የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)
2.68K subscribers
2.41K photos
35 videos
3 files
36 links
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ // www.ffic.gov.et
FFIC Communication Affairs
Download Telegram
በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁሉም ዳኞች ጋር ውይይት ተደረገ።
*********
በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሁሉም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በተገኙበት ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል አዲስ አበባ ሆቴል ውይይት ተደረገ።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፋአድ ኪያር ፍርድ ቤቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጠናውን "የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ" ሪፖርት ሰነድን አስመልክቶ በተናገሩበት ወቅት ባለፋት አምስት የስትራቴጂክ ዕቅድ ዓመታት በውስንነት ከተለዮት ችግሮች አንዱ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት መሆኑን በማስታወስ ፍርድ ቤቱ በ2018 በዕቅድ ከያዛቸው ስራዎች አንዱ የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ ማከናወን መሆኑን አስገንዝበዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸዉ የዳኝነት አገልግሎት ጥራትን ከሚያረጋግጡ ቁልፍ መሳሪያዎች አንዱ ተከታታይነት ያለው የድህረ-ውሣኔ ኦዲት ስራ መስራት መሆኑን በመግለፅ በተለይም ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ወጥነት ያለው አሠራርን ለማስፈን፣ የስልጠና ፍላጎትን ለመለየት፣ ተጠያቂነት እና ግልፅነት ለማስፈን፣ ክፍተቶችን ለይቶ ለማስተካከል እና የሕዝብ አመኔታ ለማግኘት የድህረ-ኦዲት ውሣኔ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
3
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በክረምት ተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች ይፋ አደረገ
*******************
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት፤ ከመደበኛ የፍርድ ቤት የሥራ ጊዜ ውጭ አስቸኳይ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት አሰራር ተዘርግቶ ሲሠራ ቆይቷል።
በዚሁ መሠረት መሠረታዊ የመብት ጥሰት የሚያስከትሉ በባሕሪያቸው ጊዜ የማይሰጡ እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጠባቸው ሊካስ የማይችል ጉዳት የሚያስከትሉ አጣዳፊ ጉዳዮችን አይቶ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ በተረኛ ችሎት አገልግሎት ይሰጣል።
በፍትሐ ብሔር በኩል በሚታዩ ጉዳዮች፡ አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች፣ የልጅ ቀለብ፣ አካል ነጻ የማውጣት አቤቱታዎች፣ እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች፣ ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው ላይ የሚያቀርቧቸው የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸሞች፣ ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዝ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች እንዲሁም ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ ጉዳዮች በተረኛ ችሎት ይስተናገዳሉ።
በወንጀል በኩል ደግሞ፡ የዋስትና፣ የአመክሮ፣ የአርቲዲ (እስረኛ ያላቸው የወንጀል መዛግብት)፣ በሰበር የሚቀርቡ አቤቱታዎች፣ የአራዳ ምድብ ችሎት ጊዜ ቀጠሮ፣ ለመሰየም የሚቀርብ አቤቱታ እና ሌሎች መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ አጣዳፊ የወንጀል ጉዳዮች የሚታዩ ይሆናል።
በመሆኑም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት በዚህ ወቅት ተገልጋዮች እና የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብ አሠራሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥሪ አቅርቧል።
7👍7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የድህረ ውሳኔ ምርመራ/ኦዲት ሪፖርትን ለፍ/ቤቱ ሁሉም ዳኞች ያቀረበበት መድረክን አስመልክቶ የተሰራነው ልዩ ፕሮግራም ረቡዕ ምሽት 2:00 ሰዓት በዓባይ ቲቪ እና በፍትሕ ለሃገሬ ዩቱዩብ ገፅ ላይ ስለሚቀርብ እንድትከታተሉት በአክብሮት ተጋብዣችኋል ።
9
በሰባት ምድብ ችሎቶች የኢ-ፋይሊንግ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል የስካኒንግ ስልጠና
ተሰጠ፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎቱን በማዘመን ቀልጣፋ፣ወጪ ቆጣቢ እና ተደራሽ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከልደታ እና ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎቶች በተጨማሪ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎቶች መዝገቦችን ስካን በማድረግ በዲጅታል ፎርማት ማስቀመጥ የተጀመረ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥራ ላይ የዋለውን የኢ-ፋይሊንግ ሲስተም በመጠቀም እነዚህ ምድብ ችሎቶች ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይግባኝ ስካን በማድረግ በኢፋይሊንግ ስሲተም በመላክ ላይ ይገኛሉ፡፡
1
ይህን ሥርዓት በተቀሩት ዘጠኝ ምድብ ችሎቶች ለመጀመር ስካን በማድረግ በዘላቂነት ማስቀመጥ እና ለሥራ ማዋል ጥንቃቄ የሚፈልግ እና በእውቀት ላይ ተመርኩዞ የሚሠራ ሥራ በመሆኑ በስካኒንግ ሥራ ላይ ለተመደቡ ባለሙያዎች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ በሰባት ምድብ ችሎቶች ለተመደቡ ባለሙያዎች በገለጻ እና በተግባር ልምምድ ላይ ያተኮረ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዲጂታላይዝ የመዝገብ አያያዝ እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የአንድ ቀን ሥልጠና በዋናው መስሪያ ቤት ተሰጥቷል፡፡
ከስልጠናው ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን ለአብነትም፤ ስካን የማድረግ ሥራ አላማውን በተለይም ከዲጅታል ኢትዮጵያ ጋር ተያይዞ የዲጅታል ፍርድ ቤት ለመገንባት የተጀመረውን ጅማሬ በማሳየት እያንዳንዳቸው የሚያደርጉትን አስተዋጾ ማስገንዘብ፣ ስካን ከመደረጉ በፊት እና በኋላ የሚከናወኑ ክንውኖች መግለጽ፣ ዲጅታል መረጃው ከዋናው መዝገብ ጋር ትክክለኛ ቅጂ እንዲሆን ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ከቀደመ ልምድ በመነሳት ማስገንዘብ፣ በተጨማሪም ስካን እንዴት እንደሚደረግ፣እንደሚስተካከል፣እንዴት ለዘለቄታው እንደሚቀመጥ በሙያው የቀደመ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የስካኒንግ ባለሙያ የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና ሬጅስትራር ወ/ሮ ፈትለወርቅ አንዳርጌ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከተጀመሩ ዲጂታላይዝ ትግበራ አንዱ መዝገቦችን እስካን በማድረግ በ"ኢ-ፋይሊንግ ሲስተም (e-Filing System)" ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት መላክ በመሆኑ የኢፋይሊንግ ሲስተም ያልተጀመረባቸው ዘጠኝ ምድብ ችሎት ለመጀመር መዝገቦችን ስካን በማድረግ ዝግጅት ማድረግ የሚያስፈልግ በመሆኑ ሁሉም የስካነር እና የዲጂታላይዝ የመዝገብ አያያዝ እና አስተዳደር ባለሙያዎች በተሰጠው ስልጠና መሰረት የስካኒግ ስራውን እንዲጀምሩ መልእክት አስተላልፈው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
3👍1