. ──•◈•─────•◈•─
“በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምሻው የለኝም።”
መዝሙር 73፥25 (አዲሱ መ.ት)

"...መንፈሴም በመካከላችሁ ይሆናልና አትፍሩ።"
(ሐጌ 2፥5 አመት)
(ሐጌ 2፥5 አመት)
2ኛ ቆሮንቶስ 5
14: ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤
እግዚአብሔር ባዶ ቃል የለውም። ንግግሩና ተስፋው ማንነቱንና ህልውናውን ይይዛል። ከምርኮ የተመለሰው ሕዝብ ፍርስራሹን ገና ወደ ሕንጻ ባልቀየረበትና የሚሠራው መቅደሱ ከፊተኛው ጋራ ሲነጻጸር አንሶ በታየበት ጊዜ ለመሪዎቹና ሕዝቡ እንዲህ አላቸው፤ "መንፈሴም በመካከላችሁ ይሆናልና አትፍሩ" (ሐጌ 2፥5)። ለእግዚአብሔር የቀና ሕዝብ ብቻውን አይተውም። የማይታየው ህልውናውና አብሮነቱም ልብን ያሳርፋል፤ እጆችንም ያበረታል።

❤1
ፀሎት
እግዚአብሔር የሰዎችን ዓይንና አእምሮ ለእውነት
እንዲከፍት፣ መንፈሳዊ ዕውርነትንም ከአእምሮአቸው ላይ
እንዲያስወግድ ጠይቁት።
እግዚአብሔር ሊያሳይዎት የሚፈልገውን ነገር ያዩ ዘንድ
የእርስዎን ዓይኖች እንዲከፍት ይለምኑት። የጠላትንም
(የሰይጣንን) ተንኮልና ውሸት ለይተው እንዲያውቁ ይጸልዩ።
ከእግዚአብሔር የሆነውንና ያልሆነውን ለይተው ማወቅ
እንዲችሉ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት (በእግዚአብሔር ቃል)
ውስጥ ሥር የሰደዱ ለመሆን ጸልዩ።
በዙሪያዎ ያለውን አካባቢና የሚያገኟቸውን ሰዎች በትኩረት
ለመመልከት ዓይኖችዎን ክፍት ያድርጉ። ለአንድ የተወሰነ ሰው
ወይም ስፍራ እንድትጸልዩ ሊመራዎት ለሚችለው ለሕያው
መንፈስ ቅዱስ ዘወትር ንቁና ጆሮአችሁ የተከፈተ ይሁን
እግዚአብሔር የሰዎችን ዓይንና አእምሮ ለእውነት
እንዲከፍት፣ መንፈሳዊ ዕውርነትንም ከአእምሮአቸው ላይ
እንዲያስወግድ ጠይቁት።
እግዚአብሔር ሊያሳይዎት የሚፈልገውን ነገር ያዩ ዘንድ
የእርስዎን ዓይኖች እንዲከፍት ይለምኑት። የጠላትንም
(የሰይጣንን) ተንኮልና ውሸት ለይተው እንዲያውቁ ይጸልዩ።
ከእግዚአብሔር የሆነውንና ያልሆነውን ለይተው ማወቅ
እንዲችሉ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት (በእግዚአብሔር ቃል)
ውስጥ ሥር የሰደዱ ለመሆን ጸልዩ።
በዙሪያዎ ያለውን አካባቢና የሚያገኟቸውን ሰዎች በትኩረት
ለመመልከት ዓይኖችዎን ክፍት ያድርጉ። ለአንድ የተወሰነ ሰው
ወይም ስፍራ እንድትጸልዩ ሊመራዎት ለሚችለው ለሕያው
መንፈስ ቅዱስ ዘወትር ንቁና ጆሮአችሁ የተከፈተ ይሁን
በቤተክርስቲያን ውስጥ መደረግ የሌለባቸው 11 ወርቃማ ህጎች
ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቅዱስ ስፍራ ነው፣ በቤቱ ስርአትና አክብሮት ሊኖር ይገባል!
1. ፕሮግራም አታርፍድ ⏰ እግዚአብሔር ለቀጠሮው አይዘገይም፤ አንተስ ለምን ታረፍዳለህ? በጊዜ መገኘት በረከትን ቀድሞ መቋደስ ነው። 📖 "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" (መዝሙር 122:1)
2. ድምፅህን ጠብቅ፤ አታውራ 🗣️ በአምልኮና በትምህርት ሰዓት ወሬና ጨዋታ ለእግዚአብሔር ቤት አይመጥንም። ስፍራው የዝምታና የጸሎት ነው። 📖 "ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌሶን 4:29)
3. ስልክህን እረፍት ስጠው 📱 በስብከት ወቅት ሶሻል ሚዲያ መጠቀምና ስልክ መነካካት መንፈሳዊ ትኩረትን ይሰርቃል። ስልክህ ሲደወልም አንስተህ አታውራ፤ ቅዱሱን ድባብ አታናጋ። 📖 "በላይ ያለውን አስቡ" (ቆላስይስ 3:2)
4. አለባበስህ ስርአት ይኑረው 👗 ሰውነትን ገልጦ የሚያሳይና ሌሎችን ለፈተና የሚዳርግ አለባበስ ከቤተክርስቲያን ቅድስና ጋር አይሄድም። ይህ ወንዶችንም ይመለከታል።
📖 "ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን" (1 ቆሮንቶስ 14:40)
5. አትተኛ፤ ንቃ! 😴 ቤተክርስቲያን የመንፈስ መታደሻ እንጂ መኝታ ቤት አይደለችም። ንቁ ሆነህ ቃሉን ተከታተል። 📖 "አንተ የምትተኛ ንቃ..." (ኤፌሶን 5:14)
6. ተመልካች ብቻ አትሁን፤ በመንፈስ ተሳተፍ 👀🔥 ሌሎች ሲያመልኩና በረከት ሲቀበሉ አንተ ዝም ብለህ አትመልከት። ዘምር፣ አምልክ፣ ስገድ፤ በመንፈስና በእውነት ከፈጣሪህ ጋር ተገናኝ። 📖 "እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።" (ዮሐንስ 4:24)
7. ቂም ይዘህ አትቆም ቂም ይዘህ አትጸልይ! ልብህ በቂምና በነገር ተሞልቶ አምልኮ የለም። አስቀድመህ ለበደሉህ ይቅርታ አድርግ፤ በንጹህ ልብም ፊትህ ቁም። 📖 "አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ" (ማቴዎስ 5:24)
8. ተስፋ ሰንቀህ ቅረብ ከእግዚአብሔር እጅ አንድ ነገር እንደምትቀበል አምነህ ሂድ። የምትጠብቀው ነገር ከሌለ የምታገኘውም አይኖርም። 📖 "አፍህን በሰፊው ክፈት እኔም እሞላዋለሁ" (መዝሙር 81:10)
9. አገልጋዮችን አታቅልል 🙅♂️
ከአገልጋዮች ጋር ባለህ መቀራረብ የተነሳ ቅጥ የሌለው ድፍረት አታሳይ። የእግዚአብሔርን ቅቡዓን ማክበር ለራስህ ስኬት መቆለፊያ ነው። 📖 "የቀባሁትን አትንካ" (መዝሙር 105:15)
10. ለዲያቆናትና ለአገልጋዮች ታዘዝ 🙏 ዲያቆናት የሚተጉት ስርአትን ለማስጠበቅና አንተን ለማገልገል ነው። ትህትናንና ትብብርን አሳያቸው። 📖 "ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ..." (1ኛ ጴጥሮስ 2:17)
11. ፕሮግራም ሳያልቅ አትውጣ በጸሎትና በስብከት መሃል ጥሎ መውጣት ስርአተ አልበኝነትና ሌላውን መረበሽ ነው። እስከ መጨረሻው ታግሰህ በረከቱን ይዘህ ውጣ።
📖 "ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ" (መክብብ 5:1)

