የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)
2.74K subscribers
2.5K photos
35 videos
3 files
37 links
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ // www.ffic.gov.et
FFIC Communication Affairs
Download Telegram
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል
መስከረም 27/2019 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለመስጠት ካቀዳቸው ስልጠናዎች መካከል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
ከስልጠናዎቹ አንዱ ለሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በእቅድ ዝግጅት፣ በክትትልና ግምገማ፣ በሪፖርት አዘገጃጀት እንዲሁም በፕሮግራም በጀትና (Program Budgeting) አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በአዲሶቹ የመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ በስልጠናው የሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የግዢና ንብረት አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የግዢ አጽዳቂ ኮሚቴና የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
የ2019 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ እንደመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ በዚህ ወቅት የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዕከል በመስጠት በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ማቀዱ ተገልጿል።
ስልጠናዎቹ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል።
❤10
ቀን፡- 27/01/2019 ዓ.ም

የተቀናጀ የፋይናንሰ አሰተዳደር መረጃ ሰርዓት ትግባራን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ
የኢፍሚሰ (IFMIS) Integrated Financial Management Information System) የተቀናጀ የፋይናንሰ አሰተዳደር መረጃ ሰርዓት ትግባራን በማስመልከት ለምድብ ችሎት ሂሳብ ሰራተኞች እና ቡድን መሪዎች ሰልጠና ተሰጠ፡፡
የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመንግስት ገቢ መሰብሰብያ፣ ዋስትና ተሰብሳቢ እና ክፍያን ከኢፍሚሰ (IFMIS) ትግባራ ጋር አሰመልክቶ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁሉም ምድብ ችሎቶች ሂሳብ ሰራተኞች እና ለቡድን መሪዎች በሁለት ዙር ከመሰከረም 27 እስከ ጥቅምት ቀን 2019 ዓ.ም ሰልጠና እየተሰተ ነው፡፡
❤2👍1
በስልጠናው መክፈቻ የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍረድ ቤት የደኝነት አገልግሎቱ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ከማድረግ አንፃር በ2018 ዓ.ም የተጀመረውን የ(IFMIS) የተቀናጀ የፋይናንሰ አሰተዳደር መረጃ ሰርዓት ትግባራ በጥንካሬ እና በድክመት ችግሮችን በመገምገም ያለውን ክፍተት ለማሰተካከል እና ከየምድብ ችሎቶች በሚሰበሰቡ ሪሲቶች (ደረሰኞች)፣ የዋሰትና ክፍያ እና አጠቃላይ ክፍያን በተመለከተ የሚያገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚረዳ ስልጠና መሆኑን የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የጠቅላላ ሂሳብ ቡድን መሪ አቶ አብዱ በረካ ተናግረዋል፡፡
የመንግሰት ገቢ መሰበሰብን በተመለከተ አቶ ይድነቃቸው ከበደ፣ የዋሰትና ማወራረጃን በተመለከተ ወ/ሮ ሰላማዊት መዘምር፣ በጀትን በተመለከተ ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም እንዲሁም አጠቃላይ የኢፍ-ሚሰ (IFMIS) የተቀናጀ የፋይናንሰ አሰተዳደር መረጃ ሰርዓት ትግባራን በተመለከተ የጠቅላላ ሂሳብ ቡድን መሪ አቶ አብዱ በረካ የሰጡ ሲሆን ሰልጠናው ከክፍያ ጋር ተያይዞ የሚያገጥሙ ችግሮችን ለመቀነስ ወይም እንዳይፈጠሩ የሚረዳ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
❤4