የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)
2.74K subscribers
2.5K photos
35 videos
3 files
37 links
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ // www.ffic.gov.et
FFIC Communication Affairs
Download Telegram
አቶ ሰሎሞን በዳዳ የኮሚኒኬሽን እና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ የስሜት ልህቀት ከአገልግሎት እና አገልጋይነት ጋር ያለውን ትስስር ባብራሩበት ስልጠና ስሜቶቻችንን በአግባቡ በመለየት ለተግባቦታችን እንቅፋት የሆነውን ስሜት በመግታት እንዲሁም የሌሎችን ስሜት በመረዳት ለተገልጋዩ ተገቢውን ክብር በመስጠት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው ለዚህም አገልግሎት እና አገልጋይነትን ያላቸውን ትርጉም በአግባቡ ስለ መረዳት፤ የስሜት ብስለት ለአገልግሎት አሰጣጣችን የተሻለ መሆን ያለውን ድርሻ በአግባቡ ስለ መረዳት፤ በስራ ቦታ የሚያስፈልጉ መልካም አመለካከቶችን ስለ ማዳበር፤ ከተገልጋዮች እና ከስራ ባልደረቦች ጋር የሚኖረን ግንኙነት እና በየቀኑ በስራ ቦታችን ላይ ልንተገብራቸው ስለሚገቡ ተግባራት፣ የተገልጋዮችን ፍላጎት በአዎንታዊ መልኩ ስለ መረዳት እና ፈጣን ምላሽ ስለ መስጠት፤ ግጭቶችን በውይይት እና በመግባባት ስለ መፍታት በስልጠናው ከተዳሰሱት ዋና ዋና ርዕሶች ውስጥ ይገኙበታል። በስልጠናው አቶ ሰሎሞንበዳዳ አገልጋይነት የስራ መደብ ሳይሆን የልብ አመለካከት ስለሆነ አዕምሯችንን እና ልባችንን በተገቢው አገናኝተን ሁላችንም ለተሻለ ውጤት መስራት ይገባል ብለዋል።
በመርሃግብሩ በስራ ክፍሉ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዮ እና መርሃግብሩን ላስተባበሩ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስጦታ የተሰጠ ሲሆን ይህን መሰል የአቅም ግንባታ የግንዛቤ ስልጠና እና ሰራተኞች በጋራ አዕምሯቸውን እና አካላቸውን በማዝናናት ለቀጣይ ተልዕኮ ብቁ የሚያደርግ መርሃግብር የሰራተኞችን ተነሳሽነት በመጨመር የተቋሙን የአገልግሎት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንዲኖረው ስለሚያደርግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተገልፆል።
❤2👍2
ቀን ጥቅምት 13 2019 ዓ.ም የየካ ምድብ ችሎት የባለጉዳዮች መፀዳጃ ቤት አዲስ ግንባታ እና የለሚኩራ ምድብ ችሎት የህንፃ ቀለም ቅብ እና እድሳት ተከናወነ፡፡
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የባለጉዳዮችን የአገልግሎት ምቹነት ለማሻሻል በየካ ምድብ ችሎት ያከናወነው የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ተጠናቆ ስራ ጀመረ። በተመሳሳይ በለሚ ኩራ ምድብ ችሎት የቀለም ቅብ እና የእድሳት ሥራዎች በአብዛኛው ተጠናቀው ቀሪ ሥራዎችን የማጠናቀቅ እና ርክክብ የማከናወን ሂደት ላይ ይገኛል።
በየካ ምድብ ችሎት የተገነባው የባለጉዳዮች አዲስ መፀዳጃ ቤት ስድስት ክፍሎችን የያዘ ሲሆን የግንባታ ሥራው ተጠናቆ ስራ መጀመሩ በፍርድ ቤቱ ግቢ የሚስተዋለውን የመሠረተ ልማት እጥረት ለመቅረፍ እና ከባለጉዳዮች ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት እንዲሁም የተሻለ የአገልግሎት ምቹነት ለመፍጠር እንዲያግዝ የተገነባ ሲሆን በተጨማሪም በለሚ ኩራ ምድብ ችሎት የህንፃውን የቀለም ቅብ እና እድሳት ሥራ መከናወኑ የሥራ አካባቢውን ለማሻሻል እና ለአገልግሎት የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ አቶ ሰሎሞን ፈጠነ የፍርድ ቤቱ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና አቶ ተስፋዬ ከበደ የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም በምድብ ችሎቶቹ በመገኘት በገመገሙበት ወቀት ተናግረዋል፡፡
❤1👍1
በየካ ምድብ ችሎት ለባለጉዳዮች የተገነባው መፀዳጃ ቤት በ3,999,000.29 ብር (ሶስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) ወጪ የተጠናቀቀ ሲሆን በለሚኩራ ምድብ ችሎት የቀለም ቅብ የእድሳት ሥራውን ለማከነወን 3,330,429.99 ብር (ሶስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሰላሳ ሺ አራት መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር 99 ሳንቲም) ወጪ ተደርጓል።
በአጠቃላይ በተለያዩ ምድብ ችሎቶች እየተከናወኑ ያሉት የግንባታ፣ የእድሳት እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች የፍርድ ቤቱን የአገልግሎት አቅም ለማሻሻል እና ለሰራተኞች እና ለባለጉዳዮች የተሻለ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያግዙ መሆናቸው በኃላፊዎቹ ተብራርተዋል።
👍1
ጥቅምት 17  ቀን 2019 ዓ.ም                  ለረጅም ዓመታት ላገለገሉ ሰራተኞች በባልደረቦቻው ሽኝት ተደረገ።
                               የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት  ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ሬጅስትራሮች፣ የቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች  በተገኙበት  ማክሰኞ  ጥቅምት  17 ቀን  2019  ዓ.ም ልደታ በሚገኘው  በዋናው መስሪያ ቤት አዳራሽ  ለረጅም ዓመታት ተቋሙን ከባለሙያነት እስከ ኃላፊነት  ላገለገሉ ሰራተኞችቀደም ብሎ በፍርድ ቤቱ እውቅና እና ሽልማት የተደረገላቸው ቢሆንም  በስራ ባልደረቦቻቸዎ  ዳግሞ  ሽኝት ተደረገላቸው።      
ሽኝት የተደረገላቸው   ሁለት የቀድሞ  ሴት ኃላፊ ሰራተኞች  ወይዘሮ ታደለች ጥላሁን ጋሼ  የበጀት እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩትና ለ39 ዓመታት  ያገለገሉት  ሲሆኑ  ሌላኛዋ  ወይዘሮ እጅጋየሁ ካሴ አየለ   አስተባባሪ ሬጅስትራር በመሆን ባጠቃላይ  ለ42 ዓመታት ከ 7 ወራት በጥንካሬ ያገለገሉ ናቸው።                                                    በሽኝቱ ስለ ቀድሞ ኃላፊዎቹ እና የስራ ባልደረቦች በፍርድ ቤቱ አመራሮች እና  በባለሙያዎች  ስለ ጥንካሪያቸው፣ ተግባቦታቸው እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለረጅም ዓመታት በአግባቡ ስለመወጣታቸው ተነግሯል። በመርሐግብሩ  የስጦታ ማበርከት  የተደረገ ሲሆን  ተሸኚዎቹም  የተሰማቸውን ስሜት አካፍለዋል።
❤1