ፍኖተ ሕይወት media
1.89K subscribers
188 photos
31 videos
7 files
269 links
እንኳን ደና መጣችሁ
“ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።”
— ማቴዎስ 18፥20
የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄና መልሶችን፣ኪነ ጥበብ፣ ኦርቶዶክሳዊ ፣ የእመቤታችን ታሪክ እና ዝማሬዎች እያነሳሳን እናመሰግናለን እንወያያለን ሁላችሁም ተሳታፊ እንድትሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን አድ እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን
Download Telegram
ከትንሳኤ በኃላ ያለው
ማክሰኞ (ቶማስ) ይባላል፡ ቶማስ ሐዋርያ ሲሆን፣ ቶማስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው።ከክስቶስ ትንሣኤ በኋላ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች።

አምላከ ቅዱስ ቶማስ አለማመናችንን ይርዳው አሜን በእውነት🙏
1
​​ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤት "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል።

ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?

👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን

የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጎኔን ዳስስ ብሎታል።

ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል። ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው። ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች። እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።

👉 ሰንበትን ሊያጸናልን

የአይሁድ ሰንበት፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት። በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች።

ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች። ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት። እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም። እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ

👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል። በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው።
"ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ"
(ዮሐ20:29)

