ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኞች እና አስተዳደር ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ፡፡ አርብ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ለልደታ ምድብ ችሎት ዋና ሬጂስትራር፣ ሬጂስትራር፣ ችሎት ፀሃፊዎች እና የችሎት ስነ ስርኣት ባለሙያዎች የሙስና መከላከል እና የስነ ምግባር መርሆች ዙሪያ በፍርድ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በመርሃግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ክብርት ወ/ሮ ረሂማ ጀማል ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ ሰራተኖች የዳኝነት አገልግሎቱን ግልጽ፣ ፈጣን እና ፍትሃዊ በማድረግ እንዲሁም አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅትም መልካም ስነ ምግባር የተላበሱ እና ብልሹ አሰራርን የተጸየፉ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በአቶ መሃመድ ጦይብ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፀረ-ሙስና እና ስነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የተሰጠ ሲሆን ዳይሬክተሩ ስለ ሙስና ምንነት፣ ስለ ስነ ምግባር መርሆች፣ ስለ ሙስና አይነቶች፣ ስለ ሙስና ዋነኛ ምክንያቶች፣ ሙስና በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚያመጣው ጉዳትን በሚመለከት እንዲሁም የሙስና መከላከልያ መንገዶችን ምን እንደሆኑ በገለፃቸው አብራርተዋል።

❤4
የስሜት ልህቀት አገልግሎት እና አገልጋይነትን በማሳለጥ ለተቋም ስኬት ያለው ሚና። ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ ግልፅ እና ደንበኛ ተኮር ለማድረግ ያለመ የውጤታማ የመግባባት ክህሎት ስልጠና ለክፍሉ ሰራተኞች ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ራያ ሆቴል ሰጠ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የፍርድ ቤቱ የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ከበደ ሲሆኑ የተቋሙን ራዕይ እና ግብ ለማሳካት እንዲሁም የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዩን ህብረተሰብ በላቀ ሁኔታ ለማርካት ውጤታማ የተግባቦት ክህሎትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም በ2018 በጀት ዓመት በአፈፃፀማችን የተሻለ ተብለን እውቅና ለማግኘታችን የሁላችሁም ርብርብ እና ጠንካራ ስራ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ነገር ግን አሁንም ብዙ ጉድለቶች እና ክፍተቶች ስላሉብን እነሱን ለማሻሻል እና ለመቅረፍ በተገቢው የመረጃ ልውውጥ ላይ ተመስርተን በቅንጅት የተቋሙን አሰራር እና መልካም ገፅታ ይበልጥ ማጠናከር ላይ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

❤1