መጠጦች ናቸው። ይህ ማለት ግን ሁሉም መጠጦች ቢራ ናቸው ማለት አይደለም።
👉 ዳሽን ቢራ መጠጥ ነው። ታዲያ ዳሽን ቢራ የተባለው መጠጥ ቢራ ላይሆን ይችላል ምክንያቱም ሁሉም ቢራዎች መጠጥ ናቸው እንጂ ሁሉም መጠጦች ቢራ ስላልሆኑ።

👉 ስለዚህ ዳሽን ቢራ is a beer የሚለው conclusion ውሸት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ invalid ነው።

😂 በ ነባራዊው አለም እኮ ዳሽን ቢራ እኮ ቢራ ነው🙄። ግን validity የሚወሰነው በ premises እና በ conclusion መካከል ባለው የምክንያታዊነት ዝምድና ነው እንጂ premises እና conclusion ባላቸው ነባራዊ እውነታ አይደለም።

👆ስለዚህ አንድ deductive argument በነባራዊው አለም true premises እና true conclusion ኑሮት argument ቱ invalid መሆን ይችላል።

📚 True premises and false conclusion.

😊 እሺ አሁን ደግሞ በ ነባራዊው አለም ማስረጃዎቹ(premises) እውነት የሆኑ እና conclusion ኑ ውሸት የሆነ deductive argument ን እንመልከት።

አንድ deductive argument በነባራዊው አለም ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው: በነባራዊው አለም ደግሞ conclusion ኑ ውሸት ከሆነ argument ቱ ሁልጊዜም ቢሆን invalid ነው። valid መሆን አይችልም።

👆ያዙት ፈተና ላይ ስለሚወጣ።

እስቲ ምሳሌ እንመልከት።

🌀Example

All beers are beverages.
Coca Cola is a beverage.
Therefore, Coca Cola is a beer.

👆 በነባራዊው አለም true premises እና false conclusion ነው ያለው። invalid ነው።

📚 False premises and true conclusion.

⭐️ በነባራዊው አለም ውሸት የሆነ premises እና በነባራዊው አለም እውነት የሆነ conclusion የያዘ deductive argument valid ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ invalid ሊሆን ይችላል። እስቲ ምሳሌዎችን እንመልከት።

🌀Example 1

human being is not mammal.
Hens are human beings.
Therefore, Hens are not mammals.

🥺 አሁን ተመልከቱ

😊 All human beings are not mammals እና Hens are human beings የሚሉት premises ናቸው። ሁለቱም በነባራዊው አለም ውሸት ናቸው ምክንያቱም የሰው ልጅ አጥቢ ነው እና ደግሞ ዶሮ ሰው አይደለም😂

Hens are not mammals የሚለው conclusion ደግሞ በነባራዊው አለም እውነት ነው። ምክንያቱም ዶሮ አጥቢ አይደሉም።

🤔 ታዲያ Argument ቱ valid ነው ወይስ invalid

😎 Valid ነው። እንዴት🤔

ተመልከቱ ፡

👉 የሰው ልጅ አጥቢ አይደለም።
👉 ዶሮ የ ሰው ልጅ ናት።
👉 ስለዚህ ዶሮ አጥቢ አይደለችም።

😊 ዶሮ አጥቢ አይደለችም የሚለው conclusion ውሸት መሆን አይችልም። ምክንያቱም ዶሮ የሰው ልጅ ናት ፡ የሰው ልጅ ደግሞ አጥቢ አይደለም ፡ ስለዚህ ዶሮ አጥቢ አይደለችም።

👆 ስለዚህ አንድ deductive argument በነባራዊ አለም false premises እና true conclusion ኑሮት valid መሆን ይችላል።

🤗 እሺ አሁን ደግሞ አንድ deductive argument በነባራዊው አለም false premises እና true conclusion ኑሮት invalid መሆን እንደሚችል እንመልከት።

🌀Example 2

Animals have cell wall.
Dogs have cell wall.
Therefore, dogs are animals.

Animals have cell wall እና dogs have cell wall የሚሉት premise ናቸው። ሁሉቱም በነባራዊው አለም ውሸት ናቸው። ምክንያቱም እንስሳቶች ውሻን ጨምሮ cell wall የላቸውም።

Dogs are animals የሚለው conclusion በነባራዊው አለም እውነት ነው።

ታዲያ argument ቱ valid or invalid

😊 Invalid ነው። እንዴት

Dogs are animals የሚለው conclusion ውሸት መሆን ይችላል። ምክንያቱም ፡