🔥1
‟የወለደህን አባትህን አድምጥ፤ እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት። እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ገንዘብህ አድርግ። የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ ጠቢብ ልጅ ያለውም በርሱ ሐሤት ያደርጋል። አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።”
ምሳሌ 23:22-25 NASV
ምሳሌ 23:22-25 NASV
የቆመ ይታያል፤ የጸናም ይዘልቃል። በመሠረታቸው ላይ የታነጹም የክፋት ወዳጅ አይሆኑም፤ ጌታቸውን ያውቃሉ፣ እነርሱም በርሱ የታወቁ ናቸው፤ ዐመፀኞቹን ከእውነተኞቹ ሲለይ፣ ጳውሎስ እንዲህ አለ፤ "ይሁን እንጂ፣ 'ጌታ የርሱ የሆኑትን ያውቃል' ደግሞም፣ 'የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ' የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል" (2ጢሞ 2፥19)። መሠረቱ ግልጽ ነው፤ የምንቀድሰው ስም--"ስምህ ይቀደስ"--የዐመፅ አባሪ አይደለም፤ ቀዳሽ እንጂ። ስሙን ለመጥራት ከዐመፅ መራቅ፣ ስሙንም በመጥራት ዐመፅን ማራቅ!
የመንፈሳዊ : በሽታ ምልክቱ መንፈሳዊ ፡ ጥማት ( ረሃብ) መጥፋት፡ነው
የመንፈሳዊ በሽታ ምልክት መንፈሳዊ ረሃብ/ጥማት መጥፋት ነው።
መንፈሳዊ ጤና መጥፋት የሚታወቀው በእግዚአብሔር ላይ ያለው ጥማትና ረሃብ ሲቀንስ ነው። ሰው ለቃሉ፣ ለጸሎት፣ ለአገልግሎትና ለቅድስና ፍቅር ሲጠፋ፣ መንፈሳዊ “ደዌ” ወይም ድርቀት ይጀምራል። ይህ ምልክት ብዙ ጊዜ ሰውን ወደ ዓለማዊ ነገሮች ማለትም ወደ ፡ገንዘብ፣ ደስታ ከ አለም መፈለግ ፡ እና ልማዶች ላይ ያዘንብላል።