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት

ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

💚
2
☞ሚያዚያ 15 ቀን የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አንገት ለ 15 አመታት ንስሀ ግብ እያለች ስታስተምር ኖራ ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በኢየሩሳሌም መንደር በዙሪያው መታየት በጀመረ ጊዜም የእግዚአብሔር መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አሰተካክሉ እያለ በበረኃ ይሰብክ ጀመረ፡፡ የይሁዳ የሰማርያ ሰዎች ኹሉ ቅዱስ ዮሐንስ ጥምቀት ወደ ሚያጠምቅበት ሥፍራ ይሔዱ፤ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ ኹሉንም በዮርዳኖስ ወንዝ ያጠምቃቸው ነበር፡፡ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንሥ ልብሱ የግመል ጸጉር ትጥቁም የተታታ ቆዳ ነበር ምግቡም አንቦጣና ጋጃ ማር ነበር፡፡ዳግመኛ ኄሮድስ የወንድሙን የፊልጳስን ሚስት እንዳገባ በሰማ ጊዜ የቅዱስ ዮሐንስ ልብ ተቃጠለ ወደ አንቲጳስ ሄሮድስ ቤተመንግሥት ሔዶ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባሕም ሲል ገሠጸው፡፡ ስለዚህ ነገር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን ተቀየመው አስቀድሞ ግን ቅዱስ ዮሐንስን ስለ ቅድስናው ያከብረው ነበር፡፡ አሁን ግን ሰለወደዳት ዘማዊ ሴት ሰለ ሄሮዳዳ ብሎ ተደፋፎሮ ይዞ በወኀኒ ቤት አሰረው፡፡ በተወለደበት እለት ወለተ ሄሮድያዳ ዘፈነችለት፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ቅድስት ራስ ለመነችው ሰለመሐላው ቅድት የዮሐንስ ራስ ይሰጣት ዘንድ ወደደ በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ የከበረ የዋህ ነቢይ ዮሐንስን ከሚያስገድል ለሄሮድስ መሐላውን ቢተው በተሻለው ነበር፡፡ ሰለዚህ ርጉምና የረከሰ ሄሮድስ ወታደሮቹን ላከ፡፡ ወታደሮቹም በሰይፍ የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ቆረጡ፡፡ ራሱንም በወጭት አድርገው በንጉሡ አዳራሽ በተቀመጡ አለቆች መኳንንትና ሠራዊቱ መከከል አመጡት፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ አንገት በተቁረጠች ጊዜ ዓይኖቹ ተገልጠው ፊቱም እንደ ፀሀይ ያበራ ነበር፡፡ መልካም መዓዛም ከርሱ የወጣ ነበር፡፡ ይህቺ ኄርድያዳም የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ዓይኖች ተገልጠው መልኩም ሕያው ሆኖ ፊቱም እንደ ፀሀይ ሲያበራ ባየች ጊዜ ሥልጣን ያለው ንጉሥ ሄሮድስ ያልፈሩ እነኚህ ዓይኖች እንግዲህስ እኔ በእጄ አጠፋቸዋለሁ እያለች የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ፊት ትመታ ዘንድ እጇን አነሣች፡፡ ያን ጊዜ የቅዱስ ዮሐንሥ የራስ ፀጉር በወንጭቱ ላይ ተዘረጋች በግራ በቀኝም ክንፍ አውጥታ ንስር በክንፎቹ እንዲበር የቤቱን ግድግዳ ሰንጥቃ ወደ ላይ ወጥታ በረረች፡፡ ያንጊዜ የሄሮድያዳ እጆች ከትከሻዋ ተቁርጠው ወደቁ፡፡ ምድርም አፋን ከፍታ ሰውነቷን አስከ አንገቷ ዋጠቻት ያንጊዜም ርጉም ንጉሥ ኄሮድያዳ ቤት ሔደ፡፡ የሄሮድያዳንም አንገት ከምድር ላይ ተተክሎ በግልጥ አየ፡፡ መሬቱንም ቄፍረው ሥጋዋን ያወጡ ዘንድ አዘዘ ሰውነቷን ግን ምንም አላገኙም፡፡ ከነ ሕይወቷ ወደ ጥልቀ ወርዳለችና፡፡ የተከበራችሁ ወንድሞቼ ሆይ ይህቺ የከበረች የመጥምቀ መለኮት ቅድስ ዮሐንስ አንገት ለ15 ዓመት ንስሃ ግብ እያለች ስታስምር ቆይታ በወርሐኃ የካቲት ሠላሳ ቀን ማስተማሯን ጨርሳ ካረፈች ከተገለጠች በኃላ በዚህ በወርሐ ሚያዚያ 15 ቀን በነቢይ ኤልሣ መቃብር ከተበረ ቅዱስና ክብር ሥጋው ጋር አንድነት ይህች ቅዱስ ራስ የተገናኘችበት ቀን ናት፡፡ በዚች ቀን መጥመቀ መለኮት ዮሐንስ ያደረገው ይህ ነው፡፡ ስሟ ኂሩና የተባለች አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ቅድስት ራሱ ከተከበረ ሰውነቱ ጋር በተገናኝቾበት በዚህ በወርኃ ሚያዚያ 15 ቀን የቅድስ ዮሐንስ መታሰቢያውን መብልና መጠጥን በማዘጋጀት በብዙ ጥንቃቄ በብዙ ደስታ ታከብር ነበር፡፡ ይህቺ ሴት በዚህ አገልግሎት ሳለችም ከእግር እሰከራሷ በቁስል ተመታ፡፡ ጽኑ ሕመምን ታመመች፡፡ ቁስሉም ሥጋዋም በመሽተቱ የሚጠጋት የሚያሰተምማት የለም፡፡ እነደደጉ ሳምራዊ የሆነ አንድ ካህን ግን እየመጣ ይጠይቃት ነበር፡፡ ይህ ካህን የዚችን ሴት ህመም እና ሰቃይ ባየ ጊዜ ፈጥኖ ወደ ቅድስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ሔዶ ፀበል ይዞ ወደ ዚያች ሴት ፈጥኖ ተመለሰ፡፡ ይኽቺንም ሴት ከታመመችበት ደግፎ አነሣት፡፡ በቅድስ ዮሐንስ የምታምኚ አንቺ ሴት ሆይ በወርሃ ሚያዚያ 15ቀን በእየዓመቱ አንቺ እርሱን በማመን መታሰቢያውን የምታደርጊ እግዚአብሔር ድካምሽን ከንቱ አያደርግም አላት፡፡ ይህ ፈራሄ እግዚአብሔር ካህንም ይህን ብሎ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ጠበል አጠመቃት፡፡ ሰባት ቀንም ከተጠመቀች በኃላ ይህቺ ደግ ሴት ተፈወሰች፡፡ ኹለንተናውም እንደ ቀድሞ ኾነ በአማላጅነቱ የፈወሳት ቅዱስ ዮሐንስን አመሰገነች፡፡የነብይ እና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይኹን አሜን፡፡
☞( ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዘ ሚያዝያ)
​​❤️ እንኳን ለቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††❤️

