የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት (Federal First Instance Court)
2.74K subscribers
2.5K photos
35 videos
3 files
37 links
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስቱ የፌዴራል የዳኝነት አካላት አንዱ ሲሆን በፍርድ ቤት መቋቋሚያ አዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ጊዜውን የሚመጥን የፍትህና የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡ // www.ffic.gov.et
FFIC Communication Affairs
Download Telegram
አንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
መጪው ዘመን የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ ይሁንላችሁ!
👍6❤5👏1
#የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “ርትዕ “ መጽሄት
ልዩ ዕትም
************
የ2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ3ኛው ስትራቴጂክ ዘመን መብቂያ እንደመሆኑ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከ 2014-2018 ዓ.ም የዓመስት ዓመት ቁልፍ ተግባራት ክንውን በልዩ ዕትም በመጽሄት በማሳተም እያሰራጨ ይገኛል፡፡
በልዩ ዕትም መጽሄቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባለፉት 5 ዓመታት (2014-2018) ያከናወናቸውን ቁልፍ ተግባራት የያዘ ሲሆን የፍ/ቤቱን ፕሬዝዳንት መልዕክትን ጨምሮ -ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር፣ -የዳኝነት ቅልጥፍና፣ -የዳኝነት ተገማችነት ማጠናከር፣-የፍርድ ቤት መር አስማሚነትን፣ -የዳኞች እና የሰራተኞች የስራ አፈፃፀም ምዘና እና እውቅና፣-የህፃናት መብቶች ከማስተከበር አንፃር በተቋሙ ተገልጋዮች እና ሰራተኞች የተከናወኑ ተግባራት -የዳኝነት ግልጽነት ፣ -ፍ/ቤቱ ስለተወጣቸው ማህበራዊ ኃላፊነት፣ -ስለ አቅም ግንባታ ስራዎች፣ -የዲጂታላይዜሽን ስራ፣ -ቅንጅታዊ አሰራር፣ -ስለ ተገልጋዩ እርካታ ጥናት :- በተጠያቂነት ዙሪያ ስለተከናውኑ ተግባራት ፣ -በፍርድ ቤቱ ስለተቋቋሙ ልዩ ችሎቶች፣ -ስለ በጀት እና የሰው ኃይሉ፣ -ስለኮምዩኑኬሽን እና ተደራሽነትን እና መሰል ቁልፍ ክንውኖች ተዳሰዋል፡፡
በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት ፍ/ቤቱ የገጠመው ተግዳሮት እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በመጽሄቱ የተካተቱ ሲሆን ይህ ልዩ ዕትም መጽሄት ለክቡራን ዳኞች፣ ለፍ/ቤቱ ሰራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት እየተሰራጨ ይገኛል፡፡
❤12👍3
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል
መስከረም 27/2019 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለመስጠት ካቀዳቸው ስልጠናዎች መካከል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
ከስልጠናዎቹ አንዱ ለሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በእቅድ ዝግጅት፣ በክትትልና ግምገማ፣ በሪፖርት አዘገጃጀት እንዲሁም በፕሮግራም በጀትና (Program Budgeting) አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በአዲሶቹ የመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ በስልጠናው የሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የግዢና ንብረት አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የግዢ አጽዳቂ ኮሚቴና የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
የ2019 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ እንደመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ በዚህ ወቅት የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዕከል በመስጠት በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ማቀዱ ተገልጿል።
ስልጠናዎቹ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል።
❤10
ቀን፡- 27/01/2019 ዓ.ም

የተቀናጀ የፋይናንሰ አሰተዳደር መረጃ ሰርዓት ትግባራን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ
የኢፍሚሰ (IFMIS) Integrated Financial Management Information System) የተቀናጀ የፋይናንሰ አሰተዳደር መረጃ ሰርዓት ትግባራን በማስመልከት ለምድብ ችሎት ሂሳብ ሰራተኞች እና ቡድን መሪዎች ሰልጠና ተሰጠ፡፡
የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመንግስት ገቢ መሰብሰብያ፣ ዋስትና ተሰብሳቢ እና ክፍያን ከኢፍሚሰ (IFMIS) ትግባራ ጋር አሰመልክቶ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁሉም ምድብ ችሎቶች ሂሳብ ሰራተኞች እና ለቡድን መሪዎች በሁለት ዙር ከመሰከረም 27 እስከ ጥቅምት ቀን 2019 ዓ.ም ሰልጠና እየተሰተ ነው፡፡
❤2👍1