Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት
1.6K subscribers
1.68K photos
31 videos
10 files
147 links
Will provide different Training & Consultancy on fitness & wellness industry.
Download Telegram
FIT CORNER SPORT
🏅🏅🏅 ገቢዎች ሚኒስቴር ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሰራተኞች ቀንን በድምቀት አከበረ።🏅🏅🏅
            በቢሾፍቱ አየር ሀይል ማሰልጠኛ ጊቢ ውስጥ በተካሄደው መርሐግብር ላይ የኢፌዲሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የገቢዎች ሚንስቴር ሚንስትር ኮምሽነር ዶ/ር ደበሌ ቃበታ እንዲሁም የጉሙሩክ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ እና የየተቋማቱ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
         ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ በማለዳ  አካላዊ እንቅስቃሴ በደማቅ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን ሩጫ፣የእግር ኳስ ውድድሮች እና ሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችም የመርሐግብሩ አካላት ነበሩ።
     መሰል እንቅስቃሴዎች በሰራተኞች መካከል መካሄዳቸው ጤንነታቸውን ከመጠበቅ በተጨማሪም ማህበራዊ  መስተጋብራቸውን ከፍ እንደሚያደርግ የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሣ ተናግረዋል።
https://t.me/FitCorner
https://www.tiktok.com/@netsisport?_r=1&_t=ZS-9657BjxWEZJ
1👍1
FIT CORNER SPORT
ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ጋር በመተባበር ወርሃዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄደ።
''የአካል ብቃት እንቅቃሴ ዛሬ፣ለጤናማና ደስተኛ ሕይወት ሁሌም'' በሚል መሪቃል በዛሬው ዕለት ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የወንዝ ዳር ልማት አካባቢ ሲካሄድ በመርሐግብሩ ላይ የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ሰራተኞች እና የስፖርት ቤተሰቡ ተካፋይ ሆነዋል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ከበሽታ የቅድመ መከላከል ዋነኛ መንገድ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ህብረተሰቡም በከተማ ውስት በተሰሩት የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ላይ በመገኘት ጤናውን እንዲጠብቅ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን መርሐግብሩ ያማረ እና የደመቀ እንዲሆን የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሣ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
https://t.me/FitCorner
https://www.tiktok.com/@netsisport?_r=1&_t=ZS-9657BjxWEZJ
👍2🥰21
Great trainers never stop learning.
Today’s practical training is tomorrow’s better coaching. 💪
# fit corner sport
#healthylifestyle
#netsisport
#adwa gym
5👏2