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††


††† ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ †††

††† አናንያ : አዛርያና ሚሳኤልን እንዲያው በቀድሞው አጠራር ሠለስቱ ደቂቅ (ሦስቱ ሕጻናት) እንላቸዋለን እንጂ ለእኛስ በእድሜም : በጸጋም : በትሩፋትም አባቶቻችን ናቸው::

ቅዱሳኑ የወቅቱ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጆች ናቸው:: ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ ሕዝቡን ሲማርክ አብረው ተማርከው ባቢሎን ወርደዋል::

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ:: ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ : ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ "ስገዱ" ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ከዚያች ቀን በኋላ አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል በአት አጽንተው : በጾምና በጸሎት ተወስነው ኑረዋል:: ነፍሳቸው ከሥጋቸው ስትለይ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኗል:: ቅዱስ ዳንኤልና ናቡከደነጾር ተሯሩጠው ቢሄዱ ሦስቱም በአንድነት ዐርፈው ተገኝተዋል:: ንጉሡ በእጅጉ ይወዳቸው ነበርና በወርቅ በተለበጠ ሳጥን ቀብሯቸዋል:: ስሞት ከመካከላቸው ቅበሩኝ በማለቱ ዛሬ ድረስ ለበቁ አባቶች የአራቱ መቃብር ባቢሎን ውስጥ ይታያል::

ቅዱሳን አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል (ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ) ያረፉት ግንቦት 10 ቀን ሲሆን ዘመኑም ከክርስቶስ 500 ዓመት በፊት ነው::

††† አምላካቸው ከእሳት ባወጣቸው ቀንም:-
"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ::
ስቡሕኒ ውዕቱ ወልዑልኒ ውዕቱ ለዓለም::" የሚለውን ምስጋና ፈጣሪ ገልጾላቸው ደርሰውታል:: (በእሳቱ ውስጥ ሆነው ተናግረውታል:: )

ድርሰታቸው 2 ወገን ሲሆን ባለ ስድስት አንቀጹ ምስጋናቸው ከ600 ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ የሚያሳይ ነው:: ሌላኛውና 33 አንቀጾች ያሉት ምስጋናቸው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ለ33 ዓመታት እንደሚመላለስ ያጠይቃል::

ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ካረፉ ከ900 ዓመታት በኋላ (ማለትም ከክርስቶስ ልደት በ400 ዓመታት) ታላቁ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያንን አንጾላቸው ነበርና አጽማቸውን ሊያገኝ ተመኘ::

ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ጠርቶ "አባ! አጽመ ቅዱሳንን ባቢሎን ወርደህ አምጣልኝ?" አለው:: ቅዱሱ ሐጺር ዮሐንስም በደመና ተጭኖ ባቢሎን ገባ:: በቅዱሳኑ መቃብር ፊትም ሰግዶ አለቀሰ:: ሠለስቱ ደቂቅም "ወዳጃችን! ምን ሆንክ?" አሉት::

ቅዱሱም መልሶ "ወደ ግብጽ እንሒድ:: አባ ቴዎፍሎስ ይፈልጋቹሃል" አላቸው:: እነሱም "ለቅዱሱ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው:: እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ:: ግን አጽማችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ባቢሎንን አይለቅም:: ለክብርህ ግን እንመጣለን::"

"ለምልክትም ይሆን ዘንድ መብራት ሳታበራ በሌሊት ጠብቀን በለው" ብለው ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ባርከው ሸኙት:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርም መጥቶ መልእክቱን አደረሰ:: በዕለተ ቅዳሴ ቤታቸው ቅዱሳን:- ቴዎፍሎስ : ቄርሎስ : ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና ሌሎችም ከምዕመናን ጋር በጨለማ ሳሉ ቤተ ክርስቲያኑ ቦግ ብሎ በራ::

እጅግ የሚደነቅ ብርሃንም ከበባቸው:: በብርሃኑ መካከል ሠለስቱ ደቂቅ ሲያልፉ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ሕዝቡም በደስታና በዝማሬ የቅዱሳኑን ቅዳሴ ቤት አክብሯል::

††† በረከታቸው ይደርብን::


††† ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል)
2.ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት)
3.አባ ሚካኤል ገዳማዊ
4.አባ ይስሐቅ ግብጻዊ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

"ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::" †††
(ዳን. 3:28)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
​​እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አቡነ ተጠምቀ መድኅን †††


††† ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው #ወልደ_ክርስቶስና #ወለተ_ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ #ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ #ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::

ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም::

ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::

ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት:-

1.በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል
2.ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል
3.ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና)
4."7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::

††† ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ #ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል::
እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ #በጋሾላ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል::

††† ቅድስት ማርታ †††

††† እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች::

መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን (በበዓለ ልደት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት::

ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት::

ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ25 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች::

††† የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: †††

††† ሰኔ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ማርታ ተሐራሚት
2.አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት
4.ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት

†††ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

"አልሞትም: በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ::
መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ::
ለሞት ግን አልሠጠኝም::
የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ::
ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ::
ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት::
ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ::
ሰምተኸኛልና:
መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ::" †††  (መዝ. 117:17-22)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

🪔#ስንክሳር_ዘወርሃ_ሰኔ3🕯
​​ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል።

የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19)

ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምሮ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።

ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ።

ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።

ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው።

ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @Fnote_hywet💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
3🙏2
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!

የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡

ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው!

ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል
ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣

ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣

በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤
የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡

ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤

በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣

እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤

ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው!

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡

በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡

በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ፅንሰታ ለማርያም

ነሐሴ 7 በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄም እና ሃና ይባላሉ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ ኃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፦

ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡

ሐናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋየምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግዕዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ! ብላ ምርር ብላ አለቀሰች።

እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን ፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ።  ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም  ቅድስት ቡርክት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ፦

ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት

ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ።

ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን ? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡

ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሐና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ።

ምልጃዋ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን !

https://t.me/Fnote_hywet
🥰21
🥰1
1
​​#ቅዱስ_መስቀለ_ክርስቶስ

ነሐሴ ዐሥራ አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በእስክንድርያ ሀገር ድንቅ ተአምርን አደረገ።

ስለርሱም ከአይሁድ ብዙዎች አምነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ቴዎፍሎስ እጅ ተጠመቁ እርሱም ለቅዱስ ቄርሎስ የእናቱ ወንድም ነው። ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ አገር ስሙ ፈለስኪኖስ የሚባል አይሁዳዊ ባለጸጋ ሰው ይኖር ነበር እርሱም እንደ አባቶቹ የኦሪትን ሕግ የሚጠብቅና #እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው።

ዳግመኛም ሙያተኛዎች ሁለት ድኃዎች ክርስቲያኖች አሉ በአንደኛውም ላይ ሰይጣን የስድብ መንፈስ አሳድሮበት ጓደኛውን ወንድሜ ሆይ #ክርስቶስን ለምን እናመልከዋለን እኛ ዶኆች ነን ይህ #ክርስቶስን የማያመልክ አይሁዳዊ ፈለስኪኖስ ግን እጅግ ባለጸጋ ነው አለው።

ጓደኛውም እንዲህ ብሎ መለሰለት ዕወቅ አስተውል የዚህ ዓለም ገንዘብ ከ #እግዚአብሔር የሆነ አይደለም ምንም አይጠቅምም ጥቅም ቢኖረው ጣዖትን ለሚያመልኩ ለአመንዝራዎች ለነፍሰ ገዳዮች ለዐመፀኞች ሁሉ ባልሰጣቸውም ነበር።

አስተውል የከበሩ ነቢያት ድኆች ችግረኞችም እንደነበሩ ሐዋርያትም እንደርሳቸው ችግረኞች እንደነበሩ። #ጌታችንም ድኆችን ወንድሞቼ ይላቸው እንደነበረ። ሰይጣን ግን የጓደኛውን ምክር እንዲቀበል ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ምንም ምን አልተወውም ሃይማኖቱን ለውጦ ነፍሱን እስከማጥፋት ድረስ አነሣሣው ቀሰቀሰው እንጂ።

