የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)
2.74K subscribers
2.5K photos
35 videos
3 files
37 links
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ // www.ffic.gov.et
FFIC Communication Affairs
Download Telegram
ቀን፦ 29/01/2019 ዓ.ም
#የ2019 ዓ.ም የስራ ማሰጀመረያ እና የፍርድ ቤቱን ራዕይ ለማሳካት ስለሚፈፀሙ ተግባራትን በተመለከተ ለአሰተዳደራ ሰራተኞች የግንዛቤ መሰጨበጨ ተሰጠ።
የፌዴራል መጀመረያ ደረጀ ፍርድ ቤት ንፋሰ ስልክ ምድብ ችሎት የ2019 ዓ.ም የስራ ማስጀመረያን፣ በስራ ላይ ቆይተው በጡራታ ለሚሰናበቱ የሸዕኝት ፕሮግራም እና ለአሰተዳደር ሰራተኞች በሙሉ የፍርድ ቤቱን ራዕይ ለማሳካት በሰነ-ምግባር መስራት በሚል ርእስ ስልጠና የመስጠት መርሃግብር መሰከራም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ተከናወነ፡፡
የመርሃግብሩን መክፋቻ ያደረጉት የንፋሰ ሰልክ ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ክቡር አቶ ዳንኤል ዱጋሳ ሲሆኑ በመክፋቻው በ2018 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ በተሰራ ስራ አፈፃፀማቸው 98% የተለካ መሆኑን እና ጥሩ ስኬት መሆኑን ገልፀው በቀጠይ ከዚህ በላይ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
❤3
በመቀጠልም የክቡር እንግዳ ሆነው የተጋበዙት የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍረድ ቤቱ የሰነ-ምግባር እና ፀረ- ሙሰና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሀመድ ጦይብ ካሉት ምድብ ችሎቶች ውሰጥ በአፈፃፀም እና በሰነ-ምግባር የተሻለ ተሞክሮ ስላላችሁ ለ2019 ዓ.ም የተቋሙን ራዕይ ሰኬታማ ለማድረግ ቀልጣፋ እና ከእንግልት ነፃየሆነ የስራ ስነ-ምግባር መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም የዕለቱ የፕሮግራም መሪ እና የሰልጠና ሰጪ የሆኑት የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍረድ ቤት ንፋሰ ሰልክ ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ክቡር አቶ ዳንኤል ዱጋሳ የፍርድ ቤቱን ራዕይ እንዲሳከ የአሰተዳደር ሰራተኞች ያላቸውን ሚና በአግባቡ እንዲረዱ በማድረግ እና በ2019 ዓ.ም የአሰተዳደር ሰራተኞች ባለጉዳይን በተሸለ ሁኔታ በማገልገል ወደ ተቋሙ የሚመጡት ተገልጋዮች በምድብ ችሎቱ ያላቸውን አመኔታ ማሰደግ እንደሚገባ እና ሌሎች ነጥቦችን በማንሳት ግልፅ የሆነ ማብራረያ ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም የፍርድ ቤቱን ተልዕኮ እና ራዕይ ለማሰከት ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት መሰጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
❤5
ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኞች እና አስተዳደር ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ፡፡ አርብ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ለልደታ ምድብ ችሎት ዋና ሬጂስትራር፣ ሬጂስትራር፣ ችሎት ፀሃፊዎች እና የችሎት ስነ ስርኣት ባለሙያዎች የሙስና መከላከል እና የስነ ምግባር መርሆች ዙሪያ በፍርድ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በመርሃግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ክብርት ወ/ሮ ረሂማ ጀማል ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ ሰራተኖች የዳኝነት አገልግሎቱን ግልጽ፣ ፈጣን እና ፍትሃዊ በማድረግ እንዲሁም አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅትም መልካም ስነ ምግባር የተላበሱ እና ብልሹ አሰራርን የተጸየፉ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በአቶ መሃመድ ጦይብ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፀረ-ሙስና እና ስነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የተሰጠ ሲሆን ዳይሬክተሩ ስለ ሙስና ምንነት፣ ስለ ስነ ምግባር መርሆች፣ ስለ ሙስና አይነቶች፣ ስለ ሙስና ዋነኛ ምክንያቶች፣ ሙስና በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚያመጣው ጉዳትን በሚመለከት እንዲሁም የሙስና መከላከልያ መንገዶችን ምን እንደሆኑ በገለፃቸው አብራርተዋል።
❤4
የስሜት ልህቀት አገልግሎት እና አገልጋይነትን በማሳለጥ ለተቋም ስኬት ያለው ሚና። ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ ግልፅ እና ደንበኛ ተኮር ለማድረግ ያለመ የውጤታማ የመግባባት ክህሎት ስልጠና ለክፍሉ ሰራተኞች ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ራያ ሆቴል ሰጠ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የፍርድ ቤቱ የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ከበደ ሲሆኑ የተቋሙን ራዕይ እና ግብ ለማሳካት እንዲሁም የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዩን ህብረተሰብ በላቀ ሁኔታ ለማርካት ውጤታማ የተግባቦት ክህሎትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም በ2018 በጀት ዓመት በአፈፃፀማችን የተሻለ ተብለን እውቅና ለማግኘታችን የሁላችሁም ርብርብ እና ጠንካራ ስራ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ነገር ግን አሁንም ብዙ ጉድለቶች እና ክፍተቶች ስላሉብን እነሱን ለማሻሻል እና ለመቅረፍ በተገቢው የመረጃ ልውውጥ ላይ ተመስርተን በቅንጅት የተቋሙን አሰራር እና መልካም ገፅታ ይበልጥ ማጠናከር ላይ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
❤1