ከዚህም በኋላ ወደ ፈለስኪኖስ ሒዶ በአንተ ዘንድ እንዳገለግል ተቀበለኝ አለው። ፈለስኪኖስም እንዲህ ብሎ መለሰለት በሃይማኖቴ የማታምን አንተ ልታገለግለኝ አይገባም ከቤተ ሰቦቼም ጋራ የማትተባበር ልቀበልህ አይገባኝም። ሁለተኛም ይህ ጐስቋላ ወዳንተ ተቀበለኝ እኔም ወደ ሃይማኖትህ እገባለሁ ያዘዝከኝንም ሁሉ አደርጋለሁ አለው።

አይሁዳዊው ባለጸጋም ከመምህሬ ጋር እስከምማከር ጥቂት ታገሠኝ ብሎ ከዚያም ወደ መምህሩ ሒዶ ድኃው ክርስቲያናዊ ያለውን ሁሉ ነገረው መምህሩም #ክርስቶስን የሚክድ ከሆነ ግረዘውና ተቀበለው አለው።

አይሁዳዊውም ተመልሶ መምህሩ የነገረውን ለዚያ ድኃ ነገረው ያም ምስኪን የምታዙኝን ሁሉ አደርጋለሁ አለ። ከዚህም በኋላ ወደ ምኵራባቸው ወሰደው የምኵራቡም አለቃ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ጠየቀው። ንጉሥህ #ክርስቶስን ክደህ አይሁዳዊ ትሆናለህን እርሱም አዎን እክደዋለሁ አለ።

የምኵራቡም አለቃ #መስቀል ሠርተው በላዩ የ #ክርስቶስን ሥዕል እንዲአደርጉ መጻጻንም የተመላች ሰፍነግ በዘንግ ላይ አሥረው ከጦር ጋራ እንዲሰጡት አዘዘ ከዚያም ከተሰቀለው ላይ ምራቅህን ትፋ መጻጻውንም አቅርብለት #ክርስቶስ ሆይ ወጋሁህ እያልህ ውጋው አሉት።

ሁሉንም እንዳዘዙት አድርጎ በወጋው ጊዜ ብዙ ውኃና ደም ፈሰሰ ለረጂም ጊዜም በምድር እየፈሰሰ ነበር በዚያን ጊዜም ያ ከሀዲ ደርቆ እንደ ደንጊያ ሆነ። በአይሁድ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሀት ወደቀባቸው በእውነት የአብርሃም ፈጣሪ ስለእኛ ተሰቅሏል እኛም ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው #እግዚአብሔር ልጅ እርሱ እንደሆነ አመንበት እያሉ ጮኹ።

ከዚህም በኋላ አለቃቸው ከዚያ ደም ወስዶ የአንድ ዕውር ዐይኖችን አስነካው ወዲያውኑ አየ ሁሉም አመኑ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ ሒደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ሊቀ ጳጳሳቱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ ተነሣ አባ ቄርሎስ ከእርሱ ጋራ አለ። ወደ አይሁድ ምኵራብም ሒዶ ውኃና ደም ከእርሱ ሲፈስ #መስቀሉን አገኘው ከዚያም ደም ወስዶ በግንባሩ ላይ ቀብቶ በረከትን ተቀበለ ሕዝቡንም ሁሉ ግንባራቸውን በመቀባት ባረካቸው።

ያንንም #መስቀል አክብረው ተሸክመው እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደው ያኖሩት ዘንድ አዘዘ። ደም የፈሰሰበትንም ምድር አፈሩን አስጠርጎ ለበረከትና ለበሽተኞች ፈውስ ሊሆን በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኖረው።

ከዚህም በኋላ ፈለስኪኖስ ከቤተ ሰቦቹ ሁሉ ጋራ ሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስን ተከተለው ከአይሁድም ብዙዎቹ የቀደሙ አባቶቻቸው በሰቀሉት የክብር ባለቤት በሆነ በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም አጥምቋቸው ከእርሱ ጋራ አንድ አደረጋቸው #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙንም አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ ለዘላለሙ ክብር ምስጉን የሆነ #እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደየቤታቸው ገቡ። እኛንም ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን በ #መስቀሉ ኃይል ያድነን አሜን።
1
​​​​​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡ አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @Fnote_hywet 💚
💛 @ fnote_hywet 💛
❤️ @fnote_hywet